ሠላሳ አራተኛ ዓመት ቍጥር ፵
መ ን ግ ሥ ት
ነ ጋ ሪ ት ' ጋ ዜ ጣ ።
የጋዜጣው ፡ ዋጋ ፤ ባገር ' ውስጥ ' q መት '
» በ፮ ' ወር ' ያንዱ '
ማ ው ጫ
፲፱፻፷፯ ዓ. ም.
አዋጅ ቊጥር ፵፮ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም.
የ፲፱፻፷፰ ዓ. ም. የበጀት አዋጅ
አዋጅ ቊጥር ፵፮ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም.
ለመንግሥት ሥራዎች የታወጀ የበጀት ዓዋጅ
በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ
ሊቀ መንበር ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
« ኢትዮጵያ ትቅደም »
የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግንና የሊቀ መንበሩን ሥልጣን ለመወሰን በወጣው ዓዋጅ ቊጥር ፪ ፲፱፻፷፯ ዓ: ም. አንቀጽ ፮ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ያለው ታውጅዋል "
ገጽ ፩፻፶፭
፩ ይህ አዋጅ « የ፲፱፻፷፰ ዓ. ም. የበጀት አዋጅ ቊጥር ፵፮ ፲፱፻፷፯ ዓ. ም. » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል
፪ ከሐምሌ ፩፷፯ ዓ. ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ ፴፷፰ ዓ ም. በሚፈጸመው አንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ በአገሪቷ ከሚገኘው ገቢ ገንዘብ ወይም ከሌላ ገንዘብ ላይ ከዚህ ቀጥሉ በሚገኘው ሠንጠረዥ ውስጥ ለተጠቀሱት ሥራዎችና አገልግሎቶች የኢት 1.330.966.574 (አንድ ቢሊዮን ሦስት መቶ ሠላሳ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ስድሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰባ አራት የኢት ብር ወጪ ሆኖ እንዲከፍል በዚህ አዋጅ ተፈቅዷል ።
፫ ሚኒስትሮች ወይም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የየሚኒስ ቴሩ መቤት የበላይ ባለሥልጣኖች - ለመ ቤታቸው ሥራና አገልግሎት የተፈቀደላቸውን በጀት በሚጠይ ቁበት ጊዜ የገንዘብ ሚኒስትሩ እንዲከፈል ተፈቅዷል
፬ በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ወጪ ከአንድ አርእስት ወደሌላ አርእስት ወይም ከንዑስ አርእስት ዝርዝር ወደሌላ በሚከተሉት ሁኔታዎች ማዛወር ይቻላል ።
አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ. ም.
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይታተማል
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ፴፩ (1031)