ነጋሪት ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት አሥርኛ ዓመት ቁጥር፳፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ - ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፲፮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፯ / ፲፱፻፲፮ ዓም የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የትርፍ ድልድል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፪ሺ፰፻፵፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፯ / ፲፱፻፲፮ ስለ መንግሥት የልማት ድርጅቶች የትርፍ ድልድል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የትርፍ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፯ / ፲፱፻፲፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፣ ፩ • “ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፬፻፲፪ / ፲፱፻፲፮ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ፪ የተሰጠው ትርጓሜ ይኖረዋል ፣ ፪ . “ የተጣራ ትርፍ ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ አንቀጽ ፪ / ፯ የተሰጠው ትርጓሜ ይኖረዋል ፣ ፫ . “ ባለሥልጣን ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፬፻፲፪ / ፲፱፻፶፮ የተቋቋመው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ነው ። ፬ • “ ሚኒስቴር ” ማለት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያንዱጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፰፻፵፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፫ ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻ ዓም ፫ የትርፍ ድልድል ፩ . ከመንግሥት የልማት ድርጅት የተጣራ ትርፍ ላይ በአዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፶፬ አንቀጽ ፳፱ / ፪ መሠረት የሕጋዊ መጠባበቂያ ሂሣብ ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው ትርፍ እንደሚከተለው ይደለደላል ። ሀ ) ለመንግሥት የትርፍ ድርሻ ..... ለ ) ለኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ 9 % ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከተው የትርፍ ክፍፍል ድልድል ቢኖርም ከሚኒስቴሩ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚቀርበው የውሣኔ ሃሣብ መሠረት ድልድሉ ሊሻሻል ይችላል ። ፫ • የመንግሥት የትርፍ ድርሻ በአዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻ሺ፬ አንቀጽ ፴፩ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ በቅድሚያ ለመንግሥት ፈሰስ ከተደረገ በኋላ ለኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ የተመደበው ገንዘብ ይከፈላል ። ፬ • የትርፍ መግለጫ ስለማቅረብ ማንኛውም የመንግሥት የልማት ድርጅት ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ግምት መግለጫ የዘጠኝ ወራት ክንውንና የቀሪዎቹ ሦስት ወራት ግምት መሠረት በማድረግ በበጀት ዓመቱ እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ ለባለሥልጣኑማቅረብ አለበት ። ፭ የባለሥልጣኑ ተግባር ፩ . ባለሥልጣኑ በዚህ ደንብ አንቀጽ፬ መሠረት የቀረበለትን መረጃ መሠረት በማድረግ የእያንዳንዱን የመንግሥት የልማት ድርጅት ዓመታዊትርፍና በዚህ ደንብ መሠረት ስለሚደረገው ክፍፍል የተዘጋጀ መግለጫ በበጀት ዓመቱ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ። ፪ . ባለሥልጣኑ በጊዜያዊ የሂሣብ መግለጫ ላይ ተመስርቶ በበጀት ዓመቱ የተገኘውን የተጣራ ትርፍ በጀት ዓመቱ ካለቀ እስከ ህዳር ፲፭ ቀን ድረስ ለሚኒስቴሩ ያሳውቃል ። ሆኖም በጊዜያዊ ሂሣብ መግለጫና ትርፍና በኦዲተር በተረጋገጠ ሂሣብ መግለጫ ትርፍ መካከል ልዩነት ሲኖር በውጤቱ ላይ ተመስርቶ ማስተካከያ ይደረጋል ። የፈንዱ ዓላማ ፈንዱ የመንግሥት የልማት ድርጅችን ለማሻሻል ፋፋት ፣ ወይም አዲስ ለሚቋቋሙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ፕሮጀክቶች ጥናት ማስፈጸሚያ እና ማቋቋሚያ መነሻ ካፒታል ይውላል ። የፈንዱ አጠቃቀም ፈንዱ መንግሥት በሚያወጣው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት 17. Utilization of the Fund በሚኒስቴሩ እየተፈቀደ ጥቅም ላይ ይውላል ። መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሚኒስቴሩ ለዚህ ደንብ አፈጸጸም የሚረዱ መመሪያዎችን ለማውጣት ይችላል ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሐምሌ ፳ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስቴር