የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፲፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፱ ፲፱፻፲፪ ዓም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ገጽ ፩ሺ፪፻፳፬ አዋጅ ቁጥር ፩፻፱ ፲፱፻፲፪ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስለሚሠሩ ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ የወጣ አዋጅ የጥብቅና አገልግሎት በሕግ ሙያ የሠለጠነና ሰፊ ልምድ ያለው፡ የፍርድ ቤት አሠራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ ፣ የታማኝነት ፣ የቅንነትና የእውነተኝነት መንፈስን የተላበሰ ሰው ለሕግ የበላይ ነትና ለፍትሕ መስፈን ከፍትሕ አካላት ጐን በአጋዥነት የሚሰለ ፍበት ሙያ በመሆኑ፡ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለመሥራት የሚችሉ ጠበቆችን ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ በተሟላ መልኩ በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ ፣ የጥብቅና ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን የሙያ ብቃት ደረጃ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር የተመጣጠነ ለማድረግ በሥራው ለመሠማራት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ከፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፱፲፱፻፲፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ « ፍርድ ቤት » ማለት የፌዴራል ፍርድ ቤቶችንና መሰል የዳኝነት አካላትን ያጠቃልላል ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ : ዥሺ፩ ገጽ እዚሩዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ጥር የካቲት ቀን ፲ዓም ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የሚረዱ ደንቦችን ሊያመጣ ይችላል ። W • መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሚኒስትሩ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የሚረዱ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። ፴፬ • የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ፩ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፲፩ ) እንደ ተጠበቀ ሆኖ ፡ ይህ አዋጅ በወጣበት ቀን ፡ ሀ ) የሕግ ዲግሪ ያለው ፡ ወይም ለ ) የሕግ ዲፕሎማ ያለውና በማናቸውም ፍርድ ቤት ከአሥር ዓመት ላላነሰ የጥብቅና አገልግሎት የሰጠ ወይም በማናቸውም ፍርድ ቤት በዳኝነት ወይም በዐቃቤ ሕግነት ወይም በነገረ ፈጅነት ያገለገለበት ጊዜ ተዳምሮ ከአሥር ዓመት ያላነሰ አገልግሎት ያለው ፡ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ እንደተሰጠው ይቆጠራል ። ፪ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፩ እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ይህ አዋጅ በወጣበት ቀን፡ የሕግ ዲፕሎማ ያለው : ወይም የሕግ ሰርተፊኬት ኖሮት ከአምስት ዓመት ያላነሰ የጥብቅና አገልግሎት የሰጠ ወይም በማናቸውም ፍርድ ቤት በዳኝነት፡ በዓቃቤ ሕግነት ወይም በነገረ ፈጅነት ያገለገለበት ጊዜ ተዳምሮ ከአምስት አመት ያላነሰ አገልግሎትያለው፡ ሐ ) ሰርተፊኬት ሳይኖረው ከአስር ዓመት ላላነሰ የጥብቅና አገልግሎት የሰጠ ወይም በማናቸውም ፍርድ ቤት በዳኝነት ወይም ዓቃቤ ሕግነት ወይም በነገረ ፈጅነት ያገለገለበት ጊዜ ተዳምሮ ከአስር ዓመት ያላነሰ አገልግሎት ያለውና በሚኒስቴሩ የተሰጠውን ፈተና ያለፈ፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጠበቃ ፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርደ ቤት የጥብቅና ፈቃድ እንደተሰጠው ይቆጠራል ። ፴፭ ስለተሻሩና ተፈጻሚነት ስለሌላቸው ሕጐች ስለጠበቆች በመዝገብ መግባት የወጣው ደንብ የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር ፻፷፮ ፲፱፻፵፬ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፪ : ይህን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ ወይም የተለመደ አሠራር በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፴፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ዶ ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ንኛውም ገጽ ፩ሺ፪፻፳፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም • ፪ « ጥብቅና አገልግሎት » ማለት የገንዘብ ክፍያ በመቀበል ፤ ወይም ወደፊት የሚገኝ ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ወይም ያለክፍያ ፍ / ቤት ፊት ሊቀርብ የሚችልማናቸውንም ዓይነት የውል ስምምነት ፤ የድርጅት ማቋቋሚያ፡ ማሻሻያ ወይም ማፍረሻ ሰነድ ወይም ለፍ / ቤት የሚቀርብ ሰነድ ማዘጋጀትን ፤ ሦስተኛ ወገኖችን በመወከል በፍ / ቤት ፊት ቀርቦ መከራከርን እና ማናቸውንም ዓይነት የሕግ ምክር አገልግሎት መስጠትን ያጠቃልላል ፤ « ጠበቃ » ማለት የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ለመስጠት ስሙ በመዝገብ የተመዘገበ የሕግ ባለሙያ ነው ፤ « የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ » ማለት የሕግ ምክርና አስተያየትን በመስጠትና ሕግ ነክ ሰነዶችን በማዘጋጀት ጠበቃውን የሚያግዝ ሰው ነው ፣ ፭ « የጠበቃ ረዳት » ማለት በጠበቃው ሥር በመሆን በጠበቃው የተዘጋጁ የክስማመልከቻዎችን ለፍርድ ቤት በማቅረብ ፋይል የሚያስከፍት ፤ ከፍርድ ቤት የሚወጡ መጥሪያዎችን ትእዛዞችን እና የፍርድ ግልባጮችን በማውጣት ለሚመለከታቸው ሰዎች የሚያደርስ ሰው ፮ « ደንበኛ » ማለት ስለራሱ ወይም ስለሌላ ሰው ጉዳይ ማንኛውንም የጥብቅና አገልግሎት ለማግኘት ከጠበቃ ጋር የተዋዋለ ወይም የጉዳዩን ፍሬ ነገር ለጠበቃ ያስረዳ ሰው ነው፡ ፯ : « ሚኒስቴር » ወይም « ሚኒስትር » ማለት እንደቅደም ተከተሉ የፍትሕ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ፤ « መዝገብ » ማለት ጠበቆች የሚመዘገቡበትና በሚኒ ስቴሩ የሚጠበቅ ሪኮርድ ነው ፤ ፬ « ሰው » ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ሁለት ስለፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ እና ስለጠበቆች ምዝገባ ፈቃድ ስለማስፈለጉ ፩ የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ የጥብቅና ፈቃድ ሊኖረው ይገባል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ቢኖርም የሚከተሉት ሰዎች ያለጥብቅና ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡ ሀ ) ስለራሱ ጉዳይ የሚከራከር ሰው ፤ ለ ) ያለክፍያ ለትዳር ጓደኛው ፤ ለወላጆቹ ለልጆቹ ለአያቶቹ ለእህቱ፡ ለወንድሙ እንዲሁም ሞግዚት ወይም አሳዳሪ ለሆነለት ሰው የሚከራከር ሰው ፤ ሐ ) ከሥራው በተያያዘ ጉዳይ የሚከራከር የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ፤ መ ) የግል ድርጅትን ወይም ኩባንያን በፍርድ ቤት ለመወከል ሥልጣን ተሰጥቶት የድርጅቱን ወይም የኩባንያውን ጉዳዮች በሚመለከት የሚከራከር ማንኛውም የድርጅት ኃላፊ ወይም ሸሪክ ፤ ሠ ) የመንግሥት መሥሪያ ቤትን ወይም የልማት ድርጅትን በሚመለከት የሚከራከር ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ባለሥልጣን ወይም ኃላፊ ወይም በእርሱ የተወከለ ረ ) ማንኛውም የሠራተኛ ማኅበር መሪ ወይም ማኅበሩ የሚወክለው ሰው ። ፫ . አመልካች በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወም ፡፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ፬ ፈቃድ ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ለዚሁ ተግባር በሚኒስቴሩ በተዘጋጀ ቅጽ ተሞልቶ ይቀርባል ። ፪ አመልካቹ ከማመልከቻው ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይኖርበታል፡ ሀ ) የትምህርት ማስረጃውን፡ ለ ) ከቀድሞ አሠሪው ስለ ሥነምግባሩ ወይም ስለ ሥራ አፈጻጸሙ የሚገልጽ ደብዳቤ ፣ ሐ ) እንደአስፈላጊነቱ ፈቃድ ለማግኘት የሚሰጠውን የሙያ መግቢያ ፈተና ማለፉን የሚያሳይ ማስረጃ፡ መ ) የፈቃድ ክፍያ መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ፡ ሠ ) የሙያ ኃላፊነትመድን ዋስትናመግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ፡ ረ ) ሌሎች በሚኒስቴሩ የሚጠየቁ ማስረጃዎች ፣ ማቅረብ አለበት ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሐ ) የሚቀርብ ሠርተ ፊኬት ዋጋ የሚኖረው ፈተና ማለፉ በታወቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከቀረበ ብቻ ነው ። ፈቃድ ስለመስጠት ሚኒስቴሩ የጥብቅና ፈቃድ ማመልከቻ በአንቀጽ ፬ መሠረት ተሟልቶ ሲቀርብለት ከ፵ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ውሣኔ መስጠት አለበት ። የሚጠቀሱት የሚከተሉትን ይጨምራል ፡ ሀ ) የጠበቃውን ሙሉ ስምና ዜግነት ፡ ለ ) መደበኛ የመኖሪያና የሥራ አድራሻ ፣ ሐ ) የፈቃዱን ዓይነት ፡ መ ) የፈቃድ ሰጭውን ስምና ፊርማ ። ፫ • ቋሚ ሥራ ላለው ሰው የጥብቅና ፈቃድ አይሰጥም ። ፮ የፈቃድ እድሣት ፩ የጥብቅና ፈቃድ በያመቱ መታደስ አለበት ። ፪ : ፈቃድ ለማሳደስየሚቀርብማመልከቻ ፈቃዱየሚያገለግ ልበት የአንድ ዓመት ጊዜ ከማለቁ ከአንድ ወር በፊት መቅረብ አለበት ። የሚወሰነውን የማሳደሻ ክፍያ ይከፍላል ። ፯ የፈቃድ ዓይነቶች በሚኒስቴሩ የሚሰጡ የሚከተሉት ሦስት ዓይነት የጥብቅና ፈቃዶች ይኖራሉ ፡ ሀ ) የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ፡ ለ ) የፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት ጥብቅና ፈቃድ ፤ እና ሐ ) የፌዴራል ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ። ፰ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥብቅና ፈቃድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠዋል ፡ ፩ . በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ በዲፕሎማ የተመረቀ፡ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ሕጐች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ ያለው ወይም በሕግ በዲግሪ የተመረቀ ፡ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ሕጐች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ልምድ ያለው ፡ ፪ • ለፍትሕ ሥራ አካሄድ መልካም ሥነ ምግባር ያለው ፣ ፫ ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና መግቢያ ፈተና ያለፈ ፤ ገጽ ፩ሺ፪፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም ፬ ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ ፤ ፭ የሙያ የኃላፊነት መድኅን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ ያቀረበ ። የፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠዋል ፣ ፩ . በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ ዲግሪ የተመረቀ፡የኢትዮጵያን መሠረታዊ ሕጐች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ ያለው፡ ፪ • ለፍትሕ ሥራ አካሄድ መልካም ሥነ ምግባር ያለው ፣ ፫ ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና መግቢያ ፈተና ያለፈ ፡ ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ ፣ ፭ የሙያ የኃላፊነት መድኅን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ ያቀረበ ። የፌዴራል ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ፩ : የኅብረተሰቡን አጠቃላይ መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሟገትና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፡ የፌዴራል ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠዋል ፡ ሀ ) በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ በዲግሪ የተመረቀ ፡ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ሕጐች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ ያለው ፡ ለ ) ከሚወክለው የኅብረተሰብ ክፍል ወይም ደንበኛ ምንም ዓይነት ክፍያ የማይቀበል ፣ ሐ ) ዐባዩ ይህን ኃላፊነት ለመቀበል ተስማሚ የሆነ ፣ መ ) ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ ። ፪ • የጥብቅና ፈቃድ ያለው ማንኛውም ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተገለጹትን የሚያሟላ ከሆነ ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ሳያስፈልገው አገልግሎት መስጠት ይችላል ። ነገር ግን ይህን ግልጋሎት ከመስጠቱ በፊት ሚኒስቴሩን ማስታወቅ አለበት ። ፫ : ሚኒስቴሩ ስለ ልዩ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥ ፡ በፈቃዱ ስለሚሰጠው አገልግሎት ዓይነት ፡ የአገልግሎት ጥራት እና ስለ ባለፈቃዶች ሥነ ምግባር ዝርዝር መመሪያ ያወጣል ። ፲፩ ለጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ስለመቀመጥ ፩ : በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ እና ፱ መሠረት የጥብቅና ፈቃድ የሚጠይቀውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ኢትዮ ጵያዊ የፈተና መመዝገቢያ ክፍያ ፈጽሞ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና መውሰድ ይኖርበታል ። ፪ . በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ በሕግ ቢያንስ በረዳት ፕሮፌሰርነት ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሮት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትእናከዚያ በላይ በዳኝነት ወይም ዓቃቤ ሕግነት ወይም በታወቁ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በሕግ አማካሪነት እና ነገረ ፈጅነት ቢያንስ ለአምስት ዓመት ያገለገለማንኛውም ሰው ሥራውን በለቀቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የጥብቅና ፈቃድ ማመልከቻ ካቀረበ የጥብቅና መግቢያ ፈተና እንዲወስድ አይገደድም ። ገጽ ፩ሺ፪፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የመድን ዋስትና ስለመግባት ፩ . የፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቃ ወይም የጥብቅና አገል ግሎት ድርጅት የሙያ ኃላፊነት መድን ዋስትና መግባት ይኖርበታል ። አፈጻጸሙ ሚኒስትሩ የፌዴራል ፍ / ቤት ጠበቆች የመድን ዋስትና መግባትን በተመለከተ በቂ ጥናት በማድረግ ለሚነስትሮች ም / ቤት አቅርቦ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት በሚያወጣውደንብ ይወሰናል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚያወጣው ዝርዝር የአፈጸጸምደንብ በሥራ ላይ እስከሚውልበት ጊዜ ድረስ የዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ( ፭ ) እና አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፲፫ : ቃለ መሐላ ስለመፈፀም