የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፴፩ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፩ ፲፱፻፶፪ ዓ.ም የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅ ገጽ ፭ሺ፫፻፳፯ አዋጅ ቁጥር የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፖለቲካ ሥልጣን ባለቤትነትእንዲሁም ለሕግ ልዕልና እውነት ባካሄደው ረጅም ትግል የከፈለው መስዋዕ ትነት በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈጸሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቀጩበትን ወይም የሚታረሙበትን ቀልጣፋ ኣሠራር በመዘ ርጋት ለሰናይ መስተዳድር መሠረት የመጣልን ወቅታዊ እርምጃ | good governance , by way of setting up an easily accessible የሚጠይቅ በመሆኑ፡ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የሚያከናውኗቸው ተግባሮች ከዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር ያላቸው ቁርኝትና ከመብታቸው ጋር በተሳሰረ ሁኔታ የሚኖራቸው የወሳኝነት ሥልጣን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየሰፋ በመምጣቱ ፡፡ በዚህ ሂደት የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ባለሥልጣኖ ቻቸው የሚሰጧቸውን ፍትሃዊነት የጎደላቸው ውሳኔዎችናጎ \ unjust decisions and orders of executive organs and officials ትዕዛዞች በወቅቱ፡ ማረም ወይም እንዳይደርሱ መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ፡ አስተዳደራዊ ጥፋት የተፈጸመባቸው ዜጎች ተጎድተው እንዳ ይቀሩ በቀላሉ ቅሬታቸውን የሚያሰሙበትና መፍትሄ የሚሹበት | remedies with easy access needs to be fulfilled ; ተቋም የማግኘት ፍላጎታቸው መሟላት ያለበት በመሆኑ፡ ሕግ አውጪው በሕዝብ ተወካይነቱ ሕግ አስፈጻሚው አካል \ people , has the responsibility to ensure that the executive ተግባሩን በሕግ መሠረት የሚያከናውንና የሚሰጣቸው ኣስተዳ | organ Carries out its functions in accordance with the law and ደራዊ ውሳኔዎች የዜጎችን መብቶች የማይጋፉ መሆናቸውን የማረ of citizens rights : ጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ፡ ያንዱ ዋጋ 4.85 ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪፲ሮ፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፩ ሰኔ ፳፯ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም • ፴ • ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ወይም የተለመደ አሠራር በዚህ አዋጅ ውስጥ በተጠቀሱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፴፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ : ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ገጽ ፭ሺ፫፻፷፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ይህንኑ መርህ ለማጎልበትና ስለሕግ አውጪው ሆኖ አስተዳ ደራዊ በደል እንዳይደርስ የመቆጣጠሪያ መሣሪያ በመሆን ከሚያገለ | thereof , it is found necessary to establish , and to determine the ግሉት ተቋሞች መካከል አንዱ የሆነውን የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ | powers and duties of the Office of Ombudsman , as one of the ተቋምን ማቋቋምና ሥልጣኑንና ተግባሩን በሕግ መወሰን ኣስፈላጊ parliamentary institutions instrumental in the control of the ሆኖ በመገኘቱ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) እና ( i ) መሠረት የሚከተለው | ) and ( 15 ) of the Constitution , it is hereby proclaimed as ታውጇል ። ምዕራፍ አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፩ / ፲፱፻፲፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር | 2. Definitions በዚህ አዋጅ ውስጥ ፦ ፩ “ ተሿሚ ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በምክር ቤቱ የሚሾም ዋና ዕንባ ጠባቂ፡ ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ ወይም በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ደረጃ የሚገኝ ወይም የህፃናትንና የሴቶችን ጉዳይ የሚከታተል ዕንባ ጠባቂ ማለት ነው ። ፪ . “ ሠራተኛ ” ማለት የተቋሙ መምሪያ ኃላፊዎችን፡ ባለሙ ያዎችንና ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞችን ይጨምራል፡ ፫ . “ ቤተዘመድ ” ማለት በኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ሕግ መሠረት የሥጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው ሰው ነው፡ ፬ . “ ምክር ቤት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው ፣ ጅ “ የአስተዳደር ጥፋት ” ማለት ማናቸውንም የአስተዳደር ሕግን ወይም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ሕግን ወይም ሌሎች አስተዳደር ነክ ሕጎችን በመፃረር በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ይጨምራል፡ ፮ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የሕዝብ ተመራጭ ወይም የመን ግሥት አስፈጻሚ አካል ተሿሚ ወይም ኃላፊ ነው፡ ፯ “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡ ፰ . “ ክልል ” ማለት በኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) ላይ የተመለ ከቱትማለት ሲሆን ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርንና የድሬዳዋ አስተዳደርን ይጨጨምራል፡ ፱ . “ መንግሥት ” ማለት የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥት ነው፡ ፲ . “ የመንግሥት የልማት ድርጅት ” ማለት በመንግሥት ባለቤትነት ሥር የሚገኝ የማምረቻ፡ የማከፋፈያ ፣ አገል ግሎት ሰጭ ወይም ሌላ ዓይነት ድርጅት ነው፡ ፲፩ . “ የመንግሥት መ ቤት ” ማለት ሚኒስቴር፡ ኮሚሽን ፣ ባለሥልጣን፡ ኤጀንሲ፡ ኢንስቲትዩት ማናቸውም ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ነው፡ ፲፪ . “ መርማሪ ” ማለት የምርመራ ሥራ እንዲያካሂድ በዋና ዕንባ ጠባቂው የተመደበ ሠራተኛ ነው ፡ ፲፫ . “ አስፈጻሚ አካል ” ማለት የመንግሥት መሥሪያ ቦትን፡ ወይም የመንግሥት የልማት ድርጅትን እንዲሁም በዳኝነት ሰጭ ወይም በሕግ አውጪው አካል ውስጥ የአስተዳደር ወይም የኣስተዳደር ነክ አገልግሎት የሚሰጥ አካልን ይጨጨምራል፡ “ ሕግ ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥትን፡ የክልል ሕገ መንግሥትን ፣ የፌዴራል ሕጎችንና ደንቦችን ይጨምራል ። ገጽ ፭ሺ፫፻፲፰፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፫ . መቋቋም የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ( ከዚህ በኋላ “ ተቋሙ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ተቋሙ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ይሆናል ። ፬ . የተፈጻሚነት ወሰን ፩ . በዚህ አዋጅ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ይጨምራል ። ፪ ይህ አዋጅ በክልል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ባለሥልጣኖቻቸው