የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ ኣዲስ ኣበሳ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፳፫ ፲፱፻፷፰ ዓም የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ ገጽ ፻፲፱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፫ / ፲፱፻፳፰ ዓ.ም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ . አዋጅ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፷፰ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ማሻሻል በማስ ፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | Mining Income Tax Proclamation ; መንግሥትአንቀፅ ፴፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር ( ማሻሻያ ) ኣዋጅ ቁጥር ፳፫ / ፲፱፻፷፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ማሻሻያ የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፲፱፻፷፭ | 2. Amendment አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተተክቷል ፤ “ ፩ . ማንኛውም በከፍተኛ ወይም በአነስተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረት ሥራ የተሰማራ ባለፈቃድ ግብር ከሚከፍልበት ገቢው ላይ ፴፭ ፐርሰንት የገቢ ግብር ይከፍላል ። ” ፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅከየካቲት፯ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፻፩ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፫ ፲፱፻፵፰ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ! የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፑብሊክ አስፈጻሚ አካሳትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ኑዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዝጊ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ እውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፫ ፲፱፻ T ፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ( ከዚህ በኋላ “ ኮሌጁ ” ተብሎ የሚጠራ ) እራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ጅ ኮሌጁ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ኮሌጁ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ የኢትጵያን ሕዝብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አፋጠን በተለይ በክልሎች በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሚያገለግሉ ሠራተኞችን በሥነ ጥበባትና በልዩ ልዩ ያዎች ማሰልጠን ኅብረተሰቡን በሚገባ ሊያገለግሉ የሚችሉበትን ሁኔታዎች መፍጠር ፣ ምልመላ ላይም ለሴቶችና ለኋላ ቀር ክልሎች ልዩ ግምት እንዲሰጥ ማድረግ ፤ ፪ ዕውቀት ማዳሰር ፣ ማስፋፋትና ማስተላለፍ ፡ ፫ ከዘር ፣ ከብሔር ፣ ከጾታ ፣ ከኃይማኖትና ፣ ከመሳሰሉት አድሎዎች ነጻ የሆነ በመከባበር ፣ በመተማመን ፣ በመተሳ ሰብና መቻቻል ላይ የተመሠረተና ሁለንተናዊ ስብዕናን የሚያበለጽግና የሰው ልጅ ክቡርነትን የሚያጠናክር ትምህርት መስጠት ፤ ፬ . የሥራ ክቡርነትንና የኅብረተሰብን ብልጽግና የሚያራምድ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ ማድረግ ፤ ፭ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ሳይንሳዊ የሆነ ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን ማሰራጨት ። ፬ ስለኮሌጁ ሥልጣንና ተግባር ኮሌጁ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ፋክሊቲዎችና ሌሎች የትምህርትና የምርምር ክፍሎች ወይም ተቋሞች ማቋቋም ፤ ፪ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መቀየስና ሥራ ላይ ማዋል ፤ ፫ የምስክር ወረቀት ፣ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሁም ለከፍተኛ ውጤትና ኣስተዋጽኦ አካዳሚክ ሜዳይ ፣ ሽልማትና ማዕረግ መስጠት ፤ ፬ ሴሚናሮች ፣ ወርክሾፖችና ሲምፖዚየሞችን ማዘጋጀትና ማካሔድ ፤ ጅ በሀገሪቱ ውስጥና በሌሎች ሀገሮች ከሚገኙ አቻ ተቋሞች፡ የምርምር ተቋሞችና ተመሣሣይ ዓላማ ካላቸው ጋር ግንኙነት መመስረት 1 ፮ የትምህርት መጽሔቶችና ጋዜጦችማቋቋምናማሰራጨት ገጽ ፻፳፩ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻ r ዓም : Negarit Gazeta – No. 11 15February 1996 - Page 121 • የንብረት ባለቤት መሆን ፤ ቋ ውል መዋዋል ፩ በስሙ የመክሰስና የመከሰስ ፤ ፲ ዓላማውን የሚያራምዱ ሌሎች ተግባሮችማከናወን ። ክፍል ሁለት ስለኮሌጁ የፖሊሲና የሥራ አስፈጻሚ አካላት ስለኮሌጁ ቦርድ መቋቋም ፩ ኮሌጁ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾሙ ሰባት ኣባላት ያሉት | 5. Establishment of Board of Govemos of the College ቦርድ ይኖረዋል ። ፪ ቦርዱ የራሱ ፀሐፊ ይኖረዋል ። ፮ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የኮሌጁን የአካዳሚክና የአስተዳደር አጠቃላይ ፖሊሲ ያወጣል ፣ ይወስናል ፤ ፪ ኮሌጁ የሚተዳደርበትን ቻርተር አዘጋጅቶ ለመንግሥት ያቀርባል ፤ ፫ የኮሌጁን አደረጃጀት ይወስናል ፤ ፩ የኮሌጁን ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቦ ያስፀድቃል ፤ ፭ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያፀድቃል ፤ ፯ በኮሌጁ በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሰማሩ የኣካዳሚክ ሠራተኞች የሚቀጠሩበትንና የሚ ተዳደሩበትን ሁኔታ ይወስናል ፤ ፯ • የኮሌጁን ዕቅድና ረቂቅ በጀት ያፀድቃል ፤ ፰ የኮሌጁ መለያ ምልክት የሚሆነውን አርማ እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፤ ፱ ኮሌጁ የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች ይወስናል ፤ ፲ ኮሌጁን በሚመለከት በማንኛውም የኮሌጁ አካል ወይም በኮሌጁ በተሰጠ ውሣኔ ቅር የተሰኘ ግለሰብ የሚያቀር በውን አቤቱታ መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል ፤ ፲፩ ኮሌጁ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት ጋር የሚያደርጋቸውን የአካዳሚክ ስምምነቶች መርምሮ ያፀድቃል ፤ ፲፪ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ፤ ፲፫ የኮሌጁን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባ ሮችን ያከናውናል ። ፯ የፋክሊቲካውንስል መቋቋም ( ሴኔት ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አባላት የያዘ የኮሌጁ ፋክሊቲ ካውንስል ይቋቋማል ፤ ፩ : የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ፪ የኮሌጁ ም / ፕሬዚዳንቶች ፫ የፋክሊቲውዲኖች ጅ የኮሌጁ ሬጂስትራ ጅ የተማሪዎች ዲን ፮ ከኮሌጁ በቋሚመምህራን ተመራጭ የሆኑ ሦስት መምህራን ፯ በተማሪዎች የሚመረጥ አንድ የተማሪዎች ፰ በፋክሊቲ ካውንስሉ የሚመረጥ ፰ የክሊቲ ካውንስል ሥልጣንና ተግባር የፋክሊቲካውንስሉ ተጠሪነቱ ለኮሌጁፕሬዚዳንት ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠ w ው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የኮሌጁን የትምህርት ካሌንደር መርምሮ ያፀድቃል ፤ ገጽ ደ ss ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም . Negarit Gazeta No. 11 159February 1996 – Page 122 ► ኮሌጁን ልዩ ልዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያፀድቃል ፤ ፫ ዲግሪዎች እንዲሁም ዳይና ሽልማቶች የሚሰጡበትን ሁኔታ ይወስናል ፤ ጅ የተማሪዎች አቀባበልን ፣ የትምህርት ደረጃ አወሳሰንን ፣ የዲስፕሊን ጉዳዮችንና ምረቃን የሚመለከቱ መመዘኛ መስፈርቶችን ያወጣል ፣ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ቅሬታዎችን መርምሮ ውሣኔ ይሰጣል ፣ ጅ አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ዘዴና ሁኔታን ይወስናል ! ፮ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጥ ለቦርዱ ሀሣብ ያቀርባል ፣ ሌሎች የአካዳሚክ እድገቶችን ይወስናል ፤ • የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ያወጣል ፤ # በቦርዱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። # ስለ ኮሌጁ ፕሬዚዳንትና ም / ፕሬዚዳንቶች ሹመትና ተጠሪነት ፩ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሾማል ፣ ተጠሪነቱም ለቦርዱ ይሆናል ። * የኮሌጁ ም / ፕሬዚዳንቶች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፪ ) መሠረት ይሾማሉ ፤ ተጠሪነታቸውም ለፕሬዚዳንቱ ይሆናል ። ፤ ስለኮሌጁ ፕሬዚዳንት ሥልጣንና ተግባር የኮሌጁ ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች | 10. Powers and Duties of the President of the College . ይኖሩታል ፤ ፩ : የኮሌጁን ሥራ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ይቆጣጠራል ፤ ጅ በቦርዱና በፋክሊቲ ካውንስሉ የሚሰጡ ውሣኔዎችና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፡ ያረጋ ግጣል ፤ ፫ በኮሌጁ በማስተማር ወይም በምርምር ተግባር ላይ የተሰማሩ የአካዳሚክ ሠራተኞችን ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ደመወዝና አበላቸውን ይወስናል እንዲሁም የኮሌጁን የአስተዳደር ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ያስተ ጻድራል ፤ ፪ የኮሌጁን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ለቦርዱ አቅርቦ ያስወስናል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፡ ጅ በቦርዱ ሲፈቀድ በኮሌጁ ስም የሚደረጉትን ማናቸውንም ስምምነቶችና የውል ሰነዶች ይፈርማል ፤ ፕ በኮሌጁ ስም የባንክ ሂሣብ ይከፍታል ያንቀሳቅሳል ፤ ኮሌጁን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወክላል ፤ ፰ በየሶስት ወሩ ስለ ኮሌጁ የሥራ እንቅስቃሴ ለቦርድ ሪፖርት ያቀርባል ፤ በቦርዱና በፋክሊቲ ካውንስሉ የማሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል ። ፲፩ ስለ ኮሌጁ ም ፕሬዚዳንቶች ሥልጣንና ተግባር ፩ . የኮሌጁ ም / ፕሬዚዳንቶች ከኮሌጁ ፕሬዚዳንት በሚሰ | 11. Powes and Duties of the Vice - Presidents of the College . ጣቸው መመሪያ መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩዋቸዋል ፣ ሀ ) የኮሌጁን ሥራ በሚመለከት የኮሌጁን ፕሬዚዳንት ያማክራሉ ፣ ይረዳሉ ፤ ለ ) ለነርሱ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ክፍሎችና በቦርዱና በፋክሊቲ ካውንስሉ የተሰጡ ውሣኔዎችና መመሪ ያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላሉ ! ያረጋግጣሉ ፤ ሐ ) ኮሌጁ የሚሰጣቸው ትምህርቶች በፋክሊቲ ካውንስሉ በፀደቀው የትምህርት ካሌንደርና የትምህርት ፕሮግ ራሞች መሠረት መካሄዳቸውን ይክታተላሉ'ያረጋ ግጣሉ 1 ገጽ ፻፳፫ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ - ም- Negarit Gazeta No. 11 15February 1996 Page 123 መማር ማስተማሩ ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችና አገልግሎቶች እንዲሟሉ ያደርጋሉ ፤ ቦርዱ ፣ በፋክሊቲ ካውንስሉና በፕሬዚዳንቱ ተለይተው የሚሰጧቸውን ሌሎች ተግባሮች ያከና ውናሉ ። ፪ የኮሌጁ ፕሬዚዳንት በማይኖርበትጊዜየኮሌጁ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም / ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንቱን ተክቶ የኮሌጁን ሥራ ይመራል ፣ ያስተባብራል ። ፲፪ ስለ አካዳሚክ ኮሚሽን መቋቋም እያንዳንዱ የትምህርት ፋክሊቲ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን | 12. Establishment of Academic Commission አባላት የያዘና ተጠሪነቱ ለካውንስሉ የሆነ የራሱን የአካ ዳሚክ ኮሚሽን ያቋቁማል ፤ ፩ . የፋክሊቲው ዲን ፪ የፋክልቲው ም / ዲን ፫ የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ፩ በፋክሊቲው ቋሚ መምህራን የተመረጡ ስት መምህራን ኙ ከሦስቱ የመምህራን ተወካዮች አንዱ ..... ፲፫ የአካዳሚክ ኮሚሽን ሥልጣንና ተግባር አካዳሚክ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ • የኮሌጁን የአካዳሚክ ፖሊሲ በመከተል የፋክሊቲውን የትምህርት ካሌንደርና የትምህርት ፕሮግራሞች ያዘጋጃል ፣ በፋክሊቲ ካውንስሉ ሲፀድቅም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ጅ ለየትምህርት ዓመቱ በሚፀድቀው የትምህርት ካሌንደርና የትምህርት ፕሮግራሞች መሠረት በፋክሊቲው የሚሰጡ ፈተናዎችን ይወስናል ፤ ፫ ትምህርታቸውን በሚገባ ላጠናቀቁየፋክሊቲው ተማሪዎች ዲግሪ እንዲሰጥ ለፋክሊቲ ካውንስሉ ሃሣብ ያቀርባል ፤ ፩ ወደሚቀጥለው የትምህርት እርከን የሚሸጋገሩ ተማሪ ዎችን ዝርዝር ለፋክሊቲ ካውንስሉ አቅርቦ ያስወስናል ፤ ፭ ፋክሊቲውን የሚመለከቱማናቸውንም የአካዳሚክችግሮች መርምሮ ይወስናል ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ፲፪ የኮሌጁ ሌሎች አካላት የኮሌጁ ልዩ ልዩ የትምህርትና የምርምር ክፍሎች የአመራር ኣካላት ኣመሠራረትና አሰራር በቦርዱ ይወሰናል ። ፲፭ በጀት የኮሌጁ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ፩ ከፌዴራል መንግሥቱ ከሚመደብለት በጀት ፣ ፪ ኮሌጁ ከሚሰበስባቸው የአገልግሎት ክፍያዎች ፤ እና ፫ ከሌሎች ምንጮች ። ፲፮ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች ይህን ደንብ የሚቃረኑ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ገጽ ፻፳፱ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፩ የካቲት ፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ ም • Negarit Gazeta No. 11 15February 1996– Page 124 ፲፯ ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። ኣዲስ ኣበባ የካቲት ፲ቀን ፲፱፻፳፰ ዓቅ : መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ "