×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 14057

      Sorry, pritning is not allowed

ቀንበረፀሐይ ታደሰ ፍሥሐ ወር ይህ
የሰበር መ / ቁ .14057
ጥቅምት 30 ቀን 1998 ዓ.ም ስንዱ አለሙ ሆሣዕና ነጋሽ
አሰግድ ጋሻው አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጠሪ፡- አቶ ጌታሁን ኃይሉ ስራ ክርክር - የዓመት ዕረፍት ክፍያ - የአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 79 / 2 / እና 15 / ፣ 77/5 ፣ 77 / 3 /
የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ መስርተው የ 128 ቀናት የዓመት ዕረፍት በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጣቸው የጠየቁ ሲሆን ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የተላለፈ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ከሁለት ዓመት በላይ መራዘም ስለሌለበት 128 የእረፍት ቀናት ተቀንሶ አዋጁ በሥራ ላይ ከዋለበት ጀምሮ ተጠሪ እስከተሰናበቱበት ድረስ የአንድ አመት ከአሥራ ሦስት ቀናት የዓመት ዕረፍት ክፍያ ብቻ ይከፈል በማለት ሊወሰን ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ የተጠሪ ገንዘብ የጠየቀው የአመት ዕረፍት ) ሳይቀነስ ሊከፈል ይገባል በማለት በመወሰኑ የቀረበ ኣቤቱታ ፡፡
ውሣኔ፡- የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውና የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሻሻለው ውሳኔ ተሻሽሏል ፡፡
ከሁለት ዓመት በላይ የተራዘሙ ፈቃዶች በገንዘብ የሚተኩ
አይደሉም አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ያልተጠቀመበት የዓመት
ፈቃድ ክፍያ ሁሉ , የጊዜ ገደብ ሳይኖረው በገንዘብ ተቀይሮ ሊከፈለው አይችልም ።
ሐት፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
የሰበር መ / ቁ .14057
ጥቅምት 30 ቀን 1998 ዓ.ም ፍሥሐ ወርቅነህ ስንዱ እስመ ሆሣዕና ነጋሽ
አሰግድ ጋሻው አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነ / ፈጅ ሀይሉ ተሰማ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጌታሁን ኃይሉ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ አመልካች ለሰበር ችሎት አቤቱታ ያቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመዝቁ .15313 ህዳር 25 ቀን 1996 ዓ.ም የአመት ዕረፍት ክፍያን በተመለከተ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው ፡፡
ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ነው ፡፡ የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ከሌሎች ክፍያዎች ጋር የተጠራቀመ የ 128 ቀናት የአመት እረፍት በጎንዘብ ተለውጦ እንዲከፈለው ነው ። አመልካች የአመት ዕረፍት ክፍያን አስመልክቶ በአዋጅ 42/85 አንቀጽ 79 2 እና 5 መሠረት የተላለፈው የዓመት ፈቃድ ከሚቀጥለው ሁለት አመት በላይ ሊራዘም አይችልም ተጠሪ የጠየቀው ክፍያ በሕጉ ከተሰጠው ሰላይ ስለሆነ ሊከፈሰው አይገባም በማለት መከራከሩን የፍ / ቤቱ ውሣኔ ያሳያል ።