×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 79 1991 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻ ሕፍት አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፫ አዲስ አበባ - ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፻፬ / ፲፬፻፶፩ ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ገጽ ፩ሺ፩፻፴ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፬ / ፲፱፻፵፩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አዋጅ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍትን በተቀናጀ ሁኔታ መምራት፡ የሀገሪቱን የመዛግብት የመጻሕፍትና መሰል ጽሑፎችን ፣ ቀረጸ ድምጽና ምስል ማሰባሰብ ፣ የዶክሜን | and Library in a coordinated manner , the collection of ቴሽን አገልግሎትን በዘመናዊ መልክ በአንድ ማዕከል ማደራጀትና | archives , books , related texts , audio and video recording , the የሀገሪቱን የመረጃ አገልግሎት ማዳበር አስፈላጊ መሆኑ ስለ ነበት ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻ ሕፍት አዋጅ ቁጥር ፩፻ኞ፱ / ፲፱፻፶፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ጅ የተፈጻሚነት ወሰን ፩ ይህ አዋጅ መዛግብትን በተመለከተ እንደ አግባቡ በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች : ' በፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅቶች፡እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የከተማ አስተዳደሮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ። ያንቶ ዋጋ 440 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ.ቁ : ዥሺ፩ ገጽ ፩ሺ፩፻፴፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ፪ : ሕትመትን የሚመለከቱ የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች እንደ አግባቡ በማንኛውም እትም ወይም ከፊል እትም ፣ ደራሲ፡ አታሚ፡ አሳታሚ፡ አባገር፡ አከፋፋይና ወኪል ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፫ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፡ ፩ . “ ድርጅት ” ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግ ብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት ነው : ፪ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው፡ ፫ . “ መዛግብት ” ማለት ቅርፁንና መልዕክቱ የተላለፈ በትን ሁኔታ ሳይለይ መንግሥታዊ መ / ቤቶች እንዲሁም ግለሰቦች የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴያቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የተፈጠረና አስተዳደራዊ እን ቅስቃሴው ካበቃ በኋላ በመረጃ ፋይዳነቱ ቋሚ ጥበቃ እንዲደረግለት የተመረጠማናቸውም በኦርጂናልም ሆነ በቅጅ መልክ የሚገኝ ጽሑፍ፡ ወይም በካርታ፡ በግራፍ የተገለጸ ወይም በድምጽና በሥዕል፡ በፎቶግራፍ ወይም በመሳሰለ ሠነድ ያለ ሪኮርድ ነው ፡ ፬ . “ የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ” ማለት በክልል አስተዳደር ወይም በከተማ አስተዳደር ሥር ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ መጻሕፍት ነው : ፭ “ ሪኮርድ ” ማለት መልዕክቱ የተላለፈበትን ቅርጽና የመልዕክቱን ዓይነት ( ይዘት ) ሳይለይ በአመንጪው ተቋም ወይም ግለሰብ ሥራ ሂደት የተፈጠረና ለተፈጠ ረበት ጊዜና ቦታ በመረጃነት ሊቀርብ የሚችል ነገር ግን በመረጃ ፋይዳው ተመዝኖና ተመርጦ ወደ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ያልተዛወረ ለመዛወር በሂደት ላይ የሚገኝ ማናቸውም ደብዳቤ፡ ማስታወሻ፡ ብትን ጸሑፍ፡ ጥራዝ፡ መጽሐፍ፡ ዕቅድ፡ ካርታ፡ ንድፍ፡ ቅርጸ፡ ሥዕላዊ ወይም ግራፊክ፡ ፎቶግራፍ፡ ፊልም፡ ማይክሮፊልምና ማይክሮፊሽ፡ የድምጽ ሪኮርድ፡ ቪዲዮ ቴፕ ወይም በኤሌክትሮኒክ የተመዘገበ መረጃ ነው፡ ፮ “ የታተመ ጽሑፍ ” ማለት በማናቸውም መካኒካዊ ወይም ኤሌክትሮኒካዊ ዘዴ የታተመ መጽሐፍ ወይም የመጽሐፍ ክፍል ፡ ጋዜጣ ፡ መጽሔት ፡ በራሪ ወረቀት ፣ ካርታ ፡ ዕቅድ ፡ ሰሌዳ ፡ ብትን እትም ፡ሠንጠረዥና ሌላ ተመሳሳይ ሠነድ ነው ፡ ፯- « በከፊል የታተመ ' ( ግሬይ ሊትሬቸር ) ? » ማለት ልባሱ ብቻ በማተሚያ ቤት ታትሞ የውስጥ ጽሑፉ በታይፕ ወይም በኮምፒውተር ወይም በስቴንስል ተቀርጾ የተባዛ የመረጃ ፋይዳ ያለው ሰነድ ነው ፡ “ የተባዛ ጽሑፍ ” ማለት በማተሚያ ቤት ሳይሆን በታይፕ ወይም በኮምፒውተር በወረቀት ላይ የተመታ ወይም በስቴንስል ተመትቶ የተባዛና የዶክሜንት ዋጋ ያለው ጽሑፍ ነው፡ ፬ . “ ማኑስክሪፕት ” ማለት በባሕላዊ ዘዴ የተዘጋጀ ታሪካዊ ፡ ባሕላዊ ወይም ሥነጥበባዊ ይዘት ያለው ጽሑፍ ነው ፡ ፲ “ ቀረጸ ድምጽ ” ማለት በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ አማካ ኝነት በድምጽ ተቀርጾ የሚተላለፍ መረጃ ነው ፡ ፲፩ “ ቀረጸ ምስል ” ማለት በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ አማካ ኝነት በምስል ተቀርጾ የሚተላለፍ መረጃ ነው ፡ “ ቀረጸ ምሥልና ድምጽ ” ማለት በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ አማካኝነት ድምጽና ምሥልን በማጣመር የሚተላለፍ መረጃ ነው : ገጽ ፩ሺ፩፻፴፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ፲፫ “ ትውፊት ” ማለት ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ በቃል የተላለፈና የሚተላለፍ የአንድ ሕዝብ ወይም አካባቢ ባህል ፡ ወግ ፡ እምነት ፡ ታሪክና ሌሎች ማህበራዊ ዕሴቶችን በዘፈን ፡ በዝማሬ ፡ በተረትናምሣሌ እና በሌሎች መንገዶች አማካኝነት የሚገልጽ ሥነ ቃል ፲፬ . “ የቃል ታሪክ ” ማለት በቃል ምልልስ ከሰው የተገኘና በካሴት የተቀረጸ ወይም በጽሑፍ ተገልብጦ የሚገኝ የታሪክ መረጃ ነው ፡ ፲፭ “ የመረጃ አመንጭ ” ማለት ሥራውን በሚያከናው ንበት ጊዜ የተፈጠረ የመረጃ ክምችት ያለው ሰው ነው፡ ፲፮ “ አሳታሚ ድርጅት ” ማለት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም አሳታሚ ድርጅት ነው : ፲፯ . “ አታሚ ” ማለት በመካኒካል ኃይል በመንቀሳቀስ ጽሑፎች : ቀረጸ ድምጽና ቀረጸ ምስል የሚያትም ወይም የሚያራባ ሰው ነው ፡ ፲፰ . “ ማተሚያ ቤት ” ማለት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ | 18 ) “ Printing Press ” means any entity in the country የሕትመት ሥራን የሚያከናውን ድርጅት ነው ፡ ፲፱ . “ መጽሐፍ ” ማለት የወቅታዊ ዜና ጽሑፍ ያልሆነና ቢያንስ አርባ ዘጠኝ እና ከዚያም በላይ ገጾች ያሉት የታተመ ጽሑፍ ነው ፡ ፳ “ የዶክሜንት ቅርስ ” ማለትጥንታዊ የብራና ጽሑፎች፡ | 20 ) “ Documentary Heritage ” means ancient parchment ጥንታዊ ሕትመቶች ፡ ማናቸውም ዓይነት እትምና እትም ያልሆነ እንዲሁም በከፊል የታተሙ ጽሑፎች ፡ በዲጂታል ኤሌክትሮኒክስ ፎርም የተቀረጸ ቀረጸ ድምጽ፡ ቀረጸ ምስል፡ ቀረጸ ድምጽና ምስል ሌሎችም በመረጃ ፋይሎች በቅርስነት ተጠብቀው ለትውልድ የሚተላለፉ ሠነዶችን የሚያጠቃልል ነው ፡ ፳፩ . “ ሲዲ ” ማለትኮምፓክት ወይም ኦፕቲካል ዲስክ የሆነ | 21 ) “ CD ” means compact or optical disk used in com እና በኮምፒውተር እና ሌላ ተመሳሳይ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ጽሑፍና ዳታ ድምጽና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በተናጠል ወይም በማዋሀድ ለማከማቸት እንዲሁም መረጃን ለማሠራጨት ወይም ለማስተላለፍ አገልግሎት የሚውል ነው ፡ ፳፪ • “ ሕትመት ” ማለት የታተመ ጽሑፍን ፡ በከፊል የታተመ ጽሑፍን ( ግሬይ ሊትሬቸርን ) ፡ ቀረጸ ድምጽን፡ ቀረጸ ምስልን፡ቀረጸ ድምጽና ምስልን ፡ እና በማግኔቲክ ዲስክ ( ኮምፓክት ዲስክ ) የተቀረጹ ሕትመቶችን ያጠቃ | 23 ) “ Person ” means any natural or juridical person . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ነው ። ክፍል ሁለት ስለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት ፬ . መቋቋም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝለየብቻ ራሳቸውን ችለው ሊቋቋሙ ይችላሉ ፪ ድርጅቱ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ይሆናል ። ፭ ዋናው መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ማቋቋም ገጽ ፩ሺ፩፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም የድርጅቱ አቋም ድርጅቱ ፡ ፩ አንድ የመማክርት ጉባዔ ፡ ፪ . አንድ ዋና ዲሬክተር ፡ እና ፫ . አስፈላጊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፯ የድርጅቱ ዓላማ የድርጅቱ ዓላማ የሀገሪቱን የመረጃ ሀብቶች እያሰባሰበ ፡ እያደራጀና እየተንከባከበ በመጠበቅ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለማገናዘቢያ ( ሪፈረንስ ) አገልግሎት ማቅረብ ይሆናል ። የድርጅቱ ሥልጣንና ተግባር ድርጅቱ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡ ፩ በሀገሪቱ ከሚገኝማንኛውም ተቋም የመነጩ ሪኮርዶች ወደድርጅቱ ከመዛወራቸው በፊት በያሉበት ተቋም በበቂ ቦታና አስተማማኝ ሁኔታ እንዲያዙ ያደርጋል ፡ ፪ . የታተሙ ጽሑፎች ፡ በከፊል የታተሙ ጽሑፎች ( ግሬይ ሊትሬቸር ፡ ያልታተሙ ጽሑፎች ፡ የማኑስክሪፕት ፡ የታሪካዊ መዛግብትና የሪኮርዶች እንዲሁም የትውፊ ታዊም ሆነ የቃል ታሪኮች ፡ የቀረጸ ድምጽ፡ የቀረጸ ምስል የቀረጸ ምስልና ድምጽ በአጠቃላይም የመረጃ ቅርሶች ብሔራዊ የክምችት ማዕከል ሆኖ ይሠራል ፡ ክምችቶቹን በሳይንሳዊና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለጥናትና ምርምር እንዲውሉና ረዥም ዕድሜ እንዲኖ ራቸው ጥበቃ ያደርጋል ፡ በውጭ ሀገር ያሉትን የኢትዮጵያ የስነጽሑፍ ቅርሶች ወደ ሀገር ለማስመለስ ወይም ቅጂውን ለማግኘት ጥረት ያደርጋል ፡ ተግባራቸውን ያቋረጡ መሥሪያ ቤቶችን ሪኮርዶችና ባለቤት የሌላቸውን መዛግብት ወደ ድርጅቱ እንዲዛወሩ ያደርጋል ፡ ይንከባከባል ፡ ፭ ሪኮርዶች ከየአመንጪ ድርጅቶች ተሰባስበው በአስተ ማማኝ ሁኔታ በጊዜያዊነት የሚከማቹበት ፡ ፋይዳ ያላቸው የሚመረጡበትና ወደ ብሔራዊ ቤተመዛግብት የሚተላለፉበት ፡ ያልተመረጡት የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት የሪኮርድ ማዕከል ያቋቁማል ፡ በአገሪቱ ከሚገኙ ቤተመዛግብት ፡ ቤተመጻሕፍት ፡ የዶክሜንቴሽን ማዕከላትና በሌሎች መረጃ ሰጪ አካላት መካከል የጋራ ትብብር በመፍጠር የሀገሪቱን ብሔራዊ የመረጃ ሀብት ወጥነት ባለው ሁኔታ በጋራ ያደራጃል ፡ የመረጃ ባንክ ( ዳታ ቤዝ ) ይፈጥራል ፡ በአግባቡና በተቀላጠፈ ዘዴ ለመጠቀም የሚያስችል ብሔራዊ የመረጃ ሥርዓት ይዘረጋል ፡ ጊ ብሔራዊ ቤተመዛግብትን ፡ ቤተመጻሕፍትንና ሪኮርድ ማዕከልን እንዲሁም የሪኮርድ አመንጪ ተቋማት የሪኮ ርዶች አያያዝና ደኅንነትን በተመለከተ ደንብና መመሪያ እንዲወጣ ሃሳብ ያቀርባል ፡ ተግባራዊነቱን ይቆጣጠራል፡ ፰ ለመንግሥት ወይም ለሕዝብ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውና በግለሰቦችእጅ የሚገኙመዛግብት ለሰው ሠራሽ ወይም ለተፈጥሮ አደጋ የተጋለጡ ሆነው ሲገኙ ለመንግሥትና ለሕዝብ ጠቀሜታ ሲባል ካሣ በመክፈል ወደ ድርጅቱ እንዲዛወሩ ያደርጋል ፡ ዋና ( ኦርጂናል ) መዛግብትና የዶክሜንት ቅርሶች በቋሚነት ከአገር እንዳይወጡ ቁጥጥር ያደርጋል ፡ የቅጂዎችን ይዘት በመመርመር ከሀገር እንዲወጡ ፈቃድ ይሰጣል ፡ † የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝገበ መጻሕፍትንና መዝገበ መጽሔትን ያዘጋጃል ፡ ያሳትማል ፡ ያሰራጫል ፡ ገጽ ፩ሺ፩፻፴፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም የሀገሪቱ ዓለም አቀፍ እስታንዳርድ የመጻሕፍትና የመጽሔት መለያ ሰጪ አካል ሆኖ ይሠራል ፡ ፲፪ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፲፩ ) በተደነገጉ ጉዳዮች ላይ ሀገሪቱን ይወክላል ፡ በሀገሪቱ ውስጥ ተዘጋጅተው ለሚታተሙ ወይም ከሀገር ውጪ ተዘጋጅተው በሀገር ውስጥ ለሚታተሙ በፊልም፡ በማግኔቲክ ቴፕ ወይም ማግኔቲክ ዲስክ የተቀረጹ የሥነጽሑፍ ፡ የታሪክ ፡ የሣይንስና ለሌሎች ተመሳሳይ የጽሑፍ ሥራዎች ፡ የቀረጸ ድምጽ ፡ ቀረጸ ምሥልና ድምጽ እንዲሁም የሲዲ ሥራዎች ባለቤ ትነት መብት መዝጋቢ አካል ሆኖ ይሠራል ። ይህንኑ በተመለከተም በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ማዕከል በመሆን ሀገሪቱን ይወክላል ፡ በሀገሪቱ የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም በግለሰቦች እጅ የሚገኙትን ውድና ብርቅ የሆኑትን ጥንታዊ ጽሁፎችና ሌሎች ሥዕሎች ከተቋማቱ እና ከግለሰቦቹ ጋር በሚደረግ ስምምነት በማዕከል ያሰባስባል : ማሰባሰቡ በማይቻልበት ሁኔታ በማይክሮ ፊልምና በማይክሮፊሽ በመቅረጽ ይይዛል እንዲሁም ለጥናትና ምርምር ለተጠቃሚዎች በአመቺ ሁኔታ ያቀርባል ፡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ እንዲሁም የታወቁ የጥናትና ምርምር ተቋማት ለሚያ ወጡአቸው እትሞች አከማች ይሆናል ፡ ፲፮ በመንግሥት ውሳኔ ምስጢራዊ የሆኑ መዛግብት ምስጢር መጠበቁን ያረጋግጣል ፡ ፲፯ • በክልል መስተዳድሮች ከተቋቋሙና ከሚቋቋሙ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት እንዲሁም የሕዝብ አብያ ተመጻሕፍት ጋር በመተባበር ይሰራል ፡ ድርጅቱ ለተቋቋመበት ዓላማ የሥልጠና ማዕከል ሆኖ ይሠራል ፡ ፲፬ ከሀገር አቀፍና ዓለምአቀፍ አካላት ጋር ግንኙነት በማድረግ የቤተመጻሕፍትና የቤተመዛግብት ሙያ እንዲያድግና እንዲስፋፋ ጥረት ያደርጋል ፡ ለሚሰጠው አገልግሎት እንደአስፈላጊነቱ ዋጋ ያስከ 9. Members of the Advisory Council ፍላል ፡ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ፡ በስሙ ይከሳል ፡ ይከሰሳል ። ፱ የመማክርት ጉባዔ አባላት ፩ . የመማክርት ጉባዔ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፡ ሀ ) የሚኒስቴሩ ተወካይ ለ ) የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካይ ሐ ) የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ መ ) የፍትሕ ሚኒስቴር ተወካይ ሠ ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ረ ) የሣይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ተወካይ ሰ ) የዩኒቨርስቲዎች ተወካይ ሸ ) የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ሰብሳቢ ቀን የሥነጥበባት ማኅበሮች ሰብሳቢ በ ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲ ያን ተወካይ ተ ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባዔ ተወካይ ቸ የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ባለሥልጣን ተወካይ ” ህ የኢምግሬሽን፡ የደህንነትና የስደተኞችጉዳይ ባለሥ ልጣን ተወካይ ) የድርጅቱ ዋና ዲሬክተር ...... አባልና ፀሐፊ ገጽ ፩ሺ፩፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ • ም • ፪ ከላይ የተደነገገው ቢኖርም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሌሎች ኣካላትም በአባልነት ሊወከሉ ይችላሉ ፲ የመማክርት ጉባዔው ሥልጣንና ተግባራት የመማክርት ጉባዔው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡ ድርጅቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እንዲችል ምክር ይሰጣል ፡ ፪ . ብሔራዊ የሪኮርዶች አስወጋጅ ኮሚቴን ይሰይማል ። ፲፩ የመማክርት ጉባዔው ስብሰባ ፩ ጉባዔውየራሱን የስብሰባ ሥነሥርዓት ደንብ ያወጣል ፣ ፪ ከአባላቱከግማሽ በላይ ሲገኙምልአተ ጉባዔ ይኖራል ፣ ፫ የጉባዔው ውሳኔ በአብዛኛው ድምጽ ይወሰናል ፡ ድምጽም ለሁለት በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ፣ ፬ • የመማክርት ጉባዔው አባላት በአባልነት የሚቆዩት ለአምስት ዓመት ብቻ ይሆናል ። ፲፪ ስለድርጅቱ ዋና ዲሬክተር ፩ . ዋናውዲሬክተር በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት ይሾማል ። ፪ ዋናው ዲሬክተር የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከሚኒስትሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የድርጅቱን ሥራ ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተመለከተው እንደተ ጠበቀ ሆኖ፡ ዋናው ዲሬክተር ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ለድርጅቱ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የድር ጅቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ሐ ) በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፡ መ ) ለድርጅቱ በተፈቀደው ፕሮግራም መሠረት የገንዘብ ክፍያዎችን ይፈጽማል ፡ ሠ ) የድርጅቱን የሥራ ክንውን የሚያሳይ ዓመታዊ ሪፖርት ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፡ ረ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ድርጅቱን ይወክላል ። ዋናው ዲሬክተር ለድርጅቱ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈ ልገው መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለድርጅቱ ሌሎች ኃላፊዎች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ፡ ሆኖም እርሱን ተክቶ የሚሠራው ሰው ውክልና ከሰላሳ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ ከሆነ ውክልናው ለሚኒስትሩቀርቦ መፈቀድ ይኖርበታል ። ክፍል ሦስት የብሔራዊ ቤተመዛግብት አስተዳደር የሪኮርድ አመንጪ ግዴታ ማንኛውም የሪኮርድ አመንጪ መሥሪያ ቤት ፡ ፩ . በተገቢው የተደራጀ የሪኮርድና የማኅደር አገልግሎት ዘርፍ ይኖረዋል ፡ በየዓመቱ መጨረሻ ፳፭ ዓመትየሚሞላቸውንና የማይን ቀሳቀሱ ሪኮርዶችን ወደ ድርጅቱ የሪኮርድ ማዕከል ያዛውራል ፡ ገጽ እሺ፩፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም [ ከመሥሪያ ቤቱ ተሰርቀው ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ የሚጠፉ ሪኮርዶችን በተመለከተ መሰረቃቸው ወይም መጥፋታቸው በታወቀ ፡ የመረጃን ይዘት ለመለወጥ የተፋቁ ወይም የተደለዙ ሪኮርዶችን በተመለከተ ይህ ሁኔታ በተረጋገጠ በአንድ ወር ውስጥ ለድርጅቱ ሪፖርት ያደርጋል ፡ ፬ . በመሥሪያ ቤቱ ይዞታ ስር ያሉ ሪኮርዶች ከመሥሪያ ቤቱ ውጪ በዘላቂነት የሚዛወሩበት ሁኔታ ሲፈጠር ዝውውሩ ከመከናወኑ በፊት ሁኔታውን ለድርጅቱ ማሳወቅ አለበት፡ ፭ ኤክስፐርትና ከዚያም በላይ ማዕረግ ካላቸው አባላት የተውጣጣና መወገድ የሚገባቸውን ሪኮርዶች ዝርዝር የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ያቋቁማል ፡ ፮ : የሪኮርድና ማኅደር ሥራን ዘመናዊ ለማድረግ የሚወ ጡትን መመሪያዎች ተግባራዊ ያደርጋል ፡ ፯ መሥሪያ ቤቱ በሚፈርስበት ጊዜ ሪኮርዶቹን ወደ ድርጅቱ ማዛወር አለበት ። ፲፬ ሪኮርዶችን ስለማስወገድ ፩ . ማንኛውም የሪኮርድ አመንጪ መሥሪያ ቤት ሪኮር ዶችን ማስወገድ አይችልም ። ፪ . ከ፲፱፻፳፰ ዓም በፊት የተፈጠሩማናቸውም መዛግብት አይወገዱም ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ማናቸውም ሪኮርድ የሚወገደው በድርጅቱ ብቻ ይሆናል ። ፲፭ የድርጅቱ ግዴታ ድርጅቱ፡ ፩ : ከመረጃ አመንጪዎች የተላኩለትን ሪኮርዶች ከ፭ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አደራጅቶ ለጥናትና ምርምር ሥራ ያቀርባል ፡ ዘጠየቁ ጊዜ ሁሉ በውሰት ያቀርባል ። ፲፮ . ስለተጠቃሚዎች መብትና ግዴታ የዚህ አንቀጽ አንቀጽ ፲፰ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የሀገሪቱ ሰው መዛግብትን ለጥናትና ለምርምር የመጠቀም መብት አለው ። አፈጻጸሙ ድርጅቱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል ። ፪ አመንጪዎች መዛግብታቸም የሰብ ፲፯ በመዛግብት መጠቀም ስለሚከለከልበት ሁኔታ ፩ . ከላይ በአንቀጽ ፲፮ የተደነገገው ቢኖርም ፡ ሀ ) መዝገቡ ወደ ድርጅቱ ከመዛወሩ በፊት በአመን ጪውና በድርጅቱ መካከል በተደረገ ስምምነት በመንግሥት በተወሰነው መሠረት የመዝገቡ የምስጢራዊነት ዘመን ያላለቀ ከሆነ ፡ ለ ) መዝገቡ የያዘው ምስጢር ይፋ መውጣት በሀገርና በሕዝብ ደህንነት ላይ አደጋ የሚያደርስ መሆኑን ድርጅቱ በእርግጠኝነት ሲያምንበት ፡ ሐ ) የግል መዛግብትን በተመለከተ ፡ በአስረካቢውና በድርጅቱ መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት ጥያቄው ሊስተናገድ የማይችል ሲሆን ፡ በመዛግብት ለመጠቀም የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት አያገኝም ። ፪ . ድርጅቱ ጥያቄውን ያልተቀበለበትን ምክንያት ጥያቄው በቀረበ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በጽሁፍ መግለጽ አለበት ። ገጽ ፩ሺ፩፻፴፯ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳ደን ፲፱፻፶፭ ፲፰ መዛግብትን ስለማስተላለፍና ባለቤትነትን ስለማዛወር ፩ መንግሥታዊ መዛግብትን በንግድ መልክ መማዛት ፡ መሸጥ : በስጦታ ወይም በውርስ እንዲሁም በማን ኛውም መንገድ ማስተላለፍ የተከለከለ ነው ። በግል ባለቤትነት ስር የሚገኙ መዛግብትን በውርስ ፡ በስጦታ ወይም በግዢ ወደ ድርጅቱ ማዛወር ይቻላል ። ፫ . ማንኛውም ግለሰብ ወይም ተቋም በይዞታው ስር የሚገኙ መዛግብትን በውርስ : በስጦታ : ወይም በሽያጭ መልክ ሲያስተላልፍ ለድርጅቱ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ። ክፍል አራት ስለብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት አስተዳደር ፲፱ : ሕትመቶችን በድርጅቱ የማኖር ግዴታ ፩ . ማንኛውም አታሚ ወይም አሳታሚያተመውን ወይም ያሳተመውን ማንኛውም ዓይነት ህትመት ቅጂ በድርጅቱ የማኖር ግዴታ አለበት ። ውጪ ሀገር ተዘጋጅተው ኢትዮጵያ ውስጥ የተባዙ ሥራዎች አዘጋጅ ወይም አከፋፋይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገውን የማክበር ግዴታ አለበት ። ፫ . ማንኛውም አሳታሚ ወይም ደራሲ በሙሉም ሆነ በከፊል ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘጋጅተው ውጪ ሀገር የታተሙ ህትመቶችን ፫ ቅጂ የማኖር ግዴታ አለበት ። ፳ ህትመቶችን የማኖሪያ ጊዜና ሁኔታ ህትመቶችን የማኖርግዴታ የተጣለበትማንኛውም አታሚ | 20. Time and Condition for the Deposit of Printed Matters አሳታሚ ፡ ደራሲ ፡ ኣባዢ ወይም አከፋፋይ ህትመቶችን ህትመቱ ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ በ፴ ቀናት ውስጥ በአደራ ፖስታ ወይም በልዩ መልክተኛ ለድርጅቱ ቤተ መጻሕፍት ማስረከብ አለበት ። ፳፩ የዶክሜንት ቅርሶችን ስለማስተላለፍና ባለቤትነትን ስለማዛወር እ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ተቋም የሚገኙ የዶክሜንት ቅርሶችን በውርስ ፡ በስጦታ ወይም በሽያጭ መልክ ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ ለድርጅቱ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ፡ # የዶክሜንት ቅርሶችን በዚህ ሕግ ከተደነገገው ውጫ ከሀገር ማስወጣት የተከለከለ ነው ። 