×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፱ ፲ሀየዘጊ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አንደኛ ዓመት ቁጥር ፱ አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ ዓም የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ . ፪ . … . . . . . . . . . . . . ገጽ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፯ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | መንግሥት በአንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ( “ አካባቢ ” ማለት በተፈጥሮአዊ ሁኔታቸው ወይም በሰው አማካይነት ተሻሽለው ወይም ተለውጠው የሚገኙ ሀብቶች እንዲሁም የእነዚህን ሀብቶች ጥራት ፣ መጠንና የሰው ልጅ ደህንነት የሚነኩ ውጫዊ ሁኔታ ዎችና ተጽዕኖዎች ድምር ነው ፤ “ የአካባቢ ጥበቃ ” ማለት የሰው ልጅን ጨምሮ የማንኛ ውንም አካል ሕይወት እና ዕድገት የሚወስኑ የመሬት ፣ የውሃ ፣ የአየርና የመሳሰሉ ሌሎች የአካባቢ ሀብቶች ፣ ክስተቶችና ሁኔታዎች ጥበቃ ነው ፤ “ የአካባቢ ማኔጅመንት ” ማለት አካባቢን በጠቅላላ ማጥናት ፣ መጠበቅና መንከባከብ እንዲሁም አጠቃ ቀሙን መቆጣጠር ነው ፤ ፬ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ያንዱ ዋጋ 5 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዥሺ፩ ገጽ የ፩ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲ደ፮ ዓም• _ Negarit Gazeta No . 9 - - 24 August 1995 - Page 71 የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ “ ባለሥ ልጣን ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ! እንደአስፈላጊነቱም በክልሎች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ይኖሩታል ። የባለሥልጣኑ ዓላማ _ ፬ የባለሥልጣኑ ዓላማ የአገሪቱን የሶሻልና የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴዎች የሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ የሰውን ልጅ ደህንነት ለመንከባከብ እንዲሁም ህልውናው የተመሠረተ በትን የአካባቢ ሀብቶች ዘላቂነት ባለው መንገድ ለመጠበቅ ፣ ለማልማትና ለመጠቀም በሚያስችል ሁኔታ መካሄዳቸውን ማረጋገጥ ይሆናል ። የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲና ሕጐች ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል ፤ - የሶሻልና የኢኮኖሚ ልማት ፕሮጀክቶች በአካባቢ ላይ ስለሚያደርሱት ተጽዕኖ ግምገማ ለማካሄድ የሚያስ ፈልጉ መመሪያዎችንና ሥርዓቶችን ያዘጋጃል ፣ በሥራ ላይ መዋላቸውንም ይከታተላል ፣ ይቆጣጠራል ፤ አፈርን ፣ ውሃንና አየርን እንዲሁም ሕልውናቸው በእነዚህ ሀብቶች ላይ የተመሠረተውን ሥነ ሕይወታዊ ሥርዓቶች ለመጠበቅ የሚያስችሉ ደረጃዎችን ያዘጋጃል ፣ ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል ፤ በረሀማነትን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ጥናቶችን ያካሂዳል ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሥራ ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል ፤ 5 በተሻለ ሁኔታ አካባቢን ለመጠበቅ እንዲቻል ልዩ ልዩ የማበረታቻና የቁጥጥር ዘዴዎች ሥራ ላይ ስለሚው ሉበት ሁኔታ ሃሣብ ያቀርባል ፤ የአካባቢ ጥበቃ አስፈላጊነት ግንዛቤ እንዲዳብር አስፈ ላጊውን ትምህርት ይሰጣል ፤ የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት ህገሪቱ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ውሎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ለክልሎች ምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል ፩ . የንብረት ባለቤትይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፣ በራሱስም ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፣ ፲• ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባ ሮችን ያከናውናል ። የባለሥልጣኑ አቋም ፯ የበላሀ ፡ ባለሥልጣኑ ፤ ፩• የአካባቢ ጥበቃ ጉባዔ ( ከዚህ በኋላ “ ጉባኤ ” እየተባለ የሚጠራ ) ገጽ ጅ፪ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፯ ዓም _ Negarit Gazeta – No . 9 24 August 1995 - - Page 72 ፪ በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅና አንድ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፤ ይኖሩታል ፰ የጉባኤው አባላት ጉባኤው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፤ በመንግሥት የሚሰየም ኃላፊ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ፪ : የግብርና ሚኒስትር . . . . ኣባል ፫ . የንግድና የኢንዱስትሪ ሚኒስትር . . . . . ፬• የጤና ጥበቃ ሚኒስትር . . . ፭ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ፮ : የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽነር . . ፯ የውሃ ሃብት ሚኒስትር ፰ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ የጉባዔው ስብሰባ ፩ . ጉባዔው በስድስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ከጉባዔው አባላት አብዛኛዎቹ በስብሰባው ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይኖራል ። የጉባዔው ውሣኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፣ ሆኖም ድምጽ እኩል በኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሣኝ ድምጽ ይኖረዋል ። የዚህ አንቀጽ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ጉባዔው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲ . የጉባዔው ሥልጣን ጉባዔው የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፤ ፩• የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ፣ ሃሣብ ያቀርባል ፤ ፪ . ባለሥልጣኑ የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና ደረጃዎች ይገመግማል ፣ ያፀድቃል ። ፲፩ ስለዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ሀ ) በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፮ የተመለከተውን የባለሥ ልጣኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የባለሥ ልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፤ ባለሥልጣኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደር ጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል ፤ ረ ) ስለባለሥልጣኑ የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ያቀርባል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል | ለባለሥልጣኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ገጽ ፻፫ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓም - Negarit Gazeta No . 9 – 24 August 1995 – Page 73 የባለሥልጣኑ በጀት በመንግሥት ይመደባል ። _ ፲፫ የሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች | ውብ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው | ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ብዘይ | ፲፬• የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ባለሥልጣኑ ለሥራው የሚፈልጋቸውን መረጃዎች በመስጠት የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፲፭ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፫፯ ዓ . ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፰ ቀን ፲፱፻፴፯ ዓም | ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት | ይ999 በ Ir ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?