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የፌዴሪል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠው ውሣኔ } ... የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 192 / 1 / ሠ / እዋጅ ቁጥር 64/68 የሆነውን በግልጽ የሻረው በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ አዋጅ ቁጥር 42/85 ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም የሚለው የተከሣሽ ክርክር ተቀባይነት የለውም ፣ ፣ ስለሆነም በአዋጅ ቁ 42 / 85 በአንቀጽ 79 / 5 / ሥር በአንቀጽ 79 / እና / 2 / የተላለፈ የአመት ዕረፍት ፈቃድ
ከሁለት አመት በላይ መራዘም እንደሌለበት የተደገነነ በመሆኑ በዚህ ድንጋጌ * The Afri ሠረት የካሣሽ [ 28 እረፍት ቆኞች : ቅኝጾአዋጁ በሥራጓይ ዋለበት
ከጥር 12/85 ጀምሮ እስከተሰናበቱበት ጊዜ እስከ ጥር 28/86 ዓ.ም ያለው ጊዜ የአንድ አመት ከአሥራ ሶስት ቀናት የኣመት ዕረፍት ክፍያ ብቻ በአንቀጽ 77 / 3 / መሠረት እንዲክፈል የሚል ነው ፡፡
ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፈዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት አቅርቧል ፡፡ ፍ / ቤቱም አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 79 / 5 / የአመት ዕረፍት ከሁለት አመት በላይ ሊተላለፍ አይችልም ሲል ሠራተኛው ከሁለት ዓመት በላይ ያጠራቀመው የአመት ዕረፍት ካለ አይገባውም ማለቱ አይደለም ፡፡ ይልቁንም በእዋጁ በቁጥር 77 / 5 / ላይ ያልወሰደው የአመት ፈቃድ በጠቅላላ ታስቦ እንዲከፈለው ተደንግጓል ፡፡ በመሆኑም ተጠሪ የጠየቀው የአመት ዕረፍት ክፍያ ሳይቀነስ እንዲከፈለው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ውሣኔውን በማሻሻል ወስኗል ፡፡
አመልካች የከፍተኛ ፍ / ቤት መሠረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ፈጽሟል ሲል አቤቱታ ያቀረበው በዚህ ውሣኔ ሳይ ነው ፡፡ ታህሣሥ 19 ቀን 1996 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ማመልከቻ በውሣኔው መሠረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተሰርቷል ሲል የሚያቀርባቸው ክርክሮችም ፣
የተጠሪ የዓመት ዕረፍት በገንዘብ ተቀይሮ ይከፈለኝ ጥያቄ ከሥራ ከመሰናበታቸው ጥር 30/86 ዓ.ም በፊት የነበረና በተለይም አዋጅ ቁጥር 42/85 ከመውጣቱ በፊት ሰነበረው አዋጅ ቁጥር 64/68 በአንቀጽ 34 / 4 / ከህ - ህ መሠረት ያልተሳለፈ በመሆኑ ሊጠየቅ አይገባም ፡፡ በአዋጅ አንቀጽ 79 / 2-3 / መሠረት ሠራተኛው ጠይቆ ወይም አሠሪው የሥራ ሁኔታ አስገድዶት የተላለፈ ለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የሌለ ከመሆኑም በላይ በዚህ አንቀጽ 79 / 5 / በግልጽ እንደተቀመጠው በሁለቱ ስምምነት የተላለፈ የአመት ዕረፍት ቢኖር እንኳን ከሁለት አመት በላይ ሊራዘም እንደማይችል በግልጽ ሰፍራል ። ተጠሪ በአዋጁ መሠረት የተላለፈ የእመት ዕረፍት ያላቸው ለመሆኑ ያልገለጹ ከመሆኑም በላይ አንቀጽ 79 / 5 / ከሁለት ዓመት በላይ ሊተላለፍ እንደማይችል በግልጽ የደነገገውን ከፍተኛ ፍ / ቤት ባለመቀበል በአዋጅ
አንቀጽ 77 / 5 / ሰሙሉ በገንዘብ ተቀይሮ ይከፈላቸው በማለት የሰጠው
ውሣኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚሉ ናቸው ፡፡
እቤቱታው በሰበር ችሉት እንደታይ ታዛ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥ በታዘዘው መሠረት ሚያዚያ 28 ቀን 1996 ዓ.ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል ፡፡ ሰመልሱም የከፍተኛ ፍ / ቤት ውሣኔ የህግ ስህተት እንደሌለበት በመግለጽ እንዲፀና ጠይቋል ፡፡ አመልካቹም የመልስ መልስ አቅርቧል ፡፡