7 ዞታው ስር | ክፍል አምስት ልዩልዩ ድንጋጌዎች ጽያ ደንብና መመሪያ ስለማውጣት ፩ ሚኒስትሩ የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ መመሪያዎችን ያወጣል ። ያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ ደንብ ያወጣል " ጽ የመተባበር ግዴታ ማንኛውም መንግሥታዊ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እንዲሁም ግለሰብ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የመተባበር ግዴታ አለበት ። ገጽ ፩ሺ፩፻፴፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ ሰኔ ፳፪ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም : ፳፬ . የተሻሩ ሕጎች ፩ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፰ እና የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር ፵፲፱፻፳፰ በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ። ፪ የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች የሚቃረን የማንኛውም ሕግ ድንጋጌ በዚህ አዋጅ ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፳፭ . ቅጣት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ከበድ ያለ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው ፡ ፩ . የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፫ ( ፪ ) የጣሰ እንደሆነ እስከ ኣንድ ዓመት በሚደርስ እሥራትና እስከ ፪ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል ። ፪ . የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፪ ( ፩ ) የጣሰ እንደሆነ ከአንድ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከ፪ ሺ እስከ ፳ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል ። ህገወጥ በሆነ ሁኔታ መዛግብትን : መጻሕፍትንና የዶክሜንት ቅርሶችን ከሀገር ያስወጣ እንደሆነ ከሦስት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራትና ከ፭ ሺ እስከ ፳ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል ። የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፰ ( ፩ ) የጣሰ እንደሆነ ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ፲ ሺ እስከ ፳ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል ። የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲ የጣሰ እንደሆነ እስከ ፪ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፮ የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፳፪ ( ፩ ) የጣሰ እንደሆነ እስከ ፪ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፡ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ማረሚያ ቁጥር ፪ / ፲፱፻፲፩ በኢንቨስትመንት ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፻፲፩ አንቀጽ ፪ ( ፪ ) ሥር ባለው “ አንቀጽ ፰ ( ፪ ) “ ፐርሰንት ” የሚለው “ ፳፯ ፐርሰንት ” ተብሎ ይነበብ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?