መመም እራቅቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች በ26-12-96 ለችሎቱ ጽፎ መዝገቡ ለሠበር ችሉም ናሻነት ነው ::
የሰበር መ / ቁ 16943
ኅዳር 19 ቀን 1999 ዳኞች፡ 1. አቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ 3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች የኪ.ቤኢድርጅት ተጠሪ ወ / ሮ አሰገደች ወ / ማርያም - ቀረቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፤
ፍ ር ድ
ባቀረበው የሠበር ቅሬታ ማመልከቻ
የአሁኑ አመልካች በሥር ፍ / ቤት በተጠሪ ላይ በመሠረተው ክስ ፣
የአሁኑ ተጠሪ
በወረዳ 8 ቀበሌ 22 ቁ 079 የሆነውን ቤት በማካካሻነት ይዘው በወረዳ 14 ፣ ቀበሌ 21 ፣
ቁጥር 241 እና 242 የሆነው ቤት እስኪመለስላቸው ልዩነቱን እየከፈሉ ሲገላገሉ ቆይቷል ፤
ሆኖም የምርጫ ቤታቸውን በ 13 / 10 / 83 የተመለሰላቸው መሆኑን ተገልጾላቸው በልዩነቱ
ላይ ያልከፈሉትን ቀሪ ሂሣብ ከፍለው ቤቱን እንዲያስረክቡ ቢገለጽላቸውም ፈቃደኛ
ስላልሆኑ ቤቱን እንዲያስረክቡ የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት በአመልካችና
በተጠሪ መካከል ሕዳር 1
ቀን 1982 የተደረገው
« ተጠሪ የምርጫ ቤታቸው
ሲመለስላቸው ቤቱን ይለቃሉ የሚል አንቀጽ የለም » በሚል የአሁኑ አመልካችን ጥያቄ
ውድቅ አድርጉታል ። ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፌ / ከ / ፍ / ቤትም የሥር ፍ / ቤትን ውሣኔ
አጽንቶታል ፡፡
ተጠሪ ከአመልካች የተከራየውን ቤት ሊያስረክብ አይገባም የተባለው በአግባቡ መሆን
አለመሆኑን ለመመርመር መዝገቡ ለሰበር ችሎቱ ቀርቦ የግራ ቀ , የጽሁፍና የቃል ክርክር
ተመርምሯል ፡፡
በበኩላችን በአመልካችና በተጠሪ መካከል ህዳር 1 ቀን 1982 የተደረገ የኪራይ
ያለ መሆኑን ተረድተናል ፡፡ ተጠሪም ቢሆኑ
የምርጫ ቤታቸው ሲመለስላቸው
በማካካሻነት የያዙትን የአመልካች ድርጅትን ቤት እንደሚለቁ ተስማምተው የነበረ መሆኑን
ከሥር ክርክሩ ለመረዳት ችለናል ። ሆኖም የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት « ተጠሪ የምርጫ ቤታቸው
ሲመለስላቸው ቤቱን ይለቃሉ የሚል አንቀጽ በውሉ ላይ የለም » በሚል ተጠሪ ቤቱን ሊለቁ
አይገባም በማለት የሰጠውን ምክንያት ይህ ችሎት የማይቀበለው ሆኖ አግኝቶታል ፡፡ ሆኖም
ተጠሪ እንዲረከቡ ተወስኖ ተከናውኗል የተባለው
ምርጫ ቤታቸው ለሽራተን አዲስ
ፕርጀክት ማስፋፊያ በሚል የተወሰደ መሆኑን ገልፀው ለችሎቱ ባቀረቡት ክርክር የአመልካች
ድርጅት ተወካይ የበኩሉን አስተያየት እንዲሰጥበት በቃል ተጠይቆ ይህንኑ ለችሎቱ
አስረድቷል ። ሁኔታው በዚህ መሠረት መከናወኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ተጠሪ በስምምነታቸው
መሠረት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገደዳሉ ብሎ ለማለት አልተቻለም ፡፡
በመሆኑም ይህ ችሎት የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት ተጠሪ ቤቱን ሊያስረክቡ አይገደዱም
ለማለት ውሉን መሠረት አድርጐ የገለፀውን ምክንያት በመቀየር ፣
ተጠሪ የምርጫ
ሲመለስላቸው
በማካካሻነት የያዙትን የአመልካች ድርጅት
ለመመለስ
የተስማሙ ቢሆንም ፣
ለስምምነቱ መሠረት የሆነው የምርጫ ቤታቸው ለሌላ ፕሮጀክት
ማስፋፊያ የተወሰደ በመሆኑና ይህም በግራ ቀ , ያልተካደ በመሆኑ በስምምነታቸው መሠረት
የድርጅቱን ቤት የመመለስ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ለማለት አልተቻለም በማለት የሥር
ፍ / ቤት የሰጠውን ምክንያት ቀይረን ውሣውን አጽንተናል ፡፡
ው ሣ ኔ ፣
የፌ / መ / ፍ / ቤት በ 7 / 9 / 95 በመዝገብ ቁጥር 21630 የፌ / ከ / ፍ / ቤት በመ / ቁ
22264 በ 15 / 10 / 96 የሰጡትን ውሣኔና ምክንያቱን ቀይረን አጽንተናል ፤
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
You must login to view the entire document.