ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ የሚሰመ ዓንደገና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፲፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ - የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፫ / ፲፱፻፶፫ ዓም • የፌዴራል የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፪፻፳፯ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፫ ፲፱፻፫ ዓም የፌዴራል የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ በሕግ ተለይተው በፌዴራሉ መንግሥት እንዲሰበሰቡ በተመደቡ የግብር ውሳኔዎች ላይ በግብር ከፋዮች በይግባኝ ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፫ / ፲፱፻ቹ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ ግብር ” ማለት ከቴምብር ቀረጥ በገቢና ወጪ | 2. Definitions ዕቃዎች ላይ ከሚጣሉ ቀረጦችና ታክሶች በስተቀር በፌዴራል መንግሥት እንዲሰበሰብ የተመደበ ማንኛ ቸውም ግብር ወይም ታክስ ነው ፣ ፪ . “ ባለሥልጣን ” ማለት የፌዴራል መንግሥት የአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ነው ፣ ፫ . “ ጉባዔ ” ማለት የፌዴራል የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ፬ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፭ሺ፬፻፷፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻ ዓም ክፍል ሁለት ስለ ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ፫ . ስለመቋቋም ፩ . የፌዴራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ / ከዚህ በኋላ “ ጉባዔው ” በመባል የሚጠራ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ ተቋቁሟል ። ፪ • የጉባዔው ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የጉባዔው ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ ጉባዔው በሚወስነው በአገሪቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ጽ / ቤቶች ሊኖሩት ይችላል ። ፪ • ጉባዔው ባልተቋቋመበት ክልል የሚገኘው የክልል መስተዳድር የግብር ይግባኝ ሰሚ አካል ጉባዔው በሚሰጠው ውክልና መሠረት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተደነገገው ተጨማሪ ሥልጣን ይኖረዋል ። ፭ ዓላማ የጉባዔው ዓላማ ባለሥልጣኑ በሚወስነው ግብር ላይ በግብር ከፋዮች በይግባኝ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን መርምሮ መወሰን ይሆናል ። ፮ • የጉባዔው ሥልጣንና ተግባር ማንኛውም በዚህ አዋጅ መሠረት የተቋቋመ ጉባዔ የሚከ ተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ / ሀ / መሠረት የሚመሩለትን የይግባኝ ጉዳዮች መርምሮ ይወስናል ፣ ፪ የቀረበለትን ጉዳይ ለመወሰን አግባብነት ያለውን ማንኛውም መዝገብ ወይም ሰነድ እንዲቀርብለት፡ ማንኛውም ሰው ቀርቦ የሚጠየቀውን ማንኛውንም አስፈላጊ መረጃ እንዲሰጥ ያዛል ፣ ባለሥልጣኑ አስተላልፎት የነበረውን የግብር ውሳኔ ለማጽደቅ ፣ ለመቀነስ ፣ ለመጨመር ወይም ለመሠረዝ ይችላል ። እንደዚሁም ለጉዳዩ ፍጻሜ ተገቢ ሆኖ ያገኘውን ትዕዛዝ ይሰጣል ፣ ሆኖም ጉባዔው ውሳኔውን ሊሰጥ የቻለበትን ምክንያት በውሳኔው ማስፈር ይኖር ፬ ጉባዔውየሰጠውን ውሣኔ ግልባጭ ለተከራካሪ ወገኖች እንዲደርስ ያደርጋል ። ፯ : የጉባዔው የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ፩ . ከጉባዔው አባላት ሦስቱ ሲገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ጉባዔው በቀረቡለት የይግባኝ ጉዳዮች ላይ በድምጽ ብልጫ ውሳኔይሰጣል ። ድምጽእኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፫ በሃሳብ የተለየ የጉባዔው አባል የሀሳብ ልዩነቱን በውሳኔው ያሰፍራል ። ፰ : የጉባዔው አቋም ፩ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔው ፤ ሀ ) ፕሬዚዳንት ፣ ለ ) የጉባዔ አባላት ፣ ሐ ጽሕፈት እና አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። ፪ • የጉባዔው ፕሬዚዳንት በመንግሥት ይሾማል ። ፱ • የጉባዔው ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የጉባዔው ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፪ የጉባዔው ፕሬዚዳንት በመንግሥት ይሾማል ። ገጽ ፭ሺ፬፻፷፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፰ ዓም • የጉባዔው ሰብሳቢ ሆኖ ይሠራል ፣ ፪ ለየጉባዔዎቹ ሰብሳቢ ይሰይማል ፤ አባላትን ይደለድላል ፣ ፫ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት የጽ / ቤቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ፬ የጉባዔውን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ለጉባዔው በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ፮ ከሌሎች ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ጉባዔውን ይወክላል ፣ ፯ . ለጉባዔው አባላት የሚከፈለውን አበል ያስወስናል ፣ ለጽ / ቤቱ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለጽ / ቤቱ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ይሰጣል ፣ ስለ ጉባዔው የሥራ እንቅስቃሴ በየዓመቱ መጨረሻ ወይም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ያቀርባል ። ስለጉባዔው አባላት ፩ . እያንዳንዱ ጉባዔ አምስት አባላት የሚኖሩት ሲሆን ፤ ከአባላቱ መካከል አንድ ሰብሳቢና እርሱ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ የሚሠራ ምክትል ሰብሳቢ ይኖረዋል ፣ ጉባዔው ከንግዱ ኅብረተሰብ የሚወከሉ አባላት የሚኖሩት ሲሆን ፣ የተወካይ አባላቱ ቁጥርና የሚወከ ሉበት ሥርዓት በመመሪያ ይወሰናል ፣ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እንደተጠበቀ ሆኖ ሌሎች አባላት በጉባዔው ፕሬዚዳንት አቅራቢነት በመንግሥት ይሾማሉ ፤ የጉባዔው አባላት የአገልግሎት ዘመን አራት ዓመት ይሆናል ። ሆኖም ማንኛውም የጉባዔ አባል ለተጨማሪ አንድ የአገልግሎት ዘመን ሊመረጥ ወይም ሊሾም ይችላል ። ፲፩ . የጉባዔው ሰብሳቢ ሥልጣንና ተግባር የጉባዔው ሰብሳቢ ፤ የይግባኝ ክርክር በሚሰማበት ወቅት በሰብሳቢነት | 11. Powers and Duties of the Chaimman of the the Tribunal . ይመራል ፣ ሥነ ሥርዓት መጠበቁን ይቆጣጠራል ፣ በቃለ ጉባዔ የሚያዙ ወይም በውሳኔ ውስጥየሚመዘገቡ የቃል ወይም የጽሑፉ ክርክሮች ሁሉ በሚገባ መያዛቸ ውንና መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል ። ፲፪ : ስለ ጉባዔው ጽሕፈት ቤት የጽሕፈት ቤቱ ተጠሪነት ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል ። ጽሕፈት ቤቱ ፤ ሀ ) ባለሥልጣኑ ያስተላለፋቸውን የግብር ውሳኔዎች በመቃወም በሚቀርቡ ይግባኞች በዚህ ሕግ ይግባኝ ስለማቅረብ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው መቅረባቸውን በማረጋገጥ ይቀበላል ፣ ለ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ ( ሀ ) የተቀበላቸውን ይግባኞች በሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ለጉባዔው ይመራል ፣ ሐ ) የጉባዔውን ውሳኔዎችና ሰነዶች ይጠብቃል ፣ ለጉባዔው አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ድጋፍ ይሰጣል ፣ መ ) ከጉባዔው ፕሬዚዳንት የሚመሩለትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲፫ በጀት ጉባዔው በፌዴራሉ መንግሥት በሚመደብለት በጀት ይተዳ ፲፬ • የሂሣብ መዛግብት ጉባኤው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። የጉባዔው ሂሣብ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወ 1 2 ) The account of the tribunal shall be audited annually by ክለው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል ። ክፍል ሦስት ስለ ይግባኝ ፲፭ ይግባኝ ለማቅረብ መሟላት ስላለባቸው ሁኔታዎች ባለሥልጣኑ ያስተላለፈውን የግብር ውሳኔ በመቃወም የሚቀርብ የይግባኝ ማመልከቻ በጽሑፍ ሆኖ ቢያንስ በሦስት ቅጂዎች መቅረብ ይኖርበታል ። ፪ ግብር ከፋዮች ይግባኝ ለማቅረቢያ በአንቀጽ ፲፮ የተወ ሰነው ጊዜ ኲማለፉ በፊት ለሚቀርበውይግባኝመክፈቻ ከዚህ በታች የተመለከተውን ገንዘብ ባለሥልጣኑ ዘንድ ማስያዝ አለባቸው ፤ ሀ ) በባለሥልጣኑ ከተወሰነው ግብር ሂሣብ ላይ ፪፭ ፐርሰንት ( ሰባ አምስት በመቶ ) ወይም ለ ) በይግባኝ ባዩ ላይ ባለፈው የግብር ዘመን የመጨ ረሻው ግብር ታስቦ ከተወሰነው ልክ ላይ ፻፭ ፐርሰንት ( ሰባ አምስት በመቶ ) ፣ በመያዣነት የሚከፈለው ገንዘብ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ሁኔታ ሲታሰብ ዝቅተኛ የሆነው በቂ ነው ። ሐ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ( ለ ) ድንጋጌ ቢኖርም ፣ በመያዣ የሚከፈለው ገንዘብ ፣ ግብር ከፋዩ ባስታወቀው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ ሊከፈል ከሚገባው በማናቸውም ምክንያት ማነስ የለበትም ። መ ) ግብር ከፋዩ ግብር እንዲከፍል የተጠየቀው ለመ ጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ለመያዣ የሚከፈለው ገንዘብ ቢያንስ ቢያንስ ባስታወቀው ገቢው ላይ ሊከፈል የሚገባውን ግብር ወይም የገቢውን ማስታወቂያ አላቀረበ እንደሆነ እንዲከፍል ከተ ጠየቀው ግማሹን ( H ፐርሰንት ) ለባለሥልጣኑ መክፈል አለበት ። ሠ ) ከዚህ በላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ቢኖሩም በሽያጭና ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅቁጥር፳፰ ፳፭ ( እንደተሻሻለው ) መሠረት ተወስኖ በተጠየቀው ታክስ ላይ ለሚቀርበው ይግባኝ ለባለሥልጣኑ የሚከፈለው የመያዣ ገንዘብ ከተወሰነው ታክስ ከፃ ፐርሰንት ( ሀምሣ በመቶ ) ማነስ የለበትም ። ፲፮ • ይግባኝ የማቅረቢያ ጊዜ ፩ ይግባኝማቅረብ የሚቻለው የግብሩ ውሳኔ ማስታወቂያ ለግብር ከፋዩ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ በሰላሣ ቀን ውስጥ ነው ። ፪ ግብር ከፋዩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተመለ ከተው ጊዜ ውስጥይግባኙን ካላቀረበ ወይምከዚህ በላይ በአንቀጽ ፲፭ የተመለከተውን ማስያዣ ሳያሲዝ ወይም ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ በባለሥልጣኑ የተወሰነው ግብር ትክክለኛና የመጨረሻ ሆኖ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናል ። ፲፯ ስጉባዔው በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ስለማቅረብ ባለሥልጣኑ ወይም ግብርከፋዩ ጉባዔውየሰጠው ውሳኔ ሕግ ነክ በሆነ ጉዳይ ላይ በመሳሳቱ ቅር የተሰኘእንደሆነ ጉባዔው ውሳኔ ከሰጠበት ቀን አንስቶ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ይግባኙን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ማቅረብ ይኖርበታል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት በሕግ ረገድ የተነሣውን ክርክር በመመርመር የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ካገኘው የተሳሳተውን የሕግ ጉዳይ አቃንቶ ውሳኔውን ለሁለቱ ወገኖች በማሳወቅ ለጉባዔው ይመልሰዋል ። ገጽ ፭ሺ፬፻፷፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ሁኔታ የግብር ትመናውን አስመልክቶ ውሳኔ መስጠት አይችልም ። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርብ ይግባኝ ፍ / ቤቱ በይግባኝ በተመለከተው ጉዳይ ላይ ብቻ የተወሰነ ይሆናል ። ፲፰ : ስለ ውሳኔ አፈጻጸም ፩ በጉባዔው በተሰጠ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ ይግባኝ የጉባ ዔውን ውሳኔ አፈጸጸም አያግደውም ። ፪ • የግብሩ ግምት በመጨረሻው የፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት የተሻሻለ ወይም የተለወጠ እንደሆነ ፣ ሀ ) ከሚገባው በላይ ተከፍሎ እንደሆነ በተጨማሪ የተከፈለው ለግብር ከፋዩ ወዲያውኑ ይመለሳል ፣ ለ ) ግብር ከፋዩ መክፈል ከሚገባው በታች ግብር ከፍሎ እንደሆነ ተጨማሪውን ገንዘብ ወዲያውኑ ይከፍላል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፱ • የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ይህን አዋጅ በማስፈጸም ረገድ ከግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ጋር የመተባበር ግዴታ አለበት ። ፳ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ፩ . ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በባለሥልጣኑ በተወሰነ ግብር መነሻ በግብር ይግባኝ ጉባዔ በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮች በዚህ አዋጅ መሠረት በተቋቋመው ጉባኤ ይታያሉ ። ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች በዚህ አዋጅ መሠረት በተቋቋመው ጉባዔ እንደተሰጡ ውሳኔዎች ይቆጠራሉ ። ፳፩ : ተፈጻሚነት የሌላቸው ሕጎች ፩ ከማናቸውም ገቢ ግብር ስለማስከፈል የወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፷፫ / ( እንደተሻሻለው ) ከአንቀጽ ፴፱ እስከ አንቀጽ ፰፩ ( ጨምሮ ) ያሉት ድንጋጌዎች ፣ እና ፪ : ይህን አዋጅየሚቃረኑማናቸውም ሕጎች ወይምደንቦች በዚህ አዋጅ ውስጥ የተሸፈኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፳፪ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፱ ቀን ፲፱፻ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