×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ 70/93 የኢትዮጵያ ፈንጂአምካኝ ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ ፈንጂ አጥፋ - ትማቋቋሚያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻፵ ዓም የኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ጽሕፈት ቤትማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፩ሺ፬፻፷፭ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻ዥ የኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ጽሕፈት ቤትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / i ህየዥ ፤ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፪ / ፲፱፻ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ መቋቋም ፩ . የኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ጽሕፈት ቤት ( ከዚህ በኋላ “ ጽሕፈት ቤቱ ” ተብሎ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ጽሕፈት ቤቱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፫ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ “ ፈንጂ ” ማለት የተጣሉና የተቀበሩ ቦምቦች፡ አረሮች ፡ ሼሎች እና ቁምቡላዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ ሊፈነዱ የሚችሉ የጦርነት ቅሪቶችን ይጨምራል ። ያንዱ ዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪፻፷፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻ ዓ.ም. ጽሕፈቱ ቤቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ የተቀበሩ እና የተጣሉ ፈንጂዎች በሰው ሕይወት ፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ማድረግ ፤ ፪- የተቀበሩ እና የተጣሉ ፈንጂዎች ለሁለተኛ ጊዜ በሥራ ላይ ሊውሉ በማይችሉበት ሁኔታ ማምከን ፤ ፫ ኅብረተሰቡ የተቀበሩና የተጣሉ ፈንጂዎች የሚያስከት ሉትን ጉዳት ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ትምህርት መስጠት፡ ፭ የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባር ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ የተቀበሩ እና የተጣሉ ፈንጂዎች የሚገኙባቸውን ቦታዎች ለይቶ ለማወቅ ጥናት ያካሂዳል ፤ ፪ . በፈንጂ ማምከን ተግባር የሚሰማሩ ባለሙያዎችን ያሰለጥናል፡ በሥራ ያሠማራል፡ የተጣሉና የተቀበሩ ፈንጂዎችን በማምከንና በማጽዳት ተግባር ይሠማራል፡ ኅብረተሰቡ የተቀበሩና የተጣሉ ፈንጂዎች ስለሚያስከ ትሉት ጉዳት ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ትምህርት ይሰጣል፡ በአገሪቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ጽ ቤቶችን ሊያቋቁም ይችላል፡ በአገር ውስጥና በሌሎች አገሮች ከሚገኙ አቻ ተቋማትና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አካላት ጋር የሥራ ግንኙነት ይመሠርታል፡ ጊ ፈንጂ ተቀብሮባቸው እና ተጥሎባቸው የነበሩ አካባ ቢዎች ከእነዚህ መሣሪያዎች የዐዱ ስለመሆናቸው ከሚያረጋግጡ አካላት ጋር ይተባበራል ፤ ፰ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ ይከሳል፡ ይከሰሳል፡ ፬ ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ሊጠይቅ ይችላል ፣ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ሌሎች ተግባ ሮችን ያከናውናል ። ፮ የጽሕፈት ቤቱ አቋም ጽሕፈት ቤቱ፡ ፪ ዳይሬክተር ፡ ፫ አስፈላጊ ሠራተኞች ፡ ይኖሩታል ። ፯ . የቦርዱ አባላት ጽሕፈት ቤቱ በመንግሥት የሚሰየሙ አግባብ ካላቸው ተቋሞችና የመንግሥት መ / ቤቶች የተውጣጡ ሰባት አባላት ያሉት ቦርድ ይኖረዋል ። ፰ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ጽሕፈት ቤቱ በዓላማውመሠረትተግባራዊእንቅስቃሴ ማድረገን ያረጋግጣል፡ ፪ ጽሕፈት ቤቱ የሚተዳደርበትን መመሪያ ያወጣል ፤ የጽሕፈት ቤቱን አደረጃጀት ይወስናል፡ ጽ / ቤቱ የሚስ ፋፋበትን፡ የሚጠናከርበትንና አሠራሩ የሚሻሻልበትን መንገድ ይቀይሳል፡ 0 የጽሕፈት ቤቱን ዳይሬክተር ይሾማል፡ ፭ ጽሕፈት ቤቱ የሚያስከፍላቸውን ክፍያዎች ይወስናል፡ ፮ የጽሕፈት ቤቱን ፕሮግራምና በጀት መርምሮ ያፀድቃል ። መ ) በጸሕታ ኣተሉት ምንጮች የተውጣጣ ገጸ ፩ሺ፪፻፷፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፮ ጥር ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ። ፪ : አስቸኳይ ሁኔታ ሲያጋጥም በቦርዱ ሰብሳቢ ጥሪ ወይም ከቦርዱ አባላት መካከል ቢያንስ ሁለቱ ሲጠይቁ በማና ቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። በስብሰባው ላይ ከግማሽ በላይ አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ቦርዱ ውሣኔ የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ፤ ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ሀሳብ የቦርዱ ውሣኔ ይሆናል ። ከዚህ በላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ ዝርዝር የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ለማውጣት ይቻላል ። ፲ የጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር ሥልጣንና ተግባር ፩ ዳይሬክተሩየጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሥራ ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አገላለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ዳይሬክተሩ ሀ ) ለጽሕፈት ቤቱ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል፡ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መርሆዎችን ተከትሎ ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የጽሕፈት ቤቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳ ደራል፡ ያሰናብታል፡ ሐ ) የጽሕፈት ቤቱን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት ለቦርዱ ያቀርባል፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፡ ስም ውል ይዋዋላል ። ፲፩ . በጀት የጽሕፈት ቤቱ በጀት ይሆናል፡ ፩ በፌዴራል መንግሥት ከሚመደብለት በጀት፡ ጽሕፈት ቤቱ ከሚያገኛቸው የአገልግሎት ክፍያዎች ፫ . ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ከሚያገኘው ዕርዳታ ። ፲፪ . የሂሣብ መዛግብትና ኦዲት ፩ ጽሕፈት ቤቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግ ብትና ሰነዶችን ይይዛል ። ፪ • የጽሕፈት ቤቱ የሂሣብ መዛግብትና ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ሌሎች ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?