የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፫ [ አዲስ አበባ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፯ ፲፱፻፲፬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፮፻፴፮ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፯ ፲፱፻፵፬ ዓም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤትን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ባልተጠበቀ ሁኔታ ከሚከሰቱም provides additional guaranty against unforeseeable and ሆነ አመጣጣቸው ሊታይ ከሚችል አደጋዎችና ፈተናዎች potential threats and challenges to the country's national በመጠበቅ ረገድ ተጨማሪ ዋስትና ሊያስገኝ የሚችል አሠራር መቀየስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | the Constitution of the Federal Democratic Republic of መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፵፯ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ከዚህ በኋላ “ ምክር ቤቱ ” እየተባለ የሚጠራ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ ምክር ቤቱእንዳስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ሊኖሩት | 3 Members of the Council ይችላል ። ፫ የምክር ቤቱ አባላት ፩ ምክር ቤቱ የሚከተሉት ቋሚ አባላት ይኖሩታል ፣ ሀ ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ም / ሰብሳቢ ሐ ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መ ) የመከላከያ ሚኒስትሩ ሠ ) የደህንነት ፤ ኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ረ ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ....... ሰ ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ / ቤት ኃላፊ አባልና ፀሐፊ ። ያንዱ ዋጋ [ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ? ኒስትሩ ሲጠራ በማናቸውም ግጽ ፩ሺ፮፻፴፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ • ም • ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ ቢኖርም ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሀ ) ተጨማሪ የምክር ቤት አባላትን ለመሰየም ፣ እና ለ ) ማንኛውም ሰው ሙያዊ ምክር ለመስጠት በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በአስረጅነት እንዲገኝለመፍቀድ ይችላል ። ሽ የምክር ቤቱ ተግባር ፩ . ምክር ቤቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት የሚመለከቱ የውስጥ ፣ የውጭና የመከላከያ ፖሊሲዎች እንዲጣጣሙ በማድረግና በሚገባ ተግባራዊ መደረጋቸውን በመከ ታተል ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያማክራል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ምክር ቤቱ ፣ ሀ ) ለሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት የሥጋት ምንጭ የሆኑ ሁኔታዎችን በመገምገም ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ሃሣብ ያቀርባል ፣ ለ ) የሀገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የሚመለከቱ የአፈጻጸም መመሪያዎች ያመነጫል ፣ ሐ ) የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት በሚነካ ማናቸውም ጉዳይ ላይ ይመክራል ። ፫ . ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፲፫ መሠረት የአስ ቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲደነገግም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ የሚወሰኑ ተግባሮችን ያከናውናል ። ፭ የምክር ቤቱ ስብሰባዎች ፩ ምክር ቤቱ በጠቅላይ ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ : በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አባላት ከተገኙ ምልኣተ ጉባዔ ይኖራል ። ፫ . ምክር ቤቱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ። ፮ . የምክር ቤቱ ኮሚቴዎች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት የሚቋቋሙ ኮሚቴዎች የሚኖሩዋቸው አባላትና ዝርዝር ተግባራቸው በምክር ቤቱ ይወሰናል ። ፯ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ገጽ ፩ሺ፮፻፴፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ማረሚያ ቁጥር ፩ / ፲፱፻፲፬ የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፯ / ፲፱፻፶፫ ከዚህ የሚከተለው እርምት ተደርጐበታል ፤ በአንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) “ እኤአ ” ከሚለው ቀጥሎ “ በሚቀጥለው ወር ” የሚል ተጨምሮ ይነበብ ። ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