የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳ አዲስ አበባ የካቲት ፲፫ ቀን ፲፱የኝ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፱ ፲፱፻፲ ዓ.ም የጉማሮ ሻይ ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ነጽ ፮፻፳፯ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፬ ፲፱፻፲ የጉማሮ ሻይ ልማት ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻ T ፬ አንቀጽ ፵፯ ፩ / ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርእስ ይህ ደንብ “ የጉማሮ ሻይ ልማት ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፬ ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ • መቋቋም የጉማሮ ሻይ ልማት ድርጅት ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻ T ፬ መሠረት ይተዳደራል ። ያንዱ ዋጋ 2.30 ( ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ ገጽ ፮፻፴፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ የካቲት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥት የሚሰየም አካል የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በጉማሮ ይሆናል ። እንዳስፈላጊነቱም በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡ ፩ . የሻይ ተክል ልማት ማካሄድ፡ ፪ • የሻይ ቅጠልን በመጀመሪያ ደረጃ ማዘጋጀት ፣ ፫ ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ተዛማጅ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደው ካፒታል ብር ፳፮ ሚሊዮን ፫፻፸፪ሺ ( ሃያ ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ብር ) ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፲፫ ሚሊዮን ፩፻፳፮ሺ ፬፻፲ ( አሥራ ሦስት ሚሊዮን ኣንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ብር ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ : ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፡ የካቲት ፲፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