በዚህ ጉዳይ ተመርምሮ ሊወሰን የሚገባው ዋናው የክርክር ጭብጥ አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ያልተጠቀመበትን የአመት ዕረፍት ቀናት ሁሉ የጊዜ ገደብ ሳይኖረው በገንዝብ ተለውጦ እንዲከፈለው ይገባል ወይ ? የሚለው ሲሆን ተያይዞም የአመት ዕረፍት ሠራተኛው በግልጽ በጽሁፍ ወይም በቃል ካልጠየቀ አሠሪውም በግልጽ እንዲተላለፍ ካልፈቀደ ፍቃዱ እንደተላለፈ አይቆጠርም ፡፡ ወይ ? የሚለው ጭብጥም ይታያል ፡፡
በቅድሚያ ግን አመልካች የተጠሪ የኣመት ዕረፍት በገንዘብ ተቀይሮ ይከፈለኝ ጥያቄ ኣዋጅ ቁ .42 / 85 ከመውጣቱ በፊት የነበረ መብት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 64/68 መሠረት መታየት ይገባዋል ሲል የሚያቀርበውን ክርክር ተመልክተናል ፡፡ ተጠሪ ክሱን ያቀረበው ግንቦት 14 ቀን 1990 ዓ.ም አዋጅ ቁጥር 42/85 በሥራ ላይ እያለ ነው ፡፡ አዋጅ ቁጥር 64/68 ሰአዋጅ ቁጥር 42/85 በአንቀጽ 192 / ሠ / እንደተሻረ ተገልጿል ፡፡ አዋጅ ቁጥር 64/68 በኋለኛው አዋጅ በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆነው በአዋጅ ቁጥር 42/85 በቁጥር 191 እንደተደነገገው አዋጅ ቁጥር 64/68 በሥራ ላይ እያለ ክሱ መታየት ጀምሮ ቢሆን ነበር ፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት የተሻረውን አዋጅ ቁጥር 64/68 ተፈፃሚ ለማድረግ መታየት ያለበት የኋላኛው አዋጅ ሲተካ
ሥራ ላይ ሲውል ጉዳዩ በቀድሞው ኣዋጅ መታየት የጀመረ መሆን አለመሆኑን እንጂ መብቱ የተገኘበትን ጊዜ አይደለም ፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ተጠሪ ክሱን ያቀረበው አዋጅ ቁጥር 42/85 ስሥራ ላይ እያለ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ተፈጻሚ የሚሆነው ይኸው ኣዋጅ ቁ .42 / 85 ነው ፡፡ ስለሆነም አመልካች የእዋጁን ተፈጻሚነት በተመለከተ የሚያቀርበው ተቀባይነት የለውም ፡፡
በመቀጠልም አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ያልተጠቀመበትን
የአመት ዕረፍት ሁሉ ያስጊዜ ገደብ በገንዘብ ተለውጦ ሊከፈለው ይችላል
ይህን ጭብጥ ለመመርመር በቅድሚያ የአመት ፍቃድን ምንነትና አሰፈላጊነት መመልከት ተገቢ ነው ፡፡ በአዋጅ ቁጥር 42/85 ከአንቀጽ 76-78 ካሉት ድንጋጌዎች የአመት ፈቃድ ለሠራተኛ ከክፍያ ጋር የሚሰጥ የሥራ ቀናት የዕረፍት ጊዜ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል ፡፡ በአዋጁ ቁጥር 13 / 4 /
መሠረት ሠራተኛው ለሥራ ብቁ በሆነ የአእምሮና የአካል ሁኔታ በሥራ ላይ መገኘት ይጠበቅበታል ፡፡ የአመት ዕረፍት ከሚሰጥባቸው ምክንያቶች ሠራተኛው ይህን የሚጠበቅበትን ግዴታ ማሟላት እንዲችል ነው ፡፡ በእዋጁ ስለ አመት ፈቃድ የሚናገረው ጠቅላላ ድንጋጌ በአንቀጽ 76 / 2 / ! በአመት ፈቃድ ፋንታ ገንዘብ መክፈል የተከለከለ እንደሆነ ይደነግጋል ፡፡ አንድ ሠራተኛ የአመት ፈቃድ ለማግኘት ያለውን መብት ሰማናቸውም የሚያደርገው ስምምነት ተቀባይነት እንደሌለውም የዚሁ አንቀጽ ንዑስ / 1 / ይደነግጋል ፡፡ ከነዚህ ድንጋጌዎች ገንዘብ የአመት ፈቃድን መተካት እንደማይችል ሠራተኛው የአመት ፈቃዱን ለዕረፍት መጠቀም ያለበት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ሠራተኛው የአመት ፍቃዱን ባልተጠቀመ ቁጥር ፍቃዱ ወደ ገንዘብ ተለውጦ መከፈል እንደሌለበትም ያመላክታል ፡፡
በኩል በዋናነት የአመት ዕረፍት ለሠራተኛ የሚሰጠው ሳይከፋፈል ሲሆን መስጠት ያለበትም ከእያንዳንዱ አመት የአገልግሎት ዘመን በኋላ ሳይጠራቀም ነው ፡፡ /
ቁጥር 77 / 1 / እና 78 / :: ሠራተኛው ተከፋፍሎ እንዲሰጠው ሲጠይቅና አሠሪውም ሲስማማ ለሁለት ተከፍሎ ሊሰጠው ይችላል ፡፡ 79 / 1 / እንዲሁም ሠራተኛው ሲጠይቅና አሠሪውም ሲስማማ በአሠሪውም በኩል የሥራ ሁኔታ ሲያስገድደው የሠራተኛውን የፈቃድ ጊዜ ሊያስተላልፍ ይችላል ፡፡ / አንቀጽ 79 / 1 / እና / 3 / የኣመት ዕረፍትን ከላይ እንደተገለፀው በአሠሪና በሠራተኛው ስምምነት የሚችልበት
ተደርጎለታል ፡፡ ይኸውም በአንቀጽ 79 / 5 / እንደተደነገገው የአመት ፈቃድ ከሚቀጥለው ሁለት አመት በላይ ሊራዘም አይችልም ፡፡ ይህ ድንጋጌ ከሁለት አመት መራዘም በኋላ ሠራተኛው ፍቃዱን የግድ መጠቀም ያለበት መሆኑን
ያመለክታል ፡፡
በመቀጠልም ሠራተኛው በዚህ ሁኔታ ተራዝሞ ያልተጠቀመበትን ፍቃድ ሁሉ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ የጊዜ ገደብ ሳይኖረው በገንዘብ ተለውጦ ሊከፈለው ይችላል ወይ ? ወደሚለው ጭብጥ እንመለሳለን ፡፡ የአመት በገንዘብ ተለወጦ ሊከፈልባቸው የሚችሉ ሁኔታዎች በግልጽ ተቀምጠዋል ፡፡ እነሱም 1 ኛው የሥራ ውሉ ለተቋረጠ ሠራተኛ ሲሆን 2 ኛው ደግሞ በአንቀጽ 8 ዐ እንደተገለፀው አሠሪው በፍቃድ ላይ ያለ ሠራተኛን ጠርቶ ፈቃዱን ሳይጨርስ ሥራውን እንዲቀጥል ካደረገ ነው ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰአንቀጽ 80 / 2 / ሠራተኛው ያልተጠቀመበትን ማለትም የቀረውን የአመት ፈቃድ በገንዘብ ሊከፈለው እንደሚችል ተደንግጓል ፡፡
ለያዝነው ጭብጥ አግባብነት ያለው የሥራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛን በማስመልከት ስለሚፈፀመው የአመት ዕረፍት ክፍያ ነው ፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 7 / 5 / የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ ያልወሰደው የአመት ፈቃድ ታስቦ በገንዘብ እንደሚከፈለው ይደነግጋል ፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው ዕረፍት መሠረት ህሣብ ክፍያ የሚፈፀምበት የዕረፍት ቀናት ማግኘት ቢሆንም የሥራ ውሉ
የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ ግን እንደአላማው በዕረፍቱ ሊጠቀምበት አይችልም ፡፡ በዋናነት የአመት ዕረፍት በገንዘብ እንዲተካ ሕተ ባይፈቅድም በሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛ ግን በዕረፍቱ ፋንታ ገንዘብ እንዲከፈለው በህጉ ተፈቅዷል ፡፡ ይህም የሆነው ከላይ እንደተገለፀው የሥራ ውሉ በመቋረጡ ምክንያት ሠራተኛው በዕረፍቱ ሊጠቀምበት የማይችል በመሆኑ ነው ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ክፍያ የሚፈፀምባቸው የትኞቹ ፍቃዶች ናቸው የሚለውን ነጥብ መመልከቱ ተገቢ ነው ። ከላይ እንደተመለከትነው የአመት ፍቃድ ከሚቀጥለው ሁለት አመት በላይ ሊራዘም እንደማይችል በአንቀጽ 79 / 5 / ተደንግጓል ፡፡ በአንቀጽ 76/14 እና / 2 / ኣንድ ሠራተኛ የኣመት ፈቃዱን ለመተው ስምምነት ማድረግ • እንደማይችል በአመት ፈቃድ ፈንታ ገንዘብ መክፈል የተከለከለ እንደሆነ ተደንግጓል ፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች ተገናዝበው ሲታዩ የአዋጅ አንቀጽ 77 / 5 / የሥራ ውሉ ለተቋረጠ ሠራተኛ እንዲከፈል የፈቀደው የአመት ዕረፍት
ክፍያ ሠራተኛው ሥራ ላይ ቢሆን ኖሮ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ፍቃዶችን
በመቀጠልም የአመት ዕረፍት ሠራተኛው በግልጽ በጽሁፍ ወይም
