×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 103/1990 ዓም የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድሥራአዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፳፯ አዲስ አበባ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፫ ፲፱፻፲ ዓም የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ . . . አዋጅ ቁጥር ፩፻፫ / ፲፱፻፲ የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጐት ፡ ዕውቀትና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክንያት መንቀሳቀስ ላልቻሉ ባለሀብቶች አማራጭ የገንዘብ አቅርቦት ምንጮች ማቋቋም የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ አሁን ባሉት የገንዘብ ተቋማት መፍትሔ ሊገኝለት ያልቻ ለውን ክፍተት የካፒታል ዕቃ አከራዮች ሊሸፍኑት ይችላሉ ተብሎ - የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራን በሚመለከት በሥራ ላይ ያሉት ሕጐች የተሟሉ ሆነው ባለመገኘታቸው ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት ከዚህ የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር | ፩፻፫ / ፲፱፻፲ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ያንዱ ዋጋ 3 . 40 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ . ቁ : ዥሺዕ ገጽ ፭፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም “ ማከራየት ” ማለት አከራይ አንድን የካፒታል ዕቃ በፋይናንስ ኪራይ ወይም በአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይ ወይም በዱቤ ግዥ ስምምነት መሠረት ያለምንም መያዣ በየተወሰነ ክፍለ ጊዜ የሚፈጸም ክፍያ እየተቀበለ ተከራዩ ለተወሰነ ጊዜ ለምርትና ለአገልግሎት መስጠት ዓላማ እንዲጠቀምበት የሚፈቀድበት በዓይነት የሚደረግ የፋይ ናንስ አቅርቦት ነው ፡ ፪ . “ የኪራይ ስምምነት ወይም ስምምነት ” ማለት በዚህ | አዋጅ ውስጥ እንደተተረጐመው የፋይናንስ ኪራይ ፡ | የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይ ወይም የዱቤ ግዢ ማለት ፫ . “ የፋይናንስ ኪራይ ” ማለት አከራዩ ፡ ሀ ) ቀደም ሲል ይዞት የሚገኘውን የካፒታል ዕቃ ወይም ለ ) በተከራዩ መራጭነት አቅራቢ ተብሎ ከሚጠራው ሦስተኛ ወገን የሚገዛውን የካፒታል ዕቃ ፡ ተከራዩ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት የተወሰነ ክፍያ በየተ ወሰነ ጊዜ በመፈጸም እንዲጠቀምበት የሚያከራ ይበት ፡ የኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ አከራዩ በካፒታል ዕቃው ላይ ሙሉ የባለቤ ትነት መብት ይዞ የሚቆይበትና የኪራይ ዘመኑ ሲያበቃ ሁለቱም ወገኖች ከተስማሙ ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን ሊገዛ የሚችልበት የኪራይ ዓይነት ነው ፡ ፬ . “ የዱቤ ግዢ ” ማለት አከራይና ተከራይ ባደረጉት ስምምነት መሠረት አከራይ በተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ክፍያ እየተከፈለው አንድ የተወሰነ የካፒታል ዕቃን ተከራዩ እንዲጠቀምበት የሚፈቅድበት ፡ እያንዳንዱ የኪራይ ክፍያ በተደረገ ቁጥር ለክፍያው ተመጣጣኝ በሆነ መቶኛ ልክ ለተከራዩ የባለቤትነት መብት የሚተላለፍበትና ተከራዩ የመጨረሻውን ክፍያ እንደፈጸመም በካፒታል ዕቃው ላይ ሙሉ የባለቤትነት መብት ወዲያውኑ የሚያገኝበት የኪራይ ዓይነት ነው ፡ ፡ ፭ . “ የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይ ” ማለት በአከራዩ እጅ የሚገኝ አንድ የተወሰነ የካፒታል ዕቃን ተከራዩ በሁለት ወገኖች ስምምነት የተወሰነ ኪራይ በመክፈል ከሁለት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እንዲጠቀምበት የሚከራይበት የኪራይ ዓይነት ነው ፡ “ ተከራይ ” ማለት በኪራይ ስምምነት መሠረት ለተወሰነ ጊዜ አንድን የካፒታል ዕቃ ኪራይ እየከፈለ ለመጠቀም ከአንድ አከራይ ላይ የሚከራይ ሰው ነው ፡ ፡ ፯ . “ አከራይ ” ማለት በኪራይ ስምምነት መሠረት ለተወሰነ ጊዜ አንድን የካፒታል ዕቃ ኪራይ እየተከፈለው አንድ ተከራይ እንዲገለገልበት የሚያከራይ ሰው ነው ፡ ፰ . “ የካፒታል ዕቃ ” ማለት በኢንቨስትመንት ሕጉና በዚሁ | ሕግ በተሰጠው ሥልጣን የኢንቨስትመንት ቦርዱ በሚያ ወጣው መመሪያ መሠረት የሚወሰን ዕቃ ነው ፡ ሀ• “ አቅራቢ ” ማለት ከአከራይ ወይም ተከራይ ሌላ ሆኖ የካፒታል ዕቃዎችን በመሸጥ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ነው ፡ ፲ . “ የኢንቨስትመንት ሕግ ” ማለት የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፳፯ ወይም የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፯ ህየዝቿ ወይም ሁለቱም ነው ፡ - Federal Negarit Gazeta No . 27 5 March , 1998 – Page 709 ገጽ ፯፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ፲፩ . “ ሊሠረዝ የማይችል ስምምነት ” ማለት በሕግ አፈጻጸም ወይም በስምምነት ብቻ ካልሆነ በስተቀር ሊሠረዝ የማይችል የኪራይ ስምምነት ነው ፣ ፲፪• “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፣ ፲፫ “ ሚኒስቴር ” ማለትየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ነው ፣ ክፍል ሁለት የፈቃድ አሰጣጥ ፡ የኪራይ ስምምነት ባህሪያትና የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታዎች ፫• ፈቃድ ስለመስጠት ፩ . የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ የሚካሄደው ከሚኒ ስቴሩ ፈቃድ በተሰጠው አከራይ ብቻ ነው ። ፪• የአከራይነት ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በሚመለከት ሚኒስቴሩ መመሪያ ያወጣል ። የኪራይ ስምምነቶች አጠቃላይ ባህሪያት ማንኛውም የኪራይ ስምምነት ቢያንስ የሚከተሉትን ይይዛል ፣ ፩ የኪራይ ዓይነቱን መግለጫ ፡ ፪ . የካፒታል ዕቃውን ለመለየት የሚያስችል በቂ መግለጫ ፡ | የካፒታል ዕቃውን ሙሉ ዋጋ እና በኪራይ ስምምነቱ መሠረት የሚከፈለውን ጠቅላላ ኪራይ ፣ ፫ . የእያንዳንዱ ኪራይ መጠን ፡ ጠቅላላው ኪራይ የሚከፈ ልበት ጊዜና እያንዳንዱ የኪራይ ክፍያ የሚደረግበት ቀን ወይም ቀኑ የሚወሰንበት ዘዴ ፣ ተከራዩ በውሉ መሠረት በተወሰነው ቀን ኪራዩን የሚከፍል መሆኑን ፣ ፬ . ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበትጊዜ ውስጥ ሦስተኛ ወገኖች በካፒታል ዕቃው ላይ ጉዳት ቢያደርሱበት ተከራዩ የማሠራት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ድንጋጌ ፣ ተከራዩ የካፒታል ዕቃው በተላለፈለትጊዜአገልግሎቱን የሚቀንስ ጉድለት ያለበት ሆኖ ካገኘው ስምምነቱን አቋርጦ የካፒታል ዕቃውን የመመለስ መብት ያለው ስለመሆኑ የሚያሳይ ድንጋጌ ፣ ፮ በአከራዩና በካፒታል ዕቃ አቅራቢው መካከል ከተደ ረገው የሽያጭ ውል የሚመነጩ መብቶችንና ጥቅሞችን ለተከራዩ ለማስተላለፍ አከራዩ የገባው ቃል ፡ ፯ ተከራዩ የካፒታል ዕቃ ኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆ ይበት ጊዜ ሁሉ በስምምነቱ በተገለጸው ሁኔታ በተከ ራየው የካፒታል ዕቃ ላይ ሁከት የማይደረግበት የባለ ይዞታነት መብት ያለው መሆኑን የሚያሳይ ቃል ፡ ፰ ተከራዩ በካፒታል ዕቃው ሲጠቀም በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርስ ሞት ፡ የአካል ጉዳት ወይም የንብረትጉዳት አከራዩ እንደአከራይነቱ ኃላፊነት የሌለበት መሆኑን የሚያሳይ ቃል ። ፭ የኪራይ ስምምነቶች ልዩ ባህሪያት ፩ የፋይናንስ ኪራይ ስምምነትን በሚመለከት ፡ ሀ ) ተከራዩ የኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ | የካፒታል ዕቃውን ለአከራዩ እንደባለአደራ ብቻ ሆኖ ይይዛል ፡ በካፒታል ዕቃው ላይም ምንም ዓይነት የባለቤ ትነት መብት አይኖረውም ፡ እ፯፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፯ ዓም ለ ) ስምምነቱ ውል የተገባበት ሙሉ ዋጋ በኪራይ ተከፍሎ የሚሸፈንበትና ሊሠረዝ የማይችል ስምምነት ይሆናል ፡ ሐ ) የስምምነቱጊዜ ሲያበቃ ሁለቱ ወገኖች ከተስማሙ ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን የመግዛት ምርጫ ሊኖረው ይችላል ፡ ካልተስማሙ ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን ለአከራዩ ይመልሳል ፡ ተከራዩ ለካፒታል ዕቃው መድን የመግባትና ተገቢውን እደሳ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል ። . ፪ : የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይ ስምምነትን በሚመ ሀ ) ተከራዩ የተከራየው የካፒታል ዕቃ የአከራዩንብረት ሆኖ የሚቆይና የስምምነቱ ጊዜ ሲያበቃ ሁለቱ ወገኖች በሚስማሙበት መሠረት ስምምነቱ እንደገና እንዲራዘም ወይም ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን እንዲገዛ ካልተስማሙ በስተቀር ተከራዩ የካፒታል ዕቃውን ለአከራዩ የሚመልሰው ይሆናል ፡ ስምምነቱ አለጊዜው በመቋረጡ ምክንያት በሌላው ወገን ላይ ጉዳት ያደረሰው ወገን ለደረሰው ጉዳት ካሳ የሚከፍል ሆኖ ፡ ተከራይም ሆነ አከራይ ስምምነቱን የመሰረዝ መብት ይኖራቸዋል ፡ ሐ ) አከራይ ለካፒታል ዕቃው መድን የመግባትና ተገቢውን እደሳ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል ። ፫ የዱቤ ግር ስምምነትን በሚመለከት ፣ ሀ ) እያንዳንዱ የኪራይ ክፍያ በተፈጸመቁጥር ለክፍያው ተመጣጣኝ በሆነ መቶኛ ልክ የባለቤትነት መብት እንዲሁም የመጨረሻው የኪራይ ክፍያ እንደተ ፈጸመ ወዲያውኑ የካፒታል ዕቃው ሙሉ የባለቤ ትነት መብት ለተከራዩ የሚተላለፍለት ይሆናል ፡ ለ ስምምነቱ በማናቸውም ወገን አለጊዜው በሚቋረ ጥበት ጊዜ ከስምምነቱ የሚመነጭ የባለቤትነት መብቶችና ጥያቄዎች እልባት የሚያገኙበትን ሁኔታ ሁለቱ ወገኖች በስምምነቱ ያካትታሉ ፡ ሐ ) ተከራዩ ለካፒታል ዕቃው መድን የመግባትና ተገቢውን እደሳ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል ። 1 ኪራይን ስላለመክፈልና ሌሎች ጥፋቶች ፩ ተከራዩ ኪራዩን በወቅቱ ባይከፍል ወይም ስምምነቱን የሚጥስ ሌላ ጥፋት ቢፈጽም ተከራዩ የፈጸመው ጥፋት ሊወገድ የሚችል ከሆነ በስምምነቱ መሠረት እንዲ ፈጸም አከራዩ የ፴ ቀን ጊዜ ሊሰጠው ይገባል ። ፪ : ተከራዩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ጥፋቱን ባያስወግድ አከራዩ ስምምነቱን መሠረዝ ፡ የካፒታል ዕቃውን ወደ ይዞታው መመለስና ለደረሰበት ጉዳት ካሣ መጠየቅ ይችላል ። ፫ ተከራዩ ኪራዩን በወቅቱ ያልከፈለ እንደሆነ ጥፋቱ የተወገደ ወይም ያልተወገደ ቢሆንም እንኳ አከራይ ውዝፉን ኪራይ ከወለድና ካሣ ጋርማስከፈል ይችላል ። 17 . Defects on the Leased Capital Good ፤ በተከራየው የካፒታል ዕቃ ላይ ስላሉ ጉድለቶች ፩ ስምምነቱ በተደረገበት ወቅት በተከራዩ ለታወቀ | የካፒታል ዕቃ ጉድለት ኣከራዩ ኃላፊነት የለበትም ። ገጽ ፯፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓምFederal Negarit Gazeta - No . 27 52 March , 1998 - - Page 71 ( ፪ አከራዩ የካፒታል ዕቃውን ለተከራዩ ባስረከበበት ወቅት ያወቀውን ወይም ሊያውቀው የሚገባውን ጉድለት ለተከራዩ ሳያሳውቀው ቀርቶ በካፒታል ዕቃው ጉድለት ምክንያት በተከራዩ ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት ካሣ የመክፈል ግዴታ አለበት ። በኪራይ ስምምነቱ በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር ፡ ተከራዩ በሰጠው ዝርዝር የመምረጫ መስፈርት መሠረት አከራይ የካፒታል ዕቃውን እስከገዛ ድረስ ዕቃው ለተፈ ለው ዓላማ አገልግሎት ለመስጠት ጉድለት ያለበት ወይም የማይስማማ ሆኖ ቢገኝ በኃላፊነት አይጠየቅም ። ፬ . ተከራዩ የተከራየውን የካፒታል ዕቃ በኪራይ ስምምነቱ መሠረት ወይም ተቀባይነት ያለውን ሥርዓት ወይም አጠቃቀም በመከተል የማይገለገልበት ከሆነና የተከራዩ አጠቃቀም በካፒታል ዕቃው ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ አከራዩ ለተከራዩ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ስምምነቱን ለመሠረዝና የአከራየውን የካፒታል ዕቃ ወደ ይዞታው ለመመለስ መብት አለው ። ፰ ስለመክሰር ፩ በኪራይ ስምምነቱ መሠረት ተከራዩ ግዴታውን እስከ ተወጣ ድረስ አከራዩ እንደከሰረ በፍርድ ቤት ቢወሰን እንኳን የከሰረውን አካል በሕግ የሚተካ አካል በስም ምነቱ ግዴታዎችና ሁኔታዎች መሠረት ይቀጣል ። ፪ የተከራዩ መክሰር በፍርድ ቤት ቢወሰንም በተከራየው የካፒታል ዕቃ ላይ አከራዩ ያለውን የባለቤትነት መብት አያሳጣውም የተጠበቀ ይሆናል ። ፱ ስለጉዳት ካሣ ፩ ስምምነቱ በተከራዩ በሚሠረዝበት ጊዜ ተከራዩ የተከራ የውን የካፒታል ዕቃ ለአከራዩ እንዲመልስ ተገቢው ማሳሰቢያ ተሰጥቶትካላስረከበ አከራዩ የካፒታል ዕቃውን ወዲያውኑ ወደ ይዞታው የመመለስና ለደረሰበት ጉዳት ካሣ የመጠየቅ መብት አለው ። ፪ : የሚከራየው የካፒታል ዕቃ ከአከራይ ወደ ተከራይ | ከመተላለፉ በፊት በተከራይ ጥፋት ምክንያት በአከራይ ላይ ማናቸውም ጉዳት ቢደርስበት ፡ አከራይ በቅን ልቦና እስከፈጸመና በተከራይ ጥያቄ የካፒታል ዕቃውን ለመግዛት ወጪ የደረሰበት እስከሆነ ድረስ ተከራይ በአከራይ ላይ ለደረሰው ጉዳት ካሣ መክፈል አለበት ። ፫• የፋይናንስ ኪራይን እና የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይን በሚመለከት ተከራዩ የተከራየውን የካፒታል ዕቃ የስም ምነቱ ጊዜ ሲያልቅ ሳይመልስ የቀረእንደሆነ በስምምነቱ ውስጥ በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር አከራዩ የተከራ የውን የካፒታል ዕቃ ወደይዞታው የመመለስና ለደረ ሰበት ጉዳት ካሣ የመጠየቅ መብት አለው ። መብትን ስለማስተላለፍ ተከራዩ በስምምነቱ መሠረት በካፒታል ዕቃው በሰላም | 10 . Transfer of Right ለመጠቀም ያለውን መብት እስካልተጋፋ ድረስ አከራዩ በኪራይ ስምምነቱ መሠረት ያገኘውን መብት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ የተናጠል መብት አለው ። ፲፩ ፡ በሦስተኛ ወገኖች የሚቀርብ ጥያቄ ፩ . በካፒታል ዕቃው ላይ መብት አለኝ በማለት በሦስተኛ | 11 . Claim by Third Parties ወገን የሚቀርብ ማንኛውም ክስ በአከራዩ ላይ መቅረብ | አለበት ። ገጽ ፯፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ ም Federal Negarit Gazeta - - No . 27 59 March , 1998 – Page 712 ፪ . የተከራዩን አበዳሪዎች ጨምሮ ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች በካፒታል ዕቃው ላይ ከሚያቀርቡት ጥያቄዎች ይልቅ አከራዩ ያለው የባለቤትነት መብት ምንጊዜም ቅድሚያ ይሰጠዋል ። ፫ ተከራዩ በካፒታል ዕቃው በሰላም እንዳይጠቀም በሦስተኛ ወገኖች የሚደርስበትን ችግር ወይም ሁከት ለአከራዩ ማሳወቅ አለበት ። ፬ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) በተገለጸው መሠረት ተከራዩ አከራዩን ሳያሳውቅ የቀረ ወይም የዘገየእንደሆነ አከራዩ ለሚያወጣው ወጪና ለሚደርስበት ጉዳትኃላፊ ይሆናል ። ፭ ሦስተኛ ወገን በአከራዩ ላይ በሚያቀርበው ክስ | ምክንያት የካፒታል ዕቃው ዋጋ የቀነሰ እንደሆነ ተከራይ በአዲሱ ዋጋ መሠረት ኪራዩ እንዲቀንስለት ወይም ስምምነቱ እንዲሰረዝ የመጠየቅ መብት አለው ። ፲፪• የኪራይ ስምምነት መቋረጥ ፩ . ማንኛውም የኪራይ ስምምነት በስምምነቱ በተገለጸው ቀን ይቋረጣል ። ፪• በኪራይ ስምምነቱ በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር በተከራዩ መሞት ወይም ችሎታ ማጣት ምክንያት ስምምነቱ አይቋረጥም ። ፫ የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይ ስምምነት ዘመን ሲያበቃ ተከራይ የተከራየውን የካፒታል ዕቃ እንደያዘ ቢቀርና አከራይም እንዲመለስለት ባይጠይቅ ከተዋ ዋዮቹ ወገኖች አንደኛው