የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፲፩ ዓም የውሃ ሥራዎች ዲዛይን እና ቁጥጥር ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፰፻፶፫ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፪ / ፲፱፻፲፩ የውሃ ሥራዎች ዲዛይን እና ቁጥጥር ድርጅትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት | pursuant to Article 5 of the Definition ofPowers and Duties of ልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻ T ፬ በአንቀጽ / ፩ / ( ሀ ) | the Executive Organs of the Federal Democratic Republic of መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የውሃ ሥራዎች ዲዛይን እና ቁጥጥር ድርጅት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፵፪ ፲፱፻፲፩ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም የውሀ ሥራዎችዲዛይን እና ቁጥጥር ድርጅት ( ከዚህ በኋላ “ ድርጅቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ • ድርጅቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ መሠረት ይተዳደራል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ ገጽ ፰፻፶፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ መስከረም ፳፱ ቀን ፲፱፵፩ ዓም ፫ . ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የውሀ ሀብት ሚኒስቴር የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የድርጅቱ ዋና መ / ቤት በአዲስ አበባ ይሆናል ። እንደአስፈላ ጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ድርጅቱ የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው ። ፩ . የሀይድሮሊክስ : የግድብ ፣ የመስኖ ፡ የመጠጥ ፣ የኢንዱስትሪ ፡ የፍሳሽ ማስወገጃ ውሀ ሥራዎችን እና የተፋሰስ ልማት ጥናቶችን ማካሄድ ፣ ፪ : የሀይድሮሊክስ : የሀይድሮፓወር ፣ የጆዎቴክኒክ ፣ የግድብ እና የመስኖውቅሮች ፣ የጎርፍቁጥጥር ፣ የመጠጥ ውሃ የፍሳሽ ማስወገጃ እና የመሳሰሉትን የውሀ ሥራዎች የቅየሳ የዲዛይን እና የኮንስትራክሽን ሥራ ዝርዝሮችን ማከናወን ፣ ፫ የውሀ ሥራዎች የውለታ አስተዳደር ቁጥጥርን በተመ ለከተ የአማካሪነት አገልግሎት መስጠት ፤ ፬ . የውሀ ሥራዎችን የሚመለከቱ ጥናቶች እና ዲዛይኖችን የመገምገም አገልግሎት መስጠት ፤ ፭ የውሀ ሥራዎችን በሚመለከት የጨረታ ሠነድእና ውል የማዘጋጀት ፤ ሥራ ተቋራጮችን የመምረጥ አገልግሎት መስጠት ፡ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማካሄድ ። ፮ ካፒታል ለድርጅቱ የተፈቀደ ካፒታል ብር ፴፭ ሚሊዮን ፪፻፴፭ ሺህ 16. Capital ፮፻፸፪ ከ 0 ፬ ሣንቲም ( ሠላሣ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሠላሣ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ሁለት ብር ከዜሮ አራት ሣንቲም ) ሲሆን ይኸው በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት በሙሉ ተከፍሏል ። ፯ ኃላፊነት ድርጅቱ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ አይሆንም ። ፰፡ ድርጅቱ የሚቆይበት ጊዜ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል ። ደንበ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከመስከረም ፳፱ ቀን ፲፱፻፲፩ ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ መስከረም ፳፱ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