የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፯ አዲስ አበባ - ጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፭ / ፲፱፻፲፭ ዓም • የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ገጽ ፪ሺ፫፻፭ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፭ / ፲፱፻፲፭ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ታማኝና በሕገ መንግሥቱ መሠረት ለሚወጡ ሕጎች | Prisons that adheres to the Constitution of the Federal ተገዥ የሆነ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ተቋም ማቋቋም በማስ ማረሚያ ቤቶች የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን በመፈጸም ሂደት ታራሚዎችን የመጠበቅ እና የማረም ተግባራትን በማከናወን | decisions , need to undertake the functions of the custody , ወንጀልን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ተገቢ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚጠበቅባቸው በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ -- [ of the Constitution of the Federal Democratic Republic of መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፭ / ፲፱፻፶፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፦ ያንዱ ዋጋ [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ : ዥሺ፩ ገጽ ፪ሺ፫፻፸፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም . Federal Negarit Gazeta -- No. 90 9 September , 2003– Page 2371 ፩ ሚሽን ” ማለት በዚህ አዋጅ የተቋቋመ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ነው ፣ ፪ “ የጋራ ጉባኤ ” ማለት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች የጋራ ጉባኤ ማለት ነው ፣ ፫ . “ ሚኒስቴር ” እና “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተ ላቸው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ነው ፣ ፬ . “ ማረሚያ ቤት ” ማለት በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት የሚላኩ ታራሚዎች የተወሰነባቸውን የእሥራት ቅጣት የሚፈጽሙበት ፣ የሚታረሙበት ፣ እንዲሁም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚላኩ ውሳኔ እስከሚያገኙ እንዲቆዩ የሚደረግበት የፌዴራል ማረሚያ ተቋም ነው ፣ ፭ “ ታራሚ ” ማለት በሕግ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተወሰነበትን የፍርድ ውሳኔ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ በመፈጸም ላይ የሚገኝ የሕግ ታራሚ ሲሆን በማረሚያ ቤት በቀጠሮ እንዲቆይ የተወሰነበትንም ይጨምራል ፣ ፮ “ የማረሚያ ጠባቂ ” ማለት መሠረታዊ የሆነ የማረሚያ የጥበቃ ሙያ ሥልጠና ተሰጥቶት በኮሚሽኑ ተቀጥሮ የሚሠራ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አባል ነው ። ክፍል ሁለት ስለፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን መቋቋም ፫ • መቋቋም ፩ . የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽን ” እየተባለ የሚጠራ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ • ኮሚሽኑ በሕግና በሙያው የሚኖረው ነፃነት እንደተ ጠበቀ ሆኖ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ፬ . የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት ፩ . የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ፣ ፪ • ከዚህ በፊት በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስር ሲተዳደሩ የነበሩት ማረሚያ ቤቶች በኮሚሽኑ ስር ሆነው ይዋቀራሉ ። ፫ ኮሚሽኑ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት የሚያከናውኑ አካላትን በማናቸውም ቦታ ማቋቋም ይችላል ። ፭ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ ታራሚዎችን ተቀብሎ መጠበቅ ፣ ለታራ ሚዎች የተሐድሶ አገልግሎት በመስጠት የአስተሳሰብና የስነ ምግባር ለውጥ እንዲያመጡ እንዲሁም ሕግ አክባሪ ፣ ሰላማዊና አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው ። ፮ . የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . በፍርድ ቤቶች ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ መሠረት የሚላኩ ለትን ታራሚዎች በመቀበል ይጠብቃል ፣ ያርማል ፣ እንዲሁም ከፍርድ ቤት የሚሰጡ ሌሎች ትእዛዞች ይፈጽማል ፣ ፪ • ታራሚዎችን ፍርድ ቤት ያቀርባል ፣ ፫ የታራሚዎችን ጤንነት ይጠብቃል ፣ በዚህ አዋጅ በሚወጣው ደንብ መሠረት ታራሚዎች ነፃ ሕክምና ፣ ምግብና መጠለያ እንዲያገኙ ያደርጋል ። ለታራሚዎች አካላዊና አዕምሮአዊ እንክብካቤ አስፈላጊ የሆኑ ተግባ ሮችን ያከናውናል ፣ ኣገልግሎቶችን ይሰጣል ፣ ዝርዝሩ ኮሚሽኑ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ፣ ፬ . ታራሚዎች ከተለቀቁ በኋላ ራሳቸውን ለማስተዳደር የሚችሉና ለሕግ ተገዢ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል የቀለም ትምህርት ፣ የሙያ ሥልጠና ፣ ማኅበራዊ አገልግ ሎትና የምክር አገልግሎት ይሰጣል ። ዝርዝሩ በደንብና በመመሪያ ይወሰናል ፣ ገጽ ፪ሺ፫፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ታራሚዎችን ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ወደ ክልል ማረሚያ ቤቶች ወይም ከአንድ ማረሚያ ቤት ወደሌላ ማረሚያ ቤት ኣጅቦ ያደርሳል ፣ ፮ . ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የማረሚያ ቤቱን የሥነ ሥርዓት መመሪያ በመጣስ ለሚፈጽሙት ጥፋት በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣው ደንብ ወይም መመሪያ መሠረት የሥነ ሥርዓት ቅጣቶችን ይወስናል ፣ ይፈጽማል ፣ ፯ በሀገር አቀፍ ደረጃ ታራሚዎችን በሚመለከት መረጃ ዎችን እና ስታስቲኮችን ያሰባስባል ፣ ያጠናቅራል ፣ ፰ ታራሚዎች በሚያሳዩት የባህሪይ ለውጥ በሕግ መሠረት፡ ሀ ) በአመክሮ ወይም ለ ) በይቅርታ ፣ እንዲፈቱ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ሀሳብ ያቀርባል ። ፱ ኮሚሽኑ ለሥራ አስፈላጊ የሆነ የማረሚያ ጥበቃ አባላት ይመለምላል ፣ ይቀጥራል ፣ ያሰለጥናል ፣ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑት ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ፲ የኮሚሽኑን ሠራተኞች የሙያ ብቃት ለማሳደግ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሥልጠና ዕድሎችን ያመቻቻል ፣ ፲፩ : የታራሚዎችን አጠባበቅና አያያዝ ለማሻሻል ፣ የማረሚያ ጥበቃ አባላትና ሠራተኞችን ሙያ ብቃትና አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይነት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ የሚረዱ ጥናቶችን ያከና ፲፪ • ለክልል ማረሚያ ቤቶች የሙያና የቴክኒክ እንዲሁም የምክር ድጋፍ ይሰጣል ፣ ፲፫ . ውል ይዋዋላል ፣ በራሱ ስም ይከሳል ፣ ይከሰሳል ። ፮ . የኮሚሽኑ አቋም ፩ ኮሚሽኑ፡ ሀ ) በፌዴራል መንግሥት የሚሾሙ አንድ ኮሚሽነር እና አንድ ምክትል ኮሚሽነር፡ ለ ) ኮሚሽነሩን ፣ ምክትል ኮሚሽነሩንና የዋና መምሪያ ኃላፊዎችን ያቀፈ የሥራ አመራር ጉባኤ ፣ እና ሐ ) ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ የማረሚያ ጥበቃ አባላትና የመንግሥት ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፪ የኮሚሽኑ አደረጃጀት ዝርዝር በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ይወሰናል ። ፰ የኮሚሽኑ የሥራ አመራር ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር የሥራ አመራር ጉባዔው፡ ፩ . የታራሚዎችን አጠባበቅ ፣ አያያዝ እና የማረሚያ ቤቶችን አስተዳደር ለማሻሻል የሚረዱ ሀገር አቀፍ የፖሊሲ ፣ የስትራቴጂና የስታንዳርዳይዜሽን ጥናቶችን በመመርመር ከኣስተያየት ጋር ለፌዴራል ማረሚያ ኮሚሽንና ለክልል ማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች የጋራ ጉባዔ እንዲቀርቡ ያደርጋል ፣ ፪ የኮሚሽኑን አደረጃጀት ፣ አወቃቀርና አሠራር የሚመ ለከቱ ጥናቶችን ይመረምራል ፣ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች ከአስተያየት ጋር ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ ፫ . የኮሚሽኑን የሥልጠና ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ ፬ • የኮሚሽኑን ረቂቅ በጀት ያዘጋጃል ፣ በፌዴራል መንግሥት እንዲፀድቅለትም በኮሚሽነሩ በኩል ለሚኒ ስትሩ ያቀርባል ፣ ፭ የኮሚሽኑን ዓመታዊ ዕቅድ ፣ ኦዲትና ሥራ አፈፃፀም ይገመግማል ፣ ከአስተያየት ጋር ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ ፮ በኮሚሽኑ እና በክልል ማረሚያ ቤቶች መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ያደርጋል ። ገጽ ፪ሺ፫የሮ ፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፱፭ ዓም ህ የሚኒስትሩ ሥልጣንና ተግባር ሚኒስትሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ የኮሚሽኑን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎች ይከታ ፪ • የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ሹመት እንዲጸድቅለት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባል፡ ፫ የኮሚሽኑን ዋና መምሪያ ኃላፊዎች ምደባ ያፀድቃል፡ ፬ . የኮሚሽኑን ዓመታዊ ዕቅድ፡ ረቂቅ በጀት፡ ሪፖርትና አፈፃፀም ከአስተያየት ለፌዴራል መንግሥት ያቀርባል፡ ፭ የታራሚዎች መብት መከበሩንና በአግባቡ ጥበቃ መደረጉን እንዲሁም ታርመውና አምራች ዜጋ ሆነው መውጣታቸውን ይከታተላል፡ ፮ በኮሚሽኑ የሚቀርቡትን የአደረጃጀት ፣ እና የአቅም ግንባታ መርሐ ግብር ጥናቶች ይመረምራል ፣ ያፀድቃል ፣ ፮ . የኮሚሽኑን የሥራ ብቃትና ውጤታማነት ለማሳደግ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ፣ የቁጥጥር ሥራ ያከና ፰ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም የሚረዱ አስፈላጊ እርምጃዎች ይወስዳል ። ፲ . የኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ኮሚሽነሩ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ሆኖ የኮሚሽኑን ሥራ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተባብራል ፣ ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ኣነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ፡ ሀ ) የዋና መምሪያ ኃላፊዎች ምደባ እንዲፀድቅለት ለሚ ኒስትሩ ያቀርባል ፣ ለ ) የኮሚሽኑን መተዳደሪያ ደንቦች ያስፈጽማል ፣ ሐ ) ለሥራ ኣስፈላጊ የሆነ የማረሚያ ጥበቃ አባላት ይመለምላል ፣ ይቀጥራል ፣ ያሰለጥናል ፣ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ መ ) በፌዴራል ማረሚያ አቤቱታ ሰሚ አካል እና በዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚሰጡ ውሳኔዎች በይግባኝ ሲቀርቡለት ይወስናል ሠ ) የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ እቅድና