×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት -ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፫/፲፱፻፹፰

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፩ አዲስ አበባ ጥቅምት ፳ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻ዥ፰ ዓም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . ገጽ ፳፭ አዋጅ ቁጥር ፲፫ ፲፱፻ዥ፰ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤትን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ | the House of the Federation of the Federal Democratic ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤትን ማቋቋም | Republic of Ethiopia : በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | of the Constitution of the Federal Democratic Republic of መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ኣዋጅ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻ዥ፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ” ማለት በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፴፫ መሠረት የተቋቋመ የፌዴራሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ? ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ሸሺ፩ ገጽ ፳፮ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥቅምት ፳ ቀን ፲፱፻፰ ዓም Negarit Gazeta No . 1 – 19 Octobert 1995 – Page 86 ፪ . “ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ” ማለት በሕገመንግሥቱ አንቀጽ | ፲፫ መሠረት የተቋቋመ የፌዴራሉ መንግሥት የፌዴሬሽን | ምክር ቤት ነው ፤ ፫ “ አፈ ጉባዔዎች ” ማለት በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ( ፲፱ ) | እና ኣንቀጽ ፳፪ ( ፲፩ ) መሠረት በሕዝብ ተወካዮች ምክር | ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚመረጡ አፈ ጉባዔዎች ፫• መቋቋም ፩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት | ጽሕፈት ቤት ( ከዚህ በኋላ “ ጽሕፈት ቤቱ ” ተብሎ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል በዚህ | አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ጽሕፈት ቤቱ ተጠሪነቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዮችን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆኖ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዮችን በተመለከተ | ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ይሆናል ። ፬• የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፣ ፩ ለምክር ቤቶቹ አካላት የጽሕፈት አገልግሎት ይሰጣል ፤ ፪ ለምክር ቤቶቹ ጠቅላላ ጉባዔና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የሚያስፈ | ልጉትን የመሰብሰቢያ አዳራሾች ያደራጃል ፤ ፫ የምክር ቤቶቹ አካላት ቃለ ጉባዔዎች ፡ ውሳኔዎችና ሰነዶች | 3 ) to see to it that the minutes , decisions and documents of በሚገባ ተመዝግበው እንዲጠበቁ ያደርጋል ፤ ፬ ለምክር ቤቶቹ ኣካላትና አባላት የቤተ መጻሕፍት : የምር | ምርና የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል ፡ በሚመለከተው አካል በሚሰጠው መመሪያ መሠረት የሕግ ረቂቆችን ያዘጋጃል ፤ ፭ ምክር ቤቶቹ የሚያወጧቸውን መጽሔቶችና ጋዜጦች ሕትመትና ሥርጭት ይከታተላል ፤ ፮ የምክር ቤቶቹ እንግዶች አስፈላጊውን የመስተንግዶ አገል | ግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል ፤ ፯ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፡ ውል ይዋዋላል ፡ በስሙ ይከሳል ፡ | ይከሰሳል ፣ • የምክር ቤቶቹን አካላት ሥራዎች ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች | 8 ) to perform such other duties as are conducive to the ተግባሮች ያከናውናል ። ፭ የጽሕፈት ቤቱ አቋም ጽሕፈት ቤቱ ፤ ፩ . በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጥ አንድ ኃላፊ ፣ እና ፪ አስፈላጊው ሠራተኞች ፤ ይኖሩታል ። ፮ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባር ፩ . የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ከአፈ ጉባዔዎቹ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተ ጠበቀ ሆኖ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ የተመለከቱትን የጽሕፈት ቤቱን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የጽሕፈት ቤቱን ሠራተኞች በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለአፈ ጉባዔዎቹ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፤ መ ) ለጽሕፈት ቤቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ገጽ ዥ፯ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ•ም• _ Negarit Gazeta No . 1 - 19 October 1995 – Page 87 ሠ ) ጽሕፈት ቤቱ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ጽሕፈት ቤቱን ይወክላል ፤ ረ ) የጽሕፈት ቤቱን የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለአፈ ጉባዔዎቹ ያቀርባል ፤ ሰ ) ከአፈ ጉባዔዎቹ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከና ፫ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ለጽሕፈት ቤቱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለጽሕፈት ቤቱ የበታች ኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተ ላልፍ ይችላል ። ሆኖም እርሱ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶት እንዲሠራ የሚወክለው ኃላፊ ከ፴ ቀናት በላይ የሚሰራ ከሆነ ውክልናው በቅድሚያ ለአፈ ጉባዔዎቹ ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታል ። ፯ የጽሕፈት ቤቱ በጀት የጽሕፈት ቤቱ በጀት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል ። ፫ የሂሣብ መዛግብት ፩ ጽሕፈት ቤቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። • የጽሕፈት ቤቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፀ• አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅከጥቅምት ፯ ቀን ፲፱የሞ፰ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። ኣዲስ አበባ ጥቅምት ፲ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?