×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 83/1989 ዓ•ም• የኢትዮጵያመንገዶች ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋሚያአዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፫ አዲስ አበባ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፷፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ጽ / ፲፱፻፰፱ ዓ . ም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋሚያ . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፭፻፴፬ አዋጅ ቁጥር ፰ ፲፱፻፷፱ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግ ሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንን እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፳ / ፲፱፻፶፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ እውራ ጐዳና ” ማለት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥል ጣን “ አውራ ጐዳና ” ብሎ የሚሰይመው መንገድ ነው ፤ ፪ . “ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፵፯ የተጠቀሰ ክልል “ መንገድ ” ማለት አውራ ጐዳና ወይም ብሔራዊ የመንገድ አውታር አካል ሆኖ የተመደበና የተሰየመ ማንኛውም ሌላ መንገድ ሲሆን በነዚሁ መንገዶች ላይ የሚገኝ ድልድይንም ይጨምራል ፤ ፩ . “ የመንገድ ፈንድ ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፳፮ / ፲፱፻፷፱ የተቋቋመው ፈንድ ነው ፤ ፭ . “ ሥራ ” ማለት የኮንስትራክሽን ፡ የጥገናና የማሻሻያ ተግባሮችን ማከናወን ነው ፣ ያንዱ ዋጋ ብር 2 : 30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዥሺ፩ 3 - 1 ገጽ ፭፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፫ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፩ ቁ ዘ - - - 3 ፫ እንደገና መቋቋም | የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ “ ባለሥል ጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ፥ ራሱን የቻለ የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁ 5 ፪ ፡ ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። 3 ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ውስጥ ሆኖ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን እንደአስፈላጊነቱ በሌሎች ሥፍራ ዎች ማቋቋም ይችላል ። - ፭ የባለሥልጣኑ ዓላማ . . የባለሥልጣኑ ዓላማ አውራ ጐዳናዎችን ለማልማትና ለማስተዳ ደርእንዲሁም በመንገዶች ሥራወጥነትን ለማረጋገጥና የመንገድ አውታር በተቀናጀ መልኩ የሚያድግበትን አመቺ ሁኔታ መፍ ጠር ይሆናል ። - ፮ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩• መንገዶችን እና ባለሥልጣኑን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችንና ሕጎችን ያመነጫል ፤ ፪• የመንገዶችን የዲዛይን ደረጃዎች ያወጣል ፤ ፫ ብሔራዊ የመንገድ አውታርን ይመድባል ፡ ይሰይማል ፤ ፬• የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችንና ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል ፡ ሲጸድቁም ተግባራዊ ያደርጋል ፤ ፭ . ለአውራ ጐዳና ሥራ የሚያስፈልጉትን ዲዛይኖች በብቁ አማካሪዎች አማካይነት ያዘጋጃል ፡ ለጥናትና ለአስቸኳይ ሥራ የሚያስፈልጉትን ዲዛይኖች ያዘጋጃል ፤ ፮ የአውራ ጐዳናዎችን ፊዚቢሊቲ ጥናት ያካሂዳል ፡ እንዲካሄ ድም ያደርጋል ፤ ፯ . አውራ ጐዳናዎችን በሥራ ተቋራጮች አማካይነት ያሠራል ወይም ያሻሽላል ፥ ሆኖም በሥራ ተቋራጮች አማካይነት ማሠራቱ የማያዋጣ ሆኖ ሲገኝ በራሱ ኃይል ይሠራል ፤ ፰ አውራ ጐዳናዎችን በራሱ ኃይል ይጠግናል ወይም በሥራ ተቋራጮጮች ያስጠግናል ፤ ፱ የሥራ እና የአማካሪነት አገልግሎት ውሎችን ያዘጋጃል ፡ እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፡ ይዋዋላል ሥራዎች በየውላቸው መሠረት የሚከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁጥጥር እንዲኖር ያደርጋል ፡ በበላይነት ይቆጣጠራል ፤ ፲ . አውራ ጐዳናዎችን በሚመለከት ለዲዛይን ፥ ለቁጥጥርና ለሌ ሎች ለማናቸውም ሥራ የሚያስፈልጉ አማካሪዎች የሚመረ ጡበትን ሁኔታዎች ይወስናል ፤ ፲፩ . የአውራ ጐዳናዎች ሥራ በራሱ ኃይል ፥ በአገር ውስጥ ወይንም በዓለም አቀፍ ጨረታ የሚከናወንበትን አማራጭ ይወስናል ፣ ፲፪ አውራ ጐዳናዎችን በሚመለከት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ምልክቶችን ወይንም መሣሪያዎችን ዲዛይን ይሠራል ፡ በአ ውራ ጐዳናዎችም ላይ ያኖራል ፣ ፲፫ የተሽከርካሪ ክብደትና መጠን ደንቦችን በአውራ ጐዳናዎች ላይ ያስፈጽማል ፣ ፲፬• መንገዶችን በሚመለከት የማቴሪያል ጥናት ያካሂዳል ፡ የተ ገኙ ጠቃሚ ውጤቶችንም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ፲፭ ፡ ለመንገዶች ልማትና ጥገና የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ያሰለጥናል ፡ ገጽ ፭፻፴፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ፲፮ አውራ ጐዳናዎችን ከጉዳትና አላግባብ ከመጠቀም ይጠብ ቃል ፥ በአውራ ጐዳናዎች ላይ የሚከሰቱእንቅፋቶችን ያስወግ ዳል ፡ እንዲወገዱ ያደርጋል ፤ ፲፯ ከአውራ ጐዳናዎች ግራና ቀኝ እንዲሁም በአካባቢ ለሥራው የሚያስፈልገውን የመሬት መጠን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች በዚሁ መሠረት የሚጠቀሙበትን ሁኔታዎች ይወስናል ፤ ፲፰ . ለአውራ ጐዳናዎች ግንባታና ጥገና እንዲሁም ለመኖሪያ ፡ ለመሣሪያ ማሳረፊያና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያስፈልጉ ውን መሬትና ድንጋይ ነክ ሀብቶች ያለክፍያ ይጠቀማል ፡ ሆኖም በሚጠቀምበት መሬት ላይ ለሚገኙ ንብረቶች በሕግ መሠረት ካሣ ይከፍላል ፤ ፲፱ አግባብ ላለው የክልል አካል ሲጠየቅ የቴክኒክ አገልግሎት ይሰጣል ፣ ፳ ሥልጣንና ተግባሩን በሥራ ላይ በሚያውልበት ጊዜ አካባቢ እንዲጠበቅ የሚያስፈልጉትን ጥንቃቄዎች ያደርጋል ፣ ፳፩ . የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል ፡ ይከሰሳል ፤ ፳፪ ሥልጣንና ተግባሩን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተዛ ማጅ ተግባሮችን ያከናውናል ። ፯ የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፤ ፩ . ኣባላቱና ሰብሳቢው በመንግሥት የሚሰየሙ አንድ ቦርድ ፡ ፪ . በቦርዱ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ , ባለሥልጣኑን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችንና ሕጐችን እንዲ ሁም የባለሥልጣኑን የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራሞች በጀት ለመንግሥት ከመቅረባ ቸው በፊት ይገመገማል ፡ ሲፈቀድም አፈጻጸማቸውን ይከታ · ተላል ፤ ፪ . ባለሥልጣኑ በሥራው አፈጸጸም የሚመራባቸውን ውስጠ ደንቦችና መመሪያዎች ያጸድቃል ፤ • ፫ . በባለሥልጣኑዋና ሥራ አስኪያጅ በሚቀርቡ ሌሎችጉዳዮች ላይ ይወስናል ። _ ፱• የቦርዱ ስብሰባ ፩ . የቦርዱ መደበኛ ስብሰባ በየሶስት ወሩ አንድ ጊዜ ይደረጋል ፡ ሆኖም በሰብሳቢው ሲጠራ ወይም በባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲጠየቅ ቦርዱ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ፤ ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹአባላት ከተገኙምልዓተ ጉባዔ | ይሆናል ፤ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባላት በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ። ሆኖም ድምጽ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረ ፬ . የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፤ | ገጽ ፭፴፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም• ፲• የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ሳይወሰን ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የባለሥልጣ ኑን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፷፭ መሠረት የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተ ዳድራል ፤ ሐ ) የባለሥልጣኑን የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን ፥ ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራሞችና በጀት በማዘጋጀት ለቦርዱያቀርባል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል ፤ ባለሥልጣኑ በሥራው አፈጸጸም የሚመራባቸውን ውስጠ ደንቦችና መመሪያዎች ያዘጋጃል በቦርዱ ሲጸ ድቅም ሥራ ላይ ያውላል ፤ ሠ ) በጸደቁ የባለሥልጣኑ ፕሮግራሞችና በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ረ ) የባለሥልጣኑን የሂሣብ መግለጫዎችና የኦዲት ሪፖር ቶች በየወቅቱ ለቦርዱ ያቀርባል ፤ ሰ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን የወክላል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ቦርዱን በተለይ በማስፈቀድ ክርክሮ ችን ከፍርድ ቤት ውጪ መፍታት ይችላል ፤ ፬ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ ሥራ ቅልጥፍና በሚያ ስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ሆኖም እርሱን ተክቶ ከ፴ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሠራኃላፊ ሲወክል ውክልናው በቅድሚያ ለቦርዱ ቀርቦ . መጽደቅ አለበት ። _ ፲፩ የገንዘብ ምንጭ የባለሥልጣኑ ገቢ ከሚከተሉት ምንጮች የሚገኝ ይሆናል ፤ ፩ መንገድ ፈንድ ፡ እና ፪ በመንግሥት ከሚመደብ በጀት ፲፪• የሂሳብ መዛግብትና ኦዲት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የባለሥልጣኑ ሂሣብና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ሌላ ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፫ የቴክኒክ ምርመራ በተመረጡ ሥራዎች ላይ በየዓመቱ ይከናወናል ። _ ፲፫ የተሻሩና የተሻሻሉ ሕጎች _ _ ፩ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፷፭ ( እንደተሻሻለ ) በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ገጽ ፭፻፴፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፫ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፲፱ ዓ . ም - Federal Negarit Gazeta – No . 43 5 June , 1997 - Page 538 ፲፬ ፫ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ በዚህ አዋጅ በተደነገጉ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፣ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻ቸ፱ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?