×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፫፻፳/፲፱፻፲፭ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፳፪ አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ኣዋጅ ቁጥር ፫፻፰ ፲፱፻፲፭ ዓም የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ባለሥልጣንን ማቋቋሚያ አዋጅ ገጽ ፪ሺ፫፻፳፭ አዋጅ ቁጥር ፫፻፮ / ፲፱፻፶፭ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለተፋጠነ ሀገራዊ የፖለቲካ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የሚኖረውን ከፍተኛ ድርሻ ፈር በያዘና ውጤታማ በሆነ አቅጣጫ በመምራት መጠቀም | getic and systematic use of Information and Communication አስፈላጊ በመሆኑ ፣ የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂን የዕድገት ፍጥነት ፣ ባህሪና ሽፋንን ያገናዘበና በመስኩ የጥምረት ገጽታ ላይ የተመ ሀረተ ሀገራዊ ዕድገት እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንደ አንድ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍጎልብቶ በአገርና በዓለም አቀፍእንቅስቃሴ ተወዳዳሪ የጥራት ደረጃ እንዲኖረው የተቀናጀ እርምጃ በመውሰድ ዕድገቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ በማስፈለጉ ፣ ከላይ የተገለጹትን ዓላማዎች ለማሳካትና በአገር አቀፍደረጃ የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትን ለማፋጠን በኃላ | responsible government organ , in order to fulfill the above ፊነት የሚያስፈጽም መንግሥታዊ አካልን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ | mentioned objective and accelerate national information በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ of the constitution of Federal Democratic Republic of ምንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ያንዱዋጋ 30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ቼል ገጽ ፪ሺ፫፻፳፮ ፌዴራል ቁጥር ፳፪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕሰ ይህ ኣዋጅ “ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፰ ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፦ ፩ . “ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤት ” ማለት የፌዴራልና የክልል የመንግሥት ፣ በእነዚህ ሥር ተጠሪ የሆኑ አካላትና አዲስ አበባ መስተዳድር እንዲሁም የድሬዳዋ ካውንስልን የሚያጠቃልል ነው ፣ ፪ “ ዳታ ” ማለት በቀጥታ ከመስክ ወይም ከመነሻው የተሰበሰበ ፣ ገና ያልተተነተነ ዓይነተኛ ትርጉም ያልተ ሰጠው ለጠቀሜታ ሊውል የሚችል የመረጃ ምንጭ ነው ፣ ፫ . “ መረጃ ” ማለት ከዕውቀት ወይም ከጥሬዳታ የሚመነጭ በድምጽ ፣ በጽሑፍ ፣ በምስል ወይም ከሦስቱ በሁለቱ ወይም በሁሉም ቅንጅት ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚው የሚቀ ርብና ጥቅም ላይ የሚውል ሀብት ነው ፣ ፬ . “ የመጀመሪያ ደረጃ ዳታ ” ማለት ፌዴራላዊ ፣ ክልላዊ ወይም ክፍለ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን የሚያንፀባርቅና ከመነሻው የሚሰበሰብ ዳታ ነው ፣ ፭ “ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ” ማለት ዳታን ወይም መረጃን ለማሰባሰብ ፣ ለማጠናቀር ፣ ለመተንተን ፣ ለማሠራጨት ፣ ፈልጎ ለማግኘትና ጠብቆ ለማቆየት የሚያገለግል ቴክኖለጂና ሥርዓት ነው ፣ ፮ “ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኢንዱ ስትሪ ” ማለት ከኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ በማንኛውም ሰው ወይም ተቋም የሚከ የማምረት የማልማት ወይም አገልግሎት የመስጠት የንግድ እንቅስቃሴ ወይም ሥራ ነው ፣ ፯ . “ የኮምፒዩተር መረብ ” ማለት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች መካከል ኮምፒዩተሮችን ዕርስ በርስ በማገናኘት ሥርዓቱ በሚፈ ቅደው ቴክኖሎጂ መሠረት ዳታ ወይም