×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 21389

      Sorry, pritning is not allowed

የሰ / መ / ቁ / 21389
ቀን 18/7/98 ዓ.ም
* ሳያ ፌ ር ድ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሃይ ታደሠ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ ጌታቸው ምህረቱ አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች፡- ስለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን
- ነ / ፈጅ አያሌው አለማየሁ - ቀርበዋል መ / ሰጭ፡- አቶ ፈቃዱ አካሉ - ቀርበዋል
ይህ ጉዳይ የተጀመረው በድሬዳዋ አሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ ሲሆን ተጠሪ
ውዝፍ ደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲከፈለው በአመልካች ላይ ባቀረበው
ክስ ነው ፡፡ ቦርዱም ግራ - ቀኙን አከራክሮ በ 6 / 5 / 89 በዋለው ችሎት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም
ከዚሁ ውሳኔ በኋላ በአመልካች በኩል የቀረበለትን የውሳኔ ይታረምልኝ ማመልከቻ
ተቀብሎ መጀመሪያ ሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ በማረም ውሳኔ ሰጥቷል ፡፡
ተጠሪም ለድሬዳዋ ፌ / ከ / ፍ / ቤት ይግባኝ በማቅረባቸው ፍ / ቤቱ ቦርዱ ሰጥቶ
የነበረውን ውሳኔ ሽሮታል ፡፡ አመልካችም በፍ / ቤቱ ውሣኔ የተፈጸመ የሕግ ስህተት አለ
በማለታቸው ውሣኔው እንዲታረም ለፌ / ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታቸውን
ፌደራል ፡፡ ይ ፧ ት
ጎፊ ጎል ፡፡
ቀን 13 - 0 -ዯ 8
* ፍቃጠው መመሪያ ውጪ መሆን አለመሆኑን
ያ አቅረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን የሰበር ችሎቱም አቅርበው ችሎቱ በ 21 / 9 / 96 በዋለው ችሎት በሠጠው ውሳኔ ቦርዱ የግራ - ቀኙን የመደመጥ መብት ሊጠብቅ የሚገባ በመሆኑ በእርምት አቤቱታው ላይ ግራ - ቀኙን አስቀርቦ ይወሰን በማለት ጉዳዩን ለቦርድ መልሶታል ፡፡
ቦርዱም በችሎቱ በተሠጠው መመሪያ መሠረት የውሳኔ ይታረምልኝ አቤቱታው ለተጠሪ እንዲደርስ በማድረግ ግራ - ቀኙን አከራክሮ የተጠሪን የደሞወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ይከፈለኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል ፡፡ ተጠሪም በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ በመጠየቁ ይግባኙ የቀረበለት የድሬዳዋ ፌ / ከ / ፍ / ቤት ቦርዱ በሰበር ሰሚው ችሎት የታዘዘው ተፈፅሞ የነበረ የስነ - ስርዓት ግድፈትን እንዲያርም እንጂ በፍሬ ጉዳዩ ላይ አከራክሮ ዋናውን ጉዳይ አርሞ ውሳኔ እንዲሠጥ አይደለም በማለት ቦርዱ ቀድሞ በፍሬ - ጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሣኔ ማረም ሣያስፈልገው መዝገቡን እንዲዘጋ ውሣኔ
ሠጥቷል ፡፡
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ
ቦርዱ ውሣኔ የሠጠው የሠበር ችሎቱ
ለመመርመር መዝገቡን አስቀርቦ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር አድምጧል ፡፡
ምንም እንኳን ይህ መዝገብ የተለያዩ የፍርድ ሂደቶችን ያለፈ ቢሆንም ለአሁኑ
የሠበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ቀደም ሲል ይህ ችሎት በ 21 / 9 / 95 ዓ.ም በሠጠው
