×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 22/1990 የፍትህና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፰ አዲስ አበባ ኅዳር ፲፮ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፪ / ፲፱፻፲ ዓ.ም የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፭፻፶፫ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፪ / ፲፱፻፲ የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲ ያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርእስ ይህ ደንብ “ የፍትህና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፪ ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፩ የፍትህና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰው ነት ያለው ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፫ ዋና መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት በኣዲስ አበባ ሆኖ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሲኖረው ይችላል ። የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የፍትህና የሕግ ሥርዓቱን ብቁና ዘመናዊ ለማድረግ ፥ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፮፻፶፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ኅዳር ፲፮ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፩ የሀገሪቱን ሕጎች ፡ ሀ ) ሕገ መንግሥቱን በተሟላ ሁኔታ ሥራ ላይ ለማዋል ፡ ለ ) የሕግን የበላይነት ለማረጋገጥ ፡ እና ሐ ) የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ልማትን ለማፋጠን ፡ በሚያስችል መልክ ለማሻሻል ፡ እና የፍትህ አካላትን ኣቅም ለመገንባትና ሥራቸውን ለማቀላ የሚረዱ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ ይሆናል ። ፭ ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . በሥራ ላይ ያሉ የሀገሪቱን ሕጎች በመገምገም የሕግ ማሻሻያ ምርምር ፕሮግራሞችን መንደፍ ፤ ፪ በየዘርፉ ያሉ ነባር ሕጎችን ለማጠቃለል ፡ ከወቅቱ የዕድገት ደረጃ ጋር ለማጣጣምና ለአጠቃቀም ምቹ ሆነው እንዲሻሻሉ ለማድረግ የሚያስችል ጥናትና ምርምር ማካሄድ ፣ የሀገሪቱን የሕግ ሥርዓት የተሟላ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ ሕጎችን ለማውጣት የሚረዱ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ ፣ ፬ የፍትሕ አካላት ሥራዎችን ለማቀላጠፍ የሚረዱ ጥናቶችን ማካሄድ ፣ ፭ ሕግ ነክ መረጃዎችንና የጥናትና ምርምር ውጤቶቹን ማሳተ ምና ማሰራጨት ፣ ፮ : የፍትሕና የሕግ ሥርዓቱን በማሻሻል ረገድ የፌዴራልና የክልል አካላትን መርዳት ፣ ፯ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የሕግ ትምህርትና ሥልጠናን ለማጠናከር የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድና ለተግባራዊነታቸውም አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ፤ ፰ ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ። ፮ . የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፡ ፩ አንድ ቦርድ፡ ፪ አንድ ዲሬክተር ፡ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፡ ይኖሩታል ። ፯ የቦርድ አባላት ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ ከሺ የማያንሱና ከ፬ የማይበልጡ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ፰ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩- የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፡ ይቆጣጠ ፪ . የኢንስቲትዩቱን ዲሬክተር ለመንግሥት አቅርቦ ያሾማል ፤ ፫ . የኢንስቲትዩቱን የሥራፕሮግራሞችና በጀትገምግሞ ለመን ግሥት ያቀርባል ፡ ሲፈቀዱም ተግባራዊነታቸውን ይከታተ ፬ . በኢንስቲትዩቱ ተጠንተው የሚቀርቡ የፍትህና የሕግ ሥር ዓት ማሻሻያ ሀሳቦችን ገምግሞ ለመንግሥት ያቀርባል ፤ ፭ የኢንስቲትዩቱን መዋቅርና የውስጥ ደንቦች ያፀድቃል ፡ ፮ . ለዲሬክተሩ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ኃላፊዎችን ምደባና ስንብት ያፀድቃል ፤ ፮ በኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር በሚቀርቡ ሌሎች የፖሊሲ ጉዳ ዮች ላይ መክሮ ይወስናል ፣ . ¢ መን ገጽ ፮፻፶፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ኅዳር ፲፮ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፰ የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ ያፀድ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን ያደርጋል ። እንዳስፈላጊነቱም አስቸኳይ ስብሰባ በማናቸውም ጊዜ ሊያደ ርግ ይችላል ። ፪ በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባላት በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ! ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረ ፩ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲ : ስለ ዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ . የኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈ ጻሚ ሆኖ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች ይመራል ያስተዳድራል ። ፪ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዲሬክተሩ ' ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የኢንስቲትዩ ቱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ! ለ ) ቦርዱ በሚያፀድቀው የውስጥደንብ መሠረት የኢንስቲ ትዩቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ' ያስተዳድራል ! ሐ ) የኢንስቲትዩቱን ፕሮግራሞች በጀት አዘጋጅቶ ለቦ ርዱ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ! መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግ ራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ! ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ : ኢንስቲትዩቱን ይወክላል ! ረ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸምና አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፫ ዲሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ ከሥልጣንናተግባሩ በከፊል ለኢንስቲትዩቱ ሠራተኞችበውክ ልና ሊያስተላለፍ ይችላል ፡ ሆኖም ዲሬክተሩ በማይኖር ጊዜ እርሱን ተክቶ የሚሠራው ሰው ከ፴ ቀናት በላይ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ ለቦርዱ ቀርቦ መፈቀድ አለበት ። ፲፩ : በጀት ፩ የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፣ ሀ ) በመንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፣ ለ ) ከሕትመቶች ሽያጭ የሚያገኘው ገቢ ፣ ሐ ) ከሚያገኘው ማናቸውም ስጦታና እርዳታ ፣ መ ) ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) / ለ ፡ / ሐ / እና መ / የተመለከተው ገንዘብ በኢንስቲትዩቱ ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ሆኖ የኢንስቲትዩቱን ዓላማዎች ለማስፈጸም ወጪ ይሆናል ። ፲፪ የሂሳብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ገጽ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣጥር ፥ ኅ ፲ ፲ ዓ.ም የኢንስቲትዩቱ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦተ ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱይመረመራሉ * ፲፫ ደንቡ የሚጸናበትጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላናይሆናል " አዲስ አበባ ኅር ፲ ቀን ፲ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብር ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?