የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፮ አዲስ አበባ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፸፫ / ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. የቅድመ ጭነት ምርመራ ሥርዓት ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፲፭ ያ , t ጃ እና አዋጅ ቁጥር ፩፻፸፫ / ፲፱፻፲፩ የቅድመ ጭነት ምርመራ ሥርዓት ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ወደአገር ውስጥ ለሚገቡ ዕቃዎች ለተከፈለው የውጭ ምንዛሪ ተመጣጣኝ የሆነ ዕቃ መገኘቱን ማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡ ለንግዱ እንቅስቃሴ ፈጣንና አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር የጉምሩክ ፎርማሊቲን አፈጸጸም ሥርዓት በቅድመ ጭነት ምርመራ | ditions for trade activities it has become necessary to assist መርዳት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት፡ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ዓይነት፡ ጥራት፡ . ብዛት በግዢው ውል በተዘረዘረው መሠረት መሆኑን ዕቃው with the specifications in the sales contract before they are ከመጫኑ በፊት ማረጋገጥ ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ የሚያጋጥመውን | shipped helps to avoid controversies that might arise after ውጣ ውረድ በማስቀረት ዕቃዎች በተፈለገው ጊዜ ሥራ ላይ | payment has been effected thereby facilitating the immediate እንዲውሉ የሚያስችል መሆኑን በመረዳት፡ የዕቃዎችን ዋጋ በማሳነስ በመንግሥት ገቢ ላይ የሚፈጠ ረውን ችግር ለማስወገድ የቅድመ ጭነት ምርመራ አጋዥ prevent loss of government revenue that might arise as a result ስለሚሆን ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የቅድመ ጭነት ምርመራ ሥርዓት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፪፫ / ፲፱የን፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ “ ኩባንያ ” ማለት ከመንግሥት ጋር በሚደረግ ውል ወደ ኢትዮጵያ ጉምሩክ ክልል በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የቅድመ ጭነት ምርመራ የሚያደርግ ድርጅት ነው ፣ ፪ “ የጉምሩክ ክልል ” ማለት የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሠራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰ / ፳፬ አንቀጽ ፪፱ ) የተመለከተው ነው ፣ ፫ “ ዕቃ ” ማለት ማናቸውም ሸቀጥ ሲሆን፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተዘረዘሩትን አይጨምርም ፤ . ፬ “ ውል ” ማለት የቅድመ ጭነት ምርመራ አገልግሎት ለማግኘት በመንግሥትና በኩባንያውመካከል የሚደረግ ውል ነው ፣ ፭ “ የተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት ” ማለት ኩባንያው የቅድመ ጭነት ምርመራ ካካሄደ በኋላ የምርመራው ውጤት አጥጋቢ ስለመሆኑ የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ነው ፣ ፮ . “ ድርድር የማይደረግበት የምርመራ ግኝት ሪፖርት ” ማለት ኩባንያው የቅድመ ጭነት ምርመራ ካካሄደ በኋላ የምርመራው ውጤት አጥጋቢ ስላለመሆኑ ለላኪው የሚሰጠው ሰነድ ነው፡ ፯ . “ ቦርድ ” ማለት የፌዴራሉ ገቢዎች ቦርድ ነው ፣ ፰ “ ንግድ ባንክ ” ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈቅዶለት የሚሠራ የግል ወይም የመንግሥት ንግድ ባንክ ነው ። ፫ . የተፈጻሚነት ወሰን በዚህ አዋጅ መሠረት የሚደረገው የቅድመ ጭነት ምርመራ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ በልዩ ሁኔታ ከተመለከቱት በስተቀር በማናቸውም ወደ ኢትዮጵያ ጉምሩክ ክልል በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ሁሉ ተፈጸሚ ይሆናል ። ፬ • የቅድመ ጭነት ምርመራ ግዴታ ስለመሆኑ ፩ . ማናቸውም ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ ዕቃ በማጓጓዣ ላይ ከመጫኑበፊት የቅድመ ጭነት ምርመራ ይደረግበታል ። ስለሆነም ማናቸውም አስመጪ ወይም ዕቃዎችን ወደ ኢትዮጵያ የሚልክ ሰው ወይም ድርጅት የቅድመ ጭነት ምርመራ የተደረገ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም ዕቃው የሚጫንበት አገር የቅድመ ጭነት ምርመራ የሚካሄድበትን ሥርዓት በሚመለከት የተለየ ሕግ ያለው ሲሆን፡ የምርመራው አፈጻጸም የዚያን አገር ሕግ የሚከተል ይሆናል ። ፭ የቅድመ ጭነት ምርመራ ሽፋን ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ዕቃ ላይ የሚደረገው የቅድመ ጭነት ምርመራ የዕቃውን፡ ፩ . ዋጋ እና የምንዛሪውን ተመን ትክክለኛነት፡ ፪ ጥራት፡ ፫ ብዛት፡ ፬ . የአስተሻሸግ ሁኔታ፡ ፭ የታሪፍ ምደባ፡ የሚመለከት ይሆናል ። ፮ ልዩ ሁኔታዎች በአንቀጽ ፬ መሠረት የሚደረገው የቅድመ ጭነት ምርመራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በተመለከተ በሚከተሉት ልዩ ሁኔታዎች የሚፈጸም ይሆናል፡ ገጽ ፩ሺ፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ፩ • ዕቃዎች ወርቅ፡ የከበሩ ማዕድናት፡ የኪነጥበብ ውጤቶች ድፍድፍ ዘይት እና የተጣራ ፔትሮልየም ፈንጂዎች ርችቶችእና የእነዚሁ ውጤቶች ጥይቶች፡ የጦር መሣሪ ያዎች፡ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሌሎች ዕቃዎች የቁም እንስሳት፡ ትኩስ እና የቀዘቀዙ ፍራፍ ሬዎች፡ አትክልት፡ ዓሣና ሥጋ ፣ ትኩስ ዕንቁላል ፣ ውዳቂ ብረታ ብረቶች ወቅታዊ ጋዜጣዎች እና መጽሔቶች ማዳበሪያ፡ ያገለገለ ተሽከርካሪን ጨምሮ የቤት ውስጥ እና የግል መገልገያ ዕቃዎች በፖስታ ቤት በኩል የሚመጡ ጥቅሎች ወይም የንግድ ናሙናዎች የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግባቸውም ። በፕሮፎርማ ኢንቮይስ ላይ የተመለከተው የኤፍኦቢ ዋጋቸው ፪ሺ የአሜሪካን ዶላር እና ከዚያ በታች የሆኑ ዕቃዎች የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግባቸውም ። ለ ) በአንድ የግዢ ትዕዛዝ ተገዝተው ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች ተከፋፍለው የሚላኩ ሲሆን በእያንዳንዱ ክፍልፋይ ፕሮፍርማ ላይ የተመለ ከተው የኤፍኦቢ ዋጋ ፪ሺ የአሜሪካን ዶላርእና ከዚያ በታች ቢሆንም የቅድመ ጭነት ምርመራ ይደረግበታል ። ቦርዱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለ ከተውን የገንዘብ መጠን ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደርግ ይችላል ። ልዩ ልዩ ፩ : ከዚህ በታች የተመለከቱት የቅድመ ጭነት ምርመራ አይደረግባቸውም ፤ ሀ ) የዲፕሉማቲክና የኮንሱላር ሚሲዮኖች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዩ አካላት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡዋቸው ለሥራቸው የሚያስፈልጓቸው ዕቃዎች ፤ ለ ) በእርዳታ የተገኙ ማናቸውም ዕቃዎች ። ፪ ቦርዱበቂምክንያት ሲያገኝ በዚህ አንቀጽ በልዩ ሁኔታ የተመለከቱትን ዕቃዎች ዓይነት ወይም የቅድመ ጭነት ምርመራውን አፈጻጸም በሚመ ለከት የተለየ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ። በሌተር ኦፍ ክሬዲት ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ሊከተሉት የሚገባው የአፈጻጸም ሥርዓት ፩ አስመጪው ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲከፈትለት የሚያ 17 . Procedures for Importation of Goods Though The ቀርበው ማመልከቻ የዕቃውን ዓይነት ጥራት፡ ብዛት የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ የማስጫኛው ወጪ የዕቃው ዋጋ አንዱ ክፍል ከሆነ የዕቃው መነሻ የሆነውን አገር የሚያመለክት መሆን አለበት ። ሌተር ኦፍ ክሬዲት የሚከፍተው ባንክ የሚከተሉትን ተጨማሪ ሁኔታዎች፡ ሀ ) ዕቃዎቹ የቅድመ ጭነት ምርመራ የሚመለከ ታቸው መሆኑን ፣ ለ ) አስመጪው የሌተር ኦፍክሬዲት ተቀባይ ለሆነው ሰው ወይም ድርጅት ዕቃዎቹ የቅድመ ጭነት ሊደረግባቸው የሚገባ ስለመሆኑ በደብዳቤ ወይም በቴሌክስ ማስታወቅ እንደሚ ሐ ) የሌተር ኦፍ ክሬዲቱ ተቀባይ የቅድመ ጭነት ምርመራ እንዲያካሂድ ለኩባንያው አመቺ ሁኔታ የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለበት 5 ) ሌተር ኦፍ ክሬዲት የሚከፍተው ባንክ ክፍያ የሚፈጽመው የመጨረሻ መጠየቂያ ሰነድ እና በኩባንያው ወይም በወኪሎቹየተረጋገጠና የተሟላየምርመራግኝት ሲደርሰው እንደሆነ ፤ በሌተር ኦፍ ክሬዲቱ ውስጥ ማመልከት አለበት ። ገጽ ፩ሺ፲፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም • ፫ • በኢትዮጵያ የሚገኘው የኩባንያው አገናኝ ጽ / ቤት ሌተር ኦፍ ክሬዲቱን እና የሻጩን የፕሮፎርማ ሰነድ ቅጂ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከሚከፍተው ባንክ ይወስዳል ። ፬ • የኩባንያው አገናኝ ጽ / ቤት የሌተር ኦፍ ክሬዲቱን ቅጂ መዝግቦ ወደ አገር የሚገባ የታዘዘ ዕቃ ስለመኖሩ ማስታወቂያ ለአስመጪው እና ሽያጩ በተከናወነበት አገር ለሚገኘው የኩባንያው ጽ / ቤት ይልካል ። ፭ ሽያጩ በተከናወነበት አገር የሚገኘው የኩባንያው ጽ / ቤት የምርመራ ማስታወቂያ ለዕቃው አጓዥ ፣ ለላኪው ወይም ለሻጩ ይልካል ። ፮ : ሻጩ ምርመራው ከሚካሔድበት ሰባት ቀን ቀደም ብሎ ምርመራው የሚካሔድበትን ቀንና ቦታ ለኩባ ንያው ጽ / ቤት ያስታውቃል ፤ አግባብ ያላቸውን ሰነዶችም ይልካል ። ፯ : ከዚህ በላይ የተመለከተው ቢኖርም ሻጩ ወደ አገር የሚገባ የታዘዘ ዕቃ ስለመኖሩ ማስታወቂያ ከመድረሱ በፊት የኩባንያው ጽ / ቤት በዕቃዎች ላይ ምርመራ እንዲያደርግ ሊጠይቅ ይችላል ፣ ይሁን እንጂ ማስታወ ቂያው ከመድረሱ በፊት በተደረገ ምርመራ የተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት ሊሰጥ አይችልም ። ፰ የኩባንያው ጽ / ቤት በዕቃዎች ላይ አካላዊ ምርመራ ያደርጋል ። በዚህም ምርመራ አማካኝነት የታሪፍ ምደባውን ፣ የዕቃውን ዋጋ እና ሌሎችም የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ ክፍል የሆኑ ወጪዎች ዕቃው በሚላክበት አገር ለውጪ ገበያ ለሚቀርቡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ከሚጠየቀው የገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ መሆኑን ወይም ተፈጻሚሊሆን እስከቻለ ድረስ ከዓለም የገበያ ዋጋ ጋር የሚቀራረብ መሆኑን ፤ እንዲሁም የዕቃው ጥራት እና ብዛት በግዥው ውል መሠረት እና በኢትዮጵያ ሕጎች የተመለከተውን የሚያሟላ መሆኑን ያረጋግጣል ። ፱ የኩባንያው ጽ / ቤት በምርመራው አጥጋቢ ውጤት ሲያገኝ የተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት ለሻጩ ይሰጣል ። ፲ ሻጩ ከኩባንያው ጽ / ቤት የተሰጠውን የተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት እና የመጨረሻ የክፍያ መጠየቂያ ሰነዱን ሌተር ኦፍ ክሬዲቱ ለደረሰው ባንክ ይሰጣል፡ ባንኩም ይህንኑ ሰነድ ሌተር ኦፍ ክሬዲቱን ለከፈተው ባንክ ይልካል ። ፰ : ከሌተር ኦፍ ክሬዲት ውጪ ወደ አገር ስለሚገቡ ዕቃዎች | 8. Procedures for Importation ofGoods Effected Withouta የቅድመ ጭነት ምርመራ አፈጻጸም ሥርዓት ከሌተር ኦፍ ክሬዲት ውጪ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች የሚከተሉትን የአፈጸጸም ሥርዓቶች ይከተላሉ ፤ ፩ አስመጪው ወደአገር ለማስገባት የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች የሚያሳይ ዝርዝር ከሻጩ የፕሮፎርማ ሰነድ ጋር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይሰጣል ። እነዚህ ሰነዶች የሚከተሉትን መረጃዎች የያዙ መሆን አለባቸው ፣ ሀ ) የአስመጪውን ስምና አድራሻ ለ ) የተሟላ የምርመራ ግኝት የሚሰጠውን ባንክ ፤ ግዥው የተፈጸመበትን ገንዘብ ዓይነት መ ) ጠቅላላ ወጪ እና የነጠላ ዋጋ ፤ ዕቃው የተላከው ሻጩ ከሚገኝበት አገር ውጪ ከሆነ ይህንኑ፡ ረ ) የሻጩን ስምና አድራሻ ሰ ) የዕቃውን ዓይነት፡ ጥራትና ብዛት ፤ የማስጫኛውን ወጪ ። ፪ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት መረጃዎችዕቃው ከሚጭንበት ፲፭ ቀን ቀደም ብሎ ለብሔራዊ ባንክ መድረስ አለባቸው ። ፫ ሻጩ ወይም ላኪው ዕቃዎቹ በኩባንያውእንዲመረመሩ አስፈላጊውን ማመቻቸት ማድረግ እንደሚገባቸው አስመጪው አስቀድሞ ሊያሳውቃቸው ይገባል ። ገጽ ፩ሺ፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም : ፩ በኢትዮጵያ የሚገኘው የኩባንያው አገናኝ ጽ / ቤት | 4 ) The Liaison Office shall collect the information men በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተዘረዘሩትን መረጃዎችከብሔራዊ ባንክ በመውሰድሽያጩ በሚከና ወንበት አገር ለሚገኘው የኩባንያውጽ / ቤትእናለሻጩ ወይም ለላኪው ወደአገር የሚገባ የታዘዘ ዕቃ ስለመኖሩ ማስታወቂያ ይልካል ። ፭ ሽያጩ በተከናወነበት አገር የሚገኘው የኩባንያው ጽ / ቤት የምርመራማስታወቂያ ለሻጩ ወይም ለላኪው ይልካል ። ሻጩ ወይም ላኪው ምርመራው ከሚካሄድበት ሰባት ቀን ቀደም ብሎ ምርመራው የሚካሄድበትን ቀንና ቦታ ለኩባንያው ጽ / ቤት ያስታውቃል ፤ አግባብ ያላቸውን ሰነዶችም ይልካል ። ፯ የኩባንያው ጽ / ቤት በዕቃዎች ላይ አካላዊ ምርመራ ያደርጋል ። በዚህም ምርመራ አማካኝነት የታሪፍ ምደባውን ፤ የዕቃው ዋጋ እና ሌሎች የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ ክፍል የሆኑ ወጪዎች ዕቃው በሚላክበት አገር ለውጭ ገበያ ለሚቀርቡ ተመሳሳይ ዕቃዎች ከሚጠየቀው የገበያ ዋጋጋርተቀራራቢ መሆኑን ወይም ተፈጻሚ ሊሆን እስከቻለ ድረስ ከዓለም የገበያ ዋጋ ጋር የሚቀራረብ መሆኑን ፣ እንዲሁም የዕቃው ጥራት እና ብዛት በግዥው ውል መሠረት መሆኑን ያረጋግጣል ። ፰ የኩባንያው ጽ / ቤት በምርመራው አጥጋቢ ውጤት ሲያገኝ የተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት ለሻጩ ወይም ለላኪው ይሰጣል ። ፱ ተጨማሪ የአፈጻጸም ሥርዓቶች ፩ . በማናቸውም መንገድ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች ሊከተሉት የሚገባው ተጨማሪ የአፈጸጸም ሥርዓት በኩባንያው እና በመንግሥት መካከል በሚደረገው ውል ይወሰናል ። ፪ በሌተር ኦፍክሬዲት ወይም ከሌተር ኦፍክሬዲት ውጪ ወደሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ሊከተሉት የሚገባውዝርዝር የአፈጻጸም ሥርዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያ ወጣው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ይወሰናል ። ፲ ኃላፊነት ፩ ሻጩ በግዥው ውል ካሉበት ምርመራ ምክንያት ነጻ አይሆንም ። ፪ የቅድመ ጭነት ምርመራ መደረጉ አስመጪው ወደአገር ውስጥ ስለሚገቡ ዕቃዎች በሌሎች ሕጐች የተጣለበትን ግዴታ የሚያስቀር ወይም ግዴታውን እንደተወጣ የሚያስ ቆጥር አይሆንም ። ፲፩ : የጉምሩክ ፎርማሊቲ አፈጸጸም ፩ . በዚህ አዋጅ መሠረትየቅድመጭነትቃርመራለሚደረ ግባቸው ዕቃዎች የተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት የምስክር ወረቀት ሳይደርስ የጉምሩክ ፎርማሊቲ ለመፈጸም ዲክላራሲዮን አይሞላም፡ ፪ የተሟላ የምርምራ ግኝት ሪፖርት የምስክር ወረቀት