የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፵፪ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፲፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፪ / ፲፱፻፶፪ ዓም የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ገጽ ፩ሺ፪፻፻፯ አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፪ / ፲፱፻፵፪ የብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድን ለማቋቋምና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ በድንገተኛና ባልታሰበ አደጋ ጊዜ ፈጥኖ ለመድረስ እንዲያ ስችል የተዘረጋውን ሥርዓት ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows : አዋጅ ቁጥር ፪፻፲፪ / ፲፱፻፲፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል ። በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ . “ ዕርዳታ ” የሚለው ቃልና “ የዕርዳታ ፕሮግራም የሚለው ሐረግ በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን | 2. Definitions ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲ / 1 ህደ T ፯ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) እና ( ፪ ) የተሰጣቸው ትርጉም ይኖራቸዋል፡ ፪ . “ ብሔራዊ ኮሚቴ ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፳፯ አንቀጸ ፯ ( ፩ ) የተመለከተው የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ብሔራዊ ኮሚቴ ነው ። ክፍል አንድ ስለፈንድ መቋቋም ስለፈንደ መቋቋም ብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ ( ከዚህ በኋላ “ ፈንዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ያንዱ ዋጋ 280 ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣቁ ፱ሺ፩ ገጽ ፩ሺ፪፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፪ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፈንዱ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሚያስተዳድረው የተጠቃለለ ፈንድ ውጨ ይሆናል ። የፈንዱ ባለቤት የፌዴራሉ መንግሥት ይሆናል ። የፈንዱ ዓላማ የፈንዱ ዓላማ፡ ፩ በአደጋ ወቅት የሚያስፈልግ ዕርዳታ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር እስከሚሰባሰብ ድረስ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የሰውንና የእንስሳትን ሕይወት ለማዳንና አደጋን ለመከላከል የሚያስችል አቅም መገንባት፡ እና የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያግዙና የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶችን ማስፈጸሚያ መጠባበቂያ ጥሬ ገንዘብ በመያዝ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት ነው ። የፈንዱ ምንጭ ፈንዱ ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፣ ፩ . በፈዴራሉ መንግሥት የሚደረግ ድጎማ፡ ከሀገር ውስጥና ከውጪጪ ከሚገኝ ዕርዳታ፡ ፫ • ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገቢ ፡፡ በፈንዱ የመጠቀም መመዘኛ በፈንዱ ለመጠቀም ከሚከተሉት መመዘኛዎች ቢያንስ አንዱ መሟላት ይኖርበታል፡ ፩ አደጋ ተከስቶ የማስፈጸሚያ የበጀት ክፍተት መኖሩ ሲረጋገጥና ክፍተቱን በአፋጣኝ መሙላት አስፈላጊ ፪ : አስቸኳይ አደጋ ሲፈጠርና የተከሰተውን አደጋ ለመከ ላከል ቅድሚያ መስጠቱ ሲታመንበት፡ የአደጋ መከሰትን በመደበኛነት የሚከላከሉ ፕሮጀ ክቶች መኖራቸው ሲረጋገጥ፡ በነፃ ገንዘብ እንዲሰጠው የሚጠይቀው አካል በራሱ በኩል የሚያደርገው የገንዘብ አስተዋጽኦ ሲኖርና ገንዘቡን ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችለው አስተማማኝ ሁኔታ መኖሩ ሲረጋገጥ፡ በብድር መልክ የሚሰጥ ከሆነ ገንዘቡን ለመተካት ፍላጎት ካለው ለጋሽ ለብድሩ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ የገንዘብ ልገሳ ለማድረግ የሚያበቃ ወይም የብድር ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል አስቸኳይ ሁኔታ መኖሩ ሲረጋገጥ ። ክፍል ሁለት ስለፈንዱ አስተዳደር ጊ መቋቋም ፩ . የፈንዱ አስተዳደር ( ከዚህ በኋላ “ አስተዳደሩ ” እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ • አስተዳደሩ ተጠሪነቱ ለብሔራዊ አደጋ መከላከልና | 9 . Objective ዝግጁነት ፈንድ ሥራ አመራር ቦርድ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የአስተዳደሩ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ። የኣስተዳደሩ ዓላማ የአስተዳደሩ ዓላማ ፈንዱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የሚረዳ የገንዘብ አቅም መገንባት፡ ፈንዱን ማስተዳደርና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ይሆናል ። ፲የአስተዳደሩ ሥልጣንና ተግባር አስተዳደሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ ፈንዱን ያስተዳድራል፡ የፈንዱ ንብረትና ገንዘብ በሥርዓት መያዙን ያረጋ ገጽ ፩ሺ፫፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፪ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ • ም • ፫ ከሚመለከተው አካል በመመካከር ፈንዱን ያደራጃል፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከተው መመዘኛ መሟላቱ በሥራ አመራር ቦርዱ ወይም የሥልጣን ውክልና በተሰጠው ጊዜ በቴክኒክ ኮሚቴው ሲረጋገጥ ገንዘብ በብድር ወይም በልገሳ ወጪ ሆኖ የዕርዳታፕሮግራሞችን ለሚያስፈጸሙ አካላት እንዲሰጥ ያደርጋል፡ ፭ ከለጋሾች በዓይነት የሚገኙ የዕርዳታ ቁሳቁሶችን በመን ግሥት መመሪያ መሠረት ወደ ገንዘብ ለውጦ የመጠባ በቂያ ፈንዱን ያጎለብታል፡ የፈንዱ አቅም እንዲጎለብት አስፈላጊውን ጥረት ያደርጋል፡ ፯ የንብረት ባለቤት ይሆናል፡ ውል ይዋዋላል፡ በስሙ ይከስሳል፡ ይከሰሳል፡ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ተግባሮችን ሁሉ ያከናውናል ። ፲፩ . የአስተዳደሩ አቋም አስተዳደሩ፡ የሥራ አመራር ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፡ የቴክኒክ ኮሚቴ፡ በቦርዱ ሰብሳቢ አቅራቢነት በመንግሥት የሚሾም አንድ ሥራ አስኪያጅ ፡ እና አስፈላጊው ሠራተኞች፡ ይኖሩታል ። ፲፪ . የብሔራዊ ኮሚቴው ሥልጣንና ኃላፊነት ብሔራዊ ኮሚቴው በብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፖሊሲው መሠረት የፈንዱን አስተዳደር በበላይነት ይመራል ። የሥራ አመራር ቦርድ ቦርዱ ተጠሪነቱ ለብሔራዊ ኮሚቴው ሆኖ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡ ፩ ከፈንዱ አስተዳደርና አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ፖሊሲ ነክ ጉዳዮች ላይ ውሣኔ የመስጠት፡ ፪ • ለፈንዱ አስተዳደርና ዕድገት እገዛ የሚያደርግና ከሚመ ለከታቸው አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉበት የቴክኒክ ኮሚቴ የመሰየም፡ ፫ የቴክኒክ ኮሚቴው የሚያቀርበውን የውሣኔ ሐሳብ በመመርመር ፈንዱን ለማሳደግ የሚያስችሉ እርምጃ ዎችን የመውሰድ፡ ፬ . አስቸኳይ የሆነ የምግብ እጥረት ወይም የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ ሲከሰት ከቴክኒክ ኮሚቴው የሚቀርብ ለትን የውሣኔ ሐሳብ በመመርመር ከፈንዱ ለዕርዳታ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ በብድር ወይም በነፃ የሚሰ ጠውን የገንዘብ መጠን የመፍቀድ፡ ፭ : አስቸኳይ ለሆኑ የዕርዳታ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ ከፈንዱ በተቀላጠፈ ማሠራጨት የሚቻልበትን ሁኔታ በማጥናት ለቴክኒክ ኮሚቴው ወይም ለሥራ ኣስኪያጁ እንደአግባቡ የገንዘብ ጣሪያ በመወሰን በብድር ወይም በነፃ ለመስጠት የሚያስችላቸው የሥልጣን የመስጠት፡ በብድር ለሚሰጠው ገንዘብ የሚጠየቀውን የዋስትና ዓይነትና ብድሩ ተመላሽ የሚሆንበትን የጊዜ ገደብ የመወሰን፡ ተበዳሪ ድርጅቶች የወሰዱትን ገንዘብ በተሰጣቸው ባይመልሱ የሚወሰደውን እርምጃ የመወሰን፡ ገጽ ፩ሺ፫፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፪ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : ፰ ) የፈንዱን ዕድገት የሚያፋጥኑ ስልቶችን የመቀየስናተግባ ራዊነታቸውን የማረጋገጥ ። የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፡ እንደአስፈላጊነቱም አስቸኳይ ስብሰባዎችን ሊጠራ ይችላል፡ ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ከተገኙምልዐተ ጉባዔ ይሆናል፡ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው ላይ በተገኙ አባላት ድምፅ ብልጫ ሆኖ ድምፁ እኩል ለእኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል፡ የዚህ አንቀጽ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ፣ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት የሚመለከት የውስጥ ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። የቴክኒክ ኮሚቴው ሥልጣንና ተግባር የቴክኒክ ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለቦርዱ ሆኖ፡ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ በብድርና በነፃ ሊሰጥ የሚችል በቂ ገንዘብ በፈንዱ መያዙን ያረጋግጣል፡ የፈንዱን የገንዘብ አቅም ገምግሞ ለዕርዳታ ፕሮግ ራሞች ማስፈጸሚያ ለልዩ ልዩ የዕርዳታ ድርጅቶች በብድር ወይም በነፃ ወይም በሁለቱም መንገድ ሊሰጥ የሚገባውን የገንዘብ ጣሪያ አስመልክቶ ለቦርዱ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል ፡ በራሱ ለመወሰን በቦርዱ የሥልጣን ውክልና ካልተ ሰጠው በስተቀር በብድርና በነፃ ገንዘብ እንዲሰጥ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ ለቦርዱ ያቀርባል፡ የፈንዱን መጠን ከፍ ለማድረግ ይቻል ዘንድ በጎ አድራጊዎችንና ለጋሽ መንግሥታትን ከሚመለከ ታቸው አካላት ጋር በማስተባበር ይሠራል ፣ ስለፈንዱ አተካክና ዕድገት ከአስተዳደሩ ጋር በቅርብ ሆኖ ይሠራል፡ በብድር ወይም በነፃ የተሰጠው ገንዘብ በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን የሚቆጣጠርና ሪፖርት የሚያቀርብ አካል እንደአስፈላጊነቱ ሊሰይም ይችላል፡ ፯ የቴክኒክ ምክር ለቦርዱና ለአስተዳደሩ ይሰጣል ። ፲፯ . የቴክኒክ ኮሚቴው ስብሰባ የቴክኒክ ኮሚቴው በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፡ እንደአስፈላጊነቱም አስቸኳይ ስብሰባዎችን ሊጠራ ይችላል፡ ፪ • ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ከተገኙምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፡ • ውሳኔዎች ወይም የውሳኔ ሐሳቦች በድምፅ ብልጫ ይተላለፋሉ፡ የስብሰባው ውሳኔ ወይም የውሳኔ ሐሳብ ድምዕ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ጉዳዩ ለቦርዱ ውሳኔ ይቀርባል ፡፡ የአስተዳደሩ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ሥራ አስኪያጁ የአስተዳደሩ ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የአስተዳደሩን ዕለታዊ ሥራዎች ለማከናወን የበላይ ኃላፊ ይሆናል ። ፪ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፡ ሥራ አስኪያጁ፡ ሀ ) አስተዳደሩን ያደራጃል፡ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ሠራተኞችን ያስተዳድራል፡ ለ ) የአስተዳደሩን የውስጥ ደንብ በማዘጋጀት እንዲ ፀድቅ ለቦርዱ ያቀርባል፡ ሐ ) እያንዳንዱ የበጀት ዓመት ከመጀመሩ በፊት የአስ ተዳደሩን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ዕቅድ በማዘ ጋጀት ለቦርዱ ያቀርባል፡ * እ s ሮ የፀና ይሆናል ። | 23. Effective Date ገጽ ፭ሺ፫፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፪ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. መ ) ተጠሪነታቸው ለራሱ የሆኑትን የአስተዳደሩን የሥራ ኃላፊዎች በመምረጥ ለቦርዱ አቅርቦ ያስመድባል ፡ ሠ ) ፈንዱን ለማሳደግ ይቻል ዘንድ የሚሰጠውን ዕርዳታ ሊቀበል ይችላል፡ ረ ) ቦርዱ በሚወስነው መሠረት ከፈንዱ በብድርና በነፃ ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፡ ሰ ) በብድር የተሰጠውን ገንዘብ በወቅቱ ማስመለስ ካልቻለ ለቴክኒክ ኮሚቴው በጽሑፍ ሪፖርት ያደርጋል ፣ ሸ ) የቴክኒክ ኮሚቴውን ሪፖርት ለቦርዱ ሰብሳቢ ያቀርባል ። ፲፱ . የበጀት ምንጭ የአስተዳደሩ በጀት ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል፡ ፩ . መንግሥት ከሚመድብለት ዓመታዊ በጀት፡ እና ፪ ከዕርዳታና ከሌሎች ምንጮች ከሚገኙ ገቢዎች ። ስለሂሣብ መዛግብት አያያዝና ስለበጀት ዓመት አስተዳደሩ የሂሣብ መዛግብቶችን ከደጋፊ ሰነዶች ጋር በተሟላ መልኩ ይይዛል ። የአስተዳደሩ የበጀት ዓመት ከሐምሌ አንድ ቀን እስከ ሰኔ ሠላሳ ቀን ድረስ ይሆናል ። ስለምርመራና ቁጥጥር ፩ የአስተዳደሩ የሂሣብ መዛግብትና የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ሰው ይመረመራሉ ። ፪ • የኦዲተሩ የምርመራ ውጤት የበጀት ዓመቱ ባልቀ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለቦርዱ ይቀርባል ። ፫ ለጋሾች በተናጠል ወይም በጋራ በለገሱት ገንዘብ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን አፈጸጸም መከታተልና መቆጣጠር ይችላሉ ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፪ ከሌሎች ሕጎች ጋር ስላለው ግንኙነት ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ሌሎች ሕጎች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም ። ፳፫ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ካሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም አዲስ አበባ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