የ ! ( @ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፱ አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ ፲፱፻፶፬ ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕረፍትና የሥራ ጊዜ ( ማሻሻያ ) ገጽ ፩ሺ፮፻፸፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ ፲፱፻፲፬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የዕረፍትና የሥራ ጊዜ ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕረፍትና የሥራጊዜን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ማሻሻል በማስፈለጉ ፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) እና ፲፰ የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕረፍትና የሥራ ጊዜ ( ማሻሻያ ) አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፫ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። 3. ማሻሻያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕረፍትና የሥራ ጊዜን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፴፪ ፲፱፻፳፰ እንደሚከ ተለው ተሻሽሏል ፤ ፩ . የአዋጁ አንቀጽ ፪ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ፣ ያንዱ ዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሺ፩ ገጽ ሺ፮፻፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፲ከም ዓም ፪ . የዕረፍት ጊዜ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዕረፍትጊዜ በየዓመቱ ከየካቲት ፩ እስከ የካቲት ፴ እና ከሐምሌ ፩ እስከ መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ዋዜማ ድረስ ይሆናል ። ” ፪ . የአዋጁ አንቀጽ ፫ እንደሚከተለው ተሻሽሏል ! የሥራ ጊዜ “ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜ በየዓመቱ ከመስከረም ወር የመጨረሻሳምንት ሰኞእስከ ጥር ፴እና ከመጋቢት ፩ እስከ ሰኔ ፴ ድረስ ይሆናል ። ” • አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ታህሣሥ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