የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፲፭ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፫ / ፲፱፻፶፪ ዓም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገጽ ፩ሺ፪፻፲፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፵፪ የጅማ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ w ጊ ኣንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ | of the Executive Organs of the Federal Democratic Republic አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጅማ ዩኒቨርሲቲማቋቋሚያ የሚኒስትሮችምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፰ ህየን፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ፡ ፩ . “ መንግሥት ” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ነው፡ ፪ . “ ቦርድ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፯ መሠረት የተቋቋመው የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ነው ፡፡ ፫ . “ ጉባዔ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ መሠረት የተቋቋመው የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ነው፡ “ የአካዳሚክ ሠራተኛ ” ማለት በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሠማራ ሠራተኛ ነው፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪፻፲፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : Federal Negarit Gazeta No.15 22 December , 1999 - Page 1213 ፭ “ ፕሬዚዳንት ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲ መሠረት የሚሾም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ነው፡ ፮ . “ ዩኒቨርሲቲ ” ማለት በዚህ ደንብ አንቀጽ ፫ መሠረት የተቋቋመው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ነው ። ፫ . መቋቋም ፩ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ( ከዚህ በኋላ “ ዩኒቨርሲቲውን ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል፡ ፪ ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞችን ያካትታል፡ ሀ ) ጅማ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት፡ ለ ) ጅማ እርሻ ኮሌጅ፡ ሐ ) ወደፊት በቦርዱየሚቋቋሙ ሌሎችፋኩልቲዎችና ኮሌጆች ። ፫ . የዩኒቨርሲቲው ተጠሪነት ለትምህርት ሚኒስቴር ይሆናል ። ፬ ዓላማ ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡ ፩ ዕውቀትን ማዳበር፡ ማስፋፋትና ማስተላለፍ፡ ከዘር፡ ከብሔር፡ ከዖታ፡ ከሃይማኖትና ከመሳሰሉት ኣድ ልዖዎች ነፃ የሆነ በመከባበር፡ መተማመን፡ መተሳሰብና መቻቻል ላይየተመሠረተና ሁለንተናዊ ስብዕናን የሚያ በዕግና የሰው ልጅ ክቡርነትን የሚያጠናክር ትምህርት መስጠት፡ የሥራ ክቡርነትንና የኅብረተሰብ ብልዕግናን የሚያ ራምድ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ ማድረግ፡ 6 • የኢትዮጵያን ሕዝብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን በሳይንስ በቴክኖሎጂ፡ በሥነ ጥበባትና በልዩ ልዩ ሙያዎች የሠለጠኑ፡ ኅብረተሰብን በሚገባ ሊያገለግሉ የሚችሉ ሰዎች ማፍራት፡ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የሚረዳ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፡ ጠቃሚ ውጤቶችን ማሠራጨት፡ ፮ የክልሉን ሕዝብም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማፋጠን የሚረዱ ሙያዊግልጋ ሎቶች ማበርከት፡ ፯ የአገልግሎት ክፍያን በመቀበል የምክርና ሥልጠና አገልግሎት መስጠት ። ፭ የዩኒቨርሲቲው ሥልጣንና ተግባር ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ ፋኩልቲዎች፡ ኮሌጆችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ተቋሞች ማቋቋምና ማካሄድ፡ ፪ የቅድመ ምረቃና የድኅረ ምረቃ መቀየስና ሥራ ላይ ማዋል፡ የምስክር ወረቀት፡ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሁም ለከፍተኛ ውጤትና አስተዋጽኦ አካዳሚክ ሜዳይ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት፡ ፬ . ሴሚናሮች ወርክሾፖችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋጀትና ማካሄድ፡ ? ሥ ' . ገጽ ፩ሺ፪፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta No.15 22 December , 1999- ~ Page 1214 ፭ የአገልግሎት ክፍያ በመቀበልና በገበያ ውስጥ በመግባት የማማከርና አገልግሎት መስጠት፡ በሀገሪቱ ውስጥና በሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ አቻ ዩኒቨርሲቲዎች፡ የምርምርተቋሞችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ጋር ግንኙነት መመሥረት፡ ፯ የትምህርት መጽሔቶችና ጋዜጦች ማቋቋምና ማሠራጨት፡ ፰ የንብረት ባለቤት የመሆን፡ ውል የመዋዋል፡ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ፡ ፲፩ ዓላማውን የሚያራምዱ ሌሎች ተግባሮችን ማከናወን ፡፡ ክፍል ሁለት ስለዩኒቨርሲቲው የፖሊሲና የሥራ አስፈጻሚ አካላት ፮ ስለዩኒቨርሲቲው ቦርድ መቋቋም ፩ ዩኒቨርሲቲው በመንግሥት የሚሰየሙ አንድ ሊቀመን በርና ቁጥራቸው እንደአስፈላጊነቱ የሚወሰን አባላት የሚገኙበት ቦርድ ይኖረዋል ። ቦርዱ የራሱ ፀሐፊ ይኖረዋል ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክና የአስተዳደር አጠቃላይ ፖሊሲ ያወጣል ፡ ከመንግሥት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር በተገናዘበ መልኩ ይወስናል ፡ ፪ • የዩኒቨርሲቲውን አደረጃጀት ይወስናል ፡ ፫ ዩኒቨርሲቲው ወደፊት የሚደራጅበትንና የሚተዳደር በትን ቻርተር እንዲዘጋጅ በማድረግ ለመንግሥት ያቀርባል ፡ ፬ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያፀድቃል ፡ የዩኒቨርሲቲውን ዕቅድና በጀት ያስፀድቃል ፡ ፮ የዩኒቨርሲቲውን ም'ፕሬዚዳንቶች ሹመት ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርቦ ያስጸድቃል ፡ ጊ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚቀጠሩበ ትንና የሚተዳደሩበትን ሁኔታ የሚወስን የውስጥ አስተ ዳደር ደንብ ከመንግሥት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር በማገናዘብ ያወጣል ፡ ዩኒቨርሲቲውን በሚመለከት በማንኛውም የዩኒቨር ሲቲው አካል ወይም በዩኒቨርሲቲው በተሰጠ ውሳኔ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል ፡ ፬ ዩኒቨርሲቲው ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን የአካዳሚክ ስምምነቶች መርምሮ ያፀድቃል ፡ ፲ የዩኒቨርሲቲው መለያ ምልክት የሚሆነውን ዓርማ ያጸድቃል፡ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ይወስናል ፣ ፲፪ ዩኒቨርሲቲው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች መንግሥት ባፀደቀው መመሪያ መሠረት ይወስናል ፡ ፲፫ የዩኒቨርሲቲውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ። ፭ : አጠቃላይ የፈተ .. ፀጥና ደረጃዎች አቅጣጫዎችን ገጽ ፩ሺ፪፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta – No.15 22 December , 1999- ~ Page 1215 ፫ . የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ሴኔት መቋቋም ፩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘ የዩኒቨርሲቲው ጉባዔ ይቋቋማል ፡ ሀ ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ለ ) የዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች ሐ ) የየፋኩልቲው ዲኖች መ ) የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ... ሠ ) በተቋሙ የአካዳሚክ ሠራተኞች የሚመረጡ ሁለት ወኪሎች . ረ ) ሁለት የተማሪዎች ተወካዮች ሰ ) ቦርዱ የሚሰይማቸውኣግባብነት ያላቸው ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አካላት ፪ . የጉባዔው ተጠሪነት ለቦርዱ ይሆናል ። ፬ የጉባዔው ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚያወጣው አጠቃላይ መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉባዔው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፡ ፩ . የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ካሌንደር ያጸድቃል ፡ ፪ የዩኒቨርሲቲውን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያጸድቃል፡ ፫ ዲግሪዎች : ዲፕሉማዎችና የምስክር ወረቀቶች እንዲሁም ሜዳይና ሽልማቶች የሚሰጡበትን ሁኔታ ይወስናል፡ 0 የተማሪዎች አቀባበልን ፡ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን ፡ የዲሲፕሊን ጉዳዮችንና ምረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል ፡ በነዚህም ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ፡ ይወስናል ፡ ፮ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ሠራተኞች ቅጥርመርምሮ ያጸድቃል ፡ ፯ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ለቦርዱ ሃሳብ ያቀርባል ፡ ፰ ዩኒቨርሲቲው የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች እንዲ ወስን ለቦርዱ ሃሳብ ያቀርባል ፡ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ይወስናል ፡ በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመትና ተጠሪነት ፩ . የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በመንግሥት ይሾማል ፡ተጠሪ ነቱም ለቦርዱ ይሆናል ። ፪ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች በዚህ ደንብ አንቀጸቺንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ይሾማሉ፡ተጠሪነታ ቸውም ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል ። ፲፩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የዩኒቨርሲቲው ዋና መሪና አስፈጸሚ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ በበላይነት ይመራል፡ ያስተዳ ድራል፡ ይቆጣጠራል፡ በቦርዱና በጉባዔው የተላለፉ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል ፡ ገጽ ፩ሺ ፻፲፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta No.15 22 December , 1999 - Page 1216 ፫ . የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚክ ሠራተኞች ቦርዱ በሚያ ወጣው መተዳደሪያ ደንብና መንግሥት ባጸደቀው የደመወዝ ስኬል መሠረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን የአስተዳደር ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ፩ . የዩኒቨርሲቲውን ዓመታዊ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፤ በቦርዱ ሲፈቀድ በዩኒቨርሲቲው ስም የሚደረጉ ማናቸ ውንም ስምምነቶችና የውል ሰነዶች ይፈርማል ፡ ፮ ዩኒቨርሲቲው ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ዩኒቨርሲቲውን ይወክላል ፡ ፰ ስለዩኒቨርሲቲው የሥራ እንቅስቃሴ ለቦርዱ በየሦስት ወሩ ሪፖርት ያቀርባል ፡ ፬ እንደአስፈላጊነቱ ሥልጣኑን በውክልና ይሰጣል ፡ በቦርዱና በጉባዔው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ስለዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር የዩኒቨርሲቲው ም / ፕሬዚዳንቶች በዩኒቨርሲቲው ፕሬ ዚዳንት በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩዋቸዋል ፡ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ በሚመለከት የዩኒቨርሲ ቲውን ፕሬዚዳንት ያማክራሉ ፡ ይረዳሉ ፡ ለእነርሱ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎችን ሥራ ይቆጣጠራሉ፡ በቦርዱና በጉባዔው የተላለፉ ውሣ ኔዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላሉ፡ ሐ ) በቦርዱ : በጉባዔውና በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናሉ ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በማይኖርበት ጊዜ የዩኒቨር ሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም / ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳ ንቱን ተክቶ የዩኒቨርሲቲውን ሥራ ይመራል ፡ ያስተባ ብራል ። ፲፫ . የዩኒቨርሲቲው ሌሎች አካላት የዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ፋኩልቲዎች፡ የትምህርትና የምርምር ክፍሎች፡ አመሠራረትና አሠራር እንዲሁም የአመራር አካላት አሰያየም በቦርዱ ይወሰናል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ፲፬ በጀት የዩኒቨርሲቲው በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፡ ሀ ) ከመንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፡ ለ ) ዩኒቨርሲቲው ከሚሰበስባቸው የአገልግሎት ክፍያዎች፡ ሐ ) ከሌሎች ምንጮች ። ፲፭ የሂሣብ መዛግብት ፩ ዩኒቨርሲቲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የዩኒቨርሲቲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ገጽ ፩ሺ፪፻፲፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፲፮ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ይህን ደንብ የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት እይኖራቸውም ። ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