ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚ ኖሩ የህሊና ግምቶች- የፍትሐብሔር ህግ ቁጥሮች 1856 ፣
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ .17068 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ሚ / ር ቢሮኒ አቲክፖ
ውል- የግዴታዎች መቅረት - ስለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ -
2024 ፡- ስለ አቤቱታ -ህጋዊ ስለሆኑ ግምቶች - የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ
ቁጥር 89
አመልካች ከስር ፍ / ቤት መ /
ሰጪ ያልከፈለው የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍለው
በመጠየቅ ባቀረበው ክስ መ /
ሰጪ ሳይቀርብና ኪራዩ ተከፍሏል የሚል ክርክር ሳይነሳ
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በፍ / ብ / ህ / ቁ . 2024 መሰረት ከሁለት አመት በላይ
የሆነው የኪራይ ገንዘብ እንደተከፈለ ይቆጠራል በሚል የአመልካችን ክስ በከፊል ውድቅ
ስላደረገውና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትም ውሳኔውን ስላጸናው የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የስር ፍ / ቤቶች ውሳኔ ጽንቷል ፡፡
1- የሕሊና ግምት ድንጋጊዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጊዎች የተለዩ ናቸው ፡፡
2- የቀረበላቸው ፍሬ ነገር በህግ ግምት ከተሸፈነ ተከሳሽ ፍሬ ነገሩን ካደም አልካደ
ፍ / ቤቶች የህግ ግምቱን ተፈፃሚ ማድረግ አለባቸው ፡፡
ቁጥር 17 ዐ 68 ሐምሌ 19 ቀን 1997
በ 5 ረ ማመልከቻ መነሻ የሆነው የሥር ፍርድ ቤቶች
ዳኞች መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ አብዱልቃድር መሐመድ ስንዱ ዓለሙ
ሂሩት መለሰ አመልካች
የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ ሚ / ር ቢሮኒ አቲክፖ በሌለበት )
በዚህ መዝገብ ለቀረበው አመልካች ክስ ካቀረበበት ገንዘብ መካከል ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው ሂሣብ ተከሣሽ በፍ.ብ.ሕግ ቁጥር 2024 መሠረት እንደከፈለ ስለሚቆጠር ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን ሂሣብ በሚመለከት ከሣሽ ያቀረበው የክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት በመወሰናቸው እና ሌሎችንም ክስ የቀረበባቸው ሂሣቦች ውድቅ በማድረጋቸው ነው ::
የአሁኑ አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም የቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት በማጣቱ የሰበር ማመልከቻ አቅርቧል :: የሰበር ማመልከቻው ይዘት በርካታ ነጥቦችን ያካተተ ሲሆን ዋና ዋና ነጥቦቹ የቤቱ ኪራይ በአሜሪካን ዶላር ሊከፈለን ሲገባ ታልፎብናል ፣ የውሃ ፍጆታና የአገልግሎት ሂሣብ ውድቅ ተደርጎብናል ፣ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን ሂሣብ አስመልክቶ ክሱ ውድቅ መሆኑ አግባብ አይደለም ፣ የተወሰነልን ወጪና ኪሣራም ካወጣነው ወጪ በታች በመሆኑ ትክክል አይደለም የሚል ነው ::
