የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፵፯ አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻፶፭ ዓም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማቋቋሚያ ገጽ ፪ሺ፩፻፴፭ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻፲፭ የብሔራዊ ተጠባባቂኃይል ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የሕዝቡ ሉዓላዊነትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ የመከላከያ ሠራዊቱ አካል በመሆን የሚመ ክትና የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ፈጥኖ ለሕዝቡ ሊደርስ የሚችል | Reserve Force with strong mass basis which safeguard the በሰላም ጊዜ መደበኛና የግል ሥራውን የሚያከናውን ሕዝባዊ | Forces when the constitutional order is endangered , natural መሠረት ያለው ብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጉ- መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) እና ( ፯ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፯ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፩፻፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፷፭ ዓም “ የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አገልግሎት ” ማለት በዚህ አዋጅ ኣንቀጽ ፲፪ መሠረት የሚሰጥ አገልግሎት ነው ፤ ፪ ) “ የብሔራዊ ተጠባባቂኃይል አባል ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በብሔራዊ ተጠባባቂኃይል ተመዝግቦና አስፈላ ጊውን ሥልጠና ወስዶ አገልግሎት ለመስጠት የሚጠ ባበቅ ሰው ነው ፤ ፫ ) “ አዛዥ ” ማለት በአገር መከላከያ ሠራዊት ወይም በብሔራዊ ተጠባባቂኃይል በማናቸውም የዕዝ ጠገግ ላይ የሚገኝ የሠራዊት ክፍልን ለማደራጀት ፣ ለማስተዳደር እና ለመምራት ሥልጣን የተሰጠው ሰው ነው ፤ ፬ ) “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደ ቅደም የአገር መከላከያ “ ሚኒስትር ” ወይም “ ሚኒስቴር ” ነው ፣ ፭ ) “ ምልምል ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ውስጥ ለማገልገል የተመለመለ ማንኛውም ሰው ነው ፤ “ የአገር መከላከያ ሠራዊት ” ማለት የምድር ኃይል እና የአየር ኃይል ነው ፣ “ የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ” ማለት በአገር መከላከያ ሚኒስቴር ሥር ተቋቁሞ የሚገኝ የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይልን በበላይነት የሚያ ደራጅ ፣ የሚያስተዳድርና የሚመራ ነው ፣ ክፍል ሁለት መሠረታዊ ድንጋጌዎች የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ከዚህ በኋላ “ ተጠባባቂ ኃይል ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ፣ ፪ ) ተጠባባቂ ኃይሉ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ይሆናል ዓ ላ ማ የተጠባባቂ ኃይል ዓላማ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማንኛውም አደጋ በአስተማማኝ ለመጠበቅ ፣ ፪ ) በጦርነት ወይም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅሎ ለመሠማራት ፣ ሰው ሠራሽም ሆነ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ሲከሰቱ ፈጥኖ በቦታው ላይ በመገኘት ዕገዛ ወይም እርዳታ ለመስጠት ። ፭ ስለተጠባባቂ ኃይል አደረጃጀት በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሚመራ የተጠባባቂ ኃይል በሁሉም የፌዴራሉ መንግሥት ክልሎች ይደራጃል ፣ ፪ ) የተጠባባቂ ኃይሉን የሚያደራጅና የሚያስተባብር ቢሮ በመከላከያ ሚኒስቴር ሥር ይደራጃል ፤ ፫ ) ቢሮው በክልሎች ሥራውን የሚመሩና የሚያስተባብሩ የላይዘን ጽሕፈት ቤቶች ይኖሩታል ። የላይዘን ጽሕፈት ቤቶች ሥራቸውን ከክልል መስተዳድር ጋር ተቀናጅተው ይመራሉ ፤ ፬ ) የተጠባባቂ ኃይሉ በወረዳ ደረጃ በአሃድ ተዋቅሮ እንዲ ደራጅ ይደረጋል ። ፩ ) እንደ አስፈላጊነቱ ቢሮው በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ፣ በመንግሥትና የግል ተቋማት ሕዝባዊ ማኅበር ውስጥ ተግባሩን መፈፀም የሚያስችለው የላይዘን ጽሕፈት ቤት ሊያቋቁም ይችላል ። ፮ ምዝገባና ምልመላ የተጠባባቂ ኃይሉ ቢሮ በሚያወጣው የምዝገባና የምልመላ መስፈርት መሠረት የፌዴራል መንግሥት ክልሎች የተጠባባቂ ኃይልን ምዝገባ ያካሄዳሉ ፣ የምልመላ መስፈርት የምልመላ መስፈርት በደንብ ይወሰናል ። ፰ የምዝገባ መታወቂያ ወረቀት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ መሠረት ለተጠባባቂ ኃይሉ የተመ ለመለ ፣ የሠለጠነ እና ተቀባይነት ያገኘ ሰው መታወቂያ ደብተር ይሰጠዋል ። ገጽ ፪ሺ፩፻፵፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ • ም • ክፍል ሦስት የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አገልግሎት ሁኔታዎች ፱ . ወታደራዊ ሥልጠና ፩ ) ተመልማዮች መሠረታዊ ወታደራዊ ሥልጠና ወደሚያገ ኙበት ማሠልጠኛ ማዕከል ይገባሉ ፤ ፪ ) ተጠባባቂ ኃይሉ ለተልዕኮው የሚያበቃው መሠረታዊ ወታደራዊ ሥልጠና ይሰጠዋል ፣ ፫ ) በሥልጠና ወቅት ቢሮው በሚያወጣው መመሪያ መሠረት መጠለያ ፣ ምግብ ፣ አልባሳት ፣ የኪስ ገንዘብ ፣ ሕክምና ፣ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች በነፃ ያገኛል ፣ ፬ ) ወታደራዊ ሥልጠናውን ያጠናቀቀ ምልምል የምሥክር ወረቀት ይሰጠዋል ። ፭ ) ወታደራዊ ሥልጠናው እንደተጠናቀቀ የተጠባባቂ ኃይል አባሉ ወደየመጣበት አካባቢ እንዲመለስ ይደረጋል ፣ ፮ ) ወደመጣበት ከተመለሰ በኋላ በየዓመቱ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የማጠናከሪያ ሥልጠናና ልምምድ ሊሰጠው ይችላል ። ፲ ክ ተ ት ፩ ) ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ሚኒስትሩ በሚወስነው ቦታና ጊዜ የመገኘት ግዴታ አለበት ፣ ፪ ) ጥሪው የሥልጠና ፣ የልምምድ ወይም የክተት ሊሆን ይችላል ። ፲፩ ስለ ምደባ ወታደራዊ ሥልጠናውን ያጠናቀቀ የተጠባባቂ ኃይል አሳል ለአገልግሎት በሚፈለግበትጊዜ በምድርኃይል ወይም በአየር ኃይል ውስጥ ተመድቦ ያገለግላል ። ፲፪ • የአገልግሎት ዘመን ፩ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፬ የተጠቀሰው ወታደራዊ ሥልጠና ያጠናቀቀ የተጠባባቂ ኃይል ኣባል ( መደበኛ የውትድርና አገልግሎት እንዲሰጥ በሚፈለግበት ጊዜ ) ለ፯ ( ሰባት ) ዓመት ያገለግላል ። ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረትም ውል ይፈጽማል ፣ ፪ ) ለተጨማሪ አገልግሎት በጋራ ስምምነት ሊራዘም የሚችል ሲሆን ሆኖም አገልግሎቱ ከ፴፰ ዓመት ዕድሜ ሊያልፍ አይችልም፡ ፫ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው የአገል ግሎት ዘመን በክተትና በጦርነት ጊዜ ሊራዘም ይችላል ። ፲፫ : ስለሜዳይና ሽልማት ፩ ) ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል አባል በአገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሆኖ ለሰጠው አገልግሎትና ለፈጸመው ጀግንነት በአገር መከላከያ ሠራዊት አዋጅ መሠረት ሜዳይ ወይም ሽልማት እንዲያገኝ ይደረጋል ፣ አንድ የተጠባባቂ ኃይል አባል አገልግሎቱን ጨርሶ በክብር ሲሰናበት የተጠባባቂ ኃይል ሜዳይና የምሥክር ወረቀት ይሰጠዋል ፣ ፫ ) በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ኣገልግሎቱን ቢያቋርጥ ያቋረጠበት ምክንያት ተጠንቶ የምስክር ወረቀት ሊሰጠው ይችላል ። ፲፬ ወታደራዊ ሕጐችን ፣ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን ስለማክበር ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል አባል በሚሠለጥንበትና ውትድርና አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ ወታደራዊ ሕጐችን ፣ መመሪያዎችንና ትእዛዞችን ማክበር አለበት ። ገጽ ፪ሺ፩፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. ፲፭ አቤቱታ ስለማቅረብ ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል አባል በሥልጠናም ሆነ መበደኛ ወታደራዊ አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ ለሚደር ስበት የአስተዳደር በደል በሠራዊቱ የዲስፕሊን መመሪያ መሠረት አቤቱታ የማቅረብና ውሣኔ የማግኘት መብት ክፍል አራት ስለ አገልግሎት ፣ ማዕረግና ስንብት ፲፮ ስለ አገልግሎት ፩ ) አገልግሎቱን በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ በየትኛውም ክፍልና ቦታ ተመድቦ እንደሠራዊቱ ይፈጽማል ፪ ) በመደበኛ ውትድርና አገልግሎት ላይ የሚገኝ ማናቸውም የተጠባባቂ ኃይል አባል እንደማንኛውም የመከላከያ ሠራዊት አባል ቀለብ ፣ ልብስ ፣ መጓጓዣ ፣ ቤት ፣ ሕክምና እና የማዕረጉን ደመወዝ ያገኛል ። ፲፯ ስለ ማዕረግ ፩ ) ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል አባል ከሠራዊቱ ጋር ተቀላቅሎ አገልግሎት ሲሰጥ የሥራብቃቱ ፣ ሥነ ሥርዓት አክባሪነቱ እና የሥራ አፈጻጸሙ እየተገመገመ በመከ ላከያ ሠራዊት የማዕረግ ዕድገት መመሪያ መሠረት የማዕረግ ዕድገት የማግኘት መብት አለው ። ፪ ) በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ለዕዝና ቁጥጥር የሚያስፈልጉ የኃላፊነት ደረጃዎች እየተጠኑ ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ማዕረጎች ሊሰጡ ይችላሉ ። ፲፰ አገልግሎት ስለሚቋረጥበት ምክንያት ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል አባል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምክንያቶች ሲያጋጥሙ አገልግሎቱን አቋርጦ እንዲሰናበት ይደረጋል ፤ የቅጥር ውሉ ዘመን ሲያልቅ ፣ በዕድሜ ምክንያት አገልግሎት መስጠት የማይችል የአእምሮ መታወክ ወይም የኣካል ጉዳት ደርሶበት ለአገልግሎት ብቁ አለመሆኑ ሲረጋገጥ ፣ በወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘና ጥፋቱም ለሥራው ብቁ አያደርገውም ተብሎ ሲወሰን ። ፲፱ : ስለ ካሣ የተጠባባቂ ኃይል አባል በሥልጠና ወይም በአገልግሎት ላይ እያለ ጉዳት ቢደርስበት ለመደበኛ ሠራዊት የሚከፈለው ካሣ ( ድጐማ ) በሠራዊቱ መመሪያ መሠረት ያገኛል ፣ የሞት አደጋም ካጋጠመው በጡረታ ሕግ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል ። ክፍል አምስት የተጠባባቂ ኃይል ቢሮ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባር የተጠባባቂ ኃይል ቢሮ ኃላፊ ሥልጣንና ተግባር ፩ ) ለተጠባባቂ ኃይል አባልነት የሚያበቁ የምልመላ መስፈ ርቶችን ያወጣል ፣ ፪ ) ስለተጠባባቂ ኃይል ሥልጠና ፣ ትጥቅ ፣ ጥቅማጥቅም ፣ ስለዲስፕሊን እርምጃና ጠቅላላ አስተዳደር አስፈላጊውን መመሪያ ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በተግባር ላይ ያውላል ፣ ፫ ) ተጠባባቂ ኃይሉ ስለሚከትበት ስለሚሰማራበት ፣ ስለግዳጅ አፈፃፀሙና ስለስንብቱ መመሪያ ያዘጋጃል ፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ይህ አዋጅ በሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል ፣ ከሚኒስትሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ገጽ ፪ሺ፩፻፵፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ክፍል ስድስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፩ . የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም የግል ድርጅት ይህን አዋጅ ሥራ ላይ በማዋል ረገድ የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፳፪ የወታደራዊ ሕጐችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ፩ ) በበዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ መሠረት ውትድርና አገል ግሎት የሚሰጥ የተተጠባባቂ ኃይል አባል የሚፈጽመው ወታደር ነክ ወንጀል በወታደራዊ ፍርድ ቤት ይታያል ፤ ፪ ) ማንኛውም የተጠባባቂ ኃይል አባል የሥነ ሥርዓት ጉድለት በፈጸመ ጊዜ በሀገር መከላከያ የዲስፕሊን መመሪያ መሠረት ጉዳዩ እንዲታይ ይደረጋል ። ፳፫ የተሻሩ ሕጐች የሚከተሉት ሕጎች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፤ ፩ ) የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ኣዋጅ ቁጥር ፫፻፳፪ / ፲፱፻፳፭ ፪ ) የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ደንብ ቁጥር ፩፻፵፬ / ፲፱፻፳፮ ፫ ) የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት መቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፰ ፲፱፻፸፭ ፳፬ • ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም አስፈላጊ የሆኑ ደንቦችን ማውጣት ይችላል ። ፳፭ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሚኒስትሩ ለዚህ አዋጅ አፈጸጸም አስፈላጊ የሆኑ መመሪያ ዎችን ያወጣል ። ፳፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከመጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