×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 17429

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ .17429
ጥቅምት 21 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2 አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ተገኔ ጌታነህ
4. ወ / ሮ ሆሣዕና ነጋሽ
5. ወ / ሪት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ወ / ሮ ሎሚ ሆርዶፋ
መልስ ሰጭ፡- አቶ ተስፋዬ ከበደ
የኑዛዜዎች ፎርምና ማስረጃ
በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ
ፎርም፡- የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 881
አቶ ከበደ ዳዲ በግልጽ ባደረጉት
ኑዛዜ ሰነድ ላይ የኑዛዜው
ዝርዝርና የአራት ሽማግሌዎች ያምስክሮች ስም ከተፃፈ በኋላ
ከዚህ በላይ ስማችን የተጠቀሰው ሽማግሌዎች በትክክለኛ አዕምሮኣቸው
ሆነው ሲናዘዝ ሰጥተናል ; አይተናል ” ተብሎ የተጠቀሰ ቢሆንም እና
ከቸናዛዥና እራ ምስክሮች ፊርማ ሞሉ ደግሞ ag ይሁንነቃል . com
በፊርማችን እናረጋግጣለን ” የሚል ቢሆንም ኑዛዜው
በተናዛዡና በአራቱም ምስክሮች ፊት ስለመነበቡ በግልጽ ያልተፃፈ
በመሆኑ ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ውሣኔ የፌዴራል የመጀመሪያ
ደረጃ ፍ / ቤት
በመስጠቱና ውሣኔውን
ውሣኔውን የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት
በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ ፡፡
ው ሣ ኔ
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠውና የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ያፀናው ውሣኔ በድምፅ ብልጫ ተሽሯል ፡፡
1. ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ” ሲናዘዙ ሠምተናል ፧ አይተናል ”
ተብሎ የተገለጸው የኑዛዜውን መነበብ የሚያመለክት ነው ፡፡
2. ኑዛዜው " ተነቧል " የሚል ቃል በግልጽ አለመስፈሩ ብቻ
ኑዛዜውን በምስክሮቹና በተናዛዥ ፊት አልተነበበም በማለት ኑዛዜውን ፈራሽ ለማድረግ በቂ ምክንያት አይደለም፡
የሰ / መ / ቁ 17429
ጥቅምት 21 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ
ተገኔ ጌታነህ
ሆሣዕና ነጋሽ
ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ወ / ሮ ሎሚ ሆርዶፋ - ቀረቡ
ተጠሪ፡- አቶ ተስፋዬ ከበደ - ቀረቡ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፈርደናል ፡፡
ፍ ር ድ
የአሁኗ አመልካች በሥር ፍ / ቤት የሟች ባለቤቴ አቶ ከበደ ዳዲ
የኑዛዜ ወራሽ መሆኔ ተረጋግጦ ማስረጃ ይሠጠኝ ብላ አመልክታ ተጠሪ
በተቀዋሚነት ቀርቦ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የአባቴ የሟች /
አይደለም ፣ ኑዛዜው እንዲሻር እኔም ሌላ መዝገብ ያስከፈትሁ ስለሆነ
Thariw አንድነት ፣ ው ይወስኝልኝ በማለትአመልክቷል ፡፡ .com
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤትም ሁለቱን መዛግብት መርምሮ
በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ በተናዛዡና በአራት ምሰክሮች ፊት ካልተነበበ
ምስክሮች ፊት ካልተነበበ
ይህም ሥርዓት መፈፀሙንና የተፃፈበትን ቀን የማያመለክት ካልሆነ
ፈራሽ ነው ፣
በኑዛዜው ሠነድ ላይ ኑዛዜው በተናዛዡና በአራቱም
ምስክሮች ፊት ስለመነበቡ በግልጽ ያልተፃፈ በመሆኑ በፍ / ሕ / ቁ . 881 / 2 /
መሠረት ፈራሽ ነው ሲል ወስኗል ፡፡ ከፍተኛ ፍ / ቤት ይህንኑ ውሣኔ
አፅንቷል ፡፡ አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው ፡፡
የሰበር አቤቱታው ፍሬ
ሃሣብ የኑዛዜው ፅሁፍ መነበቡን
ኑዛዜው የሚያሣይ ሆኖ ሣለ ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል
ሲሆን ፣ ተጠሪ በሥር ፍ / ቤቶች የተፈፀመ የሕግ ስህተት ስለሌለ ፍርዱ
ይፅናልኝ ሲል ተከራክራል ፡፡
በዚህ ችሎት ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው ነጥብ ኑዛዜው በፍ / ሕ / ቁ .
881 / 2 / መሠረት የተደረገ አይደለም መባሉ ተገቢ መሆን ያለመሆኑ
ጳጉሜ 5 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈው የአቶ ከበደ ዳዲ ኑዛዜ ላይ
የኑዛዜው ዝርዝርና የአራት ሽማግሌዎች ምስክሮች ! ስም ከተፃፈ በኋላ
በላይ ስማችን የተጠቀሰው
ሽማግሌዎች በትክክለኛ
አዕምሮዋቸው ሆነው ሲናዘዙ ሰምተናል ፧ አይተናል ” ተብሎ ተጠቅሷል ፡፡
ከተናዛዡና ከአራቱ ምስክሮች ፊርማ ቀጥሎ ደግሞ
ይህንኑ ቃል
ለመስማታችን ሰፊርማችን እናረጋግጣለን
ይላል ፡፡
የፍ / ሕ / ቁ , 881 / 2
ኑዛዜው በተናዛዡና አራት ምስክሮች ፊት
ካልተነበበና ይኸም ሥርዓት / ፎርማሊቲ / መፈፀሙንና የተፃፈበትንም
ቀን የሚያመለክት ካልሆነ በቀር ፈራሽ ነው
በማለት ሲደነግግ
የፍ / ሕግ ቁጥር 88 / 3 / ደግሞ “ ተናዛዡና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ
ወዲያውኑ
ፊርማቸውን
ምልክታቸውን
ካላደረጉበት በቀር ፈራሽ ነው " ይላል ፡፡
እነዚህ ሁለት ንዑሳን አንቀጾች አንድ ኑዛዜ አራት ነገሮችን
የተደረገበትን
በአራት ምስክሮች ፊት
መደረጉን ፣ ኑዛዜው በተናዛቹና በምስክሮች መፈረሙንና
መነበቡን
ማሣየት እንዳለበት ይደነግጋሉ ፤ ከፍ ሲል ከኑዛዜው ፅሁፍ ላይ ወስደን
ካሠፈርነው መረዳት የተቻለው ኑዛዜው ጳጉሜ 3 ቀን 1999 በሚል ቀን
የተፃፈበት ፣ የአራት ምስክሮች ስም ያለበት ፣ ምስክሮቹና ተናዛዡ
ሌላም በኑዛዜው ላይ
ሠምተናል ፣
ኣይተናል ”
መገለፁም
የኑዛዜውን
የሚያመለክት ነው ፡፡ ሕጉ የኑዛዜውን መነበብ አስፈላጊነት ያስቀመጠው
በሚነበብበት
ወቅት ሟች / ተናዛዥ
የተናገረው
በትክክል በፅሁፍ
መስፈሩን እንዲረዳና የተናዛዡ ፈቃድ መሟላቱን ማረጋገጥ እንዲቻል
ነው ፡፡ ከላይ በተጠቀሰው የኑዛዜው ክፍል
« ሲናዘዙ ሠምተናል ፣
አይተናል
በሚል የሠፈረው ምስክሮች ያዩትና የሰሙት ኑዛዜው
ሲደረግና የተፃፈው ኑዛዜ ሲነበብ ነው ተብሎ መገመት ይኖርበታል ፡፡
የሥር ፍ / ቤቶች ኑዛዜውን ለማፍረስ የሚያበቃ የሕግ መሠረት
በሌለበት በኑዛዜው ፅሁፍ ላይ ኑዛዜው
« ተነቧል » የሚል ቃል
ባለመኖሩ ብቻ ኑዛዜው በምስክሮችና በተናዛዡ ፊት ስለመነበቡ
አልተፃፈም በማለት ፈራሽ ማድረጋቸው ተገቢ ሆኖ አልተገኘም ፡፡
ው ሣ ኔ
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁጥር 7/93
እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 3644 የሠጧቸው
ውሣኔዎች ተሽረዋል ፡፡
ኑዛዜው በፍ / ሕ / ቁ . 881 በተደነገገው መሠረት የተከናወነ በመሆኑ