አመልካች ካቀረባቸው ነጥቦች መካከል በሰበር ሊታይ ይገባል የተባለው የሕግ ነጥብ የሥር ፍርድ ቤቶች ተከሣሽ ክሱን ለመከላከል ባልቀረበበት ሁኔታ ፍትሀብሔር ሕግ ቁጥር 2 ዐ 24 በሰፈረው የሕሊና ግምት መሠረት ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው የኪራይ ክፍያ እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት የአመልካቹ ክስ በከፊል ውድቅ ማድረጋቸው አግባብ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ ነው :: በመሆኑም አመልካች
ሲያቀርጾ ኣልስ ካለው ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጥም ለዚሁ በተያዘው ቀጠሮ አልቀረበም ፣ በመሆኑም ፍርደ ያቀረባቸው ሌሎች የቅሬታ ነጥቦች መሠረታዊ የሕግ ስህተት መኖሩን የሚያመለክቱ ስላልሆኑ ይህ ችሎት በነዚህ ቅሬታዎች ላይ ውሣኔ መስጠት አላስፈለገውም ::
የሕሊና ግምቱን በሚመለከት አመልካች መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለው : “ ሀ . በፍ / ብ / ሕ / ቁ .1856 ( 2 ) ዳኞች በገዛ ሥልጣናቸው የይርጋ ደንብን መከላከያ ሊጠቅሱ
አይችሉም በማለት የተደነገገውን በመተላለፍ በራሳቸው አነሳሽነት ክሱ በይርጋ
ውድቅ ነው በማለታቸው ፣ ለ . ተከሣሹ ለቀረበበት ክስ መልስ ለመስጠት ካለመፈለጉም በላይ እዳውን አልካደም ፣ ሐ . የሕሊና ግምት ይወሰድልኝ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም ጠፍቶብኛል ስለዚህ
የሕግ ግምት ይወሰድልኝ በማለት ተከሣሹ ሳይከራከር ፣ መ . የይርጋ ክርክር የሚያነሳው ወገን ግዴታውን ስለመወጣቱ ሳይክድ የተጣለበት ግዴታ ግን በይርጋ ቀሪ ስለሚሆን ከኃላፊነት ነጻ ነኝ አልጠየቅም የሚል
ነው » የሚሉ የክርክር ነጥቦችን በማቅረብ ነው :: መልስ ሰጭ
በሰበር እንዲታይ በተያዘው የሕግ ነጥብ ላይ የቀረበ የመልስ ሰጭ መልስ የለም ::
ችሎት አመልካች ያቀረበውን በማድረግ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2 ዐ 24 የሰፈረው የሕግ ግምት ተከሣሹ ቀርቦ ዕዳውን ባልካደበት ወይም ጭራሽ ባልቀረበበት ሁኔታ ተፈጻሚ ይሆናል አይሆንም በሚለው የሕግ ጉዳይ ትርጉም መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል ፡፡
ወደዋናው ነጥብ ከመግባቱ በፊት አመልካች ያቀረባቸው የመከራከሪያ ነጥቦች የህሊና ግምትን ከሚመለከተው የሕግ ነጥብ ጋር ያላቸውን አግባብነት መርምሮአል ፡፡
አመልካች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2 ዐ 24 የሰፈረው የሕግ ግምት ይርጋን ከሚመለከቱ ድንጋጌዎች ጋር አንድ እንደሆኑ በመቁጠር ፍርድ ቤት የሕሊናውን ግምት በራሱ አነሳሽነት ሊያነሳው አይገባም የሚል የሕግ ክርክር አቅርቧል ፡፡ ሆኖም በፍትሐብሔር ሕጉ የሰፈረው የሕሊና ግምት በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 1845 ( ወይም በሌሎች በርካታ አንቀጾች ) ከሰፈረው የይርጋ ደንብ የተለየ በመሆኑ ፍ /
ቤቱ ይህን መከራከሪያ የሚቀበለው አይደለም :: የይርጋ ደንብ አንድ ክስ በፍርድ ቤት ቀርቦ በሥረነገር እንዳይታይ የሚከለክል ሲሆን የሕሊና ግምት ( በ 2 ዐ 24 የሰፈረው የመከፈል ግምትን ጨምሮ ) በሌላ በኩል የማስረዳት ሸክምን ከአንድ ወገን ወደ ሌላው
ተፈጻሚ ይሆናል ። የማስተላለፍ ውጤት ብቻ ያለው በመሆኑ ከሣሽ ያቀረበውን ክስ ይዘት መርምሮ ውሣኔ መስጠትን የሚከለክል አይደለም ፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ ውስጥ የሰፈረውን ይርጋ ተከሣሹ ወገን ካላነሳው ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊነሳ እንደማይችል በፍትሐብሔር ሕግ ቁ .1856 የተጠቀሰ ቢሆንም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ለይርጋ ድንጋጌዎች እንጂ በሕግ ግምት የማስረዳት ሸክም ከአንድ ተሟጋች ወደ ሌላው በሚዘዋወርባቸው ሁኔታዎች አይደለም :: በመሆኑም የአመልካች ድርጅት ይርጋ Period of limitation ) ከሕግ ግምት ( resumptions ) ጋር በማመሳሰል ለይርጋ ተፈጻሚ የሚሆነው ሕግ ለህግ ግምትም ተፈጻሚ መሆን ይገባዋል በማለት ያቀረበው ክርክር የህጉን መንፈስ ፣ ዓላማና ግልጽ ይዘት ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ::
ቀጥሎ መታየት ያለበትና በዚህ መዝገብ የህግ ትርጉም የሚሰጠው ዋነኛው ነጥብ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2024 የሰፈረው የሕግ ግምት ተፈጻሚ የሚሆነው በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ? የሚል ሲሆን ተከሣሽ ቀርቦ የቀረበበትን ክስ ባልካደበት ሁኔታ
ወይስ አይሆንም ? የሚለው ነጥብም ከዚሁ ተያይዞ የሚነሳ ነው :: የሕግ ግምት አፈጻጸም የሥረነገር ( substantive ) ሕግ እና የሥነሥርዓት ( procedural ) ህግ ገጽታዎች ያሉት ሲሆን ከላይ የተነሱትን ነጥቦች በአግባቡ ለመመለስ የኢትዮጵያ ሕግ በሁለቱም ረገድ ያለውን ዝርዝር ድንጋጌ መመልከትና መረዳት ያስፈልጋል ፡፡
በኢትዮጵያ የሥረነገር ሕጎች በርካታ የሕግ ግምቶች ያሉ ሲሆን አሁን ከቀረበልን ጉዳይ ጋር አግባብነት ያለው በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2024 የሰፈረው ግምት ነው :: ይህ የህግ ግምት ስለ ውሎች ማስረጃ በሚመለከተው ክፍል የሚገኝ ሲሆን በውል የሚጠየቅ ገንዘብ እንደተከፈለ ከሚያስቆጥሩ የሕሊና ግምቶች አንዱ ነው :: ይህ ድንጋጌ ዕዳው እንዲከፈል ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈሉ የቀሩ በአንቀጽ ተዘርዝረው የተቀመጡ ዕዳዎች እንደተከፈሉ ይቆጥራል ፡፡ በዚህ ግምት ከሚሸፈኑ ዕዳዎች መካከል ለቤት ኪራይ የሚከፈል ዕዳ አንዱ ነው ፡፡ ( ቁ .2 ዐ 24 / መ )
የሕግ ግምቶች መሠረታዊ ውጤት የማስረዳት ሸክምን ከአንዱ ወገን ወደሌላው እንዲሻገር ማድረግ ቢሆንም የማስረዳት ሸክሙ የዞረበት ወገን የሕግ ግምቱን ማፍረስ የሚችልበት የሕግ ሁኔታ ይለያያል ፡፡ አንዳንድ የህግ ግምቶች የግምቱ ተጠቃሚ ያልሆነው ወገን ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ በማቅረብ የሚያፈርሳቸው ሲሆን ( Rebutable presumption ) ሌሎች የሕግ ግምቶች ደግሞ ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስን የሚፈቅዱ አይደሉም ፡፡ ( Irrebutable presumptions )
የፍትሐብሔር ሕጉ ከ 2 ዐ 20 - 2024 ያሰፈራቸውን የህግ ግምቶች ለማፍረስ ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ ከሕጉ አንቀጽ 2026 ( 1 ) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ይኸው ድንጋጌ “ ከዚህ በላይ ባሉት ቁጥሮች ላይ ለተገለጠው የሕሊና ግምት መቃወሚያ የሚሆን ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ለመቀበል አይቻልም በማለት በሕጉ የሰፈሩትን ግምቶች ለማፍረስ አንደኛው ወገን ማንኛውንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ እንደማይፈቅድለት በመርህ ደረጃ በግልጽ አስፍሯል :: ይህ አጠቃላይ መርህ ቢኖርም አንዱ ወገን ይህን አስገዳጅ የህግ ግምት ማፍረስ የሚችለው ሌላው ወገን መሀላ እንዲፈጽምለት በመጠየቅ ብቻ ነው :: በዚህ መልክ ሌላው ወገን መሃላ እንዲወርድለት በመጠየቅ የማስረዳት ሸክሙን ለመወጣት የሚሻ ወገን የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 83 በሚያዘው መሠረት ይህን ማስረጃውን ክሱን በሚያቀርብበት ወቅት እንዲጠቅስ ይጠበቅበታል ፡፡
በውል ሕግ የሰፈሩት እነዚህ ድንጋጌዎች የሥረ ነገር ሕግ ክፍሎች በመሆናቸው ፍርድ ቤቶች ሊከተሉዋቸው የሚገባ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌዎች ናቸው :: እነዚህ ድንጋጌዎች የማስረጃን አቀራረብ የሚመለከቱ ከመሆናቸው በስተቀር እንደማንኛውም ሌላ የውል ሕግ ድንጋጌዎች በባለጉዳዮች ቢጠቀሱም ባይጠቀሱም ፍርድ ቤቱ አግባብነት ባለበት ሁኔታ ሁሉ ተፈጻሚ ሊያደርጋቸው የሚገቡ ድንጋጌዎች ናቸው :: በመሠረቱ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ባለጉዳዮች ለጉዳያቸው አግባብነት ያለውን ፍሬነገርና የሚጠይቁትን ዳኝነት ከመግለጽ አልፈው በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን ወይም የማይሆነውን ድንጋጌ እንዲጠቅሱ አይጠበቅባቸውም :: በመሆኑም በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2 ዐ 24 የተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያበቃ ፍሬ ነገር የቀረበለት መሆኑን የተረዳ ፍ / ቤት በዚሁ ድንጋጌ መሠረት የሚሸፈነውን ፍሬነገር እንደተረጋገጠ የመቁጠር ግዴታ አለበት ::
የሕግ ግምቶች አስመልክቶ በፍትሐብሔር ሕጉ የሰፈረው ይህ መሠረተ ሃሣብ ፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉም በተመሣሣይ መንገድ ተደንግጎ የምናገኘው ነው :: በዚሁ ሕግ መሠረት ማንኛውም ተከሣሽ በመርህ ደረጃ ለፍርድ ቤቱ በሚያቀርበው መልስ ክስ የቀረበበትን ነገር በግልጽና በዝርዝር ማስተባበል ይጠበቅበታል ፡፡ በክስ አቤቱታ ላይ የቀረበ ማንኛውም ካልተካደ እንደታመነ ሊቆጠር እንደሚችልም ይደነግጋል ፡፡ ይህ አባባል አጠቃላይ የፍትሐብሔር መደበኛ ሙግት አካሄድን የሚመለከት ቢሆንም ተከሣሹ የሕግ ግምት ተጠቃሚ ሲሆን በግምቱ የሚሸፈነውን ፍሬ ነገር በሚመለከት ይህ ግዴታ እንደሚወርድለት የሕጉ አንቀጽ 89 በግልጽ ያስቀምጣል :: ይህ ድንጋጌ “ አስቀድሞ በአንደኛው ወገን አቤቱታ ወይም ሙግት
በግልጽ የተካደ ጉዳይ ካልሆነ በቀር አንዱ ወገን ተከራካሪ ህጋዊ በሆነ ግምት የሚደገፍበትን ነገር ወይም ሌላው ወገን ማስረጃ እንዲያቀርብ ተገቢ የሆነበትን ጉዳይ ሌላው ወገን በአቤቱታው ውስጥ መጥቀስ አይገባውም » በማለት የሕግ ግምት ተጠቃሚ የሆነ ተሟጋች በሚያቀርበው መልስ በህግ ግምት የተሸፈነውን ፍሬነገር በግልጽ የመካድ ግዴታ እንደሌለበት ያመለክታል ፡፡ በመሆኑም አንድ ተከሣሽ በሕግ ግምት የተሸፈነውን ፍሬ ነገር በማስመልከት በክስ በግልጽና በዝርዝር መካድ አይጠበቅበትም ፡፡ በመሆኑም በህግ ግምት የተሸፈነን ጉዳይ በማስመልከት ማንኛውም ፍርድ ቤት ቢሆን ተከሣሹ በግልጽ ስላልካደ እንዳመነ ይቆጠራል በማለት ፍርድ ሊሰጥ አይችልም :: ይህ መሠረተ ሃሣብ በፍትሐብሔር ሕጉ ካለው መሠረተ ሃሣብ ጋር ተመሳሳይ እና የሚጣጣም ነው ::
የሕግ ግምትን አስመልክቶ ያለው የሕግ ማዕቀፍ ይህ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ውሣኔ ይህንኑ መሠረት ያደረገ መሆን ይጠበቅበታል ፡፡ ተከሣሹ የሕግ ግምት ተጠቃሚ በሚሆንበት ወቅት የሚከተሉት ሂደትና የሚሰጡት ውሣኔም በሌሎች በመደበኛ የሙግት ሂደት ከሚከተሉዋቸው የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ደንቦች የተለዩ መሆናቸው የማይቀር ነው ::