ማናኛውም ፈቃድ የሚሰጠው ጠበቃ የሚከተለውን ቃለ መሐላ በጽሑፍ ያረጋግጣል፡ ዓም ከሚኒስቴር መ / ቤቱ የጥብቅና ፈቃድ ስቀበል በሙያዬ በቅንነትና በታማኝነት በመሥራት የምወክላቸውን የደንበ ኞቼን ጥቅም ሕግ በሚፈቅደው መጠን ላስከብር ፤ ከተከራካሪ ዎቼና ከሙያ ባልደረቦቼ ጋር በመግባባት ልሠራ እና ለፍርድ ቤቶች ተገቢውን ክብር በመስጠት ለሕግ መከበር አጋዥ ለመሆን ቃል እገባለሁ ። ፲፬ • ፈቃድን ስለመመለስ ፩ . ማንኛውም ጠበቃ ከሙያው ውጭ በሆነ ሥራ በዋናነት የተሰማራ እንደሆነ ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት ሙያዊ አገልግሎት ለመስጠት ያልቻለእንደሆነ ፈቃዱን እንደሁኔታው ለተወሰነ ጊዜ ወይም በቋሚነት ለሚኒ ስቴሩ ይመልሳል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ፈቃዱን የመለሰ ጠበቃ ፈቃዱን እንዲመልስ ያስገደደው ምክንያት እንዳበቃ ወይም እንደተወገደ ከሥራው ተለይቶ በቆየበት ጊዜ በሥነ ምግባር ጉድለት ሊያስጠ ይቀው የሚችል ጥፋት ካልፈጸመ ፈቃዱን ሊወስድ ይችላል ። ፲፭ ፈቃድን ስለማገድ ወይም ስለመሠረዝ ፩ ይህን አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት ደንቦችና መመሪያዎችን ወይም የጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብን የጣሰ ጠበቃ እንደሁኔታው ፍቃዱ ሊታገድ ወይም ሊሰረዝ ይችላል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ሚኒስቴሩ ከሚከተሉት ሁኔታዎች በአንዱ ፈቃድን ሊሰርዝ ይችላል ፣ ሀ ) ፈቃዱ የተገኘው በማታለል ወይም የሀሰት ማስረጃ ወይም መግለጫ በማቅረብ እንደሆነ ፣ ለ ) ለጥብቅና ሙያ ብቃት የሌለው መሆኑን በሚያሳይ የወንጀል ድርጊት ተከሶ ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ፣ ሐ ) ከተሰጠው የጥብቅና ፈቃድ ደረጃ በላይ ሲሠራ የተገኘ እንደሆነ፡ መ ) በማንኛውም ዓይነት የማጭበርበር ድርጊት ወይም የሙያ ሥነ ምግባሩን በከባድ ሁኔታ በመተላለፍ የጥብቅና ሥራ ማካሄዱ የተረጋገጠ እንደሆነ ፤ ሠ ) ከጥብቅና ሙያ በታገደበት ወቅት የጥብቅና ሙያ አገልግሎት መስጠቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ፤ ገጽ ፩ሺ፪፻፲፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ረ ) ለራሱ ወይም ለሌላ ጠበቃ በአገናኝ አማካይነት ሥራ ለማስገኘት ገንዘብ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ እንደሆነ፡ ሰ ) ከጥብቅና ሙያ ጋር በግልጽ የሚጋጭ ወይም የማይጣጣም ተጨማሪ ሥራ ሲያከናውን የተገኘ እንደሆነ ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ሚኒስቴሩ ከሚከተሉት ሁኔታዎች በአንዱ ፈቃድን ሊያግድ ይችላል ። ሀ ) ያለበቂ ምክንያት ፈቃዱን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ መሠረት ያላሳደሰ እንደሆነ ፣ ለ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፯ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተመለከተውን በመተላለፍ የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ ወይም የጠበቃ ረዳት አድርጐ ያሠራ እንደሆነ ። ፲፮ ስለመመዝገብ ፩ ፈቃድ የተሰጠውን ጠበቃ ስምና ዜግነት ፣ የፈቃድ ዓይነት፡ መደበኛ የመኖሪያና የሥራ አድራሻውን እና ሌሎች በሚኒስቴሩ የሚጠየቁ አስፈላጊ መረጃዎች የሚይዝ መዝገብ ይኖረዋል ። ፪ ስሙ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ሥር በተመለ ከተው መዝገብ ውስጥ ያልገባ ሰውየጥብቅና አገልግሎት መስጠት አይችልም ። መዝገቡ ለሕዝብ ግልጽ የሆናል ። ካጠበቃው ጋር የሚሠሩ ሰዎችን ስለመመዝገብ ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት በሥራው የሚያግዙትን የሕግ ዐሐፊዎች፡ የጠበቃ ረዳቶች : ፀሐፊዎች ፡ የሌሎች ሠራተኞች ስም እና የሥራ ኃላፊነት ሚኒስቴሩ ለዚህ ጉዳይ ለመደበው ባለሥልጣን በጽሑፍ በማሳወቅ ያስ መዝግባል ። ፪ • ማንኛውም ጠበቃ ከሚኒስትሩ ወይም በእርሱ ከተወከለ ባለሥልጣን ፈቃድ ሳያገኝ ፡ ህ ) ከመዝገብ ስሙ የተፋቀን ፣ ለ ) ከጥብቅና ሙያ አገልግሎት የታገደን ፤ ሐ ) በዲሲፕሊን ጥፋት ከመሥሪያ ቤቱ የተባረረን መ ) ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከስሶ የተፈረደበትን ወይም ፡ ሠ ) በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ የሚሠራን ሰው ፡ በጠበቃ ረዳትነት ወይም በሕግ ጉዳይ ፀሐፊነት መቅጠር አይችልም ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተጠቀሰው እንደ ተጠበቀ ሆኖ፡ የሕግ ትምህርት ወይም ሥልጠና ወይም ልምድ የሌለው ሰው በሕግ ጉዳይ ፀሐፊነት ሊቀጠር አይችልም ። ፲ የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅትን ስለመመዝገብና ፈቃድ ስለመስጠት ፩ የጥብቅና ሙያ ድርጅት ለማቋቋም የሚፈልጉ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጠበቆች ለሚኒስቴሩ በጽሑፍ ማመልከት ይችላሉ ። በዚህ አዋጅ መሠረት የሚቋቋመው ድርጅት የንግድ ማኅበር ያልሆነ ኃላፊነቱ ያልተወሰነማኅበር ይሆናል ። ፫ ሚኒስቴሩ ወይም እርሱ የወከለው ባለሥልጣን የድርጅት ማቋቋሚያ ሠነዱን ከመረመረ በኋላ የድርጅቱ መቋቋም ፡ ሀ ) የጠበቆችን የሥነ ምግባር ደንብ የማይጥስ ፡ ለ ) የደንበኞችን ወይም የሦስተኛ ወገኖችን ጥቅም የማይጐዳ ፡ መሆኑን ሲያምን ስሙን በመዝገብ ኣስገብቶ ፈቃድ ይሰጠዋል ። ፩ . ኮሚቴው እየ ” ኢላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ገጽ ፩ሺያደኛፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፪ ዓም ፬ • ስለጥብቅና ሙያ ድርጅት ፈቃድ አሰጣጥ እና ከዚሁ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ መመሪያ በዝርዝር ይወሰናል ። ክፍል ሦስት አስፈጻሚ አካላት ፲፬ . የሚኒስቴሩ ሥልጣንና ተግባር ሚኒስቴሩ ፡ ፩ የጥብቅና ፈቃድ ይሰጣል ፤ ጠበቆችን ይመዘግባል ፤ የጥብቅና ፈቃድን ያድሳል ፣ ያግዳል ፣ ይሠርዛል ። በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ በሚወሰነው መሠረት ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል ። | 20. License Evaluating committee ፳ የጥብቅና ፈቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ፩ የሚከተሉት አባላት የሚኖሩት የጥብቅና ፈቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚቴው ” እየተባለ የሚጠራ ) ይኖራል ፣ ሀ ) የሚኒስቴሩ ሁለት ተወካዮች ፣ ለ ) የጠበቆች ማኅበር ሁለት ተወካዮች ፣ ሐ ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተወካይ ። የአንድ አባል የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ሲሆን ፤ የኮሚቴው ሰብሳቢ ከአባላቱ ውስጥ በሚኒስትሩ ይሰየማል ። ፳፩ የኮሚቴው ሥልጣንና ተግባር ኮሚቴው ፣ ፩ የአመልካቹን ማስረጃዎች መርምሮ አመልካቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ወይም እንዳይሰጠው ለሚኒስትሩ የውሣኔ ሀሳብ ያቀርባል ፡ ፪ አመልካቹ ለፍትሕ ሥራ አካሄድ የሚስማማ የሥነ ምግባር ብቃት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ማንኛውንም ሰው መጠየቅ ወይም ማስረጃ አስቀርቦ መመርመር ይችላል ፡ ፳፪ የኮሚቴው ስብሰባ ይችላል ። ፪ ከኮሚቴው አባላት አብዛኛዎቹ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል ። የኮሚቴው ውሣኔዎች በስብሰባው በተገኙ አባላት በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፡ ሆኖም ድምጽ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሣኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደ ተጠበቀ ሆኖ፡ ኮሚቴው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፳፫ የጠበቆች የዲሲፕሊን ጉባዔ ፩ የሚከተሉት አባላት የሚኖሩት የጠበቆች የዲሲፕሊን ጉባዔ ከዚህ በኋላ “ ጉባዔው ” እየተባለ የሚጠራ ይኖራል ፤ ሀ ) የሚኒስቴሩ ሁለት ተወካዮች ፣ ለ የጠበቆች ማኅበር ሁለት ተወካዮች ፣ ሐ ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተወካይ ። የአንድ አባል የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ሲሆን ፣ የጉባዔው ሰብሳቢ ከአባላቱ ውስጥ በሚኒስትሩ ይሰየማል ። ፳፬ . የጉባኤው ሥልጣንና ተግባር ጉባኤው፡ ፩ . ይህን አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ በጠበቃ ላይ የሚቀርብ ክስን ተቀብሎ ያጣራል ፤ ይመረምራል ፤ በጠበቃው ላይ የቀረበውን ክስ ለማየት የሚያበቃ ማስረጃ መኖሩን ሲያረጋግጥ ጠበቃው መልሱን በ፴ ቀን ውስጥ እንዲያቀርብ በመጥሪያው ላይ በመግለጽ ክሱን ለጠበቃው ይልካል ፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፸፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፲፪ ዓም በጠበቃው ላይ የቀረበውን ክስና ማስረጃ እንዲሁም በጠበቃው በኩል የተሰጠውን መልስና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ፡ ሀ ) ክሱ ተገቢ ካልሆነ ወይም በበቂ ማስረጃ ካልተደገፈ ክሱን በመሠረዝ ጠበቃው እንዲሰናበት ፡ ለ ) ክሱ ተገቢና በማስረጃ የተደገፈ ከሆነ እንደ ጥፋቱ ክብደት : ፩ ጠበቃው የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው : ፪ . ጠበቃው ከአምስት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ከሥራው እንዲታገድ ፡ • ከብር ፲ሺ ( አሥር ሺ ብር ) ያልበለጠ ቅጣት እንዲጣልበት ፡ ፈቃዱ ተሠርዞ ስሙ ከመዝገብ እንዲፋቅ ፡ ወይም : ፭ ተገቢ ነው ያላቸውን ሌሎች ውሣኔዎች እንዲሰጥ፡ የውሣኔ ሃሣብ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት ተገቢውን ውሣኔ እስኪወስድ ድረስ የጥብቅና ፈቃዱን ሊያግድ ይችላል ። ፭ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጠበቃው ላይ የሚጣለውን የቅጣት መጠን ለመወሰን የወንጀል ሪኮርድ ፣ የጠበቃውን የግል ማኅደር ወይም ሌላ ተመሣሣይ ማስረጃ መስማትና መመርመር ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) ( ለ ) መሠረት የተሰጠው ማንኛውም ውሣኔ በጠበቃው የግል ማኅደር ውስጥ እንዲመዘገብ ያደርጋል ። ፤ የጠበቆች የሥነ ምግባር ብቃት የሚጎለብትበትን ፡ የጥብቅና ሙያ ክብር የሚጠበቅበትን ሁኔታ እያጠና ለሚኒስቴሩ ሀሣብ ያቀርባል ። ፰ የቀረበውን ማንኛውም ክስ ክሱ በቀረበ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የመጨጨረሻ የውሣኔ ሀሣብ ለሚኒ ስትሩ ያቀርባል ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን ለማጠናቀቅ የማይቻልበት በቂ ምክንያት ሲያጋጥም ምክንያቱን በጽሑፍ በመግለጽ ከሦስት ወር የማይበልጥ ተጨማሪ ጊዜ እንዲፈቀድለት ሚኒስትሩን በጽሑፍ መጠየቅ | 25. Meetings of the Council ይችላል ። ፳፭ የጉባዔው ስብሰባ ፩ ጉባኤው እንደ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ መሰብሰብ ይችላል ። ከጉባዔው አባላት ኣብዛኛዎቹ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል ። የጉባዔው ውሣኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፡ ሆኖም ድምጽ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሣኝ ድምጸ ይኖረዋል ። በዚህ አንቀጽ የተደነገገው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ጉባኤው የራሱን የስብሰባ ሥነ - ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፳፮ የሚኒስትሩ ሥልጣን ሚኒስትሩ በአንቀጽ ፳፩ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ወይም በአንቀጽ ፳፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት ከኮሚቴው ወይም ከጉባዔው የቀረበውን የውሣኔ ሃሣብ ከመረመረ በኋላ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጣል ። ኮሚቴው ወይም ጉባዔው በአግባቡ ያላጣራው ወይም ያላጤነው ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ካለ ይኸው ተጣርቶ ወይም ተገናዝቦ እንዲቀርብለት ለኮሚቴው ወይም ለጉባዔው ለአንድ ጊዜ መመለስ ይችላል ገጽ ፩ሺ፪፻፸፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ፳፯ የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና አዘጋጅና የችሎታ ብቃት መለኪያ ቦርድ የሚከተሉት አባላት የሚኖሩት የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና አዘጋጅና የችሎታ ብቃት መለኪያ ቦርድ ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ይኖራል ፤ ሀ ) የሚኒስቴሩ ሁለት ተወካዮች ፣ ለ ) የጠበቆች ማኅበር ተወካይ : ሐ ) የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተወካይ ፣ መ ) የሕግ ፋክልቲዎች ተወካይ ፣ ሠ ) በሚኒስትሩ የሚመረጡ ሌሎች ሁለት አባላት ። የአንድ አባል የሥራ ዘመን ለአራት ዓመት ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢ በሚኒስትሩ ይመረጣል ። ፳፰ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ፩ ከሚኒስትሩ ወይም በእርሱ ከሚወከል ባለሥልጣን ጋር በመመካከር በየዓመቱ የጥብቅና ችሎታ መመዘኛ ፈተና እያዘጋጀ በተወሰነ ጊዜና ቦታ ለአመልካቾች ይሰጣል ፡ ፪ • የፈተና ወረቀቶችን ያርማል ፡ ለማለፊያ የሚያበቃውን ነጥብ ይወስናል ፡የፈተናውን ውጤት ለሚኒስትሩ ወይም በእርሱ ለሚወከል ባለሥልጣን አቅርቦ ውጤቱን በይፋ ያስታውቃል ። ፫ የሥነ ሥርዓት ደንቡን አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፡ ሲጸድቅም ሥራ ላይ ያውላል ። ፳፱ • በሚኒስትሩ ( i ማኔ ላይ ለሚቀርብ ይግባኝ ፩ ሚኒስትሩ የሰጠው ውሣኔ ስሕተት ያለበት ሆኖ ከተገኘ ፡ በውሣኔው ቅር የተሰኘው ወገን ውሣኔው በደረሰው በሠላሣ ቀናት ውስጥ ይግባኙን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ። ፍርደ ቤቱ ወደ ፍሬ ነገር ሳይገባ በሕግ ጉዳይ ላይ ውሣኔ በመስጠት ጉዳዩን ወያ ሚኒስትሩ ይመልሰዋል ። ፫ . የሚኒስትሩ ውሣኔ የሕግ ስሕተት ያለበት ሆኖ ከተገኘ ሚኒስትሩ የፍርድ ቤቱን ውሣኔ መሠረት በማድረግ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ ያደርጋል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴ : የጠበቃው ግዴታዎች ማንኛውም ጠበቃ ፡ ፩ . ይህን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወጣውን ደንብና መመሪያ እና የሚሰጡትን ትዕዛዞችና ውሣኔዎች የማክበር ፡ ፪ • ከደንበኛው ለሚቀበለው ማንኛውም ዓይነት ክፍያ ደረሰኝ የመስጠት ፡ ፫ በደንበኞቹ ላይ በሙያው ለሚያደርሰው የፍትሐ ብሔር ጥፋት ጉዳት ካሣ እንዲሆን በአንቀጽ ፲፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተደነገገው መሠረት መድን የመግባት ፡ ፈቃድ ሲያወጣ ፡ ሲያድስና ሲተካ በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣው ደንብ የሚፈለግበትን የፈቃድ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለበት ። ፴፩ ቅጣት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው ፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ፈቃድ ሳያወጣ ወይም የጥብቅና ፈቃዱን ሳያሳድስ የጥብቅና አገል ግሎት የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ እንደሆነ ፡ ከብር ፪ ሺ ባላነሰ እና ከብር ፲ ሺ ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከስድስት ወር ባላነሰ እና ከሁለት ዓመት ባልበለጠ እሥራት ይቀጣል ።