በሚፈጸሙ የአስተዳደር ጥፋቶችም ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል ። የተቋሙ ዓላማ በሕግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶች እና | 5. Objective ጥቅሞች በአስፈጻሚው አካላት መከበራቸውን በማረጋገጥ፡ የሕግ የበላይነትን መሠረት ያደረገ ጥራት፡ ቅልጥፍናና ግልጽነት ያለው መልካም የመንግሥት አስተዳደር እንዲ ሰፍን ማድረግ ይሆናል ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ተቋሙ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ አስፈጻሚ አካላት የሚያወጧቸው አስተዳደራዊ መመሪ ያዎች : የሚሰጧቸው ውሳኔዎችና አሠራሮቻቸው የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብቶችንና ሕጎችን የማይ ቃረኑ መሆናቸውን መቆጣጠር፡ ፪ • አስተዳደራዊ ጥፋትን አስመልክቶ የሚቀርቡ ቅሬታ ዎችን የመቀበልና የመመርመር ፣ ፫ አስፈጻሚው አካል ሥራውን በሕግ መሠረት የሚያከ ናውን መሆኑን ለማረጋገጥና አስተዳደራዊ ጥፋቶች እንዳ ይፈጸሙ ለመከላከል ቁጥጥር የማድረግ ፣ አስተዳደራዊ ጥፋት መፈፀሙን ያመነበት ከሆነ የመፍትሄ ሃሳብ የመሻት፡ ፭ አስተዳደራዊ ጥፋቶች የሚሻሻሉበትን ሁኔታ የማጥናትና ሃሳብ የማቅረብ፡ ፮ የተሻለ የመንግሥት አስተዳደርን ለማስገኘት ነባር ሕጎች ወይም አሠራሮች ወይም መመሪያዎች እንዲሻሻሉ ፣ አዳዲስ ሕጎች እንዲወጡ ወይም ፖሊሲዎች እንዲቀየሱ የማሳሰብ፡ ፯ ከዓላማው ጋር የሚጣጣሙ ሌሎች ተግባሮችን የማከ ፯ የሥልጣን ገደብ ተቋሙ፡ በሕዝብ ምርጫ የተቋቋሙ ምክር ቤቶች በሕግ አውጭነ ታቸው የሚሰጧቸው ወሳኔዎችን ወይም ፣ ፪ በማንኛውም ፍርድ ቤት በየትኛውም ደረጃ በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ወይም፡ በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በመታየት ላይ ያሉጉዳዮችን ፬ . በፀጥታ ኃይሎችና በመከላከያ ሠራዊት ክፍሎች የሚሰጡ የፀጥታ ወይም የሀገር መከላከል ጉዳዮችን በሚመለከት የሚሰጡ ውሳኔዎችን፡ የመመርመር ሥልጣን የለውም ። ፰ የተቋሙ አቋም ፩ . የዕንባ ጠባቂ ጉባዔ፡ ፪ : ሀ ) ኣንድ ዋና ዕንባ ጠባቂ፡ ለ ) አንድ ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ፡ ሐ ) የሕፃናትና የሴቶችን ጉዳይ የሚመራ ዕንባ ጠባቂ ፣ መ ) የቅርንጫፍ ጸ / ቤቶች ዕንባ ጠባቂዎች እና ሠ ) አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ዋና መሥሪያ ቤት የተቋሙ ዋና መ / ቤት አዲስ አበባ ሆኖ ምክር ቤቱ በሚወ ስነው በማናቸውም ሥፍራ ቅርጫፍ ጽ / ቤት ሊኖረው ይችላል ። ገጽ ፩ሺ፫፻ሮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፩ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ፲ አሿሿም ዋና ዕንባ ጠባቂ፡ ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂና ሌሎች ዕንባ ጠባቂዎች በምክር ቤቱ ይሾማሉ ። የዋና ዕንባ ጠባቂ፡ የምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂና የሌሎች ዕንባ ጠባቂዎች አሿሿም የሚከተለው የአመራረጥ ሥርዓት ይኖረዋል፡ ሀ ) ተሿሚዎች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፩ መሠረት በሚቋቋመው ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ይመለመላሉ፡ ለ ) ዕጩዎቹም በኮሚቴው ሁለት ሦስተኛ ድምፅ የተደገፉ መሆን አለባቸው፡ ሐ ) ዕጩዎቹ በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ለምክር ቤቱ ቀርበው ድምጽ የሚሰጥባቸው ይሆናል፡ መ ) የቀረቡት ዕጩዎች በምክር ቤቱ ሁለት ሦስተኛ ድምዕ ሲደገፉ ይሾማሉ ። ፲፩ የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ጥንቅር የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፣ የምክር ቤቱ አፈጉባዔ ............. ሰብሳቢ ፣ ፪ • የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ................... አባል፡ ፫ ከምክር ቤቱ አባላት መካከል የሚመረጡ አም ስት አባላት በምክር ቤቱ መቀመጫ ካላቸው ተቃዋሚ ጋርቲዎች መካከል በጋራ ስምምነት የሚመረጡ ሁለት የምክር ቤቱ አባላት ...... ፭ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ... ፲ቡ ለሹመት የሚያበቁ መመዘኛዎች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ሰው በዕንባ ጠባቂነት ሊሾም ይችላል፡ ፩ : ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ተገዥ የሆነ፡ ፪ በሕግ ወይም በአስተዳደር ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሙያ የሰለጠነ ወይም በልምድ በቂ ዕውቀት ያካበተ፡ ፫ • በታታሪነቱ፡ በታማኝነቱ እና በሥነ ምግባሩ መልካም ስም ያተረፈ፡ ፬ . ከደንብ መተላለፍ ውጪ ባለ በሌላ የወንጀል ጥፋት ተከሶ ያልተፈረደበት፡ ፭ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ፡ ሥራውን ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ጤንነት ያለው፡ እና ፯ ዕድሜው ከ፴፭ ዓመት በላይ የሆነ ። ፲፫ • ተጠሪነት ዋና ዕንባ ጠባቂ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ይሆናል ። ፪ ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂውና ሌሎች ዕንባ ጠባቂዎች ተጠሪነታቸው ለዋናው ዕንባ ጠባቂ ይሆናል ። የሥራ ዘመን ፩ . የማንኛውም ተሿሚ የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተገለጸው የሥራ ዘመን ካበቃ በኋላ ተሿሚው እንደገና ሊሾም ይችላል ። ፫ በአንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) መሠረት ሹመቱ ቀሪ የተደረገበት ወይም ከኃላፊነት የተነሳ ሰው እንደገና ካልተሾመ በስተቀር ለስድስት ወር ያህል በሕግ አውጪ ፣ በሕግ አስፈጸሚ ወይም በዳኝነት አካላት ውስጥ የኃላፊነት ቦታ አይሰጠውም ። ገጽ ፩ሺ፪፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ፲፭ ተሿሚው ከኃላፊነት የሚነሳበት ምክንያት አንድ ተሿሚ በሚከተሉት ሁኔታዎች ከኃላፊነት እንዲነሳ ወይም ሹመቱ ቀሪ እንዲሆን ሊደረግ ይችላል፡ ሀ ) ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ለመልቀቅ ሲፈልግና አስቀድሞ የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ በጽሑፍ ሲሰጥ ፡ ወይም ለ ) በህመም ምክንያት ሥራውን በሚገባ ለማከናወን የማይችል መሆኑ ሲረጋገጥ ፡ ወይም ሐ ) በሙስና መሥራቱ ወይም ሕግን የሚጻረር ሌላ ድርጊት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ፡ ወይም መ ) ግልጽ የሆነ የሥራችሎታማነስመኖሩ ሲረጋገጥ፡ ሠ ) የሥራ ዘመኑ ሲያበቃ ። ፪ አንድ ተሿሚ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ከኃላፊነት ከተነሳበት ወይም ሹመቱ ቀሪ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ በስድስት ወሮች ውስጥ በሌላ ተሿሚ መተካት ይኖርበታል ። ፲፮ ተሿሚው ከኃላፊነት የሚነሳበት ሥነ ሥርዓት አንድ ተሿሚ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፭ ( ፩ ) ከ ( ለ ) ( መ ) በተዘረዘሩት ምክንያቶች መሠረት ሹመቱ ቀሪ እንዲሆን የሚደረገው ጉዳዩ በአንቀጽ ፲፯ መሠረት በሚቋቋመው ልዩ አጣሪ ጉባዔ ከተመረመረ በኋላ ይሆናል ። ፪ ምክር ቤቱ በልዩአጣሪ ጉባዔው አብላጫ ድምጽ ተደግፎ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ሲያምንበትና በሁለት ሦስተኛ ድምዕ ሲደግፈው ተሿሚው ከኃላፊነት እንዲነሳ ይደረጋል ። ፲፯ . የልዩ አጣሪ ጉባዔው ጥንቅር ልዩ አጣሪ ጉባኤው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል ፣ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ............... … ሰብሳቢ፡ ፪ • የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ................. አባል ፤ ፫ ከምክር ቤቱ አባላት መካከል የሚመረጡ ሦስት አባላት ፬ . በምክር ቤቱ መቀመጫ ካላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ ስምምነት የሚመረጥ አንድ የም / ቤቱ አባል ፭ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ፲፰ : በሌላ ሥራ መሰማራት ስለመከልከሉ ፩ ተሿሚው በሥራ ዘመኑ ክፍያን በሚያስገኝ በሌላ የመን ግሥትም ሆነ የግል ቅጥር ሥራ ላይእንዲሠማራ አይፈቀ ድለትም ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ቢኖርም ተሿሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚፈለግበት የተለየ የሙያ መስክ ከግምት ውስጥ ገብቶ በምክር ቤቱ ሊፈቀ ድለት ይችላል ። ምዕራፍ ሁለት የተሿሚዎች ሥልጣንና ተግባሮች ፲፬ . የዋና ዕንባ ጠባቂው ሥልጣንና ተግባር ዋናው ዕንባ ጠባቂ የተቋሙ የበላይ ኃላፊ በመሆን በዚህ አዋጅ ለተቋሙ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ያውላል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ዕንባ ጠባቂ ፣ ሀ ) የተቋሙ የዕንባ ጠባቂዎች ጉባዔ በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት ሠራተኞችን ይቀጥራል ፣ ያስተዳ ለ ) የተቋሙን በጀት አዘጋጅቶ በቀጥታ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፣ ሐ ) በቂ ምክንያት ሲኖረው አንድ ጉዳይ ከአንድ የምርመራ ክፍል ወይም መርማሪ ወደ ሌላ የምርመራ ክፍል ወይም መርማሪ ያዛውራል ፡ ወይም በማንኛውም ሥፍራ የተፈጸመ አስተዳ ደራዊ ጥፋትን በራሱ ይመረምራል፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. መ ) ተደጋጋሚ የአስተዳደር ጥፋቶችን ከመፍትሄ ሃሳብ ጋር ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡ ) አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ረቂቅ ሕጎችን አዘጋጅቶ ያቀርባል፡ በሌሎች አካላት በተዘጋጁ ላይ አስተያየት ይሰጣል፡ አስተዳደራዊ ጥፋቶችንና የተቋሙን ሥራ አካሄድ አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል፡ ሰ ) ተቋሙን በመወከል በስብሰባዎች ይካፈላል፡ ከፌዴ ራለና ከክልል መንግሥታት አካላት እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሥራ ግንኙነት ያደርጋል፡ ሸ ) ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን ያደራጃል፡ ያስተባ ብራል፡ ይከታተላል፡ ቀ ) በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከና በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ( ለ ) ፡ ( ሠ ) ፡ ( ረ ) እና በአንቀጽ ፴፭ ( ፪ ) ከተጠቀሱት በስተቀር ሌሎችጉዳዮችን በሚመለከት ዋና ዕንባ ጠባቂው ለተቋሙ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለዕንባ ጠባቂዎች ወይም ለሌሎች ኃላፊዎች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። = ፳ የምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ ሥልጣንና ተግባር ከዋና ዕንባ ጠባቂው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት፡ ፩ የተቋሙን ዋና መሥሪያ ቤት ተግባራትን በማቀድ፡ በማደራጀት፡ በመምራትና በማስተባበር ዋና ዕንባ ጠባቂውን ይረዳል ። ዋና ዕንባ ጠባቂው በማይኖርበት ጊዜ ለዋናው ዕንባ ጠባቂ የተሰጡትን ሥራዎች ያከናውናል ። በዋናው ዕንባ ጠባቂ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፳፩ • የቅርንጫፍ ጽ / ቤቶች የዕንባ ጠባቂዎች ሥልጣንና ተግባር ዕንባ ጠባቂው የቅርንጫፍ ጽ ቤቱ የበላይ ኃላፊ በመሆን በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፮ በተቋቋመበት ሥፍራ ውስጥ ለተቋሙ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ከማዋል በተጨማሪ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ . የመንግሥት የአስተዳደር ሕጎች እና ሌሎች ሕጎች፡ ደንቦችና መመሪያዎች መከበራቸውን የማረጋገጥ ፣ ፪ . በቂ ምክንያት ሲኖር አንድ የአስተዳደር ጉዳይ ከአንድ የምርመራ ክፍል ወይም ከአንድ መርማሪ ወደ ሌላ የማዛወር ወይም እራሱ ምርመራ የማካሄድ ፣ ፫ አስተዳደራዊ ጥፋቶችን በተመለከተ ለዋናው ዕንባ ጠባቂና በተቋቋመበት ሥፍራ ለሚገኝክልል መንግሥት ዝርዝር ሪፖርት የማቅረብ፡ ፬ . ከመልካም አስተዳደር መርህ ጋር የማይጣጣሙ ሕጎችና የአሠራር ልምዶች እንዲሻሻሉ ሃሳብ የማቅረብ፡ በተቋሙ በሚወጣው መመሪያ መሠረት ቅርንጫፍ ጽ ኬቱን የመምራት፡ ፮ ለቅርንጫፍ ጽ / ቤቱ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ ዎችን የመፈጸም ፣ ቪ ቅርንጫፍ ጽ / ቤቱን በመወከል ከክልል መንግሥት አካላትና በተቋቋመበት ሥፍራ ውስጥ ከሚሠሩ መንግ ሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሥራ ግንኙነት የማድረግ፡ በዋና ዕንባ ጠባቂው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች የማከናወን ። ምዕራፍ ሦስት የተቋሙ የአሠራር ደንቦች ናጀ አቤቱታ የማቅረብ መብት ፩ አቤቱታ የሚቀርበው መብቴ ተጥሶብኛል በሚል ሰው ፣ ወይም በሚስት ወይም በባል ወይም በቤተዘመድ ወይም በወኪል ወይም በሦስተኛ ወገን ሊሆን ይችላል ። ገጽ ፭ሺ፫፻ሮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፩ ሰኔ ፳፫ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ፪ • እንደተፈጸመው የአስተዳደር ጥፋት ክብደት ተቋሙ የአመልካቹ ማንነት ሳይገለዕ የሚቀርቡለትን አቤቱ ታዎች ሊቀበል ይችላል ። ፫ . ማንኛውም ሰው ስለደረሰበት የአስተዳደር ጥፋት ለተቋሙ አቤቱታ ከማቅረቡ በፊት አግባብነት ላላቸው አካላት ደረጃውን ጠብቆ ቅሬታውን ማሰማት ይኖር በአንቀጽ ፯የተደነገገውእንደተጠበቀ ሆኖ ፣ በዚህ አዋጅ መሠረት አቤቱታ የማቅረብ መብት በጉዳዩ የወንጀል ወይም የፍትሐ ብሔር ክስ መመስረትን አይከለክልም ። ፭ ተቋሙ አቤታታዎችን የሚመረምረው ያለምንም ክፍያ ነው ። ፳፫ : ስለ አቤቱታ አቀራረብ ፩- አቤቱታ በቃል ወይም በጽሑፍ ወይም በማንኛውም ሌላ መንገድ ለተቋሙ ሊቀርብ ይችላል ። ፪ አቤቱታዎች በተቻለ መጠን ከደጋፊ ማስረጃዎች ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል ። ፫ . አቤቱታ እንደሁኔታው በአማርኛ ወይም በክልሉ የሥራ ቋንቋ ሊቀርብ ይችላል ። ፳፬ . ስለምርመራ ፩ ተቋሙ የቀረቡለትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ ምርመራ ሊያካሂድ ይችላል ። ተቋሙ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በራሱ አነሳሽነት ምርመራ የማካሄድ ሥልጣን አለው ። ፳፭ ማስረጃዎች እንዲቀርቡ ስለማድረግ ተቋሙ አስፈላጊ ማጣሪያዎችን ለማካሄድ በቂ በሆነ ጊዜ ፩ ተመርማሪዎች ለጥያቄ እንዲቀርቡ ወይም መልስ እንዲሰጡ፡ ፪ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ፡ ለጉዳዩ ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ የያዘ ማንኛውም ሰው ይህንን ማስረጃ እንዲያቀርብ፡ ለማድረግ ይችላል ። ፳፮ መፍትሔ ስለመስጠት ተቋሙ የቀረበለትን አቤቱታ በስምምነት ለመጨረስ የተቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት ። የምርመራውን ውጤት ከነአስተያየቱ ለሚመለከተው አካል የበላይ ኃላፊ እና ለአቤቱታ አቅራቢው በጽሑፍ ያሳወቃል ። ተቋሙ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የሚሰጠው አስተያየት ለተፈጸመው የአስተዳደር ጥፋት ምክንያት የሆነው ደርጊት ወይም አሠራር እንዲቆም ወይም ለጥፋቱ ምክንያት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነቱ ቀሪ እንዲሆንና የተፈጸመው የአስተዳደር ጥፋት እንዲ ታረም ወይም ተገቢ የሆነ ማንኛውም ሌላ እርምጃ እንዲወሰድ በግልጽ የሚያመለክት መሆን ይኖርበታል ። ፬ • ለተቋሙ የሚቀርቡ ኣቤቱታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ማግኘት ይኖርባቸዋል ። ፳፯ ቅሬታ የማሰማት መብት ፩ . ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ ወይም ተመርማሪ የተቋሙ የበታች ተሿሚ ወይም ኃላፊ በሰጠው የመፍትሔ ሃሳብ ቅሬታ ያለው ከሆነ የመፍትሔ ሀሳቡ በዕሑፍ ከደረሰው ጊዜ አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በደረጃው ቀጥሎ ለሚገኘው የተቋሙ ተሿሚ ወይም ኃላፊ ቅሬታውን የማሰማት መብት አለው ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ቅሬታው የቀረበለት ተሿሚ ወይም ኃላፊ የተሰጠውን የመፍትሄ ሃሳብ ማሻሻል፡ ማገድ፡ መሻር ወይም ማዕናት ይችላል ። በዋና ዕንባ ጠባቂው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል ። ፳፰ ጥፋት መፈጸሙን የማስታወቅ ግዴታ ተቋሙ የምርመራ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ወንጀል መሠራቱን ያመነ እንደሆነ ለሚመለከተው አካል ወይም ኃላፊ ወዲያውኑ በጸሑፍ የማስታወቅ ግዴታ አለበት ። ገጽ ፩ሺ፫፻፳፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ፳፱ : ስለ ሥልጣን መደራረብ ፩ በተቋሙና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሥልጣን ሥር የሚወድቁ ጉዳዮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ በማንኛቸው እንደሚመረመሩ በሁለቱ የጋራ ምክክር ይወሰናል ። አንድን ጉዳይ የትኛው አካል እንደሚመረምር በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት መወሰን ካልተቻለ አስቀድሞ የቀረበለት አካል ይመረምራል ። ምዕራፍ አራት ስለተቋሙ ዕንባ ጠባቂዎች ጉባዔና ስለተቋሙ ሠራተኞች አስተዳደር የተቋሙ ዕንባ ጠባቂዎች ጉባዔ የተቋሙ ዕንባ ጠባቂዎችጉባኤ ( ከዚህ በኋላ “ ጉባዔው እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ . ጉባዔው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡ ሀ ) ዋና ዕንባ ጠባቂ ...... ለ ) ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ . ም ሰብሳቢ ሐ ) ሌሎች ዕንባ ጠባቂዎች . .አባላት ። ጉባዔው የራሱን ዐሐፊ ከአባላቱ መካከል ይመርጣል ። ጉባዔው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥነሥርዓት ደንቦች ሊያወጣ ይችላል ። ፴፩ የጉባዔው ሥልጣንና ተግባር ጉባዔው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ ይህን አዋጅ ሥራ ላይ ለማዋል መመሪያዎችንና የውስጥ ደንቦችን ያጸድቃል፡ በተቋሙ ረቂቅ በጀት ላይ ይመክራል ። የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማ በመከተል የተቋሙ ሠራተኞች የሚተዳደሩበትን መመሪያ ያጸድቃል፡ መምሪያ ኃላፊዎችን ይሾማል፡ ፭ . የሚቀርቡለትን የሠራተኛ ኣስተዳደር ጉዳዮች - ጥያቄዎች ወይም አቤቱታዎች መርምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ፡ የመምሪያ ኃላፊዎችን የዲሲፕሊን ጉዳዮች ያያል ። ፪ ይግባኝ የማቅረብ መብት ፩ . ጉባዔው በሚሰጠው የአስተዳደር ውሳኔ ቅር የተሰኘ የተቋሙ መምሪያ ኃላፊ ውሳኔው ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቅሬታውን ለምክር ቤቱ አፈ ጉባኤማቅረብ ይችላል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል ። ፫ : በሌሎች ባለሙያዎች ስለመገልገል ተቋሙ ለተለየ ሥራና ለተወሰነ ጊዜ ተገቢ የሆነውን ክፍያ በመፈጸም ለሥ ራ የሚያስፈልጉትን የራሱ ያልሆኑ ባለሙያ ዎችን መድቦ ሊያሠራ ይችላል ። ፬ . ሚስጥር ስለመጠበቅ በፍርድ ቤት ካልታዘዘ ወይም በዋናው ዕንባ ጠባቂ ካልተ ፈደቀ በስተቀር ማንኛውም የተቋሙ ተሿሚ ወይም ሠራተኛ ወይም በኣንቀጸ ፴፫ መሠረት የተመደበ ባለሙያ በሥራው አጋጣሚ ያወቀውን ምስጢር በማንኛውም ጊዜ የመጠበቅ ግዴታ አለበት ። 3. ልዩ መብት ማንኛውሃ ” የተቋሙ፡ ፩ ተሿሚ ከሆነ ምክር ቤቱ፡ መርማሪ ከሆነ ዋና ዕንባ ጠባቂው፡ ሳይፈቅድ ወይም ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር አይያዝም፡ አይታሠርም ። የሚያደርገው ሌላ ዓይነት መጸጸፍ በስ ” ር ሌላ ገጽ ፩ሺ፫፻፸፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ምዕራፍ አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴፮ : በጀት ፩ የተቋሙ በጀት ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) በመንግሥት በሚመደብ በጀትና ድጎማ ለ ) ከዕርዳታ፡ ከስጦታና ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ። ፪ . ለተቋሙ ከተፈቀደው በጀት ውስጥ የየሦስት ወሩ ድርሻ የሆነ የሥራ ማስኬጃ በቅድሚያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወይም ባንኩ በሚወክለው ሌላ ባንክ ተቀማጭ ሆኖ በመንግሥት የፋይናንስ ሕግ መሠረት ለተቋሙ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ ይውላል ። ፴፯ የሂሳብ መዛግብት ተቋሙ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሒሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የተቋሙ ሂሳብ ምክር ቤቱ በሚሰይመው አካል በየዓመቱ ይመረመራል ። ፴፰ የመተባበር ግዴታ ተቋሙ ሥልጣንና ተግባሩን ሥራ ላይ ለማዋል እንዲችል | 38. Duty to Cooperate ማንኛውም ሰው አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት ይኖርበታል ። ፴፱ መግለጫ ስለመስጠት ተቋሙ እንደአስፈላጊነቱ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል ። ፪ • ተቋሙ መደበኛ ሪፖርቶች ማቅረብን ጨምሮ አሠራሩን በሙሉ ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ ይኖርበታል ። በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) የተደነገገው ቢኖርም የአገሪቱ ጸጥታና ደኅንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ለማድረግ ወይም የግለሰቦችን የግል ሕይወት መብት ለመጠበቅ ሲባል በምስጢር ሊያዙ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተቋሙ ጥንቃቄ የመውሰድ ግዴታ አለበት ። ፵ በስም ማጥፋት ስላለመጠየቅ በዚህ አዋጅ መሠረት የቀረበ አቤቱታ በስም ማጥፋት አያስጠይቅም ። ፪ • ተቋሙ ስለሚያካሂደው ምርመራ ውጤት ምክር ቤቱ የሚያቀርበው ሪፖርት ወይም ሥራውን በማስመልከት ማጥፋት የሚያ ስጠይቅ አይሆንም ። ፴፩ ስለ ቅጣት ፩ . ማንኛውም ሰው በተቋሙ መጥሪያ ደርሶት ወይም ሁኔታ ተጠርቶ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ ወይም መልስ ካልሰጠ ወይም ሰነዶች ለማቅረብ ወይም ለማስመርመር ፈቃደኛ ካልሆነ ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር በሚደርስ እሥራት ወይም ከብር ሁለት መቶ እስከ ብር አንድ ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ፪ • በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር፡ ምሥክሮች ሆነው በቀረቡ ወይም ሰነድ ባቀረቡ ሰዎች ላይ ጥቃት ካደረሰ ወይም በተቋሙ በቀረቡ ሪፖርቶች፡ በተሰጡት የማሻሻያ አስተያየቶችና ሀሳቦች ላይ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ያለበቂ ምክንያት እርምጃ ካልወሰደ ወይም እርምጃ የማይወስድበትን ምክንያት ካልገለጸ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥራት ወይም ከብር ስድስት ሺ እስከ ብር አሥር ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም ይቀጣል ። ፴፪ የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች ይህ አዋጅከመውጣቱ በፊት በምክር ቤቱ መታየትየተጀመሩ የአስተዳደር ጥፋቶችን የሚመለከቱ አቤቱታዎች በተቋሙ ይታያሉ ።