የፀና ነው ብለናል ፤ ይፃፍ ፥ መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡
የሃሳብ ልዩነት
ስሜ በተራ ቁጥር አራት የተጠቀሰው ዳኛ አብዛኛው ድምፅ
የኑዛዜውን ሕጋዊነት በማረጋገጥ በሰጠው ውሣኔ የማልስማማ በመሆኑ
የሃሳብ ልዩነቴን እንደሚከተለው አስፍራለሁ ፡፡
ከሦስቱ ዓይነት ኑዛዜዎች አንዱ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ነው ፡፡
| የፍ / ብ / ሕግ / ቁ . 880 / ሀ / : ይህ አይነት ኑዛዜ ለማፅናት በተናዘዝና
ሰአራት ምስክሮች ፊት መነበብና ይኸም ስርዓት መፈፀምን ማመልከት
ይኖርበታል ፡፡ የፍ / ብ / ሕግ / ቁ .881 / 2 / ፡፡ ኑዛዜ የሟቹ ጥብቅ የሆነ ራሱ
የሚፈፅመው ሥራ ነው ፡፡ የፍ / ብ / ሕግ / ቁ .857 / 1 / የማንበብ ሥርዓት
አስፈላጊ የሆነው በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማናቸውም
ሌላ ሰው ሊፅፈው ስለሚችል በሌላ ሰው የተፃፈው ቃል በትክክል የሟች
ቃል መሆኑን ለማረጋገጥ ነው ፡፡ ምስክሮቹ ኑዛዜ የተፃፈበትን ቋንቋ
ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ
ያላቸው መሆንም አለባቸው ፡፡ / የፍ / ብ / ሕግቁ .837 / ይህም ድንጋጌ
በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ የመነበብ ስርዓት አስፈላጊና መነበቡም በትክክል
በማያጠራጥር ሁኔታ መፈፀም ያለበት መሆኑን ያመላክታል ፡፡
ወደ ጉዳዩ ስንመጣ አብዛኛው ድምፅ ኑዛዜው ተነቧል
የሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰው የአቶ ከበደ ኑዛዜ የአራቱን ምስክሮች
ስም ከጠቀሰ በኋላ
ሲናዘዝ ሰምተናል አይተናል
እንዲሁም
ከተናዛና
ከምስክሮች
ለመሰማታችን
ሰፊርማችን እናረጋግጣለን
በመስፈራቸው ነው ። በእኔ እምነት ምስክሮቹ
በእኔ እምነት ምስክሮቹ ሰምተናል አይተናል
የሚሉት ሟች ኑዛዜውን በመስጠት ላይ እያለ የተናገረውን ሊሆን
ስለሚችል እነዚህ ቃላቶች በርግጠኝነት መነበብን አያመለክቱም ከነዚህ
ቃላቶች ሕጉ እንዲፈፀም የሚፈለገውን የማንበብ ሥርዓት መፈፀም
አለመፈፀም
በትክክል ማረጋገጥ አይቻልም ፡፡ ተፈፅሟል ለማለትም
ያዳግታል ፡፡ ይህ ሕጉ በግልፅ እንዲፈፀም የሚፈልገው ስርዓት መፈፀም
ሳይረጋገጥ ደግሞ ኑዛዜው ሊፀና አይገባም ፡፡ በመሆኑም የስር ፍ / ቤቶች
ውሣኔ የሚሽርበት ምክንያት ስለሌለ ሊፀና ይገባል
ተለይቻለሁ ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?