×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሲትዮጵያ ብሴሱሴዊ ምርጫ ቦርድ ደንዞች

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፵፩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻፵፩ ዓ • ም • | National Electoral Board of Ethiopia Regulations No. 2/1999 መራጮች በተመራጮች ላይ አመኔታ ያጡ መሆኑን የሚገልጹ በትን ሥርዓት ለመወሰን የወጣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደንብ .. ገጽ ፬፻፵፯ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደንብ ቁጥር ፪፲፱፻፲፩ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች አባላት የመረጣቸውን ሕዝብ አመኔታ በሚያጡበት ጊዜ ከአባልነት የሚወገዱበትን የአፈጻጸም ሥርዓት ለመወሰን የወጣ ደንብ ምዕራፍ አንድ ፩ አውጪው ባለሥልጣን ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመራጮቻቸው አመኔታን በሚያጡበት ጊዜ ስለሚወሰድ እርምጃ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰ / ፲፱፻፷፬ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፡ ( ፪ ) እና ( ፫ ) እንዲሁም ክልሎች ባወጧቸው አዋጆች አግባብነት ያላቸው አንቀጾች በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፪ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ መራዮች በተመራጮች ላይ አመኔታ ያጡ መሆኑን የሚገልጹበትን ሥርዓት ለመወሰን የወጣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዩንብ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፫ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ “ ያወራዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ” ማለት ፣ ሀ ) የምርጫ ክልሉ በሚገኝበት ወራዳ በቦርዱ የቋሚ ምርጫ አስራሚነት መታወቂያ የተሰጠው የወረዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነው ፣ ያንዱ ዋጋ [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዥሸክ ስለሚቀርብበት ሥም ሆኑ መራፎች ገጽ ፱፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፴፰ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. ለ ) ከአንድ በላይ የሆኑ ወረዳዎች በአንድ የምርጫ ክልልነት በተጣመሩበት ሁኔታ የመጀመሪያ ደረጃ የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች በብዛት በሚገ ኙበት ወረዳ የሚገኘውየወረዳምርጫ ጽሕፈትቤት ኃላፊ ነው ፤ ፪ “ የምርጫ ክልል ” ማለት ለምርጫው አፈጸጸም ተግባር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰየመውና ለየምክር ቤቶቹ የተወሰነ ብዛት ያላቸው ተመራፎች የሚወከ ሉበት አካባቢ ነው : ፫ . “ ቦርድ ” ማለት የኢትዮጵያን የምርጫ ሕግ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥትጋር ለማጣጣም በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፩ / ፳፯ አንቀጽ ፫ መሠረት የተቋቋመው ብሔራዊ የምርግ ቦርድነው } ፬ . “ የምርጫ ጣቢያ ” ማለት ቦርዱ ባወጣው መመሪያ መሠረት በየቀበሌው የተቋቋመ ምርግአስፈጻሚ አካል ፭ “ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ” ማለት በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ደንብ ቁጥር ፩ / ፲፱፻፷፮ አንቀጽ ፵፰ መሠረት በምርጫ ጣቢያ ወይም በወረዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት ደረጃ የተቋቋመና በዚህ ደንብ አፈጸጸም ሂደት በሚነሱ አቤቱታዎች ላይ አስተዳደራዊ ውሣኔ ለመስጠት ሥልጣን የሚኖረውኮሚቴ ሲሆን ፤ የቦርዱጽሕፈት ቤት በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ፤ በቀበሌ ምርጫ ጽሕፈት ቤት ደረጃ የሚቋቋመውንም አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይጨምራል ። ምዕራፍ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ የይውረድልን ጥያቄ ፬ . የይውረድልን ጥያቄ አቀራረብ ፩ በመጀመሪያ ደረጃ አንድ መቶ ( ፪ የይውረድልን ጥያቄያቸውን በሚኖሩበት ለሚገኘው የወረዳምርማጽሕፈትቤትኃላሪ ለቅረብ ይችላሉ ። ፪ በየትኛውም ደረጃ በተቋቋሙ ምክር ቤቶች አባላት ላይ የይውረድልን ጥያቄ ሊያቀርቡ የሚችሉት ተመራው በሚወክለው የምርጫ ክልል የሚኖሩ መራፎች ብቻ ናቸው ። ፫ የወረዳው ምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የይውረድልን ጥያቄማመልከቻውን የሚቀበለው የቦርዱ ጽሕፈት ቤት በሚያወጣው መመሪያ መሠረት እና ማመልከቻው በምርግ ሕግ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፩ / ፳፯ አንቀጽ ፲፱ መሠረት የመምረጥ መብት ባላቸው ግለሰቦች የቀረበ ሊሆንብቻ ነው ። + 2 ረው ቀርግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በዚህ አንቀጽ ላ አቅጽ በተጠቀሰው መሠረት የተቀበለውን ። ያልተከሀን አለመሟላቱን ፣ ገጽ ፱፻፷፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ የካቲት፪ቀን ፲፱፻፩ ዓም ለ ) የተሟላ ከሆነ መሟላቱን ፣ አረጋግጦከቦርዱጽሕፈት ቤት በሚላከውቅጽ ላይ የራሱን እና የሁለቱን የወረዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት አባላት ፊርማ በማኖርከአሥራአምስት ( ፲፭ ) ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወደ ቦርዱ ጽሕፈት ቤት የመላክ ግዴታ አለበት ። የቦርዱ ጽሕፈት ቤት የቀረበውን ማመልከቻ ለቦርዱ አቅርቦ ቦርዱተገቢውን ውሣኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል ። ፮ ቦርዱ ፤ !! . ሀ ) የቀረበውማመልከቻለይውረድልን ጥያቄው መነሻ ሊሆን አይችልም ብሎውሣኔከሰጠ ፤ ጽሕፈት ቤቱ ይህንኑ ውሣኔ በመገናኛ ብዙሃን እንዲገለጽ ያደርጋል ፤ ወይም ለ ) ማመልከቻው ለይውረድልን ጥያቄው መነሻ ብቁ ነው ብሎ ከወሰነ ፤ ጽሕፈት ቤቱ በምርጫ ክልሉ አግባብ ያለው ብዛት ያላቸው መራጮች ይህንኑ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በየምርጫው ጣቢያ እየቀረቡ እንዲመዘገቡ ፤ ( i ) ምዝገባው የሚጀመርበትን ቀን ፤ ( ii ) ምዝገባው የሚጠናቀቅበትን ቀን ፤ ( iii ) የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎቹ የተመዘገ ቡባቸው መዛግብት ለሕዝብ ይፋ የሚሆኑባ ቸውን ቀናት ፣ የጊዜ ሠሌዳ አዘጋጅቶ ለቦርዱ በማቅረብ ሲጸድቅ በመገናኛ ብዙሃን በይፋ ለሕዝብ ያሳውቃል ። ምዕራፍ ሦስት የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች አመዘጋገብ ሥርዓት ፭ የአመዘጋገብ ሥርዓት ፩ : ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት የይውረድልን | 5. Registration Procedure ጥያቄ አቅራቢዎችን ለመመዝገብ ምርጫ ጣቢያዎች ክፍት ሆነው ሥራቸውን ያካሂዳሉ ። ፪ . የይውረድልን ጥያቄ ለማቅረብ መመዝገብ የሚችሉት ፤ ሀ ) ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፡ ለ ) በምርጫ ክልሉ ቢያንስ ሁለት ዓመት የኖሩ ፤ ሐ ) ዕድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ( ፲፰ ) ዓመት ያላነሰ ፤ መ ) በአዕምሮ በሽታ ምክንያት ለመወሰን ያልተሳ ሠ ) በፍርድ የተወሰነባቸው የእሥራት ቅጣት ካለ ይህንኑ የፈጸሙ፡ ግለሰቦች ናቸው ። ፫ የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች መመዝገብ የሚችሉት በሚኖሩበት ቀበሌ በሚገኝ ምርጫ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ ብቻ ነው ። ማንኛውም የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢ አንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ ብቻ አንድ ጊዜ ይመዘገባል ። ፭ ማንኛውም የይውረድልን ጥያቄ ለማቅረብ መመዝገብ የሚፈልግ ግለሰብ ለምዝገባው በተወሰኑት ቀናት