ነጋሪት ጋዜጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር፳፫ / ፲፱፻ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳ / ፲፱፻፲ ዓም የኢትዮጵያ የስብሰባ ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ .. ገጽ ፮፻፶፯ የኢትዮጵያ የስብሰባ ማዕከልን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጸሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርእስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የስብሰባ ማዕከል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር / ፲፱፻፶ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡ ፪ መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ የስብሰባ ማዕከል ( ከዚህ በኋላ “ ማዕከሉ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግ ሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ የማዕከሉ ተጠሪነት ለማስታውቂያና ባህል ሚኒስቴር ( ከዚህ በኋላ “ ሚኒስቴሩ ” እየተባለ የሚጠራ ) ይሆናል ። ፫ ዋና መሥሪያ ቤት የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ውስጥ ይሆናል ። ፬ ዓላማ የማዕከሉ ዓላማ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጥበባዊ ሥራዎ ችን በማስተናገድ በመካከላቸው መተዋወቅና መቀራረብ እንዲኖር ማድረግ ይሆናል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፴ሺ፩ ገጽ ፮፻፶፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ታህሣሥ ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : ፭ ሥልጣንና ተግባር ማዕከሉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ሕብረተሰቡን ሊያስተምሩና ሊያዝናኑ የሚችሉ ባሕላዊና ዘመናዊ የሥነ ጥበብ ሥራዎች ማቅረቢያ መድረክ በመሆን ማገልገል፡ ፪ . ልዩ ልዩ አካላት በተለይም የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ለአባሎቻቸውና ለሌሎችም ተሳታፊዎች የሚያ ዘጋጁዋቸውን ስብሰባዎች፡ ሴሚናሮችና ወርክሾፖች ማስተ ፫ የሕገ መንግሥቱን ዕንሰ ሀሳቦች በልዩ ልዩ መንገዶችለሕዝብ ማስተማሪያ መድረክ በመሆን ማገልገል፡ ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ለሕዝብ የሚቀርቡ ዝግጅቶችን ማስተናገድ ። ፮ . የማዕከሉ አመራር ማዕከሉ፡ ፩ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ እና ፪ . አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ዋናው ሥራ አስኪያጅ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ሚኒስቴሩ በሚሠጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የማዕከ ሉን ሥራዎች ይመራል፡ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፣ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የማዕከሉን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የማዕከሉን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋ ጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ሐ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች ተከትሎ ሚኒስቴሩ በሚያፀድቀው መመሪያ መሠረት የማዕከሉን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ መ ) ለማዕከሉ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ማዕከሉን ይወክላል፡ ረ ) የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ ሪፖርት ኣዘጋ ጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለማዕከሉ ሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለማዕከሉ ሌሎችኃላፊዎ ችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ሆኖም እርሱ በማይኖር ጊዜ ተክቶ እንዲሠራ የሚወከለው ሰው ከ፴ ቀናት ለበለጠ ጊዜ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው በቅድሚያ ለሚኒስቴሩ ቀርቦ መፈቀድ አለበት ። ፰ በጀት የማዕከሉ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የሚውጣጣ ይሆናል፡ ፩ . ማዕከሉ ከሚሠጠው ማናቸውም አገልግሎት ከሚያገኘው ፪ ከፌዴራሉ መንግሥት ከሚሰጥ ድጎማ፡ እና ፫ : በእርዳታ ከሚገኝ ገቢ ። ፱ . ስለሂሣብ መዛግብት ፩ ማዕከሉ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይ ገጽ ፮፻፶፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ታህሣሥ ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓም : ፪ • የማዕከሉ የሂሣብ መዛግብቶችና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲ ስለሚተላለፍ ንብረት ከሕገ መንግሥት ኮሚሽንና ከሕገ መንግሥት ጉባዔ የተላለፈለት ንብረት የማዕከሉ ንብረት ይሆናል ። ፲፩ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፲ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት