, አቤቱታ መነሻነት ነው ። ተጠሪ በሥር ክሱ
የሰ / መ / ቁ 12380
ጥቅምት 16 ቀን 1999
1.ከር የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ህዳር 27 ቀን 1994
ዳኞች፡ 1. አቶ ከማል በድሪ
ፍስሐ ወርቅነህ ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች የግብርና ምርት ማሣደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት ተጠሪ አቶ ጀማል አሕመድ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ።
ፍ ር ድ
ለጉዳዩ መነሻ የሆነው
ለፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት ጽፎ ባቀረበው
በአመልካች መ / ቤት ውስጥ በጫኝነትና አውራጅነት ሥራ ከ 1974 እስከ 1994 መስከረም
ወር ድረስ ለሥራ መደቡ ለተያዘው ቦታ ብር 1000 እየተከፈለው የሰራ መሆኑን ገልጾ
ያለምንም ጥፋትና ማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉ በሕገወጥ መንገድ የተቋረጠ መሆኑን ገልጾ
ወደ ሥራ እንዲመለስ ወይም ውዝፍ ደሞዝ ፣ ካሣ ፣ የስንብት ክፍያ ፣ የማስጠንቀቂያ ክፍያ
የዓመት ዕረፍት ክፍያ ፣ የ 17 ዓመታት የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲከፈለው ጠይቋል ፡፡
የአሁኑ አመልካች በበኩሉ ተጠሪ እንደማንኛውም ወዛደር የመጫንና የማውረድ ሥራ
እየተጠራ ከሚሰራ በስተቀር ከድርጅቱ ጋር የፈጠረው የሥራ ውል የለም :: የሥራ
ውል በሌለበት ሁኔታ ውሉ ተቋርጧል ማለት አይቻልም ብሏል ። ጉዳዩ የቀረበለት ፍ / ቤት
የቀረቡትን ምስክሮች ከሰማ በኋላ የአሁኑ አመልካች የሥር ከሣሽ ሥራ ባለ ጊዜ ብቻ
እየተጠራ ይሰራል ያለውን ባለመቀበል በግራ ቀ , መካከል የሥራ ውል አለ በማለት
ደምድሞ የስራ ውሉ በሕገወጥ መንገድ ተቋርጧል በማለት የሥር ከሣሽ የጠየቀውን
መዝገቡ ለሰበር ይቀርባል በማለት ወቦ ' .
ጠቅላላ የዕረፍትና በበዓላት ቀናት ክፍያ ፣ ካሣና የሥንብት ክፍያ እንዲከፈለው ወስኗል ።
የፌ / ከፍ / ፍ / ቤትም ውሣኔን አጽንቶታል ፡፡
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ላይ የቀረበ ሲሆን አመልካች በሰበር
ቅሬታ ማመልከቻው የሥር ፍ / ቤት ሕጉ ከሚፈቅደው ውጭ የአሁኑ ተጠሪ ቋሚ ሠራተኛ
ነው በማለት ወስኖ ከ 1977
1994 ድረስ ያለ የዓመት ዕረፍትና የሕዝብ በዓላት ክፍያ
ይከፈል መባሉ ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል ፡፡ የአሁኑ አመልካች የሰበር ቅሬታ ማመልከቻውን
ባቀረበም ጊዜ የአሁኑ ተጠሪ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በመሆን ቀደም ሲል በተመሣሣይ
ሁኔታ የቋሚነት ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ የተደረገ መሆኑን የሚያሣይ የውሣኔ ግልባጭ አያይዞ
አቅርቧል ፡፡
ይህ የሰበር ችሎት ግንቦት 12 ቀን 1996 በዋለው ችሎት ተጠሪ በሥር አቅርቦት
የነበረው ክስ በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 5 መሠረት ውድቅ ሊደረግ ይገባል ወይስ አይገባም ?
አሁን በድጋሚ ክፍያ ይከፈለው
ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር
የግራ ቀን የጽሁፍ ክርክር መርምሯል ፡፡
የአሁኑ ተጠሪ ሰኔ 15 ቀን 1996 መልስ የሰጠ ሲሆን አመልካች በበኩሉ ክርክሩን
አጠናክሮ የመልስ መልስ አቅርቧል ፡፡
በዚህ ጉዳይ ከፍ ሲል እንደተገለፀው በዋንኛነት ታይቶ ሊወሰን የሚገባው ጭብጥ
የአሁኑ ተጠሪ ክርክር በፍ / ሕ / ሥ / ሥ / ቁ 5 መሠረት ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል ? ወይስ
አይገባም ? የሚለው ይሆናል ፡፡
በመሠረቱ በዚህ ጉዳይ ቀደም ሲል የአሁኑ ተጠሪ ከሌሎች በተመሣሣይ የሥራ
መስክ ከተሰማሩ ሠራተኞች ጋር በመሆን ሐምሌ 11 ቀን 1980 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ
የቋሚ እንሁን ጥያቄ ለሥራ ክርክር ኮሚቴ አቅርበው የነበረ መሆኑን ፤ በወቅቱ ጉዳዩ
ተመርምሮ ቋሚ ሊሆኑ አይገባም ተብሎ ተወስኖ የነበረ መሆኑን ፤ በመቀጠል በሽግግሩ
ወቅት ተቋቁሞ ለነበረው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአዲስ መልክ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ውሃ
ሣይሰጥበት ኮሚቴው በመፍረሱ ጉዳዩ ለግልግል ዳኛ ተመርቶ የነበረ መሆኑንና ቋሚ
ሠራተኞች ሊሆኑ ይገባል ተብሎ በመወሰኑን በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀ ይቻቻሉ ፣ ቀርቦ ታህሣሥ 25 ቀን 1993 ዓም ቁጥር 572/84 በሆነ የሥራ ክርክር ይግባኝ መዝገብ ሠራተኞቹ
የተሰጠው የፍ / ሕ / ሥ / ሥ /
ቁን የሚተላለፍ ነው በማለት ውሣው ውድቅ መደረጉን ከሥር ክርክሩ ለመረዳት ችለናል ።
ይህ በዚህ እንዳለ የአሁኑ ተጠሪ በጉዳዩ ላይ ቀደም ሲል ሥልጣን ባለው አካል ውሣኔ እንዳልተሰጠ በማስመሰል በድጋሚ ኅዳር 27 ቀን 1994 ዓ.ም አዲስ ክስ በማቅረብ ተወስኖ እንዲፀና የተደረገው ውሣኔ የፍ / ሕ / ሥ / ሥ / ቁ 5 የሚቃረን መሠረታዊ የሕግ ሥህተት ነው ብለናል ፡፡
ው ሣ ኔ - የፌ / መጀመሪያ ደ / ፍ / ቤት ግንቦት 25 ቀን 1995 በመ / ቁ 01644 ውሣ
እና የፌ / ከፍ / ቤት በመ / ቁ 21507 በ 23.10.95 የሰጡዋቸው ውሣኔዎች ተሽረዋል ፣ - የዚህን ፍ / ቤት
- መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
You must login to view the entire document.