ረቂቅ በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ በፌዴራል መንግሥት ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ረ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደለት በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ የኦዲትና የኢንስፔክሽን ሥራዎች እንዲሠሩ ያደርጋል ፣ ሰ ) የኮሚሽኑን አደረጃጀት ፣ አሠራርና አቅም ግንባታ የሚመለከቱ ጥናቶች ፣ የታራሚዎችን አጠባበቅና አያያዝ ለማሻሻል የሚረዱ ጥናቶች ፣ እንዲሁም የማረሚያ ጥበቃ ሙያና አገልግሎት ተመሳሳይነት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶች እንዲከናወኑ ያደርጋል ፣ ሸ ) በኮሚሽኑ እና በክልል ማረሚያ ቤቶች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ያደርጋል ፣ ቀ ) የኮሚሽኑን የአመራር ጉባዔ በስብሳቢነት ይመራል ፣ በ ) ኮሚሽኑን አስመልክቶ የውጭ ግንኙነት ያደርጋል ። ፲፩ የምክትል ኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ምክትል ኮሚሽነሩ ፦ ሀ ) የኮሚሽኑን ተግባራት በማቀድ ፣ በማደራጀት ፣ በመ ምራትና በማስተባበር ኮሚሽነሩን ይረዳል ፣ ለ ) በኮሚሽኑ መዋቅር መሠረት የሥራ ክፍፍሎች በማድረግ ከኮሚሽኑ ዘርፎች ከፊሉን ይከታተላል ፣ ገጽ ፪ሺ፫፻፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፷፭ ዓም ሐ ) ኮሚሽነሩ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶት ይሠራል ፣ መ ) በኮሚሽነሩ ተለይተው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፪ ምክትል ኮሚሽነሩ ተጠሪነቱ ለኮሚሽነሩ ይሆናል ። ፲፪ በጀት የኮሚሽኑ በጀት በፌዴራል መንግሥት ይመደባል ። ፲፫ • የሂሣብ መዛግብትን የሂሳብ ምርመራ ፩ ኮሚሽኑ የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ፣ ፪ የኮሚሽኑየሂሳብ መዛግብትናገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ክፍል ሦስት ስለ ፌዴራል ማረሚያ ጥበቃ አስተዳደር ፲፬ ለማረሚያ ጥበቃ አባልነት የሚያበቁ መመዘኛዎች ፩ በፌዴራል ማረሚያ ጥበቃ ኣባልነት ለመመልመል ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚከተሉትን መመዘኛዎች በሙሉ ማሟላት ይኖርበታል ሀ ) ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ተገዥ የሆነ ፣ ለ ) ለማረሚያ ጥበቃ ኣባልነት ለመመልመል የሚያበቃ የትምህርት ደረጃ፡ አካላዊ ብቃት እና የተሟላ ጤንነት ያለው ፣ ሐ ) መልካም ሥነ ምግባር ያለው ፣ መ ) በፍርድ ቤት የተወሰነ የወንጀል ጥፋተኛነት የፍርድ ሪኰርድ የሌለው ሠ ) ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ፣ ረ ) የማረሚያ የጥበቃ ሙያ ሥልጠናን ያጠናቀቀ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚደረገው ምልመላ የፆታ ፣ እንዲሁም የብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሚዛናዊ ተወጽኦ ያካተተ ይሆናል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የተመለመለ ማንኛውም ዜጋ የፖለቲካ ድርጅት አባል የሆነ እንደሆነ በማረሚያ ጥበቃ ሲቀጠር የፖለቲካ ድርጅት አባልነቱን መተው ይኖርበታል ። ፲፭ ቃለ መሐላ ስለመፈፀም ለማረሚያ ጥበቃ ሥራ የተቀጠረ ማንኛውም ምልምል ለፌዴራሉ ሕገ መንግሥት ታማኝ በመሆን የተጣለበትን ሕዝባዊ አደራና ሙያዊ ኃላፊነት ለመወጣት ቃለ መሐላ ይፈጽማል ። የቃለ መሐላው ይዘት በደንብ ይወሰናል ። ፲፮ : የአገልግሎት ዘመን ፩ : የማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ አባል የግዴታ አገልግሎት ዘመን ሰባት ዓመት ይሆናል ። ዝርዝር አፈጻጸሙ በደንብ ይወሰናል ፣ ፪ የማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ አባል ቅጥር ከሚከተሉት መካከል በማናቸውም ምክንያት ይቋረጣል ሀ ) በሞት ፣ ለ ) በደንቡ መሠረት የስንብት ጥያቄ ቀርቦ ተቀባይነት ሐ ) በሐኪሞች ቦርድ በተረጋገጠ ሕመም ወይም የአካል ጉዳት ለሥራው ብቁ ሳይሆን ሲቀር ፣ መ ) በፍርድ ቤት በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘና በደንቡ መሠረት ወንጀሉ ለሥራው ብቁ አያደር ገውም ተብሎ ሲወሰን ፣ ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል ፣ ሠ ) በሥራ አፈጸጸም ወይም ዲሲፕሊን ጥፋት ፣ ገጽ ፪ሺ፫፻ሮ፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ጳጉሜ ፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ረ ) በጡረታ ሲገለል ። ፲፯ መብት ፩ . ማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ አባል ፦ ሀ ) በፌዴራል መንግሥት በሚፀድቅ የደመወዝ ስኬል መሠረት ደመወዝ ያገኛል ፣ ለ ) በኮሚሽኑ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት ቀለብ ፣ ልዩ ልዩ አበሎች ፣ የደንብ ልብስና የሕክምና አገልግሎት ያገኛል ፣ ሐ ) በጡረታ ሕግ መሠረት የጡረታ መብት ይኖረዋል ፣ መ ) ሥራውን በተገቢው መንገድ በመወጣት ላይ እያለ ለሚደርስበት ተጠያቂነት በመሥሪያ ቤቱ ወጪ የጥብቅና አገልግሎት ያገኛል ፣ ዝርዝር አፈጻጸሙ በደንብ ይወሰናል ፣ ሠ ) ከሥራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ወይም ከፊል የመሥራት ችሎታውን በዘላቂነት ያጣ የማረሚያ ጥበቃ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ የተሰጠው መብት ይከበርለታል ። ፪ . ማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ አባል ፦ ሀ ) የበላይ ኃላፊዎችን በአግባቡ የመጠየቅ ፣ ስህተት ሲያይ የመጠቆም እና ችግሮችን በውይይት የመፍታት መብት አለው ፣ ለ ) የሥልጣን ተዋረድን ጠብቆ ኣቤቱታ ማቅረብ ይችላል ። ፲፰ ግዴታ ማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ ኣባል፡ ፩ . በሕገ መንግሥቱና ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መሠረት የተረጋገጡትን ሰብዓዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ በማክበር እንዲሁም በሌሎች አግባብ ባላቸው ሕጐች መሠረት ሥራውን የማከናወን ፣ ፪ የማረሚያ ጥበቃ ሥራውን ሲያከናውን ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ የማሳየት ፣ ግዴታ አለበት ። ፲፱ • የጡረታ መውጫ ዕድሜ ማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ አባል በጡረታ የሚገለልበት ዕድሜ ጣሪያ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ መሠረት ለመን ግሥት ሠራተኞች የተወሰነው የጡረታ መውጫ ዕድሜ ይሆናል ። ፳ ስለ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አቤቱታ ሰሚ በኮሚሽኑ ውስጥ አቤቱታ የሚሰማ የፌዴራል ማረሚያ ኮሚሽን ኣቤቱታ ሰሚ አካል ይቋቋማል ፡ ዝርዝሩ ኮሚሽኑ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ፳፩ : ስለ መተዳደሪያ ደንብ የማረሚያ ጥበቃ አባሎች መተዳደሪያ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወጣል ። ክፍል አራት ስለታራሚዎች አያያዝ ፳፪ : መ ር ህ ፩ ታራሚዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታ ዎች የመያዝ መብት አላቸው ፣ ፪ • የታራሚዎች አያያዝ ፣ ታራሚዎቹ የተወሰነባቸውን ቅጣት ጨርሰው ሲወጡ ሕግ አክባሪ ሆነው ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር የሚያስችላቸው መሆን ይኖር በፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ያሉ እንዲሁም የፍትሐብሔር ታራሚዎች ከወንጀል ድርጊት ነፃ እንደሆኑ ተቆጥረው በወንጀል ቅጣት ከተወሰነባቸው ታራሚዎች ተለይተው መያዝ ይኖርባቸዋል ። ፳፫ : ታራሚን ስለመቀበል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር ኮሚሽኑማንኛውንም | 23. Admission of Prisoners ሰው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ መቀበል የለበትም ። ገጽ ፪ሺ፫፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ፳፬ • ልዩነት ማድረግ የተከለከለ ስለመሆኑ በታራሚዎች መካከል በፆታ ፣ በሃይማኖት ፣ በፖለቲካ አመለ ካከት ፣ በብሔር ብሔረሰብ አባልነት ወይም በማኅበራዊ ምንጭ ልዩነት ማድረግ የተከለከለ ነው ። ፳፭ ታራሚዎችን በፈርጅ ለይቶ ስለመያዝ ፩ ሴት ታራሚዎች ከወንድ ታራሚዎች ሙሉ በሙሉ የተለዩ ክፍሎች ይኖራቸዋል ፣ ፪ ሁኔታው በፈቀደ መጠን ታራሚዎች ፣ በዕድሜያቸው ፣ በፈጸሙት ወንጀልና በሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች ተለይተው መያዝ ይኖርባቸዋል ። ፳፮ : የታራሚዎች ክፍሎች ሁኔታ ፩ ታራሚዎች የሚኖሩባቸው ክፍሎች እና ግቢያቸው በጤና ላይ ጉዳት የማያስከትሉ ፣ ንፁህ አየርና በቂ ብርሃን የሚያገኙ መሆን ይኖርባቸዋል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የታራሚዎች መኖሪያ ክፍሎች ሲዘጋጁታራሚው በሚያ ሳየው የባህርይ ለውጥና በወንጀል ድርጊት የመፀፀት ሁኔታ አኳያ ለይቶ ለመጠቀም የሚያስችሉና ታራሚ ዎችን በቀና ተወዳዳሪነት መንፈስ ወደመታረምና ተሃድሶ የሚያተጉ ሊሆኑ ይገባል ። ፳፯ ስለምግብና የጤንነት እንክብካቤ ታራሚዎች በተቻለ መጠን ጤናቸውን ለመጠበቅ የሚያበቃ ቸውን በቂ ምግብና አስፈላጊውን የሕክምና አገልግሎት በነፃ ማግኘት ይኖርባቸዋል ። ፳፰ ሕፃን ልጅ ስላላት ሴት ታራሚ ለልጁ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፣ ዕድሜው ከአሥራ ስምንት ወራት ያልበለጠና የእናቲቱ የቅርብ ክት የሚያስፈልገው ሕፃን ከሴት ታራሚ እናቱ ጋር አብሮ ማረሚያ ቤት ውስጥ ሊቆይ ይችላል ፣ ፪ ኮሚሽኑ ለልጁ ጤንነትና እንክብካቤ አስፈላጊውን የማድረግ ኃላፊነት አለበት ፣ ፫ የእናቲቱ የእሥር ቆይታ በልጁ አካላዊ ወይም ሥነ ልቦናዊ አቋም ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ሆኖ ሲገኝ ሕፃኑ አሳዳጊ ወይም ሞግዚት እንዲያገኝ ኮሚሽኑ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ። ፳፱ ከጎብኚዎች ጋር ስለመገናኘት ታራሚዎች ከትዳር ጓደኞቻቸው ፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ፣ ከጓደኞቻቸው ፣ ከሐኪሞቻቸው ፣ ከሕግ አማካሪዎችና ከሃይ ማኖት አባቶች ጋር የመገናኘት መብት አላቸው ፣ ዝርዝሩ ኮሚሽኑ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ፴ ስለመታሠርና ዝውውር መረጃ የማስተላለፍ መብት ማንኛውም ታራሚ መታሠሩን ወይም በማናቸውም ምክንያት ከታሠረበት ተቋም ወደ ሌላ ተቋም መዛወሩን ወዲያውኑ ለቤተሰቦቹ ወይም ለሚፈልገው ሰው የመናገር መብት አለው ። ፴፩ በሥራ ስለማሠማራትና ስለ ፈቃድ በፍርድ ቤት የተወሰነበትን ቅጣት በማረሚያ ቤት | 31. Engagement in work and permission በመፈፀም ላይ ያለ ማንኛውም ታራሚ ከችሎታውና ከሙያው ጋር የሚስማማና ጤንነቱን የማይጎዳ ተመጣጣኝ ሥራ እንዲሠራ ይደረጋል ፣ በኮሚሽኑ በሚወጣ መመሪያ መሠረት እንደሁኔታው ለሥራው ክፍያ ያገኛል ፣ ፪ . ታራሚዎች በማረሚያ ጥበቃ አባል አጃቢነት ለልዩ ልዩ ማኅበራዊ ችግሮቻቸው ማቃለያ ፍቃድ የሚያገኙበት ሁኔታ በመመሪያ ይወሰናል ። ገጽ ቪጀት ፤ ዱራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጳጉሜ ፪ ቀን ፲፱፵፩ ዓም • ፴ጅ የታራሚ ግዴታዎች ለጥበቃ ሥራ ሥነ ሥርዓት አከባበር ጽዳት፡ ጤና አጠባበቅ፡ ማኅበራዊ ግንኙነት እና ስለሌሎችም ጉዳዮች በሚወጣ ደንብ ወይም መመሪያ የሚገለጹ የሥነ ሥርዓት ግዴታዎችን ታራሚዎች የማክበር ግዴታ አለባቸው ። ፴ የወንጀል ድርጊት ማንኛውም ታራሚ በማረሚያ ቤት ቆይታው የወንጀል ድርጊት ቢፈጽም በወንጀል ሕግ ተጠያቂ ይሆናል ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴፬ ኮሚሽኑ ከክልል ማረሚያ ቤቶችኃላፊዎች ጋር ስለሚኖረው የሥራ ግንኙነት ፩ የማረሚያ ቤቶችን አስተዳደርና አሠራር የታራሚ ዎችን አያያዝና አጠባበቅ ለማሻሻል ፣ እንዲሁም ለማረሚያ ጥበቃ አባሎች እና ሠራተኞች የሥልጠና ዕድሎችን ለማመቻቸት ፣ ከክልል ማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች ጋር ግንኙነት ያደርጋል ። ፪ ኮሚሽኑና የክልል ማረሚያ ቤትኃላፊዎች በጋራ በሚወ ስኑት በማናቸውም ጊዜ የጋራጉባኤ ሊያካሂዱ ይችላል ፣ የጋራ ጉባኤውን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር ይመራል ፣ የጋራ ጉባኤው፡ ሀ ) የጋራ የአሠራር ውስጠ ደንብ ያወጣል ፣ ለ ) የማረሚያ ቤቶች የሥራ እንቅስቃሴዎችን በመገ ምገም የልምድ ልውውጥ ያደርጋል ፣ የአሠራር ደንብና መመሪያዎች በይዘት ረገድ እንዲሻሻሉና ወጥነት እንዲኖራቸው ያደርጋል ፣ ሐ የማረሚያ ጥበቃ የሥልጠናን ኣቅጣጫ ይዘትና ደረጃን በሚመለከት በጋራ ይቀይሳል ፣ መ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት በኮሚሽኑ በሚቀርቡ ጥናቶች ላይ ይወያያል ፣ በጥናቶቹ መሠረት ሊወሰዱ የሚገ ባቸው እርምጃዎች እንዲወሰኑ ለሚመለከተው አካል ያቅርባል ፣ እንደየሁኔታው በአግባቡ ይወስናል ፣ በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል ። ፭ ኮሚሽኑና የክልል የማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች በጋራ ጉባኤው ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች መተግበራቸውን በየበኩላቸው ይከታተላሉ ። ፮ የክልል ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት ሪፖርትና ስታትስቲክስ በየጊዜው ለኮሚሽኑ ያስተላልፋሉ ። ፴፭ ወታደራዊ ማዕረግ ስለመቅረቱ ፩ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ የማረሚያ ጥበቃ አባል ወታደራዊ ማዕረግ አይኖረውም፡ ሆኖም የማረሚያ | 35. Termination of military ranks ጥበቃ አባል የሆነማዕረግናምልክትይኖረዋል ። ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል ፣ ጅ ማንኛውም የማረሚያ ጥበቃ አባል የሥራ መደቡን የሚያመለክት የመለያ ደንብ ልብስ እንዲሁምማንነቱን የሚገልጽ ፣ ስሙን ፣ መለያ ቁጥሩን ፣ ክፍሉንናኃላፊነቱን የያዘ ባጅ ወይም ምልክት ይኖረዋል ። ፪ አሠራር ፩ . በኮሚሽኑ መዋቅር በየደረጃው ባሉት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የቡድን አሠራር ዋና ተግባር አፈጻጸም አቅጣጫ ይሆናል ። የቡድን አሠራሮች የጋራና የነጠላ ኃላፊነትን ያስከትላሉ ፣ # በኮሚሽኑ መዋቅር በየደረጃው የሚገኙኃላፊዎች በተሰ ጣቸው ሥልጣን መሠረት በመወሰን ኃላፊነታቸውን የመወጣት ግዴታ አለባቸው ፣ ገጽ ፪ሺ፫፻ኞቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም • ፫ • የኮሚሽኑ አሠራር የተጠያቂነትና የግልጽነትን መርህ የተከተለ ፣ እንዲሁም የሕዝብ ተሳትፎን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል ። ፴፯ የተከለከለ ድርጊት ማንኛውም ኢሰብአዊ ወይም ክብርን የሚነካ አያያዝ ወይም ድርጊት የተከለከለ ነው ። ፴፰ የተሻሩ እና ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ፩ . የወህኒ ቤቶች አስተዳደርን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር ፴፭ ፲፱፻፴፮ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ፣ ፪ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሌላ ሕግ በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም ። ፴፱ : ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚረዳ ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፣ ፪ • ኮሚሽኑ ይህን አዋጅ እና በአዋጁ መሠረት የሚወጣ ደንብን ለማስፈጸም የሚረዱ መመሪያዎችን የማውጣት ሥልጣን ይኖረዋል ። ፵ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጳጉሜ ፬ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት