ሠላሳ ሰባተኛ ዓመት ቍጥር ፫
የጋዜጣው ፡ ዋጋ
ባገር ውስጥ ፡ ባመት '
በ፮ ፡ ወር ' ያንዱ ፡
፡
ወ ታ ደ ራ ዊ መ ን ግ ሥ ት
ነ ጋ ሪ ት ፡ ጋ ዜ ጣ ።
12 ብር
ማ ው ጫ
አዋጅ ቊጥር ፩፻፴፪ ፲፱፻፸ ዓ. ም.
የሕጋዊ የገንዘብ ኖቶች ሕጎች ማጠናከሪያ አዋጅ (ማሻሻያ) አዋጅ
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፶፯ ፲፱፻፸ ዓ. ም. የሕጋዊ ቅንስናሽ ገንዘቦች ደንብ
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፶፰ ፲፱፻፸ ዓ. ም. የኢትዮጵያ የስኳር ድርጅት ማቋቋሚያ
q ኅብረተሰብኣዊት - ዜያዊ ወታደራ
በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
ገጽ ፲፱
ገጽ ፳፩
አዋጅ ቍጥር ፩፻፴፪ ፲፱፻፸ ዓ. ም.
የሕጋዊ የገንዘብ ኖቶች ሕጎች ማጠናከሪያ አዋጅን
ለማሻሻል የወጣ አዋጅ
ገጽ ፳፪
« ኢትዮጵያ ትቅደም »
የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግንና የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ኃላፊነት እንደገና ለመወሰን በወ ጣው አዋጅ ቍጥር ፩፻፲ ፲፱፻፷፱ ዓ. ም. በአንቀጽ ፭ ፮) መሠ ረት ቀጥሎ የተመለከተው ታውጅዋል ።
፩ ፤ አጭር ርእስ ፤
ይህ አዋጅ « የሕጋዊ የገንዘብ ኖቶች ሕጎች ማጠናከ ሪያ አዋጅ (ማሻሻያ) አዋጅ ቍጥር ፩፻፴፪ ፲፱፻፸ ዓ. ም. » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ።
ኢትዮጵያ መን 7 ሥት
፪ ፤ መሻሻል
የሕጋዊ የገንዘብ ኖቶች ሕጎችን ለማጠናከር በወጣው አዋጅ ቍጥር ፩፻ ፲፱፻፷፱ ዓ. ም. አንቀጽ ፬ ውስጥ የሚ ከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ፫ በመጨመር ተሻሽሏል ፤ « ፫- የሕጋዊ ቅንስናሽ ገንዘቦች ደንብ ቍጥር ፶፯ ፲፱፻፸ ዓ. ምን የጣሰ ማናቸውም ሰው ወይም የሕግ ሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት በልዩ የጦር ፍርድ ቤት ተ h ሶ ሲፈረድበት እስከ ፶ሺ (ሃምሳ ሺህ) ብር በሚ ደርስ የገንዘብ መቀጮ ወይም እስከ ፲ (አሥር) ዓመት በሚደርስ እሥራት ወይም በሁለቱም ይቀጣል " »
አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፲ ቀን ፲፱፻፸ ዓ. ም.
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይታተማል ።
የፖስታ ሣጥን ቊጥር ፩ሺ፴፩ (1031)