ውስጥ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ በማቅረብ በምርጫ ጣቢያው ተገኝቶ ይመዘገባል ። ፮ የተመዝጋቢውን ማንነት የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ በምርጫ ጣቢያው ውስጥ በሚገኘውየይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች መዝገብ ውስጥ ይሰፍራል ። ፯ ቀጥሎም ተመዝጋቢው የጽሑፍ ፊርማውን ወይም የቀኝ አውራጣት አሻራውን በይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች መዝገብ ውስጥ ከራሱ ስም አንፃር ሚገኘው ክፍት ቦታ ላይ እንዲሰፍር ያደርጋል ። ገጽ ፱ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ የካቲት ፤ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ፮ ስለሕዝብ ታዛቢዎች እና ወኪሎች ፩ . የምርጫ ጣቢያው ኃላፊ ቀደም ሲል በተከናወኑ ምርጫዎች በምርጫ ጣቢያው የሕዝብ ታዛቢዎች የነበ ሩትን ግለሰቦችየይውረድልኝ ጥያቄ አቅራቢዎችምዝገባ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ የምዝገባውን ጣቢያው በመገኘት እንዲታዘቡ ያደርጋል ። ፪ የይውረድልን ጥያቄ የቀረበበት ተመራጭ ፤ ቦርዱ የወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ፤ በየምርጫ ጣቢያው የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች ምዝገባ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ እንዲሁም እንደ አግባብነቱ በምርጫ ጣቢያ ፣ በቀበሌ ወይም በወረዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት የተመዝጋቢዎች ብዛት በሚጠቃለልበት ጊዜ ወኪሎቹን የመመደብ መብት አለው ። ምዕራፍ አራት በይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች አመዘጋገብ ላይ ስለሚቀርብ አቤቱታ እና የውሣኔ አሰጣጥ ፯ : ስለአቤቱታ አቀራረብ ፩ ቅሬታ አቅራቢዎች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በተጠቀሱት ምክንያቶች ብቻ በማንኛውም ጊዜ በተመዝጋቢዎቹ ላይ አቤቱታቸውን ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላሉ ። ፪ ቅሬታ አቅራቢዎች በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተጠቀሰው ውጪ የአመዘጋገብ ሂደቱንም ሆነ የተመዝ ጋቢዎችን ብዛት ማጠቃለልን አስመልክቶ አቤቱታ ቸውን እንደ አግባብነቱ ለምርጫ ጣቢያው ፡ ለቀበሌ ወይም ለወረዳው አቤቱታ ሰሚኮሚቴማቅረብ ይችላሉ ። ፫ የምርጫ ጣቢያው ወይም የቀበሌው አቤቱታሰሚኮሚቴ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ወይም ( መሠረት ለቀረበለት አቤቱታ በሃያ አራት ( ፳፬ ) ሰዓት ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ይሰጣል ። ፬ . የምርጫ ጣቢያው ወይም የቀበሌው አቤቱታ ሰሚኮሚቴ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ወይም ( ፪ መሠረት ለቀረበለት አቤቱታ በሃያ አራት ( ፳፬ ) ሰዓት ጊዜ ውስጥ ውሣኔ ካልሰጠ በአቤቱታ አቅራቢው ጥያቄ እንደተ ስማማ ይቆጠራል ። ፭ የምርጫ ጣቢያው ወይም የቀበሌውኣቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሣኔ በሰጠ በአርባ ስምንት ( ፵፰ ) ሰዓት ጊዜ ውስጥ እንደ አግባብነቱ ለቀበሌው ወይም ለወረዳው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ካልቀረበ የይግባኙ መብት በይርጋ የታገደ ይሆናል ። ፮ : የቀበሌው ወይም የወረዳው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴይግባኙ በቀረበለት በሃያ አራት ( ፳፬ ) ሰዓት ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ካልሰጠ እንደ አግባብነቱ የምርጫ ጣቢያው ወይም የቀበሌው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ እንዳ ፀናው ይቆጠራል ። ምዕራፍ አምስት የይውረድልን ጥያቄ ስለሚረጋገጥበት ሥርዓት ፰ ስለማረጋገጥ ፩ የወረዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ፤ * ዜ ውስጥ ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት ገጽ ፬፻፶፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፰ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ሀ ) የይውረድልን ጥያቄው በምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፩ / ፳፯ አንቀጽ ፲፬ መሠረት የመምረጥ መብት ባላቸው መራፎች የቀረበ መሆኑን ፣ ለ ) የይውረድልን ጥያቄውን ያቀረቡት መራጮች ብዛት አግባብ ባለው መጠን መሠረት መሟላቱን ወይም አለመሟላቱን ፤ ሐ ) የይውረድልን ጥያቄው የቀረበው በልዩ ምርጫ ክልል ተወካይ ላይ ከሆነ ደግሞ የቅሬታ አቅራ ቢዎችብዛት በየጊዘው ቦርዱ በሚወስነው መጠን መሠረት መሆኑን ወይም አለመሆኑን ፤ በማረጋገጥ ከቦርዱ ጽሕፈት ቤት በሚላከው የሪፖርት ማስተላለፊያ ቅጽ ላይ የራሱን እና የሁለቱን የወረዳ ምርጫ ጽሕፈት ቤት አባላት ፊርማ በማኖር ቦርዱ ከወሰነው የምዝገባ ማጠና ቀቂያ ዕለት ጀምሮ ከአሥራ አምስት ( ፲፪ ) ቀናት ባልበለጠ ይልካል ። ፪ የወረዳው ምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፤ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተጠቀሰው ሪፖርት ጋር በማያያዝ ፤ የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎችን ወይም ሌሎች የአመዘ ጋገብ ሂደቱንም ሆነ የተመዝጋቢዎችን ብዛት ማጠቃ ለልን አስመልክቶ የቀረቡ አቤቱታዎች ካሉ ፤ ሀ ) የምርጫ ጣቢያው ወይም የቀበሌው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ የሰጠ ከሆነ የውሣኔውን ግልባጭ ፤ ለ ) ውሣኔ ያልሰጠ ከሆነ የአቤቱታውን ግልባጭ ፤ ሐ ) በይግባኝ ለመጣለት አቤቱታ የቀበሌው ወይም የወረዳው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ የሰጠ ከሆነ የውሳኔውን ግልባጭ ፣ ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት ይልካል በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎቹ ብዛት የወረዳ ወይም የቀበሌ ምክር ቤቶች ድጋፍ የሚያስ ፈልገው ከሆነ ፤ የወረዳው ምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይኸው ድጋፍ መሰጠቱን የቦርዱ ጽሕፈት ቤት በሚያ ወጣው መመሪያ መሠረት አረጋግጦ በሪፖርት መላኪያ ቅጽ ላይ በመሙላት ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት ይልካል ። ፬ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ከወረዳው ምርጫ ጽሕፈት ቤት የቀረበለትን ሪፖርት ለቦርዱ በማቅረብ ቦርዱ ተገቢውን ውሣኔ እንዲሰጥ ያደርጋል ። ሀ ) በቀረበው ሪፖርት አግባብ ያለው የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች ብዛት አልተሟላም በማለት የይውረድልን ጥያቄው ውድቅ እንዲሆን ከወሰነ ፤ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ይህንኑ ውሳኔ በመገናኛ ብዙሃን በይፋ እንዲገለጽ ያደርጋል ። ለ በቀረበው ሪፖርት አግባብ ያለው የይውረድልን ጥያቄ አቅራቢዎች ብዛት የተሟላ ነው በማለት ጥያቄው የቀረበበት ተመራጭ የመረጠውን ሕዝብ አመኔታ አጥቷል ብሉ ከወሰነ ፤ የሕዝብ አመኔታን ባጣው ተመራጭ ምትክ በምርጫ ክልሉ የማሟያ ምርጫ ለማካሄድ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት የምርጫ አፈጸጸም የጊዜ ሠሌዳ አዘጋጅቶ ለቦርዱ በማቅረብ ሲጸድቅ በመገናኛ ብዙሃን በይፋ እንዲገለጽ ያደርጋል ። ሆኖም የማሟያ ምርጫው መካሄድ ያለበት ቦርዱ ተመራጩ የመረጠውን ሕዝብ አመኔታ አጥቷል ብሎ በይፋ ከወሰነበት ቀን ጀምሮ ከሦስት ( ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ነው ። ፱ . ቅጣት ይህን ደንብ በሥራ እንዳይልናስይዘህን ደንብ ድንጋፋ የቀለፈ ለውይ በየሰዓት ብት የተሰጠው አካል አባብ ባለው ፤ የትግ ሕረይትግል ፲ ደንቡናበትጊዘ ይህ ደንብ ከመጋቢት ፲፬ ቀን ፲፱፻፵ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓ.ም. ከግል በድሪ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?