×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፲፱፻፶፭ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፵ አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ የኢትዮጵያ ዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳ / ፲፱፻፲፭ ዓም የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ ገጽ ፪ሺ፩፻፳፰ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፲፱፻፲፭ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ አእምሯዊ ንብረትን የሚገዙ ብሔራዊ ሕጎችን የሚያስ ፈጽም ወይም ተፈፃሚነታቸውን የሚከታተል እንዲሁም አስፈላ ጊውን አቅም በመገንባት ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት | implementation of national laws governing intellectual የሚሰጥ መንግሥታዊ አካል ማቋቋም በማስፈለጉ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ ትርጓሜ ፩ . “ አእምሯዊ ንብረት ” ማለት የሰው ልጅ አእምሮ ውጤት | 2. Definition በሆኑ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ያለ ሕጋዊ መብት ሲሆን ፓተንትን ፤ የንግድ ምልክትን ፣ የምስክር ወረቀትንና ኮፒራ ይትን ይጨምራል ። ፪ “ ፓተንት ” ማለት የፈጠራ ሥራን ለማስጠበቅ የሚሰጥ መብት ሲሆን በፈጠራ ፣ በአነስተኛ ፈጠራና በኢንዱስት ሪያዊ ንድፍአዋጅቁጥር ፩፻፳፫ / ፲፱፻፷፯መሠረት በፈጠራ ፣ በአነስተኛ ፈጠራና በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ የሚሰጠውን የአስገቢ ፓተንት ፣ የግልጋሎት ሞዴል ምስክር ወረቀትና የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ የምዝገባ የምስክር ወረቀትን ይጨምራል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ሺ፩፻፳፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፫ . “ የንግድ ምልክት ” ማለት አንድን ምርት ወይም አገል ግሎት ከተመሳሳይ ምርት ወይም አገልግሎት ለመለየት የሚያስችል ምልክት ወይም የምልክቶች ቅንጅት ነው ። ምልክቶቹ ፊደላት ፣ ቃላት ፣ ቁጥሮች ፣ ምስሎችና የቀለሞች ቅንጅት ወይም የተዘረዘሩት ምልክቶች ማንኛውም ቅንጅት ሊሆን ይችላል ። ፬ . “ ኮፒ ራይት ” ማለት እንደ ሥነ ጽሑፍና ኪነ ጥበብ ባሉ ሥራዎች ላይ ያለ መብት ሲሆን አጎራባች መብትንም ይጨምራል ። ፭ “ ኣጎራባች መብት ” ማለት ከዋኞች ፤ የቀረፀ ድምጽና የኦዲቪዥዋል አሳታሚዎች የብሮድካስቲንግ ኬብል አሰራጪዎች በሥራዎቻቸው ላይ ያላቸው መብት ነው ። ፫ • መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በኋላ “ ጽሕፈት ቤት ” እየተባለ የሚጠራ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው መንግሥታዊ አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ጽሕፈት ቤቱ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ይሆናል ። ዋናው መሥሪያ ቤት የጽሕፈት ቤቱ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈ ላጊነቱ ድሬዳዋን ጨምሮ በክልሎች ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊኖሩት ይችላል ። ፭ የጽሕፈት ቤቱ ዓላማዎች ጽሕፈት ቤቱ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ዋና ዋና ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ ፩ አእምሯዊ ንብረት በቂ የሕግ ጥበቃ የሚያገኝበትንና በአገር ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፤ ፪ . በፓተንት ሰነዶች የታቀፉ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ማሰባሰብ ፣ ማደራጀት ፣ ማሰራጨትና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማበረታታት ፣ ፫ • የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲዎችን ህጎችን ማጥናት ፣ መተ ንተንና ለመንግሥት ሃሳብ ማቅረብ ፣ ፬ • በሕዝቡ ዘንድ የአእምሯዊ ንብረት እውቀትና ግንዛቤ እንዲዳብር ማድረግ ። ፮ የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባራት ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉትን ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፩ • የፓተንትና የንግድ ምልክት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማመልከቻዎችን በመቀበል አግባብ ባለው ሕግ መሠረት አስፈላጊውን ምርመራ በማካሄድ ወይም እንዲካሄድ በማድረግ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ፣ ፪ : በሕጋዊ ሰነድ ጥበቃ የተደረገላቸውን የውጭና የአገር ውስጥ የፈጠራ ሥራዎችን በጥቅም ላይ መዋላቸውን መከታተል ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የግዴታ ፈቃድ መስጠት ፣ ፫ • የፓተንት ማመልከቻ ከመቅረቡ ወይም ቴክኒካዊ ችግሮችን ለመፍታት ምርምር ከመደረጉ በፊት በመስኩ የተሰሩተመሳሳይየፈጠራ ሥራዎች መኖራቸውን ለማረ ጋገጥ የፍለጋ መጠይቆችን መቀበል ፤ የፍለጋ አገልግሎት መስጠት ፤ ፬ የንግድ ምልክት ማመልከቻዎች ከመቅረባቸው በፊት ቀደም ሲል ተመሳሳይ ምልክቶች አለመመዝገባቸውን ለማረጋገጥ የፍለጋ መጠይቆችን መቀበል ፤ የፍለጋ አገል ግሎት መስጠት ፤ ፭ የአእምሮአዊ ንብረት መብቶች ማተምና ማሠራጨት ፣ ገጽ ፪ሺ፩፻፴ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 9 መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፭ ዓ.ም ፮ • የአእምሯዊ ንብረት መብቶችን የሚመለከት የመረጃ መፍጠርና ለተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ፣ ፯ መንግሥት የሚያወጣቸው የአእምሯዊ አዋጆችና ደንቦች ሥራ ላይ ማዋል ፤ ፭ በቅድሚያየትኩረት መስኮች በፓተንት ሰነዶች የታቀፉ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን መምረጥና ማሰራጨት እንዲሁም ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲውሉ ማበረታታት ፤ ፱ የፓተንትና የንግድ ምልክት የጥበቃ ጊዜ ማራዘምና የእድሳት ማመልከቻዎችን መቀበል መሰብሰብና ማደራጀት ፤ በሕግ መሠረት ውሳኔ መስጠት ፤ ፲ በሕዝቡ ዘንድ የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ ለመፍጠርና ለማጠናከር ሰፊና የተቀናጀ የአህዝቦት ስልት መቀየስና ሥራ ላይ ማዋል ፤ ፲፩ በአእምሯዊ ንብረት ጉዳዮችና ጭብጦች ላይ ጥናቶች ማካሄድ ፣ በብሄራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ በአእምሯዊ ንብረት መስክ ያሉትን እድገቶች መከታተል የሕግና የፖሊሲ ሃሳቦችን ኣዘጋጅቶ ለመንግሥት ማቅረብ ፤ ፲፪ የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲዎችንና ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ሥራላይማዋል እና / ወይም ሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል ፣ ፲፫ በአእምሯዊ ንብረት ጉዳዮች ላይ ለሕዝብ ፣ ለመንግሥት ፣ ለግል ድርጅቶችና የሙያ ማኅበራት እንዲሁም ለግለ ሰቦች የምክር አገልግሎት መስጠት ፤ ፲፬ . የፈጠራ ሠራተኞች ፣ የደራሲያን ፣ የሙዚቀኞችና መሰል ማኅበራት እንዲቋቋሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፣ ማኅበ ራቱን መደገፍና ማጠናከር ፣ ፲፭ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤቶችንና የፈጠራ ሥራቸውን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚሹ ባለሃብቶችን ለማገናኘት የሚረዱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፣ ፲፮ • ከሌሎች የውጪ አገር ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የእእ ምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤቶች ጋር ግንኙነትና ትብብር መፍጠር ፣ ፲፯ • ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ ማስከፈል ፣ ፲፰ የንብረት ባለቤት መሆንና ውል መዋዋል ፣ ፲፱ • በራሱ ስም የመክሰስና መከሰስ ፣ ፳ ዓላማውን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ። ፯ የጽሕፈት ቤቱ አቋም ጽሕፈት ቤቱ ፤ ፩ ብሔራዊ የአእምሯዊ ንብረት ምክር ቤት ከዚህ በኋላ “ ምክር ቤት ” እየተባለ የሚጠራ ፪ በመንግሥት የሚሾም አንድ ዳይሬክተር ጄኔራል እና ፫ አስፈላጊ ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የምክር ቤቱ አባላት የምክር ቤቱ ሰብሳሲና አባላት በመንግሥት ይሰየማሉ ። ፱ የምክር ቤቱ ሥልጣንና ተግባራት ምክር ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ ለመንግሥት በሚቀርቡ የፖሊሲ ሃሳቦች ላይ ጽሕፈት ቤቱን ማማከር ፤ ፪ በጽሕፈት ቤቱ ተዘጋጅተው በሚቀርቡ መመሪያዎች ፣ ፕሮግራሞች እና የአፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ ማማከር ፫ በዳይሬክተርጄኔራሉ በሚቀርቡ የጽሕፈት ቤቱ አስተዳደር እና አመራር በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ማማከር እና ፬ የራሱን የአሠራር ደንብ ማውጣት ። - ኅኖች የተውጣጣ ጽ ፳፩ ራል ቁጥር ፲ መጋቢት ፴ደ፵፭ዓም ፤ የምክር ቤቱ ስብሰባ ፩ ምክር ቤቱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ይኖረዋል ። ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባሄ ይሆናል ። ፫ ምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርበው በተባበረ ድምፅ ይሆናል ። የተባበረ ድምፅ ከሌለ በድምፅ ብልጫ የውሳኔ ሃሳብ ይተላለፋል ። የድምጽ አሰጣጡ እኩል በእኩል የተከፈለ ሲሆን ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፲፩ የጻይሬክተር ጄኔራል ሥልጣንና ተግባር ፩ ዳይሬክተር ጀኔራሉ የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆን ጽሕፈት ቤቱን የማስተዳደርና ሥራውንም የመምራትኃላፊነት አለበት ። ፪ ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተውን አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ፣ ሀ ) በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ሠራተኞችን ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ለ ) የጽሕፈት ቤቱን የአጭር ፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅዶች አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ። ሐ ) የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፣ እንዲሁም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል ፣ መ ) ለጽሕፈት ቤቱ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪያደርጋል ሠ ) ጽሕፈት ቤቱ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ሁሉ ጽሕፈት ቤቱን ይወክላል ። ፫ ዳይሬክተርጄኔራሉተግባሩን በከፊል ለሌሎችየጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል ። ፲ በጀት የጽሕፈት ቤቱ በጀት ከሚከተሉትን ሀ ) ከፌዴራል መንግሥቱ የሚመደብ ድጎማ ፣ ለ ) ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ እና ሐ ) ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገቢ ። ፪ ጽሕፈት ቤቱ የሚያገኘውን ገቢ በአገሪቱ የፋይናንስ ሕግና ደንብ መሠረት ሥራ ላይ ያውላል ። ፲፫ • የሂሳብ መዛግብት ፩ የጽሕፈት ቤቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ፣ ፪ የጽሕፈት ቤቱ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ • የመተባበር ግዴታ ማናቸውም ሰው ወይም መንግሥታዊ ወይም የግል ድርጅት ወይም ተቋም ለጽሕፈት ቤቱ ሥራ አፈፃፀም የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፲፭ ተፈፃሚነት የማይኖራቸው ህጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ህጎች በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም ። ጽ 1 ራል ነጋሪት ቁጥር 9 • ጋቢት ። ፲ን መብትና ግዴታን ስለማስተላለፍ በዚህ አዋጅ እና በአዋጅ ቁጥር / ፲፰ ፓተንትና የመሳሰሉትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን የተሰጠውን መብትና ግዴታ ፪ ከንግድ ምልክት ጋር በተያያዘ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያሉ አግባብነት ያላቸው ሰነዶችና መመሪ ፫ በአዋጅ ቁጥር ፩፻፷፮ / ፲፱፵፩ ኮፒራይትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መፃሕፍት ድርጅት ያለው መብትና ግዴታ፡ ለጽሕፈት ቤቱ ተላልፋል ። ፲፯ . የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ጽሕፈት ቤቱ የንግድ ምልክት ማመልከቻን የመቀበልና የማስተናገድ ተግባራትን የንግድ ምልክት ሕግ እስኪወጣ ድረስ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ይጠቀምበት በነበረው መመሪያ መሠረት ያከናውናል ። ፲፰ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከመጋቢት ፴ ቀን ፲፭ ዓም ጀምሮ የፀና | 18. Effective Date ይሆናል ። አዲስ አበባ መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላምቀ S ርትታት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?