መረጃን የማስተ ላለፍ ፣ የማቀናጀት ወይም አገልግሎት የመስጠት ሥርዓት ነው ፣ ፰ “ አፕሊኬሽን ” ማለት አንድን ተግባር ወይም ሥራ በኮምፒዩተር ለማጠናቀር የሚያስችል የኮምፒዩተር ፕሮግራም ነው ፣ ፱ . “ ዶሜይን ኔም ” ማለት በኢንተርኔት ላይ አንድን ተቋም ወይም ተመሳሳይ አካሉ ለመለየት የሚያስችል ለተቋም ወይም ለተመሳሳይ አካል የሚሰጥ ስም ነው ፣ ፲ . “ ካንትሪ ኮድ ቶፕ ሌቭል ዶሜይን ” ማለት አንድን ተቋም ወይም ተመሳሳይ አካልን በኢንተርኔት ላይ ለመለየት ከተሰጠ ስም ቀጥሎ በአህፅሮት የሚቀመጥ ተቀጥላ ነው ፣ ፲፩ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ጓጽ ፪ሺ፫፻፳፯ ቁጥር ፳፪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፭ ክፍል ሁለት ፫ መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ ባለሥልጣኑ እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ፣ ፪ . ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለኣቅም ግንባታ ሚኒስቴር ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ አዲስ ኣበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱም በክልሎች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊያቋቁም ይችላል ፡ ፭ ዓላማ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአገሪቱን ማኅበ ራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲሁም የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታን ለማፋጠን በሚያግዝ መልክ በጥቅም ላይ ማዋል ነው ። ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፦ ፩ . የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፖሊሲ ፣ ስትራቴጂ ፣ ሕጐችና መመሪያዎች እንዲቀ ረጹና እንዲሻሻሉ በጥናት ላይ የተመረኮዘ ሀሳብ ያቀርባል ፣ ሲጸድቅም በተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል ፣ ፪ . በዚህ ቴክኖሎጂ ኣጠቃቀም ምክንያት ሊመጡ የሚችሉ ሀገራዊ የደህንነት ችግሮችን ከመቋቋምና ከማስወገድ ኣንፃር ምክርና ድጋፍ ለሚመለከታቸው አካላት ይሰጣል ፤ የማኅበረሰብና የግለሰብ ሕገ መንግሥታዊ መብቶች በቴክኖሎጂው ምክንያት እንዳይደፈሩ የተጠ ቃሚዎች ደህንነት ሊጠበቅ የሚችልበትንም ሁኔታ ያመቻቻል ፣ ፫ . የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፖሊሲን በብቃት ለማስፈጸም የሚያስችል አቅም በተቋማት እንዲገነባ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ሲፈቀድም ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል ፣ መረጃን ለመሰብሰብ ፣ ለማከማቸት ለማጠናቀር ለመተን ተንና ለማሠራጨት የሚያስችል እንዲሁም ጥራቱ ፣ ደህንነቱና አስተማማኝነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አንድ ወጥ አሠራር ( Standard ) ያወጣል ፣ በሥራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል ፣ ፭ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከሚገኙ የመረጃ ምርቶች ፣ አገልግሎቶችና አጠቃቀ ማቸው ጋር የተያያዙ ተግባራትን ለማፋጠንና ለማቀ ላጠፍ የሚያስችሉ ሕጐች እንዲወጡ ያደርጋል ፤ ሲወጡም መተግበራቸውን ይቆጣጠራል ፣ በመንግሥታዊ ተቋማት የመረጃ ሥርዓትን ከመገንባትና ከማቀናጀት አንፃር የመንግሥት የዶሜይን ስም ( Government domain name ) ይደለድላል ፣ አድራሻ ይሠጣል፡ ይመዘግባል ፡ ይቆጣጠራል ፡ ገጽ 3 ሺ፫፻፳፰ ፌዴራል ቁጥር ፳፪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፶፭ ዓ • ም • የአገሪቱን የከፍተኛውን ደረጃ መለያ ዶሜይን ስም | 7 . Coordinate all stake holders for the creation and proper የአስተዳደር ሥርዓት እንዲፈጠርና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚመለከታቸውን ያስተባብራል ፣ ለአፈፃ ፀሙም እገዛ ያደርጋል ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ እን ዲያድግ ምቹ ሁኔታዎችን ይቀይሳል ፣ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል ፣ ፱ መረጃ በተፋጠነ መልክና በተመጣጠነ ወጪ ማግኘት