በመሆኑም የቀረበላቸው ፍሬ ነገር በህግ ግምት እስከተሸፈነ ድረስ ፍርድ ቤቶች ተከሣሽ ካደም አልካደ የሕግ ግምቱን ተፈጻሚ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ ተከሣሹ በሌለበት ጉዳዩ እንዲቀጥል መደረጉም አስገዳጅ የሆኑ የሕግ አንቀጾች አፈጻጸም ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም :: ተከሣሹ ፍርድ ቤት ቢቀርብም በግልጽ እንዲክድ የማይገደደውን ፍሬ ነገር ጉዳዩ በሌለበት በመቀጠሉ እንዳመነ የሚቆጠርበት በቂ የሕግ ምክንያት የለም ::
አሁን በቀረበልን ጉዳይ ክስ ከቀረበበት የኪራይ ክፍያ በከፊል መጠየቅ ከነበረበት ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው ስለመሆኑ ከከሣሽ ክስ መረዳት ይቻላል ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ተከሣሽ ባያነሳውም ወይም በሌለበት ቢታይም በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2024 ያለውን የሕግ ግምት ተፈጻሚ ማድረግ ዕዳው እንደተከፈለ መቁጥር ተገቢ ነው :: የሥር ፍርድ ቤቶችም ያደረጉት ይህንኑ ነው :: ስለዚህ ፍርድ ቤቶች ህጉን በትክክል ተፈጻሚ ያደረጉ ስለሆነ ውሣኔው የሚነቀፍ አይደለም ::
1. የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ፀንቷል ፡፡ 2. ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
' ኣፍ ብ / ሕ / ቁ . 2024 የተመለከተው የሕሊና ግምት ከተያዘው ክርክር ጋር
የሀሣብ ልዩነት በአብዛኛው ድምጽ በተሰጠው ውሣኔ በፍ / ብ / ሕ / ቁ 2024 የተመለከተውም ሆነ ሌሎች የሕሊና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ የተለየ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን እኛ
ም ይህን የምንቀበለው ነው :: የሕግ ግምት የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት የማስረዳት ሸክምን በግምቱ ተጠቃሚ ከሆነው ወገን ወደ አልሆነ ተከራካሪ ማሻገር ብቻ መሆኑንም የምናምንበት ነው ::
ይሁን እንጂ ፍርድ ቤት አንድን ሕግ ተመሥርቶ ፍርድ ለማስፈር የቀረበለት ወይም የያዘው የፍሬ ነገር ክርክር ከተጠቃሹ ሕግ ጋር ግንኙነት ያለው እንዲሆን ያስፈልጋል ፡፡ ፍ / ቤቱ ሕጉን መሠረት አድርጎ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊትም ሕጉ ለክርክሩ አግባብነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ፡፡
ያለውን አግባብነት መርምረናል ፡፡ አብዛኛው ድምጽ እዳ እንዲከፍል የተጠየቀው ተከሳሽ ቀርቦ እዳውን ባይክድም ወይም ጭራሹን ባይቀርብም ፍ / ቤት ይህን ድንጋጌ ተመሥርቶ በሕሊና ግምቱ ተጠቃሚ ሊያደርገውና እዳው እንደተከፈለ ሊቆጥርለት ይገባል ሲል ለድንጋጌው በሰጠው ትርጓሜ እና በደረሰበት መደምደሚያ ግን ባለመስማማት እንደሚከተለው በሐሣብ ተለይተናል ፡፡
እንደሚታወቀው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልተከፈለ እዳ እንደተከፈለ ይቆጠራል ዘንድ ሕግ ግምት የወሰደበት የፍ / ብሕ / ቁ . 2024 ማስረጃ የማቅረብ ግዴታና ሰለአቀባበሉ በተዘረዘረበት የፍ / ብ / ሕግ ምዕራፍ ሰባት ክፍል አንድ ስር የሚገኝ ነው :: በዚህ ምዕራፍ ስር ያለ የሕሊና ግምት ልክ እንደ ጽሑፍ ፣ ምስክር ፣ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ሁሉ አንድ የማስረጃ አይነት ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው መሆኑን ከፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2002 ላይ መገንዘብ የሚቻል ነው :: ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እዳው እንደተከፈለ መቆጠሩን ቀሪ ማድረግ እንደሚቻል የሚደነግገው የፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2025 ግምቶች እራሣቸው ማስረጃዎች መሆናቸውን የሚያደረግልን ነው :: ስለሆነም የፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2024 ጨምሮ በዚህ ምዕራፍ ክፍል ሦስት ውስጥ የተደነገጉት ተጠያቂው ገንዘብ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የሕሊና ግምቶች በሙሉ እንደ አንድ የክርክር ማስረጃ የሚወሰዱ እንጂ ሕግ በፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ የሕሊና ግምት የወሰደባቸው ናቸው ሊሰኙ የሚችሉ አይደሉም :: ለአንድ ውሣኔ መሠረት የመሆናቸውም ጉዳይ ከዚህ የሕጉ መንፈስና አላማ ጋር እየተዛመደ ሊታይ
የሚገባው ነው ፡፡ ይህንንም ግልጽ ለማድረግ ጉዳዩን የፍትሐብሔር ሙግት ከሚመራበት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች አኳያ ማየቱ አስፈላጊ ነው ::
አንድ ክስ የቀረበበት ተከሣሽ የተከሰሰበትን ነገር በግልጽ መካድ እንደሚገባውና ይህን ካላደረገ ደግሞ ክሱን እንደአመነ ሊቆጠር እንደሚገባው በፍ / ብ / ሕ / ቁ . 83 ፣ 334 ( 1 ) ( መ ) እና 235 ላይ ተመልክቷል :: እንበልና የሁለት ዓመት ጊዜ ያለፈው የኪራይ ሂሣብ እንዲከፍል ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ቀርቦ አለመክፈሉን ( እዳውን ) ቢያምን ወይም በግልጽ ባይክድ ፍ / ቤቱ የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 242 ን ተመስርቶ በእምነቱ መሰረት ፍርድ ሊሰጥ እንጂ በፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2024 ወደ ተጠቀሰው የሕሊና ግምት ሊገባ የሚችልበት ሁኔታ አይታይም :: የያዘውም ፍሬ ነገር የዚህን ስረ ነገር ሕግ ተፈፃሚነት የሚጠይቀው አይሆንም ::
በሌላ በኩል ደግሞ ይኽን የኪራይ ሂሣብ እንዲከፍል ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ክፍያለሁ ቢልና የቀረበበትን ክስ ቢክድ ፍ / ቤቱ 1 ኛ ተከሣሹ እዳውን ሊከፍል የሚገባው ስለመሆን ፣ አለመሆኑ ጭብጥ ሊይዝ 2 ኛ / በተከሣሹ ቢጠቀስም ባይጠቀስም የፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2024 ን ሊመሠረትና ተከሣሹን በሕሊና ግምት ማስረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን ሊያደርገው ይገባዋል :: በሕሊና ግምት ተጠቃሚው ተከሣሽ ሌላ ማናቸውንም አይነት ማስረጃ ከማቅረብ ግዴታ ነፃ የሚወጣ ሲሆን ከሣሹ ግን ይህ የሕሊና ግምት በፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2026 ( 2 ) መሠረት በመሐላ ብቻ እንዲፈርስለት ለመጠየቅ ይችላል ፡፡
በተያዘው ጉዳይ ሁለት ዓመት ያለፈው የኪራይ ሒሣብ እንዲከፍል ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ቀርቦ መልስ የሰጠ ወይም መከራከሪያውን ያሰማ አይደለም ፡፡ ይህ ደግሞ አግባብነት ካላቸው የፍ / ብ / ሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ ሲታይ ተከሣሹ እዳውን አለመክፈሉን ወይም ክሱን ማመኑን የሚያሳየን እንጂ በምንም መለኪያ ክሱን ክዷል ወደሚል መደምደሚያ ላይ ሊያደርሰን የሚችል አይሆንም :: ፍ /
ቤቱም በፍሬ ነገርም ሆነ በሕጉ ረገድ ልዩነት የተፈጠረበት ክርክር ቀርቦለታል የሚያሰኝ ባለመሆኑም ውሣኔ ሊያሳርፍበት የሚገባ ጭብጥ ለመያዝ አይችልም ፡፡ ይልቁንም ተከሣሹ መከላከያ መልስ አላቀረበምና በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 246 መሠረት በጉዳዩ ጭብጥ አንዲይዝ የሚገደድበት አይሆንም :: ይህ ደግሞ ተከሣሹ ክሱን እንዳመነ ተቆጥሮ በእምነቱ መሠረት ፍርድ ሊሰጥበት እንደሚገባ የሚያመለክተን ነው :: ከላይ እንደተገለፀው የእምነት መነሻ ተደርጎ ፍርድ ሲሰጥ ደግሞ ወደ ሕሊና ግምት ማስረጃው መሄድ አላስፈላጊ ነው :: በውጤቱም ተከሣሹ በሕሊና ግምት ማስረጃው ተጠቃሚ መሆን እንደማይገባውና የፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2024 ም እዳው ባልተካደ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ተከሣሹ ቀርቦ መልስ ( መከላከያ ) ባላቀረበ
* ፋይደሉም :: ስለሆነም በእኛ እምነት ይህ ድንጋጌ ከመሠረቱም ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚገናኝ አይደለ ” በሎምር በስረ ነገር ሕጉ ምዕራፍ 7 ክፍል 3 ስር ጊዜም በፍ / ቤት አነሳሽነት ቀርቦ መልስ ( መከላከያ ) ባላቀረበ ጊዜም በፍ / ቤት አነሳሽነት ለውሳኔ መሠረት ሊሆን እንደማይችል የሚያረጋግጥልን ነው ::
በተጨማሪም አብዛኛው ድምጽ የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 89 ን በመጥቀስና ይህ ድንጋጌ የሕሊና ግምቱ ተጠቃሚ የሆነው ወገን የፍሬ ነገር ክርክር የማቅረብ ግዴታውን የሚያስቀርለት ነው በማለት ድንጋጌው ከስረ ነገር ሕጉ ጋር ይጣጣማል የሚል ማጠቃለያ ላይ መድረሱን ተረድተናል :: እኛም ምንም እንኳን የዚህ ድንጋጌ የአማርኛ ቅጅ በጣም ግልጽ ሆኖ ባናገኘውም ከእንግሊዝኛው ቅጂ ጋር በአንድነት ሲታይ አንደኛ ድንጋጌው በፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ የተደረገ የሕግ ግምትን እሳቤ አድርጎ የተደነገገ መሆኑን ፣ ሁለተኛ የግራ ቀኙን ተሟጋቾች በክርክር ውስጥ መኖር የሚጠይቅ መሆኑን ፣ እንዲሁም ሦስተኛ አንደኛውን ወገን ተከራካሪ ባይከራከርበትም በሕግ ግምቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ጉዳዩ በሌላው ወግን ያልተካደ ይሆን ዘንድ የሚፈልግ መሆኑን ለመረዳት ያህል ግን የሚበቃ መሆኑን ተገንዝበናል :: እነዚህ ሕጉ የሚፈልጋቸው መስፈርቶች ደግሞ እንደ ማስረጃ ከሚቆጠረው የፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2024 ጋርም ሆነ በጉዳዩ ከተያዘው ፍሬ ነገር ጋር የተያያዙ
እንዲሁም የፍ / ሕ / ቁ . 2024 ን እንደተከፈሉ ይቆጠሩ ዘንድ የሕሊና ግምት የተወሰደባቸውን እዳዎች አስመልክቶ ክስ ሲቀርብ ሙግቱ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕጉ የመለከተውን መደበኛ የሙግት ሥርዓት ተከትሎ የሚከናወን እንጂ የተለየ ደንብ ሊከተል የሚገባው ሆኖ አላገኘነውም :: ተከሣሹ ቀርቦ እዳው ( ክሱን ) በመካድ ነፃ ሊሆን አይገባውም :: ይልቁንም የሕሊና ግምቱ ለፍርድ መሠረት ሊደረግ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለምና ክሱን በማስረጃ አስደግፎ ያቀረበው ከሳሽ ( አመልካች ) ክሱን በመሰረትክበት ጊዜ ያልተከፈለኽ ስለመሆኑ በመሐላ እንዲረጋገጥ አልጠየቅክም በሚል ምክንያት እዳው አይከፈልኽም ሊባል የሚገባው ሆኖ አላገኘውም ::
በእነዚህ ምክንያቶች ስማችን በ 2 ኛ እና በ 4 ኛ ተራ የተጠቀሰው ዳኞች የስራ ፍ / ቤቶች የሰጡት ፍርድ ተሽሮ አመልካቹ የጠየቀው የቤት ኪራይ እንዲከፈለው ሊወሰን ሲገባ መጽናቱ ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው ፍርዱ ሊሻር ይገባው ነበር ስንል በሐሣብ
ተለይተናል ::
You must login to view the entire document.