ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ .ዓደገና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አሥራሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፴፩ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬፻፲፭ / ፲፱፻፲፰ ዓ.ም የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲን እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ... ገጽ ፫ሺ፪፻፳፭ አዋጅ ቁጥር ፬፻፲፭ / ፲፱፻፵፰ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተግባሩን በብቃት ለማከናወን በሚችልበት ሁኔታ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፲፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠ ረት የሚከተለው ታውጇል ፡፡ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፬፻፲፭ / ፲፱፻፲፰ ” ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ፪ . መቋቋም ፩ / የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ I ከዚህ በኋላ “ ኤጀንሲ ” እየተባለ የሚጠራ / የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል ፣ ፪ / የኤጀንሲው ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ፡፡ ፫ ዋና መሥሪያ ቤት የኤጄንሲው ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ስፍራ ቅርን ጫፍ ሊኖረው ይችላል ፡፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ ፱ሺ፩ ፈዴራል ጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ.ም ፬ . ዓ ላ ማ የኤጀንሲው ዓላማ የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራ ሞች እንዲጠናከሩና እንዲስፋፉ ማድረግ ይሆ ፩ . ሥልጣንና ተግባር ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ / የማህበራዊ ሕጎችን ፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በሥራ ላይ ያውላል ፣ ፪ / የማህበራዊ ዋስትና መዋጮ አሰባሰብ ሥርዓት ይዘረጋል ፣ መዋጮ ይሰበሰባል ፣ አሠሪ መሥ ሪያ ቤቶች ሥርዓቱን ተግባራዊ ማድረጋቸ ውን ይቆጣጠራል ፣ አስፈላጊ ሲሆን ሰነዶ ችንና መዛግብትን አስቀርቦ ወይም በአሠሪ መሥሪያ ቤቶች ተገኝቶ ይመረምራል ፣ ፫ / የማህበራዊ ዋስትና ፈንዶችን ያስተዳድራል ፣ ፬ / ለማህበራዊ ዋስትና መብት ብቁ የሚያደርጉ ማስረጃዎችን በቅድሚያ አሰባስቦ ይይዛል ፭ መዋጮ በወቅቱ በማይከፍሉ ፣ መዋጮ ሂሣብ መዝገብ በማይዙ ፣ ማስረጃ በማይልኩ እና መረጃ በማይሰጡ መሥሪያ ቤቶችና ግለሰቦች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ፣ ፮ / የማህበራዊ ዋስትና መብትን ለማስከበር የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ብቃት ፣ የጥቅም ዓይነት እና መጠኑን ይወስናል ፣ ይፈጽማል ፣ ፯ / በማህበራዊ ዋስትና መብትና` ጥቅም ጥያ ቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ፣ ፰ / የማህበራዊ ዋስትና ፈንድን ትርፋማና አስተ ማማኝ በሆኑ የኢቨስትመንት ሥራዎች ላይ ያውላል ፣ ፱ / የማህበራዊ ዋስትና ፈንዶች በየተወሰነ ጊዜ በሂሳብ ስሌት አዋቂዎች በአክቹዋሪ እንዲ ጠኑ ያደርጋል ፣ ፲ / የማህበራዊ ዋስትና ሽፋንና ፕሮግራሞች ስለ ሚጠናከሩበትና ስለሚስፋፉበት ሁኔታ ጥናት እያካሄደ ለመንግሥት ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፣ ፩ / ቦርዱ የኤጀንሲውን ሥራዎት ፌዴራል ጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፲፰ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta No. 31 29 June , 2006 ... page በሥልጣንና ተግባሩ ሥር የሚካተቱ ጉዳዮ ችን በሚመለከት የሥራ አፈጻጸም መመሪያ ዎችን ያወጣል ፣ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፣ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል ፡፡ የኤጀንሲው ኣቋም ኤጀንሲው ፣ ፩ / የሥራ አመራር ቦርድ / ከዚህ በኋላ “ ቦርድ ” እየተባለ የሚጠራ / ፣ ፪ / በመንግሥት የሚሾሙ ዋና ዳይሬክተርና እንደአስፈላጊነቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ፣ ፫ / አስፈላጊ ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ፡፡ ፯ የቦርዱ አባላት ፩ / የቦርዱ ሰብሳቢና አባላት በመንግሥት ይሰ ቁጥራቸውም እንደአስፈላጊነቱ ይወሰናል ፡፡ ፪ / የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የቦርዱ አባልና ፀሐፊ ይሆናል ፡፡ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ፪ / በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ፣ ሀ / የኤጀንሲውን ስትራቴጂ ፣ ዕቅድ ፣ በጀ ትና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸድ ለ / የጡረታ ዕቅዱንና ፈንዱን የሚመለከቱ አጠቃላይ የፖሊሲ ጉዳዮችን ለመንግ ሥት አቅርቦ ያስወስናል ፣ ሐ / የኤጀንሲውን የሠራተኛና ፣ የንብረት ፣ የፋይናንስ ሥራ አመራርና ሌሎች አስተ ዳደር ነክ መመሪያዎች ያወጣል ፣ መ / የኤጀንሲውን ድርጅታዊ መዋቅር ፣ የሥራ ደረጃ ምደባ ፣ የደመወዝ ስኬል ፣ ጥቅማ ጥቅምና የአበል መጠን ይወሰ ፌዴራል ጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ.ም የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ፣ ሆኖም አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ፡፡ በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተ ገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ / የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው ላይ ከተገኙት አባላት በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ፡፡ ሆኖም ድምጹ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ፡፡ ፬ / ቦርዱ የራሱን የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፡፡ የዋና ዳይሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ / ዋና ዳይሬክተሩ የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሥራዎች ይመራል ፣ ይቆጣጠራል ፡፡ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / የተመለከ ተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ዳይሬክተሩ ፣ ሀ / በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተመለከተውን የኤጀንሲውን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ያውላል ፣ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ያሰናብታል ፣ ሐ / የኤጀንሲውን ስትራቴጂ ፣ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ / ለኤጀንሲው በተፈቀደለት በጀት መሠ ረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሠ / ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙ ነቶች ኤጀንሲውን ይወክላል ፣ ረ / የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀርባል ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ለኤጀንሲው ሥራ ቅልጥ ፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለኤጀንሲው ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ፡፡ ጉባዔው የራሱን የአሠራር ሥነ ሥርዓት ፌዴራል ጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta No. 31 29 June , 2006 ... page የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ፩ / የማህበራዊ ዋስትና መብትና ጥቅምን በሚመ ለከት ኤጀንሲው በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርቡትን ይግባኞች እየመረመረ ውሳኔ የሚሰጥ የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ይቋቋማል ። ፪ / የጉባዔው አደረጃጀትና የአባላት አሰያየም በመንግሥት ይወሰናል ፡፡ የይግባኝ ለጉባዔው የሚችለው ይግባኝ በሚባልበት ጉዳይ ላይ ውሳኔ በተሰጠ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጉባዔው ሥራውን የሚያከናውነው በጡረታ ለማስፈጸም ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ይሆናል ፡፡ ፭ / ጉባዔው ይግባኝ የቀረበበትን የኤጀንሲውን ውሳኔ መለወጥ ፣ ማሻሻል ፣ ወይም ማጽናት ይችላል ፣ ውሣኔውም የመጨረሻና ይሆናል ፡፡ ፮ የጉባዔው ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባሎች በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ው ፡፡ ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው መሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ደንብ ያወጣል ፡፡ ፲፪ . በ ጀ ት ኤጀንሲው ከጡረታ ፈንዱ በሚመደብ በጀት ይተዳደራል ፡፡ ፲፫ . ስለሂሣብ መዛግብት መዛግብት ኤጀንሲው ይይዛል ፣ የኤጀንሲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በየዓመቱ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች ይመረመ የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ፩ / የማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ፴፰ / ፲፱፳፰ በዚህ ተሽሯል ፡፡ ፌዴራል ጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ.ም ፪ / ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም ሕግ በዚህ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ፡፡ ፲፭ . ኣዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፰ ዓ.ም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት