የፌዴራል ነጋሪትጋዜጣ ' ' የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክረሲያዊ ሪፐብሊክ እራተኛ ዓመት ቁጥር ፵፬ አዲስ አበባ - ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር / ፲፱፻፲ ዓም የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ( ማሻሻያ ) ደንብ ገጽ ፯፻፵፰ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፮ / ፲፱፻፲ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብን ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው | Duties of the Executive Organs of the Federal Democratic አዋጅ ቁጥር ፴፮ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በኢንቨስትመንት አዋጅ | Republic of Ethiopia Proclamation No. 4/1995 and Article 9 ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፴፰ ( እንደተሻሻለ ) አንቀጽ ፱ መሠረት ይህን ደንብ | of the Investment Proclamation No. 37/1996 ( as amended ) . አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ( ማሻሻያ ) ደንብ ቁጥር ፴፮ / ፲፱፻፶ ” ተብሎሊጠቀስ ይችላል ። ፪ ማሻሻያ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር፯ / ፲፱፻፷፰ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፤ ፩ . የደንቡ አንቀጽ፮ንዑስ አንቀጽ ( ፪ተራፊደል ( ሀ ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ተራ ፊደል ( ሀ ) ተተክቷል ፤ ሀ ) ካፒታሉ እስከ ብር ጀሚሊዮን ሲሆን ሆኖም ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ፕሮጀክቱ የተመ ደበው የኢንቨስትመንትካፒታል የድርጅቱን ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ካፒታል ቢያንስ ወደ ብር ፪፻፶ሺህ ከፍማድረግ አለበት ” ፪ የደንቡ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አኝቀጽ ( ፪ ) ፣ ( ፪ ) እና ( W ተሠርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፩ ) ተተክተዋል ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፯፻፵፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፲ ዓም “ ፬ • ማናቸውም የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቅዳል ። ሆኖም ከውጭ የሚገቡትን ሊተኩ የሚችሉ የካፒታል ዕቃዎችና መሣሪያዎች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ከሆነ ከውጭ የሚገቡት ከቀረጥ ነፃ ሆነው እንዳይገቡ ቦርዱ በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ ሊያግድ ይችላል ። ፭ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆኖ የገባ ማናቸውም ዕቃ ሊከፈልበት ይገባ የነበረው የጉምሩክ ቀረጥ አስቀድሞ ሳይከፈልበት የቀረጥ ነፃ መብት ለሌለው ሰው ሊተላለፍ አይችልም ። ” ፫ • ከደንቡ አንቀጽ ፳፪ በኋላ የሚከተሉት አዲስ አንቀጾች ፳፫፡ ፳፬፡ ፳፭፡ ፳፩ እና ፳፯ ተጨምረዋል ፣ “ ፳፫ ለመከላከያ ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፫ ( እንደተሻሻለ ) የተደነ ገገው ለመከላከያ ኢንዱስትሪም ተፈጻሚ ይሆናል ። ፳፬ . ለኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች ለኢንዱስትሪ መንደር የሚያስፈልጉ መሣሪያ ዎችና ዕቃዎች እንዲሁም በቀጥታ ለኢንዱ ስትሪ መንደር ሕንፃ ግንባታ የሚያገለግሉ በሀገር ውስጥ የማይመረቱ መሣሪያዎችናማቴሪ ያሎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፳፭ : ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎትኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚያስፈልጉ ቋሚ መሣሪያዎችና ዕቃዎች በዋጋ ከ፲፭ % ከማይበልጥ የመለዋወጫ ዕቃዎቻቸው ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነውእንዲገቡይፈቀዳል ። ፳፮ ለምርምርና ስርዐት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች ለምርምርና ስርፀት ኢንቨስትመንት የሚያስ ፈልጉ ቋሚ ዕቃዎችና መሣሪያዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ፳፯ ለካፒታል ዕቃዎች ኪራይ አገልግሎት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፭፡ ፲፰ - ፳፪ የተመለከ ቱትን እንዲሁም ለማዕድንና ለፔትሮሊየም ሥራዎች እንደ ካፒታል ዕቃ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ለኪራይ አገልግሎት ለማዋል ከጉምሩክ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል ። ” ፬ . የደንቡ አንቀጽ ፳፫፡ ፳፬ እና ፳፭ እንደ ቅደም ተከተ ላቸው አንቀጽ ፳፰፡ ፳፬ እና ፴ ሆነዋል ። ፭ በደንቡ ሠንጠረዥ አንድ ተራ ፊደል “ መ ” ሥር የሚከተሉት አዲስ ተራ ቁጥር ፬ እና ፲፩ ተጨምረዋል ፤ “ ቧ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ( 2927 ) ፣ ፲፩- የኢንዱስትሪ መንደር ( 7010 ) ። ” ፮ በደንቡ ሠንጠረዥ አንድ ሥር የሚከተሉት አዲስ ተራ ፊደል “ ረ ” ፣ “ ሰ ” : “ ሸ ” እና “ ቀ ” ተጨምረዋል ፤ “ ረ ) የቴሌኰሙኒኬሽን አገልግሎት ( 6420 ) ፣ ሰ ) ምርምርና ስርዐት ( 7310 ፣ 7320 ) ። ” ገጽ ፯፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ሸ ) ትምህርት ፩ . ጠቅላላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ( 80210 ) ፪ የሁለተኛ ደረጃ የቴክኒክና የሙያ ትምህርት ፫ ከፍተኛ ትምህርት ( 80300 ) ቀ ) ጤና ፩ ሆስፒታሎች ( 85110 ) ( ከአዲስ አበባ ውጭ ፪ የዲያግኖስቲክስ ማዕከሎች ( 85190 ) ( ከአዲስ አበባ ውጭ ሲሆን ) ” ፯ . የደንቡ ሠንጠረዥ ሁለትተራፊደል “ ረ ” ተራቁጥር፫ ፣ ፬ እና ፭ ተሠርዘዋል ። ፰ የደንቡ ሠንጠረዥ ሁለት ተራ ፊደል “ ሰ ” ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ተራ ፊደል “ ሰ ” ተተክቷል ፤ ፩ • ሆስፒታሎች ( 85110 ) ( አዲስ አበባ ውስጥ ፪ የጤና ጣቢያዎች ( 85120 ) ፫ . የዲያግኖስቲክ የምርመራ ማዕከሎች ( 85190 ) ( በአዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን ) ፬ . ክሊኒኮች ( 85120 ) ” ፱ በደንቡ ሠንጠረዥ ሦስት ሥር የሚከተለው አዲስ ተራ ፊደል “ ሰ ” ተጨምሯል ፤ “ ሰ ) የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት ( 7112 7113 ፣ ፫ : ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፵ ዓ.ም. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር