×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ ፲፱፻፲፭ የአካባቢ ጥበቃ ኣካላት ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፯ አዲስ አበባ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ / ፲፱፻፶፭ ዓም የአካባቢ ጥበቃ አካላት ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፪፻፴፱ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ / ፲፱፻፶፭ የአካባቢ ጥበቃ ኣካላት ማቋቋሚያ በአንድ በኩል የአካባቢ ልማትና አያያዝ የሥራ እንቅስቃሴ ganizations forenvironmental development and management ዎችን ፣ በሌላ በኩል የአካባቢ ጥበቃ ፣ ቁጥጥርናክትትልተግባራትን | activities on the one hand , and environmental protection , ለተለያዩ አካላት መስጠት የሥራ ኃላፊነቶች አለመጣጣምንና | regulations and monitoring on the other is instrumental for the የሥራ ድግግሞሽን በማስወገድ በአካባቢያዊ ሀብቶች በዘላቂነት | sustainable use of environmental resource , thereby avoiding ለመጠቀም የሚረዳ በመሆኑ ፣ በፌዴራልና በክልል የአካባቢ ጥበቃ መሥሪያ ቤቶች መሀል የተቀናጀ፡ ነገር ግን የየቅሉ የሆነ ኃላፊነትን የሚያጠናክር ሥርዓት | siblities among environmental protection agencies at federal መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአካባቢ ጥበቃ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፭ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ ባለሥልጣን ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፫ መሠረት እንደገና የተቋቋመው የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪፻፵ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፤ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፪ “ አግባብ ያለው መሥሪያ ቤት ” ማለት ቃሉ የተጠቀ ሰበት ድንጋጌ በሚነካው ጉዳይ ላይ በሕግ የተሰጠ ኃላፊነት ያለው የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥት አካል ነው ፤ ፫ . “ አካባቢ ” ማለት በመሬትና በከባቢ አየር በአየር ሁኔታ እና በአየር ንብረት፡ በውሃ ፣ በሕያዋንና በድምፅ በሽታ ፣ በጣዕም፡ በማኅበራዊጉዳዮችእና በሥነ ውበትሳይወሰን ፣ በተፈጥሮአዊ ሁኔታቸው ወይም በሰው አማካኝነት ተሻሽለው ወይም ተለውጠው የሚገኙ ነገሮች በሙሉ ያሉበት ቦታ እንዲሁም መጠናቸውን ወይም ሁኔታ ቸውን ወይም ደግሞ የሰው ወይም የሌሎች ሕያዋን በጎ ሁኔታን የሚነኩ ተስተጋብሮቶቻቸው ድምር ነው ፬ “ የአካባቢ ጥበቃ አካላት ” ማለት ባለሥልጣኑ ምክር ቤቱና በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ እና ፲፭ ድንጋጌዎች የተጠቀሱት የዘርፍየአካባቢ አሃዶችና የክልል የአካባቢ መ / ቤቶች ናቸው ፭ “ እደገኛ ነገር ” ማለት በሰው ጤና ወይም በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ጠጣር ፈሳሽ ወይም የጋዝነት ባህሪይ ያለው ነገር ወይም ተክል ፣ እንስሳ ወይም ረቂቅ ሕዋስ ፕ “ ጥበቃ ” ማለት የተፈጥሮ ባህርይ እንዳይናጋ በመጠ በቅና የተፈጥሮ ሀብቶች ምንጭ አቅምን በማጎልበት፡ የአሁኑን ትውልድ ፍላጎት የማርካቱ ሂደት የመጪውን ትውልድ ዕድል ሳያሰናክል እንዲሟላ ማስቻል ነው ፤ ፯ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፤ ፰ ክልል ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፯ ( ፩ ) የተመለከቱት የአገሪቷ ክፍሎች ማለት ሲሆን፡ ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የድሬዳዋ አስተዳደሮችንም ይጨምራል ፤ ፬ “ የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤት ” ማለት ለአካባቢና ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ወይም ቁጥጥር በክልሉኃላፊነት የተሰጠው ማንኛውም የክልል የመንግሥት አካል ነው ። ክፍል ሁለት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ፫ መቋቋም ፩ ባለሥልጣኑራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል ። ጅ ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል፡ | 4 Head Office እንደአስፈላጊነቱም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊኖሩት ይችላሉ ። የባለሥልጣኑ ዓላማ የባለሥልጣኑዓላማማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊየልማት እንቅስ ቃሴዎች የሰውን በጎ ሁኔታ እና የአካባቢን ደኅንነት በዘላ ቂነት