የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ዥ፭ ፲፱፻፰፱ ዓ•ም• በግል ክፍለ ኢኮኖሚ ለተሠማሩት አነስተኛና መካከለኛ ድርጅ ቶች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካይነት በመልሶ ማበደር የሚተላለፍ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ . . . . . . ገጽ ፮፻፪ አዋጅ ቁጥር ፴፭ ፲፱፻፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ በግል ክፍለ ኢኮኖሚ በፋብሪካ ፡ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፡ በማዕድን ፡ በቱሪዝም እና በመሳሰሉት የሥራ እንቅስቃሴዎች ለተሠማሩት አነስተ | ኛና መካከለኛድርጅቶች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካይነት በመልሶ ማበደር የሚተላለፍ መጠኑ ፲ ሚሊዮን ( አሥር ሚሊዮን ) ኢኪው የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክ ራሲያዊ ሪፐብሊክና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል እ ኤ . አ . ዲሴምበር ፲፰ ቀን ፲፱፻ን፮ በሉግዘምበርግ የተፈረመ በመሆኑ ፡ ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፡ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ በግል ክፍለ ኢኮኖሚ ለተሠማሩት አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካይነት በመልሶ ማበደር የሚተላለፍ ፡ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ብድር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፳፭ ፲፱፻፳፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። | ያንዱ ዋጋ 2 . 30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ዝሺ፩ ገጽ ፭፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ) ሰኔ ፳፮ቀን ፲፱፻ዥሀ ዓም ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ “ የብድር ስምምነት ” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአውሮፓ ኢንቨስትመ ንት ባንክ መካከል እ . ኤ . አ . ዲሴምበር ፲፰ ቀን ፲ህየን፮ በሉግዘምበ ርግ የተፈረመው ቁጥር ፯ ፡ ፩ዜሮሮ ኢትዮ የብድር ስምምነት ፫ የገንዘብ ሚኒስትሩ ሥልጣን የገንዘብ ሚኒስትሩ በብድር ስምምነቱ የተገኘውን ፲ ሚሊዮን ( አሥር ሚሊዮን ) ኢኪው በብድር ስምምነቱ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ በዚህ አዋጅ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። ፬• አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፡ ሰኔ ፳፮ ቀን ፲፱፻T፬ ዓ . ም . ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