ሠላሳ ስምንተኛ ዓመት ቊጥር ፲፫
የአንዱ ዋጋ ብር 0.60
ማ ው ጫ
፲፱፻፸፩ ዓ. ም.
ወ ታ ደ ራ ዊ
ነ ጋ ሪ ት ፡ ጋ ዜ ጣ ።
አዋጅ ቍጥር ፩፻፷፬ ፲፱፻፸፩ ዓ. ም.
E ብረተ ûkE ት - ያዊ ወታ L
የዋናው ኦዲተር ሥልጣንና ተግባር
በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂነት የወጣ
ገጽ ፩፻፴፪
አዋጅ ቍጥር ፩፻፷፬ ፲፱፻፸፩ ዓ. ም.
የዋናውን ኦዲተር ተግባርና ሥልጣን ለመወሰን የወጣ አዋጅ
« ኢትዮጵያ ትቅደም »
የዋናውን ኦዲተር ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ የቅልጥፍናና የብቃት ምርመራ እንዲደረግና መንግሥታ ዊና ሕዝባዊ ድርጅቶች በልዩ ልዩ የልማት መስኮች የሚያካሒ ዷቸው ተግባሮች እንዲመረመሩ የማይደነግግ ሆኖ በመገኘቱ ፤
በልዩ ልዩ የልማት መስኮች የተሠማሩ መንግሥታዊና ሕዝ ባዊ ድርጅቶች ብቁ የሆነ የገንዘብ አስተዳደር ያላቸው መሆኑንና ፕሮግራማቸውንም በሚገባ ማስፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ተገቢ የሂሳብ አያያዝና የሂሳብ ምርመራ ሥርዓት መመሥረት አስ ፈላጊ መሆኑን በማመን ፤
እነዚህንም ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ የዋናውን ኦዲተር ተግባርና ሥልጣን እንደገና መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤
የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግንና የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ሥልጣንና ኃላፊነት እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቍጥር ፩፻፲ ፲፱፻፷፱ ዓ. ም. አንቀጽ ፭ (፮) መሠረት የሚከተለው ታውጅዋል ።
፩ ፤ አጭር ርእስ ፤
ይህ አዋጅ « የዋናው ኦዲተር ሥልጣንና ተግባር አዋጅ ቍጥር ፩፻፷፬ ፲፱፻፸፩ ዓ. ም. » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ።
ኤትዮጵያ
፪ ፤ ትርጓሜ ፤
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤
፩ « መሥሪያ ቤት » ማለት ሚኒስቴሮች ፤ ኮሚሽኖች ፤ ባለሥልጣኖች ፤ ተቋሞች ኤጀንሲዎች ወይም ማናቸ ውም ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ነው ።
አዲስ አበባ ሐምሌ ፮ ቀን ፲፱፻፸፩ዓ. ም.
የፖስታ ሣጥን ቍጥር ፩ሺ፴፩ (1031)