የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፴፪ አዲስ አበባ መጋቢት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር ፴፫ / ፲፱፻፲ ዓም የጥቃቅን እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎች ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፯፻፳፮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፵ የጥቃቅን እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎች ልማት ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፴፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። | pursuant to Article 5 of the Definition ofPowes and Duties of the ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጥቃቅን እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎች ልማት | 1. Short Title ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፫ / ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የንግድና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ፪ “ የጥቃቅን ንግድ ሥራ ” ወይም “ ኣነስተኛ ንግድ ሥራ ” ማለት ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት መሥፈርቱ የሚወሰንላቸው የንግድ ሥራዎችማለት ሲሆን ፣ የቴክኖሎጂና የምክር አገልግሎት ተቋማትን አይጨምርም ፫ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ / ፩ / የተመለከቱትን ክልሎች ማለት ሲሆን ለዚህ ደንብ አፈጸጸም ሲባል የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አስተዳደርንም ይጨምራል ። ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ሸሺ፩ ያንዱ ዋጋ 2:30 ገጽ ፯፻፳፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ መጋቢት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፩ የጥቃቅን እና አነስተኛ የንግድ ሥራዎች ልማት ድርጅት / ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” ተብሎ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • የድርጅቱ ተጠሪነት ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። የድርጅቱ ዓላማ የድርጅቱ ዓላማ የጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ሥራዎች እንዲያድጉና እንዲስፋፉ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን ማበረ ታታት ፡ ማስተባበርና መደገፍ ይሆናል ። የድርጅቱ ሥልጣንና ተግባር ለሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕግ ተለይተው የተሰጡት ሥልጣንና ተግባሮችእንደተጠበቁ ሆነው ድርጅቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ : ስለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራዎች ልማትና መስፋፋት የሚያግዙ የፖሊሲና የስትራቴጂ ሃሣቦችን ማቅረብ ፡ ሲፈቀዱም ተግባራዊ መደረጋቸውን ማረጋገጥ ፤ ፪ • የጥቃቅንና የአነስተኛንግድ ሥራዎችን ልማት ለማፋጠን አስፈላጊ የሆኑ የሥልጠና ፍላጎቶችን በማጥናት ለነዚሁ ተስማሚ የሆኑ የአሰልጣኞች ስልጠና ፕሮግራሞችን በማዕከል ማካሄድ ፤ ፫ የሙያ ማሻሻያ ፡ የቴክኒክና የሠርቶ ማሳያ ማዕከላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እንዲቋቋሙ ማበረታታትና ድጋፍ መስጠት ፣ ፬ . የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራዎች ስለሚለሙበትና ስለሚስፋፉበት ሁኔታ ከክልል መስተዳድር ኣካላት ፥ ለዚሁ ዓላማ ከሚቋቋሙ የክልል ድርጅቶችና ከግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ጋር የተቀናጀ የሥራ ግንኙነት መፍጠር የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራዎችን ለማስተዋወቅና ለማልማት የሚያስፈልጉ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን በመምረጥ የቴክኖሎጂና የፕሮጀክትፕሮፋይሎችን ማዘ ጋጀትና ማሰራጨት፡ አግባብ ካላቸው የምርምር ተቋሞች ጋር የሥራ ግንኙነት በመፍጠር ለክፍለ ኢኮኖሚው የሚጠቅሙ የቴክኖሎጂ ምርምርና ሥርዐት ሥራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ ፡ ውጤታቸውንም ማስተዋወቅ ፣ ፯ . ለክፍለ ኢኮኖሚው አግባብ ያላቸው የገበያ፡ የንግድ ሥራዎችና የሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች መረጃዎችን መሰብሰብ፡ ማጠናቀርና ማሰራጨት ፰ . ለክፍለ ኢኮኖሚው ተስማሚ የሆኑ የንግድ ትርዒቶችን ማዘጋጀትና ማስተባበር፡ በድርጅቶች መካከል የእርስበርስ ግንኙነትና የመረጃ ልውውጥ ቁርኝት የማድረግ ኣስፈላጊነትን ማስተ ፲ ስለጠቅላላ ጥራት አስተዳደርና በድርጅቶች መካከል በውል ሊፈጠር ስለሚችል የሥራ ቁርኝት አሠራር ማስተዋወቅና ማዳበር ፣ ገጽ ፯፻፳፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ መጋቢት ፳፭ ቀን ፲፱ጅ ዓም ፲፩ ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራዎች የድጋፍ አገል ግሎት ለመስጠት አቅም ለሚያንሳቸው ክልሎች አቅ ማቸውን እስከሚያጎለብቱ ድረስ ማንኛውንም ድጋፍ መስጠት፡ ፲፪ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዋጋ ማስከፈል ፣ ፲፫ . የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል : በስሙ መክሰስ ፥ መከሰስ ፣ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባራት ማከናወን ፯ የድርጅቱ አቋም ድርጅቱ ፣ ፩ : አንድ የሥራ አመራር ቦርድ / ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ / ፣ ፪ . በቦርዱ አቅራቢነት በሚኒስትሩ የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። የቦርዱ አባላት ፩ • ቦርዱ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ በመንግሥት የሚሰየሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል ። የቦርዱ ሰብሳቢ ከአባላቱ መካከል በመንግሥት ይመደባል ። ፱ • የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የድርጅቱን ሥራዎች በሚመለከቱ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ለሚኒስቴሩ የውሳኔ ሃሣቦች ማቅረብ ፤ ፪ የድርጅቱን የረጅምና የአጭር ጊዜ እቅዶች ፣ ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት መርምሮ ለሚኒስቴሩማቅረብ ፤ ሲፈቀድም አፈጸጸሙን መቆጣጠር ፤ ፫ . የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ መርሆዎች በመከተል የድርጅቱ ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚተ ዳደሩበትን ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ማቅረብና ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ማረጋገጥ ፤ ፬ . ለዋናው ሥራ አስኪያጅ አጠቃላይ የሥራ መመሪያ መስጠት፡ ፭ ለዋና ሥራ አስኪያጁ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ የድርጅቱን የሥራ ኃላፊዎች ቅጥር ፣ ምደባና ስንብት ማጽደቅ ። ፲ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ ከቦርዱ አባላት መካከል ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ይሆናል ። ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ቦርዱ ውሣኔ የሚሰጠው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ። ድምጹ እኩል ለእኩል በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ . የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ - ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ገጽ ፯፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፪ መጋቢት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፲፩ የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የድር ጅቱን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የድርጅቱን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የድርጅቱን ሠራተኞች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) በተደነገገው ሁኔታ በሚጸድቀው መመሪያ መሠረት ይቀጥራል ፤ ያስተዳድራል ፤ ያሰና ብታል ፤ ሐ ) የድርጅቱን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለድርጅቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ድርጅቱን ይወክላል ፡ ረ ) የድርጅቱን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለድርጅቱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለድርጅቱ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፪ : በጀት የድርጅቱ በጀትከሚከተሉትምንጮች የተውጣጣይሆናል ፤ ፩ . የፌዴራሉ መንግሥት ከሚሰጠው የበጀት ድጎማ ፣ ፪ ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ፣ እና ፫ ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ። ፲፫ የሂሣብ መዛግብት ፩ . ድርጅቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ ይይዛል ። ፪ የድርጅቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ ደጡሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፳፭ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት