×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
ደንብ ቁጥር 10/1989 ዓ•ም• የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሪሽን ማቋቋሚያ የሚ ኒስትሮች ም/ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ 1 ፋብ ቁጥር ፲ ፲፱፻፷፱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ኅዳር ፲፱ ቀን ፲፱፻፳፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ ደንብ ቁጥር ፲ ፲፱፻፳፱ ዓም የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፪፻፳፪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽንን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፫፬ በአንቀጽ ፵፯ ፩ / ሀ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲ / ፲፱፻፵፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ( ከዚህ በኋላ “ ኮርፖሬሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኮርፖሬሽኑ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፫፬ መሠረት ይተዳደራል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣፖሣቁ ተሺ፩ ገጽ ፪፻፳፫ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፮ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመንግሥትየሚሰየም አካል የኮርፖሬሽኑተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ፬ ዋና መሥሪያ ቤት የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ፤ ፩ የመንግሥትን የልማት ፖሊሲናቅድሚያ ትኩረት መሠረት በማድረግ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ማቋቋም ፡ ማካሄድ ፡ መጠገንናማስፋፋት ፤ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የቴሌፎን ፡ የቴሌክስ ' የቴሌ ፋክስ እና ሌሎች የኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን መስጠት ፤ ፫ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ተቀብሎ ማስተላለፍን ጨምሮ በተቀናጀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሚሰጡ የኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን መስጠት ፤ ፬ የቴሌኮሙኒኬሽንናተዛማጅ መሣሪያዎችን መጠገን መገጣ ጠምናማምረት ፤ ፭ ለቴሌኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የሥልጠና አገልግሎት መስጠት ፤ • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፲ : ካፒታል ለኮርፖሬሽኑ የተፈቀደለት ካፒታልብር ፩ቢሊዮን ፬፻፸፫ ሚሊዮን ፱፻፲ ሺህ ፭፻፳፰ ( አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰባ ሦስት ሚሊዮን | 6. Capital ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ፬፻፳ ሚሊዮን ፱፻፶፱ ሺህ ፭፻፸፰ ( አራት መቶ ሰማንያ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሣ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ) በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ተከፍሏል ። ፯ : ኃላፊነት ኮርፖሬሽኑካለው ጠቅላላንብረት በላይ በእዳ ተጠያቂ አይሆንም ። ፰ ኮርፖሬሽኑ የሚቆይበት ጊዜ ኮርፖሬሽኑ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ፱ . የመብትና ግዴታ መተላለፍ በአዋጅ ቁጥር ፩፻፴፩ / ፲፱፻፵፭ መሠረት ይተዳደር የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን መብትና | 9 . Transfer of Rights and Obligations ግዴታዎች በዚህ ደንብ ለኮርፖሬሽኑ ተላልፈዋል ። ፲ : ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም : መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?