×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 18931

      Sorry, pritning is not allowed

ነው ' ,
የሰበር መ / ቁ .18931
ሐምሌ 21 ቀን 1998
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኢት የእህል ንግድ ድርጅት - አልቀረበም
መልስ ሰጭ፡- አቶ አዳነ ኮሬ - ቀረበ
Afri
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
ቦርድን ስልጣን የሚመለከት
በመ / ሰጭ በአሰሪና ሰራተኛ
ክሱ የቀረበው ቋሚ ልሁን በሚል ነው ፡፡
አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ክሱን ለማየት ስልጣን
አለው በማለት የተሰጠ ነው ፡፡ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለዚህ ችሎት ያቀረበው
የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት
መ / ሰጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
ችሎቱም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ውሳኔ ቦርድ የስራ ክርክሮች ምን አይነት
ናቸው የሚለውን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበለትን ውሳኔ አግባብነት
ካለው ህግ ጋር አገናዝቦ መርምሯል ፡፡ ይህ ችሎት በመ / ቁ . 18180 አግባብነት ያላቸውን
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎች በመተርጎም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ
የማየት ስልጣን የተሰጠው የውል የስራ ክርክር ጉዳዮችን ነው ፤ አንድ የስራ ክርክር
- -ራቱ ብቅይ ወደ ቤት
የወል የስራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ
አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፤ በአንፃሩ አንድ
የስራ ክርክር የወል ሳይሆን የግል የስራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት
በተከራካሪው ሰራተኛ / ሰራተኞት / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ ሲገኝ ነው በማለት
የህግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
መ / ሰጭ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ቋሚ ልሁን በሚል ያቀረበው ክስ
የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት
የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የስራ ክርክር አይደለም ፡፡ በመሆኑም ጉዳዩን ለማየት
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን አለው በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሳ ኔ
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመቁ 83/01/97 ቀን በ 30 / 2 / 97
የሰጠው ውሳኔና
ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ / ቁ .35118 በ 5 / 4 / 97
የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ፋራሱ ቀይ ፍርድ ቤት
ችክፊ ለውጭ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?