×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የኢትየጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፯/፲፱፻፹፯

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

3 ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፤ ኣዲስ ኣበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፳፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፯ ፲፱፻ዥ፯ ዓም የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ማቋቋሚያ . . . . . ገጽ ፳፫ አዋጅ ቁጥር ፯ ፲፱፻ዥ፯ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽንን ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ . ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ | ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፯ ፲፱፻፫ ፤ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። | ፪• መቋቋም ፩ : የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽን ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሆናል ። ፫• ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ማቋቋም ይችላል ። ያንዱ ዋጋ - ነጋሪት ጋዜጣ ፖ . ሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፷፬ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፫፯ ዓም• _ Negarit Gazeta No . ጉ – 24 August 1995 – Page 64 ፬ ዓላማ የኮሚሽኑ ዓላማ የሃገሪቱን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት 1 ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሳይንስና ቴክኖሎጂእንቅስቃሴ ዎችን ማበረታታትና ማጐልበት ይሆናል ። ፭ . ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩• የሃገሪቱን የዕድገት ዓላማዎች ተግባራዊነት የሚያግዝ ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ መንደፍ ፡ በመን ግሥት ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን መከታተል ፣ ፪ ሁለገብ የሆኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕቅዶችን ማቀድና የዘርፍ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲዎች ፡ ዕቅዶች ፕሮግራ ሞችና ፕሮጀክቶች እንዲዘጋጁ መመሪያ መስጠት ፤ ተዘጋ ጅተው ሲቀርቡም መገምገምና በመመሪያው መሠረት መዘጋጀቱን ማረጋገጥ ፡ ለመንግሥት አቅርቦ ማስፀደቅ ፫ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት አስተዋጽኦ የሚኖራቸው የምርምርና ስርፀት ማዕከላትና ተቋማትን መርዳትና ማበረ ታታት ፣ ሕ - - ፬ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ወይም ማበረታቻ መስጠት ፤ ፭ ለኢትዮጵያ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለመፈለግ ፡ ለመምረጥ ፥ ለመደራደር ፡ ለመግዛት ፡ ለማስገባት የሚያስችል አቅም መገንባትና ስርዓትን መዘርጋት ፤ ፮• የቴክኖሎጂ ሽግግርን የሚያግዙ የፈጠራ ሥራዎችን ለተግባ ራዊነት እንዲበቁ የሚያበረታታና የፈጠራና መሰል ሥራዎች እንዲነቃቁና እንዲጐለብቱ የሚረዳ የፓተንት ሕግ ማዘጋጀት ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ ፤ ፯ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚኖራቸው ማሕበራት እንዲደራጁ የመርዳትና የማበረታታት እንዲሁም በሙያ ማሕበራት አማካኝነት የሚዘጋጁ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ነክ ጽሑፎችን ለሕትመት እንዲበቁና እንዲሰራጩ ድጋፍ መስጠት ፤ በሃገር ውስጥ በቀል የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻልና ለማሳደግ የሚደረጉ ጥናቶችን የምርምርና ስርፀት ተግባ ሮችን ማበረታታትና ተግባራዊነታቸውን ማረጋገጥ ፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክንውኖች ፡ የምርምር ሥራዎችንና ውጤቶችን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚሰባሰቡበትን ሥርዓት መዘርጋት ፤ ፲ በምርምርና ሥርፀት ተግባር ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ድርጅቶችን ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ። ፮• የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ ፡ ፩ ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት ( ከዚህ በኋላ | 6 . Organization of the Commission “ ምክር ቤት ” እየተባለ የሚጠራ ) ፤ ፪ በመንግሥት የሚሾም አንድ ኮሚሽነር አንድ ምክትል ኮሚሽነር እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ኑ አቋምህ ገጽ ፷፭ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፯ ዓም Negarit Gazeta No . 7 24 August 1995 – Page 65 ፯ የምክር ቤቱ አባላት ምክር ቤቱ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፡ ፩• የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር . . . . . - ሰብሳቢ ፪• የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር . ተወካይ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ፫• የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ . . . ፩ . የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተወካይ . . . . ፭ የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ ፮ : የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተወካይ . . ፯ ፡ በኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሚሰየሙ ሶስት ታዋቂ ባለሙያዎች . | አባላት ፰• የምክር ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ምክር ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩• በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ላይ መምከር ፡ ሃሣብ ማቅረብ ፤ | 8 . Powers and Duties of the Council ፪ : የየዘርፉን የሳይንስና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎችን መገምገም ፤ ፫ ፡ የተለያዩ መመሪያዎችንና የሥራ ፕሮግራሞችን ማውጣት ። ፱• የምክር ቤቱ ስብሰባ ፩ ምክር ቤቱ በሶስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪• የምክር ቤቱ አባላት አብዛኛው በስብሰባ ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይኖራል ። ፫• የምክር ቤቱ ውሣኔዎች በድምፅ ብልጫ ያልፋሉ ፡ ሆኖም ድምፁ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ። ፬ . የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲• የኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ - ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የኮሚሽኑን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽነሩ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተመለከተውን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) የኮሚሽኑን ሠራተኞች በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ መ ) ለኮሚሽኑ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ኮሚሽኑ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙ ነቶች ሁሉ ኮሚሽኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለኮሚሽኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለኮሚሽኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ገጽ ፳፮ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻ዥ፯ ዓ . ም . _ Negarit Gazeta _ No . 7 24 August 1995 – Page 66 ፲፩ : በጀት የኮሚሽኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። ፲፪• የሂሣብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የኮሚሽኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሠነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፫• የመተባበር ግዴታ ማናቸውም ሰው ወይም መንግሥታዊ ወይም የግል ድርጅት ወይም ተቋም ለኮሚሽኑ ሥራ አፈጻጸም የመተባበር ግዴታ ኣለበት ። ፲፬• የተሻረ ሕግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፩ _ ፲፱፻፳፯ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፲፭ መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፷፯ ዓ . ም . ተቋቁሞ የነበረው የሳይ ንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ ለኮሚሽኑ ተላልፈዋል ። ፲፮• አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፫፯ ዓ . ም . ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?