×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 17191

      Sorry, pritning is not allowed

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ .17191
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ወ / ሮ አስቴር አርአያ
መልስ ሰጪ፡- አቶ ግርማ ወይጆ
የውል ጉዳይ አወሳሰን - ስለ ውሎች ውጤት- ውልን በመተርጎም ሰበብ ዳኞች
አንድ ውል ሊፈጥሩ ስላለመቻላቸው
ስለ አንዳንድ ውሎች የተፃፉ ልዩ ደንቦች የፍትሐብሔር ህግ ቁጥሮች 1711፣1731፣1676 / 2 / ፣ 2635፣2640፣2646
የፌደራል ከፍተኛ ፍ / ቤት አመልካች ባቀረበችው ክስ በጠየቀው መሰረት
አመልካችና ተጠሪ ከከፈለው በር 35.000 / ስላሳ አምስት ሽህ / በተጨማሪ በፍርዱ
ከተገኘው ጥቅም 2 ዐ % ብር 124.188.59 / አንድ መቶ ሃያ አራት ሺህ አነድ መቶ
ሰማንያ ስምንት ብር ከሃምሣ ዘጠኝ ሳንቲም / ለአመልካች እንዲከፍል ሲወሰን ጉዳዩ
በይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት በበኩሉ አመልካች ለሰጠው አገልግሎት
ካገኘችው መደበኛ ክፍያ በተጨማሪ ከፍርድ ከሚገኘው ጥቅም 2 ዐ % ታስቦ እንዲከፈላት
በውል የተደረገው ቃል በፍትህ ሆነ በርትዕ የሚደገፍ አይደለም በሚል የከፍተኛውን
ፍ / ቤት ውሳኔ በመሻሩ የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ውሳኔ ተሻሽሏል
ህግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች ውጭ ተዋዋይ ወገኖች የሚዋዋሉበትን
ጉዳይ እንደፈለጋቸው የመወሰን መብት ያላቸው ሲሆን በዚህ መሰረት የሚደረጉ
የውል ስምምነቶች በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ ፡፡
ሆኖም ልዩ የዕውቀት ጠበይ ያላቸውን የስራ ውሎች የሚያደርጉ ተዋዋዮች
ስምምነት ላይ የደረሰባቸው የሥራ ዋጋዎች ከመጠን በላይ መሆናቸውን ግልጽ
በሆነ ጊዜ እና ለሙያ ሥራ ተግባሩም ክብር ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ መጠኑን
ዳኞች በመ
ው ሊቀንሱት ይችላሉ ፡፡
የመ / ቁ .17191
ሐምሌ 29 ቀን 1997 ዓ.ም
• በአፍ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡ ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ » አብዱልቃድር መሐመድ 4. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
5. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች አስቴር አርአያ
ግርማ ወዳጆ
መዝገቡን መርምረን
በሰበር ችሎቱ ለቀረበው ጉዳይ መነሻ የሆነው ክስ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ በሰጡት የጥብቅና አገልግሎት ሥራ የካቲት 3 ቀን 1987 ዓ.ም የተደረገውን የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ውል መሠረት በማድረግ ተጠሪ ለአመልካች ከከፈለው ብር 35 , ዐዐዐ ( ሠላሣ አምስት ሺ ) በተጨማሪ “ ከፍርዱ ከሚገኝ ጥቅም * 20 % ሊከፍል የተስማሙበትን ብር 52 ዐዐዐዐ ( አምስት መቶ ሃያ ሺ ብር ) አመልካች በክሱ ምክንያት ካወጣው ወጭና የጠበቃ አበል ጋር ይከፈል በማለት ክስ መስርቷል ፡፡
ፍ / ቤቱም ግራቀኙን አከራክሮ የአሁኑ ተጠሪ « ጥቅም » አላገኘሁም በሚል በሙያ አገልግሎቱ ውል የተስማማበትን ክፍያ አልከፍልም ማለቱ አግባብ አለመሆኑን ገልጾ ፣ የቤቱን ሽያጭ ዋጋ ግምት መሠረት በማድረግ 124,188,59 ( አንድ መቶ ሃያ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከሃምሣ ዘጠኝ ሣንቲም ) የዳኝነቱንና የጠበቃ አበሉን ጨምሮ ይክፈል በማለት ወስኗል ፡፡
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት በበኩሉ ፣ አንድ የጥብቅና ሙያ አገልግሉት የሚሰጥ ሙያተኛ ለአገልግሎቱ እንዲከፈለው ከተወሰነለት መደበኛ ክፍያ
3. ፊታወቀው ማንኛውም ውል በተዋዋይ ወገኖች ፈቃድ ላይ ተመስርቶ በተጨማሪ ከፍርድ ከሚገኘው ጥቅም » ታስቦ እንዲከፈለው የሚደረግ የውል ቃል በርትዕም ሆነ በፍትህ የሚደገፍ አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙሉ ሽሮታል ፡፡
የአሁኑ አመልካች በሰበር እንዲታይለት ያቀረበው ማመልከቻ የህግ ትርጉም የሚያስነሱ ነጥቦች ያሉት መሆኑን በማመን ጉዳዩ ለሰበር እንዲቀርብ ተድርጓል ፡፡ በዚህ መሠረት ተጠሪ መልሱን አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን እንዲያቀርቡ ተደርጎ ክርክሩ አብቅቷል ::
ይህ የሰበር ችሎት ጉዳዩን መርምሯል ፡፡ በዚህ ጉዳይ በዋንኛነት የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ጭብጥ የእውቀት ጠባይ ያላቸው የሥራ ውሎችን አስመልክቶ በተዋዋይ
ስምምነት በተደረሰባቸው አለመግባባቶች ሲነሱ የዳኞች ሚና ምን ይሆናል ? የሚለው ነጥብ ነው ::
የሚደረግ ስምምነት · ነው :: ህግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች ውጭ ተዋዋይ ወገኖች የሚዋዋሉበትን ጉዳይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት ያላቸው መሆኑን የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1711
1 ያስገነዝበናል ፡፡ ውሉን ለመዋዋል ህጉ በሰጠው ነጻነት መሠረት የሚደረጉ የወል ስምምነቶች በግራ ቀኝ ተዋዋይ ወገኖች መካከል መብትና ግዴታዎችን የሚጥሉ በመሆናቸው ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ እንደ ህግ የሚያገለግሉ መሆናቸውን ከፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 1731 መገንዘብ ይቻላል ፡፡
በያዝነው ጉዳይ የአሁኑ አመልካችና ተጠሪ የካቲት 3 ቀን 1987 ዓ.ም የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ውል ያደረጉ መሆኑን ተረድተናል ፡፡ በዚህ ውል ስምምነት መሠረት ተጠሪ በህገወጥ መንገድ ተይዞብኛል የሚለውን ቤት በማስመለስ ረገድ የአሁኑ አመልካች ለሚያበረክተው ሙያዊ የጥብቅና አገልግሎት ብር 35,000 ( ሠላሣ አምስት ሺህ ) ለመክፈልና ከፍርዱ ከሚገኘው ጥቅም 20 % ለመክፈል የተስማሙ መሆኑን ከሥር መዝገቡ ተረድተናል ፡፡ በዚህ የውል ስምምነት ቤት የተመለሰለት የአሁኑ ተጠሪ ብር 35 , ዐዐ ( ሠላሣ አምስት ሺህ ) ለአመልካች የከፈለ ቢሆንም ከፍርድ ከሚገኘው ጥቅም ለመክፈል የተስማሙበትን እንዲከፍል ክስ በቀረበበት ጊዜ « ጥቅም » አላገኘሁም በሚል ሲከራከር የቆየ ቢሆንም ጉዳዩን የመረመረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ውሉን መሠረት በማድረግ የንብረቱን ግምት አስልቶ ተጠሪ ብር 124,188.59 ( አንድ መቶ ሃያ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከአምሣ ዘጠኝ ሣንቲም ) እንዲከፍል በማለት ወስኗል ፡፡
ያግሳየት
እንደሞከርነው የየትኛውም ህጋዊ ውል መሠረቱ በፈቃድ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ / ቤት ከፍ ሲል የገለጽነውን የውል ህግ መሠረታዊ መርህ የሆነውን በፈቃደኝነት ወዶ መዋዋልን » መሠረት አድርጎ ውሣኔ የሰጠ ቢሆንም የዚህን መርህ አፈጻጸም በፍትሐብሄር ሕጉ ውስጥ አግባብ ካላቸው ልዩ ድንጋጌዎች ጋር እንዴት መገናዘብ እንደሚገባው ሳይመረምር ከውሣኔ እንደደረሰ ለመገንዘብ ችለናል ፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ /
ቤት በበኩሉ በግራቀኙ መካከል በህጋዊ መንገድና በፈቃደኛነት የተቋቋመን ግልጽ ውል ትርጉምንና ርትዕን ምክንያት በማድረግ የፍትሐብሔር ሕግ ቁ .1711፣1714 ( 2 ) እና 1733 ከሚደነግጉት ውጭ እና በወቅቱ በሥራ ላይ ያልነበረን ደንብ ዋቢ በማድረግ « ከፍርድ የሚገኝ ጥቅም አገልግሎት በሚደረግ ስምምነት ውስጥ ሊጠየቅ አይገባም በማለት ተዋዋይ ወገኖች በስምምነት ያስቀመጡትን ግልጽ የውል ቃል ያለምንም የውል ማፍረሻ ምክንያት ወድቅ እንዲሆን
መሠረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል ::
ከፍ ብለን መስጠት ላይ የተመሠረተ ስምምነት መሆኑ አያከራክርም :: ተዋዋይ ወገኖች ሕጉ በሰጣቸው ነጻነት ተጠቅመው ንብረትነትን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ፣ ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ስምምነት ማድረግ እንደሚችሉ ይታወቃል :: ይህ በጠቅላላ ክፍሉ የተነገረው የውል መሠረታዊ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህን ጠቅላላ ደንቦች የሚለውጡ ወይም የሚያሟሉ ስለ አንዳንድ ውሎች የተጻፉ ልዩ የሆኑ ደንቦች ካሉ በፍትሀብሄር ሕጉ 5 ኛ መጽሐፍ እና በንግድ ሕጉ የሚመለከቱ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 1776 ( 2 ) ያስገነዝባል ፡፡
በዚህ መሠረት አሁን ግራቀኙ እየተከራከሩበት ያለው ሙያዊ የዕውቀት ሥራን የሚመለከት ውል በፍትሐብሄር ህጉ በ 5 ኛው መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙት ውሎች መካከል አንደኛው እንደሆነ እንገነዘባለን ፡፡ ልዩ የእውቀት ጠባይ ያላቸው የሥራ ውሎች ደግሞ በፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 2632 እና በሚቀጥሉት ቁጥሮች ውስጥ በተመለቱት ድንጋጌዎች የሚመሩ ናቸው :: እነዚህ የውል ዓይነቶች ልዩ ዕውቀትን የሚመለከቱ በመሆናቸው የተለየ ስምምነት ከሌለ በቀር የእውቀት ሥራውን የተዋዋለው ሰው ግዴታዎቹን ራሱ መፈፀም እንደሚጠበቅበት ከህጉ ቁጥር 2636 ( 1 ) መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ተዋዋይ ወገኖች ውልን ፈቅዶ የመዋዋል መርህን ተጠቅመው እነዚህን ዓይነት መሰል ውሎች መዋዋል ቢችሉም በነዚህ ልዩ ውሎች መሠረት ስምምነት ላይ የተደረሱባቸወ የሥራ ዋጋዎች ከመጠን በላይ መሆናቸው ግልጽ በሆነ ጊዜ እና ለሙያ ሥራ ተግባሩም ክብር ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የሥራ ዋጋ መጠኑን ዳኞች በመሰላቸው ሊቀንሱት
* ጉዳይ ግራቀኙ የልዩ ዕውቀት ፀባይ ያለው የአገልግሎት ሥራ ውል እንደሚችሉ ተደንግጓል ፡፡ በዚህ ህግ ዓይነተኛ ዓላማ የተለየ ዕውቀት በሚሻው ጉዳይ ዙሪያ አማራጭ የሌለውን ወይም አማራጩ በእጅጉ ሊጠብበት የሚችለውን ተዋዋይ ወገን የሙያውን ተግባር ከሚያናውነውና ልዩ ዕውቀት ካለው ሙያተኛ ተዋዋይ ወገን ጋር ውልን ፈቅዶ በመዋዋል ረገድ የሚኖረውን ቦታ Position ) በተቻለ መጠን ለማቀራረብ እንደሆነ ይገመታል ፡፡ በዚህ ረገድ በአብነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት ጉዳዮች
መካከል ከቀዳጅ ሀኪሞች ፣ ከጥርስ ሐኪሞች ወይም ከአእምሮ በሽታ ሐኪሞች እና ሰዎችን ከማከም ኪነጥበብ ጋር ተያይዘው የሙያቸውን ተግባር የሚያናውኑ ሰዎች ከበሽተኞቻቸው ወይም ከወኪሎቻቸው ጋር ባደረጉዋቸው ውሎች መነሻነት ስምምነት የተደረሰባቸው የሥራ ዋጋዎች ከመጠን በላይ ሆነው በተገኙ ጊዜ እና ህይወትን መታደግ ዋንኛ ሙያዊ መርህ አድርጎ ከተነሣው ከህክምና ሙያ ክብር ጋር ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ዳኞች የዋጋውን መጠን ሊያሻሽሉት እንደሚችሉ የፍትህግ ቁጥር 264 ዐ እና 2646 ይደነግጋሉ ፡፡
በያዝነው ያደረጉ መሆኑ ይታመናል :: ንብረቱ የተወሰደበት የአሁኑ ተጠሪ ለሚሰጠው ሙያዊ አገልግሎት በውሉ የተመለከተውን ብር 35 , ዐዐ እና በፍርድ ከሚገኘው ጥቅም 20 % ለመስጠት ተስማምቶ የነበረ መሆኑን ይህ ችሎት በሚገባ ተገንዝቧል ፡፡ ይህ ስምምነት ውልን ፈቅዶ በመዋዋል መርህ ላይ ተመስርቶ የተደረገ ውል አይደለም ለማለት እንኳን የሚያስችል ነገር ባይኖርም ከፍ ብለን ከላይ ሕጉ ሊጠብቃቸው ከተነሣው ዓላማ አኳያ ጉዳዩን በጥልቀት ስንመረምረው የአሁኑ አመልካች በሥር ፍ / ቤት ለሰጡት ሙያዊ አገልግሎት ብር 35 , ዐዐ ( ሠላሣ አምስት ሺህ ) የተከፈላቸው መሆኑ ታውቋል ፡፡ ይህ ክፍያ ከንብረቱ ግምት አኳያ በመቶኛ ሲሰላ 17 % ይሆናል :: አሁን አመልካች በተጨማሪ እንዲከፈላቸው እየጠየቀ ያለው 20 % ከቀድሞው ክፍያ ጋር ሲደመር የአሁኑ አመልካች የጠቅላላ ቤቱን ግምት 37 % እየጠየቀ ያለ መሆኑ ታውቋል ፡፡ የተጠየቀው የገንዘብ መጠን ደግሞ ከንብረቱ ዋጋ ጋር ሲነጻጸርና በተለምዶም ለአገልግሎቱ ከሚጠየቀው ክፍያ ጋር ሲታይ እጅግ በጣም የተጋነነና ለሙያውም ሥራ ክብር ቢሆን ተቃራኒ የሆነ መሆኑን አምነንበታል ፡፡
በመሆኑም ስምምነት የተደረሰበት የሥራ ዋጋ መጠን የበዛ እና ለሙያ ሥራ ክብሩም ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ዳኞች መጠኑን እንዲቀንሱት ህጉ የሰጣቸውን
ተጠቅመን ለአመልካች የንብረቱን ግምት ማለትም የብር 620,942,98 ( ስድስት መቶ ሃያ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሁለት ብር ከዘጠና ስምንት ሣንቲም ) 1 ዐ % ( አሥር በመቶ ) የሆነውን ገንዘብ እንዲከፍል ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ
አግኝተነዋል :: አመልካች ቀደም ሲል በውሉ መሠረት የወሰደውን ብር 35 , ዐዐ ከክፍያው ገንዘብ ላይ ተቀናሽ ሊሆን የሚገባ መሆኑን አምነንበታል ::
ተጠሪ ብር 27,094.37 ( ሃያ ሰባት ሺህ ዘጠና አራት ብር ከሠላሣ ሣንቲም ) ይህ ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለአመልካች ይከፈል ፤ የዚህን ፍ / ቤት ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ ይቻቻሉ ፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ሐምሌ 8 ቀን 1996 ዓ.ም በፍ / ብ / ይ / መ / ቁ .14821 የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሏል ፡፡ መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?