×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 97/1990 ዓም በባንክ በመያዣ ስለተያዘንብረት የመማ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፲፮ አዲስ አበባ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፯ ፲፱፻፲ ዓ . ም በባንክ በመያዣ ስለተያዘ ንብረት የወጣ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፮፻፪፬ | አዋጅ ቁጥር ፲፯ ፲፱፻፲ በባንክ በመያዣ ስለተያዙ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች የወጣ አዋጅ በባንኮች በዋስትና የተያዙ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲሸጡ ለፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰንና | judgement , from courts of law , for sale of property mortgaged ውሳኔውንም ለማስፈጸም የሚወስደው ጊዜ በጣም ረጅም በመሆኑ ፤ በቁጠባ ሂሣብ መልክ ከሕዝብ የሰበሰቡትንና ከተለያዩ ምንጮች ያገኙትን ገንዘብ በማበደር በሚገኘው የወለድ ገቢ የሚተዳደሩ ባንኮች ሥራ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳደሩ ፤ ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴው አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ባንኮች ለተለያዩ የንግድና የልማት እንቅስቃሴ የሚሰጧቸው ብድሮችን በተቀላጠፈ መንገድ ለመሰብሰብ እንዲችሉና ለወደፊቱ ጥሩ የንግድ አሰራር ባህል እንዲዳብር ለማድረግ ለባንክ ብድር በመያዣ የተሰጡየማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ሽያጭ በሚመ ለከት በሥራ ላይ ያሉትን ሕጎች ማሻሻልና አዲስ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን | ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ በባንክ በመያዣ ስለተያዘ ንብረት የወጣ አዋጅ | ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ . ሣቁ• ሺ፩ ገጽ ፮፻ሮ፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta - No . 16 19 February , 1998 – Page 675 በዚህ አዋጅ ውስጥ “ ሬጅስትራር ” ማለት በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለመብትን በተመለከተ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመመዝገብ ኃላፊነት ያለው የክልል ወይም የከተማ አካል ወይም በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ መብትን በተመለከተ የስምምነቱን መፈረም የሚያረጋግጠውና ስምምነቱን የሚያ ስቀምጠው የክልል ወይም የከተማ አካል ነው ። የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ስምምነት የ፲፱፻፶፪ የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ ፪ሺ፰፻፵፩ እና አንቀጽ ፫ሺ፰ ድንጋጌ ቢኖርም ፡ የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና የያዘ ባለገንዘብ ባንክ የሚፈልገው እዳው እንዲከፈል በተወሰነው ጊዜ ሳይከፈለው ቢቀርከሠላሳቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ ለባለዕዳው በመስጠት በመያዣ የያዘውን የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ለመሽጥና የባለቤትነት መብቱንም ለገዢው ለማዛወር ወይም ለሁለተኛ ጊዜ በወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ | መሠረት ገዥ ካልቀረበ ንብረቱን በብድር ውሉ ውስጥ | በሰፈረው የዋጋ ግምት መሠረት ለመውሰድና የባለቤትነት መብቱ በስሙ እንዲዛወርለት ለማድረግ ከባለዕዳው ጋር የሚያደርገው ስምምነት ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። በማይንቀሳቀስ ወይም በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ የመያዣ መብት ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀ ሳቀስ ንብረት በመያዣ የያዘና ዕዳው እንዲከፈል በተወ ሰነው ጊዜ ያልተከፈለው ባለገንዘብ ባንክ ለባለዕዳው ከሠላሳ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በመያዣ የያዘውን የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ለመሽጥና የባለቤትነቱንም መብት ለገዢው ለማዛወር ወይም ለሁለተኛጊዜ የወጣየሐራጅማስታወቂያ መሠረት ገዢ ካልቀረበ ንብረቱን በብድር ውሉ ውስጥ በሰፈረው የዋጋ ግምት መሠረት ለመውሰድና የባለቤትነት | መብቱ በስሙ እንዲዛወርለት ለማድረግ ይችላል ። በባንክና በባለዕዳው መካከል ስለሚኖር ግንኙነት በዚህ አዋጅአንቀጽ ፫እና፬ መሠረት በባንክ የተደረገ ሽያጭ | ባለዕዳውን በመወከል እንደተፈጸመ ይቆጠራል ። በሐራጅ ሽያጭ ላይ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ተፈጻሚነት ባንክ በመያዣ የያዘውን የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀ ሳቀስ ንብረት በሐራጅ የመሽጥ ሥልጣን በሥራ ላይ በሚያውልበት ጊዜ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ከቁጥር ፫፻፴፫ ፬፻፬ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደአግ | 7 . ባብነታቸው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል ። ስለባንክ ተጠያቂነት ባንክ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮የተጠቀሱትን አግባብ ያላቸውን ድንጋጌዎች በመተላለፍሽያጩን በመፈጸሙ በባለዕዳው ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት በኃላፊነት ተጠያቂ ይሆናል ። ገጽ ፭፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓም Federal Negarit Gazeta – No . 16 19 February , 1998 Page 676 . ፰ የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መዝጋቢ ሥልጣንና ኃላፊነት ፩ : ሬጅትራሩ ለማይንቀሳቀስ ወይም ለሚንቀሳቀስ ንብረት የሐራጅ ሽያጭ አፈጻጸም የሚረዱ አስፈላጊእርምጃዎችን የመውሰድ ሥልጣንና ኃላፊነት ይኖረዋል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ሬጅስትራሩ ለሚወስደው እርምጃ የፖሊስ ኃይል መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ያገኘው እንደሆነ ፖሊስን ማዘዝ ይችላል ። በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ስላሉ ጉዳዮች የማይንቀሳቀስ ወይም የሚንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና በያዘ ባለገንዘብ ባንክ አመልካችነት ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት | በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ክስ ወይም አፈጸጸም ተቋርጦ በዚህ አዋጅ መሠረት ባንክ ንብረቱን በሐራጅ ለመሸጥና የባለቤትነቱንም መብት ለገዢ ለማስተላለፍ ይችላል ። የተሻረ ሕግ የፍትሐብሔር ሕግ ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻TU በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። መሸጋገሪያ ድንጋጌ ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት የፍትሐብሔር ሕግ ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻ዥ፬ መሠረት በአፈጻጸም ላይ ያሉ ጉዳዮች በዚህ አዋጅ መሠረት ይመራሉ ። ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ሕጎች ይህንን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ሕግ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። _ ፲፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፮ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና | ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?