×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 21939

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ .21989
ቀን ሐምሌ 12/98
ዳኞች፡- 1- አቶ ፍሠህ ወርቅነህ
2- አቶ ጌታቸው ምህረቱ
3- አቶ አሰግድ ጋሻው
4- አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5- ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- ኪንግናም ኢንተርፕራይዝ ሊሚትድ -ነ / ፈጅ ተስፋዬ ደገፋ
መልስ ሰጭ፡- አቶ አክሊሉ በቀለ - ቀረቡ
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ
ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር አንድ ሰራተኛ ከስራ የተሰናበተው
በህገወጥ መንገድ
ተረጋግጦ ወደ ስራ እንዲመለስ በአዋጅ ቁ .42 / 85 መሰረት
ሲወሰን ከስራ ከተሰናበተበት ጊዜ
ወደ ስራ እንዲመለስ ውሳኔ እስክተሰጠበትና
ስራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው ይግባል ? ወይስ አይገባም ?
የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የስር ፍ / ቤት መ / ሰጭ ከስራ የተሰናበተው በህገወጥ
መንገድ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎ ወደ ስራው እንዲመለስ የወሰነ ሲሆን
ውሳኔውን ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም አጽንቶታል ፡፡ አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም
ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መ /
ሳጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
ለችሎቱም አንድ ሰራተኛ ከስራ የተሰናበተው በህገወጥ መንገድ መሆኑ
ተረጋግጦ ወደ ስራ እንዲመለስ በአዋጅ ቁ .42 / 85 መሰረት ሲወሰን ከሰራ ከተሰናበተት
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክእል ግልጭ
ቀን .18- (
ፊርማ ይዛ .
4 ኣሮሚያ
ጊዜ ጀምሮ ወደ ስራ እንዲመለስ ውሳኔ እስከተሰጠበትና ስራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል ? ወይስ አይገባም ? የሚለውን ነጥብ መሰረት በማድረግ የቀረበበትን ውሳኔ አግባብነት አገናዝቦ መርምሮታል ፡፡
ይህ ችሎት በመ / ቁ .17189 አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁ .42 / 85 ን ድንጋጌዎች በመተርጎም ህጉ ስራ ላልተሰራበት ጊዜ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የሚፈቅድ አይደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል ፡፡ በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ለመ /
ሰጭ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሳ ኔ ይህ ችሎት መ / ሰጭ ውዝፍ ደመወዙ ሊከፈል አይገባም በማለት ወስኖ
አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመ / ቁ .463 / 01 / 96 ሚያዝያ 19
የኦሮሚያ ጠቅላይ በመ / ቁ .09977 ህዳር 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሏል ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ፈደፋ 4 ' ' ፡፡ ፍርድ ይት
የል ግልባጭ
ዞን ( 9 -- የፈ
ፊርማ ' ነው

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?