እንዲተላዕ s ወይም ሊራዘመ የሚችሉና የደረሱ ፍቃዶችን ይጨምራል ፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ከሁለት አመት በላይ የተራዘመ ፍቃዶች በገንዘብ የሚተኩ አይደሉም የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል ፡፡
ሲጠቃለል ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት አንድ ሠራተኛ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ያልተጠቀመበት የኦመት ፍቃድ ክፍያ ሁሉ የጊዜ ገደብ ሳደኖረው በገንዘብ ተቀይሮ ሊከፈለው አይችልም ፡፡ የከፍተኛው ፍ / ቤት ሠራተኛው የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ያልተጠቀመበት የአመት ዕረፍት ሁሉ ያለምንም የጊዜ ወሰን ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሊከፈለው እንደሚችል በመቁጠር የአዋጁ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 77 5 / ን መተርጎሙ የኣመት ፈቃድ አላማንና መሠረተ ሃሣብን ያላገናዘበ በመሆኑ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ፡፡ ሊታረም ይገባል ፡፡ ካልጠየቀ አሠሪውም
እንደተላለፈ ኣይቆጠርም ወይ ? የሚለውን ጭብጥ እንመለከታለን ፡፡ የአዋጁን አንቀጽ 79 / 2 / የኣመት ፈቃድ ሠራተኛው ሲጠይቅና አሠሪውም ሲስማማ ሊተላለፍ እንደሚችል ይደነግጋል ። ለማስተላለፍ የአሠሪውና የሠራተኛው ስምምነት አስፈላጊ ያስገነዝባል ፡፡ ስምምነት በግልጽ ወይም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ሊደረግ ይችላል ። ስምምነት ከአሠራርም ሊታይ ይችላል ። ሠራተኛው በስምምነት እንኳን ሊተወው የማይችል የአመት ዕረፍት በሕግ ተሰጥቶታል ፡፡ ፍቃዱን መብቱም ግዴታውም ነው ፡፡ አሠሪው ኘሮግራም አውጥቶ ለሠራተኛው ፍቃድ መስጠት እንዳለበት የአዋጁ ቁጥር 78 / 2 / ይደነግጋል ፡፡ የአመት ዕረፍትን ለተወሰነ ጊዜ ማራዘም እንደሚቻል ከላይ በ 1 ኛው ጭብጥ ተመልክተናል ፡፡ እንግዲህ ሠራተኛው መውሰድ ባለበት ጊዜ ሳይወስድ ሲቀር አሠሪውም ሳይሰጠው ሥራውን እንዲቀጥል ቢያደርግ ከአሠራራቸው ፍቃዱን ለማራዘም የተስማሙ መሆኑን መረዳት ይቻላል ፡፡ ስምምነቱም ፍቃዱ
ፍቃዱ በሕግ እንዲራዘም እስከተፈቀደ ጊዜ ድረስ ብቻ እንደተደረገ ሊቆጠር ይገባል ፡፡
ሲጠቃለል ፍቃድን ስለማስተላለፍ የሚደነግገው ኣዋጁ ድንጋጌ The / አንቀጽ ca / 9la ፍቋድን i ለማስተላለፍ w ኦሪውና ca ሠራተኛው hi መስማማት
አለባቸው የሚለው ክርክሩ ተቀባይነት የለውም " , ያለባቸው መሆነን ቢያስገነዝብም ስምምነታቸው ግን ግዴታ በግልጽ መሆን እንደሚገባው የግልጽነት ፎርማሊቲን እንዲያሟላ አያስገድድም ፡፡ ስምምነት መኖሩን ደግሞ አሠራር መረደት ይቻላል ፡፡ በመሆኑም አመልካች ፍቃድ ተላልፏል ለማለት አሠሪውና
አሠሪውና ሠራተኛው የግድ መስማማት
ው ሣ ኔ 1. ተጠሪ ወደ ገንዘብ ተለውጦ እንዲከፈለው የጠየቀው የአመት
ዕረፍት ቀናት ክፍያ ሁሉም ሊከፈለው አይገባም ፡፡ 2. ተጠሪ የ 1984 የ 1985 እና የ 1986 ከሥራ እስከተሰናበተበት
እስከ ጥር 30 ድረስ ያለው የአመት ዕረፍት በገንዘብ ተቀይሮ
እንዲከፈለው ። 3. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በሥራ ክርክር መዝገብ
ቁጥር 1438 ነሐሴ 16 ቀን 1994 ዓ.ም እንዲሁም የከፍተኛ ፍ / ቤት በመዝገብ ቁጥር 15313 ህዳር 25 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጡት ውሣኔ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ .348 / 1 / መሠረት ተሻሽሎ ተወስኗል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?