ሊያራምዱ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን ፣ ሥልቶችን ፤ ሕጎችንና ደረጃዎችን ማዘጋጀት እና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የሚከናወነውን ተግባር በግንባር ቀደምትነት መምራት ነው ። የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ . በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ የአካባቢ ደኅንነት ዓላማ ዎችና በአካባቢ ፖሊሲው የተመለከቱት መሠረታዊ መርሆዎች ከግብ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ የሚያ ስችሉ ተግባራትን ያስተባብራል ' ጅ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ከሌሎችጉዳዩ ከሚመ ለከታቸው አካላትና ከሕዝብ ጋር በመመካከር የአካባቢ ፖሊሲዎችን ስልቶችንና ሕጎችን ያዘጋጃል ይገመ ማል፡ ያሻሽላል ወይም እንዲዘጋጁ ያስደርጋል ፣ ሲፈቀዱም በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፣ ይቆጣ ገጽ ፩ሺ፪፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ፫ አካባቢን ለመጠበቅና የተጎዳ አካባቢን መልሶ እንዲያ ገግም ለማድረግ ፣ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ግንኙነት ይፈጥራል ፣ እንደአስፈላጊነቱም የኣቅም ግንባ ታዎች ድጋፍ ይሰጣል ፣ ፬ በመንግሥትም ሆነ በግል ፕሮጀክቶች ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ የልማት ፖሊሲዎች ፣ ሥልቶች ፣ ሕጎችና መርሐ ግብሮች ላይ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ለማካሄድ የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል ፤ የሥራ ፈቃድ የመስጠት ፣ የመተግበር ወይም ክትትል የማድረግ ሥልጣን የፌዴራል መንግሥት የሆነባቸው ወይም ክልል ተሻጋሪ የአካባቢ ተፅዕኖ ሊያስከትሉ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ዘገባ ይገመግማል ፣ ለፈቃድ ሰጪው አካል ውሳኔውን ያሳውቃል ፤ እንደተገቢነቱም የትግበራው ይሁንታ ሲሰጥ በተመለከቱ ግዴታዎች መሠረትፕሮጀክቶቹ መተግበራ ቸውን ያረጋግጣል ፣ ይቆጣጠራል ፣ ፮ . አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመሆን በረሀማ ነትን ለመከላከል የድርቅን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል ፣ መፍትሔዎችን ያዘጋጃል ፤ ለአተገባበራቸውም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ፣ ፯ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር የአካባቢ ደረጃዎችን ይወስናል ፣ መከበራቸውንም ያረጋ ፰ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር በዓለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነቶች ድርድር ላይ ይሳተፋል ፣ እንደተገቢነቱም ስምምነቶቹ እንዲፀድቁ ሃሳብ ያቀርባል ፤ ወይም እንዲቀርብ ያስደርጋል ፤ ፱ . አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢ ውሎች ለመተግበር ተፈላጊ የሆኑ ፖሊሲዎችን ፣ ስልቶችን ፣ ሕጎችንና መርሐ ግብሮችን እንደሁኔታው ያዘጋጃል ፣ ወይም እንዲዘጋጁ ሃሳብ ያመነጫል ፣ አዘገጃጀ ታቸውን ያስተባብራል ፣ ሲፈቀዱም በሥራ ላይ መዋላ ቸውን ያረጋግጣል ፣ ፲ አደገኛነገሮችን ወይም ዝቃጮችን ማምረትን ፣ ወደ ሀገር ማስገባትን ፣ አያያዝንና አጠቃቀምን ፣ እንዲሁም ሕያዋንን በዘረመል ምሕንድስና መለወጥን ፣ ልውጥ ወይም ባዕድ ሕያዋንን ወደ አገር ማስገባትን ፣ አያያዝንና አጠቃቀምን የሚመለከቱ የአካባቢ ደኅንነት ፖሊሲዎ ችንና ሕጎችን አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀዱም በሥራ ላይ መዋላ ቸውን ያረጋግጣል ፣ ፲፩ በልማት ዕቅዶችና በኢንቨስትመንት መርሐ ግብሮች ውስጥ የሚካተቱ የአካባቢ የአዋጪነት ማስሊያ ቀመሮ ችንና የስሌት ሥርዓትን ኣግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ እንደሁኔታውም በጥቅም የመዋላቸውን ሂደት ይከታ ፲፪ ዘላቂነት የጎደለው የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀምንና ልምድን ፣ የአካባቢ ጉስቁልናን ወይም ብክለትን ለመከ ላከል በሚያስችሉ የመግቻ እርምጃዎች ወይም የማበ ረታቻ ዘዴዎች መጠቀምን በተመለከተ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር ሃሣብ ያቀርባል ፣ ፲፫ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመመካከር የአካባቢ መረጃ አሰባሰብን ፣ አደረጃጀትን እና አጠቃ ቀምን የሚያቀላጥፍየአካባቢ መረጃሥርዓትን ይዘረጋል፡ ፲፬ የአካባቢ ጥበቃ ምርምሮችን ያስተባብራል፡ ያበረታታል፡ እንደአስፈላጊነቱም ራሱ ያካሂዳል፡ ፲፭ አግባብ ባላቸው የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የአካባቢ ጥበቃ ግዴታዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ በፌዴራሉ ሥልጣን ሥር ወደሚገኝማንኛውም መሬት፡ ቅጥር ግቢ ወይም ሌላ ቦታ ይገባል፡ ኃላፊነቱን ለመወጣት ተገቢ ሆኖያገኘውን ማንኛውንም ነገርይፈትሻል፡ ናሙናዎችን ይወስዳል፡ ፲፭ የሀገሪቱን የአካባቢ ሁኔታ ዘገባ በየወቅቱ እያዘጋጀ ለመንግሥትም ለሕዝብም እንዲደርስ ያደርጋል፡ ገጽ ፩ሺ፱፻፵፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ • ም • ፲፯ • መደበኛ ያልሆኑ የአካባቢ ትምህርት መርሐ ግብሮችን ያስፋፋል ፣ ትምህርቱን ይሰጣል ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮችን በመደበኛ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ለማካተት አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ትብብር ያደርጋል ፣ ፲፰ የአካባቢ ጥበቃ የድርጊት ዕቅዶችንና ፕሮጀክቶችን ዝግጅት ያበረታታል ወይም ያግዛል ፥ ለድርጊት ዕቅዶቹና ፕሮጀክቶቹማስፈጸሚያ የሚውሉእገዛዎችንያሩልጋል፡ ፲፬ . የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችን ተፈጻሚ ለማድረግ መመሪያ ዎችን ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀዱም በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል ፣ ፳ የአካባቢ አያያዝን እና ጥበቃን ተቀዳሚ ዓላማው በማድረግ ለሚሠራ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ምክር እንዲሁም የሚቻል ሲሆንና የአካባቢ ምክር ቤት ሲስማማበት የፋይናንስ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል ፣ ፳፩ የአካባቢ አያያዝን እና ጥበቃን በሚመለከት ለክልሉች ምክርና ድጋፍ ይሰጣል ፣ ፳፪ • አግባብ ያላቸው መሥሪያ ቤቶች በዚህ አዋጅና በሌሎች የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከቱ ሕጎች የተጣሉባቸውን ኃላፊነቶች በሚወጡበት ሁኔታ ላይ ምክር ይሰጣል፡ እንደአስፈላጊነቱም እርምት ሊወሰድባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሃሳብ ለመንግሥት ያቀርባል፡ ፳፫ በአካባቢ ላይ የሚደርሱ ድንገተኛ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ስለሚወሰዱ አስፈላጊ እርምጃዎች መንግ ሥትን ያማክራል ፣ ፳፬ ተገቢ ሆኖ ሲታየው ከኃላፊነቶቹና ከተግባሮቹ በከፊል ለሌሎች መሥሪያ ቤቶች በውክልና ይሰጣል፡ ፳፭ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፣ ይከሰሳል ፣ ይከሰሳል ፣ እንዲሁም ፳፮ ዓላማዎቹን ለማሳካት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎችተግባራትን 7. Organization of the Authority ያከናውናል ። የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፩ የአካባቢ ምክር ቤት ከዚህ በኋላ « ምክር ቤቱ » እየተባለ የሚጠራ ፣ ፪ : በመንግሥት የሚሾሙ አንድ ዋና ዳይሬክተርና አንድ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ፫ . አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። የምክር ቤቱ አባላት ምክር ቤቱ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡ ሀ ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም በእርሱ የሚሰየም ሰብሳቢ ለ ) በፌዴራል መንግሥት የሚሰየሙ ሐ ) ከእያንዳንዱ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚሰየሙ . መ ) የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ተወካይ ሠ ) በኣካባቢ አያያዝ የተሰማሩ ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካይ፡ ረ ) የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ተወካይ ፣ እና ሰ ) የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር • የምክር ቤቱ ሥልጣን ምክር ቤቱ ፩ . የኢትዮጵያ የአካባቢ ፖሊሲ ተግባራዊነትን በሚመ ለከት ባለሥልጣኑ በሚያቀርበው ዘገባ መሠረት ግምገማ ያካሂዳል ፣ ተገቢውን ምክር ይሰጣል፡ ፪ ተዘጋጅተው የሚቀርቡለትን የአካባቢ ፖሊሲዎች ስልቶችና ሕጎች ይመረምራል ፣ የውሳኔ ሃሳብ ለመን ግሥት ያቀርባል ፣ ባለሥልጣኑ የሚያዘጋጃቸውን የአካባቢ ደረጃዎች እንዲሁም መመሪያዎች ይገመግማል ፣ ያፀድቃል ። ፲ የምክር ቤቱ ስብሰባ ፩ ምክር ቤቱ በስድስት ወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ፣ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል፡ ገጽ ፩ሺ፪፻፵ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ አብላጫ ቁጥር ያላቸው አባላት ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይሆናል ፣ ፫ • የምክር ቤቱ ውሳኔዎች በድምፅ ብልጫ ያልፋሉ ፣ ሆኖም ድምፅ እኩል በእኩል የተከፈለእንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ፣ የዚህ ኣንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፡ ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፲፩ : ስለ ዋናው ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባሮች ዋና ዳይሬክተሩ የባለሥልጣኑ ዋና የሥራ ኃላፊ በመሆን የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፤ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ፣ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ የተመለከቱትን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የባለሥል ጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የባለሥልጣኑን ፕሮግራምና ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ መ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ መርሐ ግብር መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ባለሥ ልጣኑን ይወከላል ፣ ረ ) የባለሥልጣኑን የሥራ እንቅስቃሴ ዘገባ ያቀርባል ። ፫ ዋና ዳይሬክተሩ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስ ፈልግ መጠን ፣ ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለባለሥ ልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፡ ለሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፲፪ የምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ሥልጣንና ተግባራት ፩ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ከዋና ዳይሬክተሩ በሚሰጥ መመሪያ መሠረት፡ ሀ ) የባለሥልጣኑን ተግባሮች በማቀድ፡ በማደራጀት በመምራትና በማስተባበር ዋና ዳይሬክተሩን ይረዳል፡ ለ ) በዋና ዳይሬክተሩ የሚሰጡትን ሌሎች ሥራዎች ያከናውናል ። ዋና ዳይሬክተሩ በማይኖርበት ጊዜ ለዋና ዳይሬክተሩ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ያከናውናል ። ፲፫ በጀትና የሂሣብ መዛግብት ፩ . የፌዴራል መንግሥትየባለሥልጣኑን በጀት ይመድባል ። ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ መዛግብት ይይዛል ። የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ሌሎች ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ክፍል ሦስት የዘርፍ የአካባቢ አሀዶችና የክልል የአካባቢ መሥሪያ ፲፬ • የዘርፍ የአካባቢ አህዶች እያንዳንዱ አግባብ ያለው መሥሪያ ቤት የሥራ እንቅስቃ ሌዎቹ ከዚህ አዋጅናከሌሎች የአካባቢ ጥበቃ ግዴታዎች ጋር ተጣጥመው መካሄዳቸውን የመከታተልና የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለው የአካባቢ አህድ በሥሩ ያቋቁሟል ወይም ይሰይማል ። ፲፭ ስለክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤቶች እ እያንዳንዱ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የአካባቢ ፖሊሲና እንክብካቤ ስልት በመመስረትና በውሳኔ ሂደት ሕዝቡን በማሳተፍ ሀ ) የክልሉን የአካባቢ እንክብካቤ ስልት የሚያዘጋጅ እንዲሁም የአተገባበር፡ ዮምገማና ሥራዎችን የሚያስተባብር፡ ለ ) የክልሉን የአካባቢ ሁነታክትትልና ጥበቃናቁጥጥር ተግባር የሚያከናውን ራሱን የቻለ የአካባቢ መሥሪያ ቤት ያቋቁማል ወይም ከነባር መሥሪያ ቤቶች መካከል አንዱን ለዚሁ ተግባር ይሰይማል ። ገጽ፩ሺ፪፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 1 ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፶፭ ዓም ፪ የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤቶች የፌዴራል የአካባቢ ደረጃዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣሉ፡ እንደአ ስፈላጊነቱም ከፌደራሉ የጠበቁደረጃዎችን በማውጣት ሥራ ላይ ሊያውሉ ይችላሉ ። ፫ • የክልል የአካባቢ መሥሪያ ቤቶች የየክልላቸውን የአካ ባቢና የዘላቂ ልማት ሁኔታ በተመለከተ ዘገባ በማዘ ጋጀት ለባለሥልጣኑ ያቀርባሉ ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፮ የተሻሩ ሕጎች ፩ • የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፱ / ፲፱፻፳፯ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፪ ከዚህ አዋጅ ጋር ተቃራኒ የሆኑ ሕጎች በዚህ አዋጅ ውስጥ በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራ ፲፯ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ • ም • ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?