ስለሚቻልበት ሁኔታ ጥናቶችን ያካሂዳል ፣ የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባል ፣ ሲፀደቅም ተግባራዊነቱን ይከታተላል ፣ በፌደራልና በክልል መንግሥታት ተቋማት መካከል እንዲሁም የፌዴራልም ሆነ የክልል ተቋማት ውስጥ ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን መረብ መዘርጋቱን ይከታተላል ፣ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል ፣ ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል ፣ ፲፩ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም በተናጠል እየተደረጉ የሚገኙ ወይም ወደፊት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ውጤቶች በተሻለና በሀገራዊ ደረጃ ተቀናጅተው የበለጠ ጥቅም ሊሰጡእንዲችሉ የሚያደርግ ሥርዓት ይዘረጋል ፣ ፲፪ • ለሕዝብ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ያተኮሩ መሠረታዊ ሲስተሞችና አገልግሎቶች በኮምፒዩተር የተደገፉ እንዲ ሆኑና ደረጃ በደረጃም ለተጠቃሚዎች በቀጥታ አገል ግሎት ሊሰጡ በሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸታቸውን | 13. Assist in identifying the role of the private sector and ያረጋግጣል ፣ ፲፫ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፣ አጠቃ ቀምና ዕድገት ረገድ የግል ዘርፍና የሌሎች ተዋናይ አካላት ሚና በግልጽ እንዲታወቅና ከመንግሥታዊ ተቋማት ጋር ሊኖር የሚገባው የጋራ የአሠራር ሥርዓት እንዲጠናከር እገዛ ያደርጋል ፣ ፲፬ . የአገሪቱን ልማት ለማፋጠን የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒ ኬሽን ቴክኖሎጂ በኢኮኖሚ ዘርፎች የልማት ፕሮግ ራሞች ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ያደርጋል ፣ ፲፭ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትን አስመ ልክቶ ተገቢውን መረጃ መከታተል ፣ ማሰባሰብና መተንተን የሚያስችል ሥርዓትና አገራዊ አቅም ይገነባል ። ፲፮ በሥራ ላይ የሚገኙትንና ወደፊትም በሥራ ላይ የሚውሉ የኮምፒዩተር መረቦችና አፕሊኬሽኖች ከቴክኒክና አሠራር አኳያ መቀናጀትና መናበብ መቻላቸውን ያረጋ ግጣል ፣ ፲፯ . የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ወደ ኅብረተሰቡ ሰርጾ ጥቅም እንዲሰጥ በየደረጃው የማስተ ዋወቅ ሥራ ይሠራል ፣ ፲፰ አገራዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትን በማስረጽ ውጤታማ አስተዋጽኦ ለሚያስመ ዘግቡ ተቋማትና ባለሙያዎች ሽልማት ይሰጣል ፣ በሂደቱም ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ ዝግጅቶችን ያስተባብራል ፣ ፲፱ በመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የተቀናጀ የኢንፎ | 19. Give training , advice on project administration and ርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረግ ሂደትን ለማፋጠን ሥልጠና ፣ የፕሮ ጀክት አስተዳደርና አፈጻጸም ምክር ይሰጣል ፣ መመሪያ ያወጣል ፣ ስለአፈጻጸሙ ክትትል ያደርጋል ፣ ገጽ፻፳፬ ፌዴራል ቁጥር ፳፪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱ : ፲፭ዓም : ፳ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን ዕድገትና የውጤቱን ደረጃ ለመለካት የሚያስችሉ የመመዘኛ መሥፈርቶችን በየጊዜው ያዘጋጃል ፣ ለዚህ የሚያስፈልጉ ዳታዎችን በመሰብሰብ ይተነትናል ፣ ፳፩ . በመንግሥታዊ ተቋማት መካከል የተቀናጀ ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰትና እንዲኖር ያማክራል ፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ ስለመዋሉይከታተላል ፣ በየጊዜውም የቴክኖሎጂውን ዕድገት በማጣጣም እንዲ ሻሻል ሃሳብ ያቀርባል ፣ ፳፪ • የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ በዓይነት በብዛትና በጥራት ለማፍራት ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች እንዲነደፉና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል ፣ ፳፫ . የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ወደ ኅብረተሰብ በማስረጽ ላይ የሚያተኩሩ ምርምርና ልማት ሥራዎችን ያስተባብራል ፣ ድጋፍ ይሰጣል ፣ ፳፬ . የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም ደጋፊ ቴክኖሎጂዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር ብቃታቸውን ያረጋግጣል ፣ ፳፭ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሀገራዊ ልማት ጥረት ውስጥ የግል ክፍለ ኢኮኖሚውን ተሳትፎ ለማጎ ልበት የሚያስችሉ የፕሮጀክት ሀሳቦችን ያመነጫል ፣ ያዘጋጃል ፣ ፳፮ የመጀመሪያደረጃ ዳታ አሰባሰብ ፣ አተናተንናሥርጭትን የሚያግዝ የአሠራር ሥርዓት መኖሩን ያረጋግጣል ፣ ፳፯ • የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፣ በራሱ ስም ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፣ ፳፰ : ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንደአስፈላጊነቱ የአገል ግሎት ክፍያ ይሰበስባል ፣ ፳፱ : ዓላማውን ከግብ ለማድረስና ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች አስፈላጊ ተግባሮችን ያከናውናል ። የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፦ ፩ ብሔራዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ልማት አማካሪ አካል ፣ ፪ • በአቅም ግንባታ ሚኒስቴር አቅራቢነት በመንግሥት አንድ ዳይሬክተር ጄኔራል እና ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራሎች እና ፫ አስፈላጊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ብሔራዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት አማካሪ አካል ፩ ተጠሪነቱ ለአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ሆኖ ብሔራዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት አማካሪ አካል ( ከዚህ በኋላ “ አማካሪ አካሉ ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ፣ ፪ • አማካሪ አካሉ ከሰባት ያላነሱ በአቅም ግንባታ ሚኒስቴር አቅራቢነት በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ፬ . የአማካሪ አካሉ ሥልጣንና ተግባር አማካሪ ኣካሉ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፣ ፩ ከሀገራዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፖሊሲ የሚመነጩ የአጭር ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፕሮግ ራሞችና ሥልቶች ላይ የውሣኔ ሃሳብ ያቀርባል ፣ ገጽ ፪ሺ፫፻፴ ቁጥር ፳፪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ • ም • ፪ . በዳይሬክተር ጄኔራሉ የሚቀርቡ ረቂቅ ሃሳቦችን በመገ ምገም አዳብሮ ለውሳኔ እንዲቀርብ ያደርጋል ፣ ፫ በዳይሬክተር ጄኔራሉ የሚቀርቡ ረቂቅ ሕጎችንና መመሪ ያዎችን ይገመግማል ፣ ለውሳኔ ለሚመለከተው የመን ግሥት አካል ያቀርባል ፣ በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት የተገኙት ውጤቶችን ይገመግማል ፣ ስለ ኣሠራሩ የራሱን የውስጥ ደንብ ያወጣል ፣ ፤ ስብሰባ ፩ አማካሪ አካሉ በስድስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፣ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የስብሰባው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ፣ ፪ • ከአማካሪ ኣካሉ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይኖራል ፣ ፫ የአማካሪ አካሉ ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፣ ሆኖም ድምጹ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። በዚህ አንቀጽ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ አማካሪ አካሉ የራሱን የስብሰባ ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፩ . ስለዳይሬክተር ጄኔራሉ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ተጠሪነቱ ለአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ሆኖ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የባለሥልጣኑን