ስምምነቱ እንዲቋረጥእስከሚ ጠይቅ ድረስ በመጀመሪያ የተገባው የኪራይ ስምምነት እንደተራዘመ ይቆጠራል ። ፲፫ : ተከራዩ በካፒታል ዕቃው ላይ ግዴታ መፍጠር የሌለበት ስለመሆኑ ፩ ተከራዩ በተከራየው የካፒታል ዕቃ ላይ ማናቸውንም የክፍያ ወይም ሌላ ግዴታ መግባት አይችልም ። . ፪• የክፍያ ወይም ሌላ ማናቸውም ግዴታ በካፒታል ዕቃው ላይ በተከራዩ የተገባ እንደሆነ ፡ ይኸው ግዴታ ዋጋ የሌለው ይሆናል ። ፫ በካፒታል ዕቃው ላይ በአከራዩ የተገባ ግዴታን ወይም የሚጠየቅ ግብርን የሚችለው አከራዩ ነው ። ፲፬• የካፒታል ዕቃውን ስለመያዝና ስለመጠበቅ _ _ ፩ ተከራዩ የካፒታል ዕቃው በእጁ እስካለ ድረስ በጥንቃቄ ይይዛል ፡ ይጠብቃል ። ፪ ተከራዩ ያለአከራዩ ፈቃድ የካፒታል ዕቃውን አጠቃቀም ሁኔታ መቀየር አይችልም ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ማበረታቻዎች አከራይ ለኪራይ ተግባር የሚውሉ የካፒታል ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ በኢንቨስትመንት ሕጉና | በዚሁ ሕግ በተሰጠው ሥልጣን የኢንቨስትመንት ቦርዱ | በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ | የመሆን መብት አለው ። ገጽ ፤ የነ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ጊ የካቲት ፳፮ ቀን ፲ህየ1 ዓ . ምFederal Negarit Gazeta – No . 27 5 March , 1998 - Page 713 ፲ጌ ስለ እርጅና ቅናሽና በገቢ ላይ ስለሚጣል ግብር ፩ . የፋይናንስ ኪራይን እና የአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ኪራይን በሚመለከት አከራይ የካፒታል ዕቃው ባለቤት በመሆን የካፒታል ዕቃዎቹ የእርጅና ቅናሽ ከሚገኘው የኪራይ ገቢ ላይ ተቀናሽ ይደረግለታል ። ሆኖም የዱቤ ግዥ ስምምነትን በሚመለከት የእርጅና ቅናሽ የሚታ ሰበው ለተከራዩ ይሆናል ። ፪• በኪራይ ስምምነት መሠረት አከራይ የሚያገኘው ኪራይ እንደገቢ ይቆጠራል ። ፫ በተከራይ የሚከፈል ኪራይ እንደመደበኛ ወጪ ተቆጥሮ ለግብር ዓላማ ከተከራይ ገቢ ላይ ተቀናሽ ይሆናል ። ፲ጊ የሚኒስቴሩ ሥልጣንና ተግባር ሚኒስቴሩ ፡ ፩ . የካፒታል ዕቃ ኪራይ ስምምነቶችን ይመዘግባል ፡ ፪• ተከራዩ የተከራየውን የካፒታል ዕቃ የመመለስ ግዴታ | ቢኖርበትና ባይመልስ የካፒታል ዕቃው ለአከራዩ መመለሱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አግባብ ያላቸውን እርምጃዎች ይወስዳል ፡ ለአፈጻጸም እንዲረዳው ፖሊስን ፫ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች መመሪያ ዎችን ያወጣል ። ፲፰ የሌሎች ሕጐች ተፈጻሚነት በዚህ አዋጅ በሌላ ሁኔታ ካልተወሰነ በስተቀር አግባብነት | 18 . Applicability of Other Laws ያላቸው የፍትሐብሔር ሕግ እና የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች | በኪራይ ስምምነት ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ኣዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፯ ዓ ም ጀምሮ የጸና | ይሆናል ። አዲስ አበባ ፡ የካቲት ፳፮ ቀን ፲፱፻፲ ዓ . ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?