ውሣኔ ጉዳዩን በመመሪያ ለቦርድ በመመለሱና ቦርዱም በተሠጠው መመሪያ መሠረት
ግራ ቀኙን አከራክሮ የሠጠውን ውሣኔ ፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመሻሩ ነው ፡፡ በመሆኑም
ጉዳዩ እልባት ያገኝ ዘንድ ይህ የሠበር ችሎት ለቦርዱ ሠጥቶ የነበረውን መመሪያ
መረዳት ተገቢ ነው ፡፡
ቀን .3-0 ዲ *
ከመድረሱ በፊት ግን የሾ w
የሰበር ሰሚው ችሎት በውሣኔው ቦርዱ በመደበኛ ፍ / ቤቶች በሚሠራባቸው የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ አቀራረብ ደንቦች ሣይወሰን የተሻለ መስሎ በታየው በማናቸውም ዘዴዎች ተጠቅሞ አግባብ ነው በሚለው በማናቸውም አካሄድ ውሣኔ ላይ መድረስ የሚችል መሆኑ በአ / ቁ / 42 / 85 የተመለከተ ቢሆንም ቦርዱ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተመልክቶ የሰጠው ውሣኔ በአመልካች በቀረበ የውሣኔ ይታረምልኝ ጥያቄ መልስ
ሣይጠራና ሣያከራክር በአዋጁና መንግሥቱ የተቀመጠውን የመደመጥ መብት የጣሠ በመሆኑ ቦርዱ ግራ ቀኙ ባለበት ጉዳዩን በድጋሚ አይቶ እንዲወስን ትዕዛዝ ሠጥቷል ፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው ለቦርዱ የተላለፈው መመሪያ ምንም እንኳን ቦርዱ በአመልካች በቀረበው የውሣኔ ይታረምልኝ የሚለውን ለመስጠት የሚያመለክተውንና ተገቢ ነው የሚለውን አካሄድ ሊከተል ቢችልም ውሣኔ ላይ
ወገን ብቻ ሣይሆን የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ መሆን
እንዳለበት አዋጁም ሆነ ህገ መንግሥቱ ስለሚያስገድዱት የሁለቱንም ክርክር ሰምቶ
የመሰለውን እንዲወስን ነው ፡፡ በመሆኑም ቦርዱ አከራክሮ እንዲወሰን ጉዳዩ በመመሪያ
የተመለሰለት አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ ብቻ ሣይሆን ዋናውን ጉዳይ ጭምር ነው ፡፡
በይግባኝ ሰሚ ፍ / ቤት አንድን ጉዳይ እንደገና እንዲያይ የታዘዘ ፍ / ቤትም ሆነ በተያዘው
ጉዳይ ቦርድ ደግሞ በትዕዛዙ መሠረት ሊፈጽም እንደሚገደድ የፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ / 343 / 2 /
ያስገነዝባል ፡፡ ስለሆነም ቦርዱ እንደገና እንዲያይ በተላለፈለት መመሪያ መሠረት የግራ
ቀኙን ክርክር ሰምቶ ውሣኔ መስጠት ህግ የጣለበት ግዴታ በመሆኑ አመልካችና
መ / ስጪን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ውሣኔ በመሰጠቱ የፈፀመው ስህተት የለም ፡፡
ፌያፈራ { } : ቀ ን ያ 4 ፡ 4 . ኒነ
ቀን 03-10ዓ a
በዚህም ምክንያት የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት ቦርዱ የሥነ ሥርዐት ግድፈት ካለ ብቻ
እርምት እንዲያደርግ
እና ከሌለው ዋናውን ጉዳይ ማረም ሣያስፈልግ መዝገቡን
እንዲዘጋ የሰጠው ውሣኔ የሰበር ችሎቱን ውሣኔ ያላገናዘበ ነው ፡፡
ው ሣ ኔ
1. የፌ / ከፍተኛ ፍ /
ቤት በመ / ቁ / 1173 ሐምሌ 12/1997 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ።
2. የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የካቲት 5/1996 ዓ.ም የሠጠው ውሣኔ
ፀንቷል ፡፡
3. ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ።
መዝገቡ ተዘግቷል ለመዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
ፈያ ... ል ... ይ ::
ፊርማ .. AWA

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?