የሰበር መ / ቁ 21758
መጋቢት 20 ቀን 1998 ዓም
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ
ሐጉስ ወልዱ
መስፍን ዕቁበዮናስ
ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የአርባምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት
ተጠሪ፡ ግሪንላንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉባዳይ የቦታ አገልግሎት ( የአፈር ኪራይ ) ክፍያ
ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ፣
ክርክሩ የተጀመረው
በአሁኑ አመልካች ከሣሽነት ነው ::
አመልካች በደቡብ ብ / ብ / ሕ / ክ / መ / ለጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍ / ቤት ባቀረበው ክስ ተጠሪ
ከህዳር ወር 1990 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ የሚፈለግበትን ኪራይ እንዲከፍል
ይወሰንበት ዘንድ ጠይቆአል ፡፡ ፍ / ቤቱም የተጠሪን የመከላከያ መልስ ከሰማ በኋላ ክርክሩን
መርምሮ ተጠሪው ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለአመልካች እንዲከፍል ወስኖአል ፡፡ በዚህ ውጭ
ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤትም እንደዚሁ ክርክሩን የሰማ ሲሆን ፣
በመጨረሻም የከፍተኛው ፍ / ቤት የሰጠውን ውሣ አፅንቶአል ። የሰበር አቤቱታ የቀረበለት
የክልሉ ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ችሉት ግን ሁለቱ የስር ፍ / ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በማሻሻል
ተጠሪ ኪራዩን መክፍል ያለበት በሙሉ ሣይሆን ፣ ከፊሉን ብቻ ነው በማለት ውሣ
ሰጥቶአል ፡፡ አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ማለት የሰበር ችሎቱ በመ.ቁ 6694 በ 24.1.98
ዓም በሰጠው ውጭ ላይ ነው ፡፡
ጊዜ ኪራዩን እንድከፍል አልገደድም ። የሚል ምክንያት በመሰጠት ነው ። የጠ / ፍ / ቤቱ ሰበር
እኛም አመልካች በ 4.2.98
ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ
በማድረግ
አስቀርበን
ክርክሩን
ሰምተናል ፡፡
እንዲመረመር የተፈለገው ነጥብ ተጠሪ የተጠየቀውን የቦታ አገልግሉት ኪራይ በሙሉ
የማይከፍልበት የሕግ ምክንያት አለ ወይ ? የሚለው በመሆኑም ይህንኑ መርምረናል ።
አመልካች የቦታ አገልገሎት ኪራይ እንዲከፈለው የጠየቀው በእሱ እና በተጠሪው
መካከል በተደረገው ውል መሠረት ተጠሪ 30,000 ካሬ ሜትር የሆነ የመንግሥት ቦታ
( መሬት ) ይዞ እየተጠቀመበት መሆኑን መነሻ በማድረግ ነው ። ይህ ፍሬ ነገርም በሁለቱ
ወገኖች አልተካደም :: የአገልግሉት ኪራይ እንዲከፈል በሕግ የተደነገገ መሆኑ ግልጽ ነው ።
ተጠሪም ይህን አይካድም ፡፡ ኪራዩን መክፈል የለብኝም በማለት የተከራከረው አመልካች
የሊዝ ውሉ መፍረስ አለበት በማለት ሲከራከረኝ ስለቆየ ፤ እኔም የሁከት ይወገድልኝ ክስ
መስርቼ ውሉ አይፈርስም የሚል ውጭ በፍ / ቤት ያሰጠሁበት በመሆኑ በክርክር ለቆየንበት
ችሎትም ይህን ክርክር በመቀበል ነው አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ የሰጠው ።
የቦታ አገልግሉት ኪራይ የሚጠየቀውና የሚከፈለው ይህን በሚመለከት በተደነገገው
ሕግ መሠረት ነው :: የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁ 80 / 1968
በአንቀጽ 5 ላይ ስለኪራዩ አከፋፈል በዝርዝር ያመለክታል ፡፡ በአንቀጽ 14 ደግሞ ከኪራይ
ክፍያ ነፃ የሚሆኑትን ወገኖች ለይቶ አስቀምጦአል ፡፡ በያዝነው ጉዳይ እንደምናየው ተጠሪ
ከኪራይ ክፍያ ነፃ አይደለም ፡፡ ኪራይ የተጠየቀበትን ቦታም በይዞታው ስር እንዳለ
ተመልክተናል ፡፡ በአመልካች በኩል ውሉ እንዲፈርስ ፍላጎት የነበረ ቢሆንም ፤ ተጠሪ ግን
ውሉ መፍረስ የለበትም በማለት እና በበኩሉም የሁከት ይወገድልኝ ክስ በመመስረት
ተከራክሮ ቦታውን እንደያዘ እንዲቀጥል ተወስኖለታል ፡፡
ክርክር ሲካሄድ በነበረበት ጊዜም ቦታው ከተጠሪው እጅ አልወጣም ። በመሆኑም
በአንድ በኩል በቦታው እጠቀማለሁ ። አለቅም ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሕግ የተጣለብኝን
ግዴታ አልወጣም ለማለት የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለውም ፡፡ የጠ / ፍ / ቤቱ ሰበር
ችሉትም የተጠሪውን ክርክር በመቀበል ውሣ በመሰጠቱ አመልካች በሕግ የተጠበቀለትን
* ን 2-23
የቦታ አገልግሉት ኪራይ የመሰብሰብ መብቱን አሳጥቶታል ። ስለዚህም ውሣው ( አቤቱታ
የቀረበበት ) መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል ፡፡
ው ሣ ኔ
ብ / ብ / ሕ / ክ / መ.ጠቅላይ
ችሎት በመ.ቁ 6694
በ 24.1.98 ዓ.ም የሰጠው ውሣ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ 348 ( 1 ) መሠረት ተሽሮአል ።
2. ተጠሪ ክስ የቀረበበትን የበታ አገልግሎት ኪራይ በሙሉ ይክፈል በማለት
ወስነናል ፡፡
ፌራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ሪሶ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.