×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 21913

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ 21918
ቀን 25/9/98
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ነ / ፈጅ ቀርቧል
መልስ ሰጭ፡- አቶ ገነነ ታደሰ ቀርቧል ፡፡
ፍ ር ድ
ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ
ቦርድን ስልጣን የሚመለከት ነው ፡፡
በመ / ሰጭ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ክሱ የቀረበው በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ላሉት
ሠራተኞች የተሰጠው ደረጃ ይሰጠኝ በሚል ነው ፡፡ አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ አሰሪና
ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ክሱን ለማየት ሥልጣን አለው በማለት የተሰጠ ነው ፡፡
አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ
ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ / ሰጭ መልሱን
አቅርቧል ፡፡
ችሎቱም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የሥራ ክርክሮች ምን አይነት
ናቸው የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበለትን ውሣኔ
አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝቦ መርምሯል ፡፡
ፌዴራ፩ በነች ። ጎር❖ ክት
ትክክል ጎራ ! ”
የሥራ ክርክር ኦ ኦ ር ♥
ይህ ችሎት በመ / ቁ . 18180 አግባብነት ያላቸውን የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ
ድንጋጌዎች በመተርጎም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን
የተሰጠው የውል የሥራ ክርክር ጉዳዮችን ነው ፤ አንድ የሥራ ክርክር የወል የሥራ
ክርክር ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም
ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፤ በአንፃሩ አንድ የሥራ
ክርክር የወል ሳይሆን የግል የሥራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት
በተከራካሪው ሠራተኛ / ሠራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ ሲገኝ ነው በማለት
- የሕግ ትርጉም ሰጥቷል ።
መ / ሰጭ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ላሉት
ሠራተኞች የተሰጠው ደረጃ ይሰጠኝ በሚል ያቀረበው ክስ የጋራ በሆነ የሠራተኞች
መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል
በመሆኑም ጉዳዩን ለማየት በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
ቦርድ ስልጣን አለው
የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት
ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመ.ቁ. 67/02/95 የካቲት 1 ቀን
1997 ዓ / ም የሰጠው ውሣኔና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ / ቁ . 37573
የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
ፌደራል ስነቅላይ ፍርድ ቤት
ትነነቱ ግል
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?