ተግባራት ይመራል ፣ ያስተዳ ድራል ፣ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ። ህ ) በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፮ የተመለከተው የባለሥል “ ጣኑን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የባለሥል ጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የባለሥልጣኑን ፕሮግራምና ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፣ ባለሥልጣኑ በተፈቀደለት ፕሮግራምመሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሀ ) ባለሥልጣኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደር ጋቸው ግንኙነቶች ባለሥልጣኑን ይወክላል ፣ ረ ) ስለባለሥልጣኑ እንቅስቃሴ ያቀርባል ፣ ሰ ) በማይኖርበት ጊዜ ከምክትል ዳይሬክተር ጄኔራሎቹ ውስጥ አንዱን ይወክላል ፣ ፲፪ የምክትል ዳይሬክተር ጄኔራሎቹ ሥልጣንና ተግባር ፩ ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራሎች ተጠሪነታቸው ለዳይሬ ክተር ጄኔራሉ ይሆናል ፣ ፪ : በዳይሬክተር ጄኔራሉ ተለይተው በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ተግባራት ያከናውናሉ ፣ ፫ • ዳይሬክተር ጄኔራሉ በማይኖርበት ጊዜ በሚሰጠው ውክልና መሠረት እሱን በመተካት የባለሥልጣኑን ተግባራት ያከናውናሉ ፣ ገጽሺ፫፻፴፩ ፌዴራል ቁጥር ፳፪ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፫ • በጀት የባለሥልጣኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፣ ፩ . ከመንግሥት ከሚመደብ በጀት ፣ ባለሥልጣኑ ከሚሰበስበው የአገልግሎት ክፍያ እና ፫ ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገቢ ፣ ፲፬ . ስለሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆነ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ፣ ፪ . የባለሥልጣኑ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሠነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፭ የቅንጅት ግዴታ ፩ . ማንኛውም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆነ መሥሪያ ቤት በባለሥልጣኑ አስተባባሪነት የኢንፎር ሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን በሚመለከት ለሀገራዊ አገልግሎት እንዲውሉ ተዘጋጅተው የፀደቁትን መመሪ ያዎች ፣ ደንቦች ፣ ሕጎችና ቅንጅታዊ የአሠራር ሂደቶችን የመከተል ግዴታ አለበት ፣ ፪ . ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊነቱንና ግዴታውን ለመወጣት የሚያከናውናቸው መሠረታዊ ተግባራት በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲታገዙ የተዘጋጁ የአሠራር ሥርዓት ዕቅዶችን ወይም ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሂደት ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶች ለባለሥልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ። ሀገራዊ ቅንጅትን በተመለከተ የግል ድርጅቶች ፣ መንግ ሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ስለሚኖራቸው ግዴታ በሕግ ይወስናል ፣ ፲፮ : የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ለዚህ አዋጅ አለበት ። የመተባበር ግዴታ ፲፯ : ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ በሥራ ላይ የሚያስችል ደንብ የማውጣት ሥልጣን ይኖረዋል ። ፲፰ ተፈፃሚነት የማይኖረው ሕግ የኢትዮጵያ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፯ / ፲፱፻፷፯ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃ ሚነት አይኖረውም ። የመሸጋገሪያ ድንጋጌ በኢትዮጵያ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ብሔራዊ የኮምፒ ዩተርና ኢንፎርሜሽን ማዕከል ሲሠሩ የነበሩ ሥራዎችና ኃላፊነቶች ወደ ባለሥልጣኑ ተዛውረዋል ። አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ- ሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?