×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ 5 1991 የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፵፯ አንቀጽ ፭ መሠርይ ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ነሐሴ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፬ / ፲፱፻፲፩ ዓ.ም የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፩ሺ፩፻፲ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፵፬ / ፲፱፻፵፩ የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት | 1. Short Tite ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፵፬ ፲፱፻፶፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ : የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት / ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፫ : ዋና መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ በማና ቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፬ ዓላማ የኢንስቲትዩቱ ዓላማ በአገሪቱ ልማት ላይ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ይሆናል ፡፡ ያንዱ ዋጋ 2.30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፩፻፵፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፰ ነሐሴ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ፭ ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ የልማት ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ የሚረዱ ጥናቶችና ምርምሮችን የማካሄድ፡ ፪ መንግሥት ሥራ ላይ ያዋላቸው የልማት ፖሊሲዎች ያስከተሉትን ውጤት የመገምገም፡ ፫ • ለሚያካሂደው ጥናትና ምርምር የሚያስፈልጉትን መረጃዎች የመሰብሰብና በሌሎች አካላት የተሰበሰቡ ትንም የመጠቀም፡ የምርምር ውጤቶችን የማሳተምና የማሰራጨት፡ ፭ በልማት መስክ የምክር አገልግሎት የመስጠት፡ ለዓላማው መሳካት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ከሚችሉ የአገር ውስጥም ሆኑ የውጭ አገር ተቋሞች ጋር ግንኙነት የመመሥረት፡ ፯ የንብረት ባለቤት የመሆን፡ ውል የመዋዋልና በስሙ የመክሰስና የመከሰስ፡ ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን የማከናወን ። ፮ . የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ፡ ፩ በመንግሥት የሚሾም አንድ ዲሬክተር፡ እና ፪ አስፈላጊው ሠራተኞች፡ ይኖሩታል ። ፯ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ የኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች ይመራል፡ ያስተዳድራል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዲሬክተሩ፡ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የኢንስቲት ዩቱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጎችን መሠረታዊ ዓላማዎች በመከተል የኢንስቲትዩቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ሐ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ ፕሮግራሞችና በጀት አዘጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ / ቤት ያቀርባል ፤ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፡ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኢንስቲትዩቱን ይወክላል ፣ ረ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርት ኣጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ / ቤት ያቀርባል ። ፫ ዲሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ፤ ሆኖም ዲሬክተሩ በማይኖርበት ጊዜ እርሱን ተክቶ የሚሠራው ሰው ከ፴ ቀናት በላይ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ / ቤት ቀርቦ መፈቀድ አለበት ። ፰ በጀት ፩ የኢንስቲትዩቱ ከሚከተሉት ምንጮች 8. Budget የተውጣጣ ይሆናል፡ ገጽ ፩ሺ፩፻፵፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፰ ነሐሴ ፳፩ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም ሀ ) በመንግሥት ከሚመደብለት በጀት ፤ ለ ) ከምክር አገልግሎት ክፍያዎችና ከሕትመቶች ሽያጭ ገቢ ፤ ሐ ) ከሚያገኘው ማናቸውም ስጦታና ዕርዳታ ። በዚህ አንቀጽንዑስ አንቀጽ ፩ ( ለ ) እና ( ሐ ) የተመለከተው ገንዘብ በኢንስቲትዩቱ ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ሆኖ ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደው በጀት መሠረት ወጪ ይደረጋል ። ፱ • የሂሳብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ • የኢንስቲትዩቱ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ነሐሴ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?