የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር አዲስ አበባ – ህዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፪ / ፲፱፻፵፩ ዓም የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ . . . ገጽ ፰፻፵፯ | አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፪ / ፲፱፻፲፮ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ዘርፍ ካሉበት የአሠራር ችግሮች በማላቀቅ በዘርፉ የተሠማሩ ድርጅቶች በዓለምአቀፍ ገበያዎች ተወዳዳሪነታቸውን ማጐልበት በማስፈለጉ ፤ ይህንን ዓላማ ለማሳካት አስፈላጊው ሥልጣንና ተግባር የተሰጠውና ቀደም ሲል ተቋቁሞ በነበረው የኢትዮጵያ የንግድ ማስተባበሪያና የመረጃ ልውውጥ ማዕከል ሲከናወኑ የነበሩ ሥራዎችን ጭምር አካቶ የሚሠራ አንድ ራሱን የቻለ ኤጀንሲ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ _ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፪ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ( ፪ መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድማስፋፊያ ኤጀንሲ ( ከዚህ በኋላ “ ኤጀንሲው ” ተብሎ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለውና ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ የኤጀንሲው ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ። | ያንዱ ዋጋ 2 . 30 | ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ | ገጽ ፰፻፰፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ህዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ ም Federal Negarit Gazeta No . 9 24 November , 1998Page 888 ፫ ዋና መሥሪያ ቤት - የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት ኣዲስ ኣበባ ሆኖ እንደአስፈላ | The Agency shall have its head office in Addis Ababa ጊነቱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ይኖሩታል ። ፬ . የኤጀንሲው ዓላማ የኤጀንሲው ዓላማ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ማስፋፋት ይሆናል ። ፭ የኤጀንሲው ሥልጣንና ተግባር | ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የመንግሥትን የወጪ ንግድ ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ለማስፋፋት የሚያ ስችሉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስና ጥናቶችን በማካሄድ ለላኪዎች ልዩ ልዩ ሙያዊ እገዛዎችንና ሥልጠናዎችን መስጠት ፡ ፪• ከወጪ ንግድ ጋር ግንኙነት ያላቸው መሥሪያ ቤቶች አሠራር ለወጪ ንግዱ መስፋፋት በሚያመች መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን በማረጋገጥ ላኪዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች እንዲወገዱ ማድረግ ፡ ፫ . በአምራቾች ፡ በአቅራቢዎች ፡ በላኪዎችና በአገልግሎት ሰጪዎች መካከል ቀልጣፋ ግንኙነትና ቅንጅት ያለው አሠራር እንዲኖር ማበረታታት ፡ ፬ አገሪቱ በውጭ ገበያ ያላትን ተወዳዳሪነት ለማዳበር ስለወጪ ምርቶች የአቅርቦትና የገበያ ጥናት ማካሄድና ለላኪዎች ማሠራጨት ፡ ፭ በአዳጊ ገበያዎች ውስጥ ለመግባትና አሁን ኣገሪቷ ባላት ገበያ ውስጥ ተጠናክሮ ለመቆየት የሚያስችል የምርቱ የማስተዋወቂያ ስልቶችን በማዘጋጀትና ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የማስተዋወቅ ሥራ በማካሄድ የኢትዮጵያ ላኪዎችን ከገዢ ድርጅቶች ጋር ማገናኘት ፡ ፮ . ላኪዎች በተለያዩ አህጉራዊና ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒ ቶችና ሌሎች የንግድ ማስፋፊያ መድረኮች ላይ እንዲ | ሳተፉ ተገቢውን እገዛ ማድረግ ፣ ቪ በሌሎች አገሮች ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት ጋር የተጠናከረ ትብብር እና ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ፤ ለወጭ ንግድ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ከሚገኙ ምንጮች በማሰ ባሰብ መረጃዎችን በማጠናቀር ፣ በማዘጋጀትና ለተጠቃ ሚዎች በማሰራጨት ከላኪዎችና ከውጭ ገዢዎች ለሚቀርቡ የንግድ መረጃ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ፤ ፬ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዋጋ ማስከፈል ፤ ፲ በዚህ አዋጅ የተሰጡትን ተግባራት ለማከናወን አግባብ ካላቸው የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ ፤ ፲፩ . የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል ፣ በራሱ ስም መክሰስና መከሰስ ፡ ፲፪ ዓላማዎቹን ከግቡ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ማከናወን ። የኤጀንሲው አቋም ኤጀንሲው ፡ ፩ . የዲሬክተሮች ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ | የሚጠራ ) ፤ ፪• በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ዲሬክተር ፣ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ገጽ ፰፻፴፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ህዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ ም Federal Negarit Gazeta – No . 9 24 November , 1998 – Page 889 ፯ ስለ ቦርድ አባላት ፩ ቦርዱ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ በመንግሥት የሚሰየሙ ሰባት አባላት ይኖሩታል ። ፪ የቦርዱ ሰብሳቢ ከአባላቱ መካከል በመንግሥት ይመደባል ። ፰ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር | ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የኤጀንሲውን የረዥምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት መርምሮ ለመን ግሥት ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይከታተላል ፣ ፪ . የኤጀንሲውን ድርጅታዊ መዋቅር ይወስናል ፡ ይህንን አዋጅ መሠረት በማድረግ የሚዘጋጁ የኤጀንሲውን ድርጅታዊ መዋቅርና የውስጥ ደንቦች ያፀድቃል ፣ ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል ፤ ፫ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ መርሆዎች በመከተል የኤጀንሲው ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚተዳደሩበትን መመሪያዎች ያጸድቃል ፤ የሠራተ ኞችን የደመወዝ ስኬልና ሌሎች የማነቃቂያ ክፍያዎችን ይወስናል ፡ ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል ፤ ፩ . ኤጀንሲው ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን ስምምነቶች ያፀድቃል ፤ ኤጀንሲው ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍ ለውን የክፍያ ተመኖች ይወስናል ፣ ፮ የኤጀንሲውን የሥራ አመራር አባላት ቅጥር ፣ ምደባና ስንብት ያጸድቃል ፡ ፯ የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸምና የሂሣብ ሪፖርት በየስ ድስት ወሩ ገምግሞ ከአስተያየት ጋር ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያቀርባል ። ፬ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በሶስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሰብሳቢው በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ። ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ውሳኔ የሚሰጠው በድምፅ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምዑ እኩል ለእኩል የተከፈለ ከሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምዕ ይኖረዋል ። ፬• የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ | 10 . Powers and Duties of the Director General የራሱን የስብሰባ ሥነሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። | 1 ) The Director General shall be the chief executive ፲ የዋና ዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዋና ዲሬክተሩ የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኤጀን ሲውን ሥራ ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ዲሬክተሩ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የኤጀን ሲውን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የኤጀንሲውን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፤ ሐ ) ለኤጀንሲው በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ መ ) ይህንን አዋጅ መሠረት በማድረግ የኤጀንሲውን ድርጅታዊ መዋቅርና የውስጥ ደንቦች አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፡ ገጽ ፰፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ህዳር ፲፭ ቀን ፲፩ ዓ ም . Federal Negarit Gazeta – No . 9 24 November , 1998 - Page 890 ሠ ) የኤጀንሲውን የሠራተኛ አስተዳደር መመሪያ ፣ የደመወዝ ስኬልና ሌሎች የማነቃቂያ ክፍያዎችን አጥንቶ ለቦች ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፤ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ኤጀን ሲውን ይወክላል ፤ ሰ ) የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፤ ፫ ዋና ዲሬክተሩ ለኤጀንሲው ሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኤጀንሲው ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲፩ በጀት የኤጀንሲው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ፩ በፌዴራል መንግሥት ከሚሰጠው የበጀት ድጐማ ፤ ፪ ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ እና ፫ ከዕርዳታ ፣ ከስጦታ እና ከማናቸውም ሌሎች ምንጮች | ከሚገኝ ገቢ ። ፲፪ የሂሣብ መዛግብት ፩ ኤጀንሲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪• የኤጀንሲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ፡ ፡ ፲፫ የተሻረ ሕግ የኢትዮጵያ የንግድ ማስተባበሪያ የመረጃ ልውውጥ ማዕከል | ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፲፱፶ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ የኢትዮጵያ የንግድማስተባበሪያና የመረጃ ልውውጥማዕከል | 15 . Effective Date መብትና ግዴታዎች ለኤጀንሲው ተላልፈዋል ። ፲፭ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከህዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ህዳር ፲፭ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ . . የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማ / ድርጅት