ሳይኖራቸው ወደ አገር የገቡ ዕቃዎች በጉምሩክ ባለሥ ልጣን ቁጥጥር ሥር ውለው በጉምሩክ አዋጅ መሠረት ተገቢው ይፈጸምባቸዋል ። ፫ በተሟላ የምርመራ ግኝት ሪፖርት ላይ የተመለከተው የዕቃዎች ዋጋ፡ የኢንሹራንስ አረቦን እና ለማጓጓዣ የተከፈለው ወጪ ድምር የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ለመወሰን መሠረት ይሆናል ። ፲፪ በኩባንያው እና በመንግሥት መካከል ስለሚደረግ ውል በኩባንያው እና በመንግሥት መካከል የሚደረገው ውል በዚህ ሳይወሰን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መያዝ አለበት ፤ ' .ዴታዎች በቅድመ ጭነት ገጽ ፩ሺ፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ፩ የቅድመ ጭነት ምርመራ የሚደረግበትን ዝርዝር የአፈ ጻጸም ሥርዓት፡ ኩባንያው ለሚሰጠው የቅድመ ጭነት ምርመራ አገል ግሎት የተመረመረውን ዕቃ የአፍኦቢ ዋጋ መሠረት በማድረግ በመንግሥት የሚከፈለውን በድርድር የሚወሰን የምርመራ ዋጋ ፤ • የኩባንያው የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ የሚፈጸምበትን መንገድ ፤ ፬ • የኩባንያው ሪፖርት ይዘት ምን መሆን እንዳለበትና በምን ያህል ጊዜ እንደሚቀርብ ፤ ፭ ኩባንያው ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ ባይወጣ የሚኖርበትን ተጠያቂነት ፣ የምርመራው ውጤት አጥጋቢ በማይሆንበት ጊዜ ስለሚሰጥ ድርድር የማይደረግበት የምርመራ ግኝት ሪፖርት፡ ፯ ውሉ ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ ። ፲፫ የውል አስተዳደር በኩባንያው እና በመንግሥት መካከል የሚደረገውን ውል መንግሥትን በመወከል የሚፈርመው እና የውሉን አስተ ዳደር የሚመራው የፌዴራል ገቢዎች ቦርድ ይሆናል ። ፩ የቅድመ ጭነት ምርመራ ተደርጐባቸው ወደአገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ አስመጪው ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በተጨማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወሰን የማስከፈያ ልክ ለጉምሩክ ባለሥልጣን የአገልግሎት ዋጋ ይከፍላል ። የአገልግሎት ዋጋው የሚሰላው በጉምሩክ የመቅረጫ ዋጋ ላይ ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተነገረው ቢኖርም የፌዴራል ገቢዎች ቦርድ በቂ ምክንያት ሲያገኝ አስመጪው ከአገልግሉት ዋጋ ክፍያ በሙሉ ወይም ፲፭ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ በከፊል ነጻ እንዲሆን ሊፈቅድ ይችላ c መራ | 15 . Transitory Povisions ፩ . በዚህ አዋጅ የተመለከተው የቅድመ ጭነት ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ ከጸናበት ቀን ጀምሮ ሌተር ኦፍክሬዲት ለሚከፈትላቸው ዕቃዎችይሆናል ። ይህ አዋጅ ከጸናበት ቀን በፊት የሌተር ኦፍ ክሬዲት የተከፈተላቸው ዕቃዎች የቅድመ ጭነት ምርመራ አይመለከታቸውም ። ይሁን እንጂ አዋጁ የሚጸናበት ቀን እና ከዚያም በኋላ በሌተር ኦፍክሬዲቱ ላይማሻሻያ የተደረገ እንደሆነ ዕቃዎቹ የቅድመ ጭነት ምርመራ ይደረግባቸዋል ። ፪ ከሌተር ኦፍክሬዲት ውጪ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎችን በሚመለከት በቢል ኦፍ ሌዲንግ ወይም በኤርዌይ ቢል የተመለከተው ቀን አዋጁ ከጸናበት ቀን በኋላ ከሆነ የቅድመ ጭነት ምርመራ ይደረግባቸዋል ። ገጽ ፩ሺ፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም ፲፮ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ሕጐች በዚህ አዋጅ የተሸፈኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፲፯ አዋጁ የሚጸናበት ቀን ይህ አዋጅ ከሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም • ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