×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 14414

      Sorry, pritning is not allowed

ሰበር መ / ቁ .14414
ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
4. አቶ አሰግድ ጋሻው
5. ወ / ሮ ደስታ ገብሩ
አመልካች፡- የጊምቢ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት
መልስ ሰጭ ወ / ሮ መረርቱ፡ ፈቃዱ
ስለ እዋጅ ቁ .42 / 85 ተፈፃሚነት የአሰሪና ሰራተኛ ትርጓሜ
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ .42 / 85 አንቀጽ 2 / 1 / ፣ 3 / 2 / / ሠ /
መ / ሰጭ የአዋጅ ቁ 42 / 85 ን መሠረት በማድረግ አመልካች
ይኸንኑ ሕግ ተላልፎ ከስራዬ ያገደኝ በመሆኑ
ከስራዬ ያገደኝ በመሆኑ ወደ ሰራ እንድመለስ
ይወሰንልኝ በማለት
ወረዳ ፍ / ቤት ያቀረበችውን ክስ ፍ / ቤቱ
መ / ሰጭ
ከታገደችበት
ቀን ጀምሮ
ጀምሮ ያለው
ተከፍሏት ወደ ሥራ እንድትመለስ አለዚያ በአዋጅ ቁ . 42/85 አንቀጽ
39 ፣ 40 እና 43 የተመለከተው ካሣ ተከፍሏት እንድትሰናበት ፍ / ቤቱ
በመወሰኑና ውሣኔውንም የምዕራብ ወለጋ ከፍተኛ ፍ / ቤት እና የክልሉ
ሰበር ችሎት በማጽናታቸው የቀረበ አቤቱታ ::
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሉት ፣ የምዕራብ ወለጋ
ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት እንዲሁም የግምቢ ወረዳ ፍ / ቤት የሰጡት ውሣ
ተሽሯል ፡፡
1. አንድ ክርክር በአዋጅ ቁ . 42/85 አግባብ የሚዳኘው በአዋጁ
እንደተሰጠው ትርጓሜ አንድ ወገን ተከራካሪ አሰሪ ሌላው
ወገን ተከራካሪ ደግሞ ሰራተኛ የሚባሉ ከሆነ ነው ::
2. በአዋጁ " አሰሪ ' ተብሎ ለሚጠራ " ድርጅት " የተሰጠው ትርጓሜ
የሕዝብ አስተዳደር ስራ የሚያከናውኑ አካላት " ድርጅት "
ሊባሉ እንደማይችሉ በግለጽ ያመለክታል ።
በአዋጁ ትርጓሜ " አሰሪ " ተብሎ የማይጠራ " ድርጅት " ጋር
የስራ ውል ያለው ሰራተኛ በአዋጁ ትርጓሜ " ሠራተኛ " ሊባል
አይችልም ፡፡
ኣንድ በሕዝብ አስተዳደር አካል ውስጥ የሚሰራ ሰራተኛ
በመንግሥት ሰራተኞች አስተዳደር አዋጅ አለመሸፈኑ በራሱ
በአዋጅ ቁ 42/85 የሚሸፈን አያደርገውም ፡፡
የሰ / መ / ቁ . 14414
ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ኣቶ ፍስሐ ወርቅነህ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
አቶ አሰግድ ጋሻው
ወ / ሮ ደስታ ገብሩ
አመልካች፡- የጊምቢ ከተማ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት - አላዛር ኢተፋ
ቀረበ ፡፡
ተጠሪ፡- ወ / ሮ መረርቱ ፈቃዱ- አልቀረበችም ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ የግምሲ ወረዳ ፍ / ቤት የአሁን ተጠሪ የአዋጅ ቁ .
42 / 85 ን መሠረት በማድረግ የአሁኑ አመልካች ይኸን ሕግ ተላልፎ
አግዶኛልና
ኪሣራዬን
እንዲመልሰኝ
ይወሰንልኝ ስትል በአቀረበችላት ክስ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ከሥራ
ከታገደችበት እለት ጀምሮ ያለው ደመወዝዋ እንዲከፈላት እና ወደ
የተመለከተው ካሳ እንዲሰጣት እና እንድትሰናበት ወስዶ ሓ ሥራዋ እንድትመለስ
አለዚያ የአዋጁ አንቀጽ
39፣40 እና
የወለጋ ከፍተኛ ፍ / ቤት ይህን ውሣኔ ያፀናው ሲሆን በመቀጠል
ይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ
ፍ / ቤት ደግሞ በዚህ ጉዳይ
የከፍተኛ ፍ / ቤት ውሣኔ የመጨረሻ ፍርድ በመሆኑ ጉዳዩን ለማየት
ሥልጣን የለኝም ሲል መዝገቡን ዘግቶታል ፡፡ የክልሉ ሰበር ሰሚ
ችሉትም በውሣኔው መሠረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈፀመም በማለት
በአመልካች የቀረበለትን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል ።
አመልካችና
ያቀረቡለትን
መርምሯል ፡፡
ሊፈታ የሚገባውም የጉዳዩ ጭብጥ የተከራካሪዎቹ ግንኙነት
ቁ . 42/85 ይሸፈናል ? ወይስ አይሸፈንም ? የሚለው ሆኖ
ኣግኝቶታል ።
በአዋጅ ቁ . 42/85 አንቀጽ 2 / 1 / መሠረት አንድ አካል አሠሪ
ለመሰኘት ሰአዋጁ አግባብ ሰራተኛን ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ ወይም
ድርጅት ሊሆን ይገባዋል ፡፡ ድርጅት የሚባለው ደግሞ የንግድ
የኢንዱስትሪ ፣
የኮንስትራክሽን ወይም
ሕጋዊያን ተግባራትን
ለማከናወን የተመሠረተ ተቋም መሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 2/2 ላይ
ተተርጉሟል ፡፡ ይኸ ለጅርጅት የተሰጠው ትርጓሜ የሕዝብ አስተዳደር
ሥራ የሚያከናውኑ አካላት ድርጅት ሊባሉ እንደማይችሉ በግልጽ
ያመላክታል ፡፡ በሌላም በኩል የመንግሥት አስተዳደር ሰራተኞች በልዩ
ሕግ ከሚተዳደሩ ሌሎች ሠራተኞች ውስጥ የተመደቡ መሆናቸው እና
ከአሰሪያቸው ጋር ላላቸው ግንኙነት የአዋጅ ቁ .
42/85 ተፈፃሚ
እንደማይሆን በአንቀጽ 3 / 2 / ሠ / ላይ ተጠቅሷል ።
አመልካች የሕዝብ አገልግሎት ሥራ የሚያካሂድ የመንግሥት
ከስያሜው
መገንዘብ
ይቻላል ፡፡
የቀረበውም ክርክር አመልካች ድርጅት ነው በሚል እና ይህንንም
በማስረዳት ላይ የተመሠረተ አይደለም ፡፡ ክርክሩ ተጠሪ በመንግሥት
ሠራተኝነት የታቀፈች አይደለችም እስከ 1994 ዓ.ም ድረስም ሠራተኞቹ
በመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር አዋጅ የታቀፉ አልነበሩም ተጠሪ
ክስ ከመሠረተች በኋላ የወጣው የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት
ሠራተኞች አስተዳደር አዋጅ ቁ . 6 / 94 ም ወደ ኋላ ሄዶ ስለማይሰራ
ግንኙነታችን በኣዋጅ ቁ . 42/85 የሚሸፈን ነው የሚል ነው ፡፡
በዚህ ችሎት እምነት የአንድ ሙግት ይዘት ከአዋጅ ቁ . 42/85
አግባብ የሚዳኝ ነው የሚል
መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የአዋጁ
እንደተሰጠው ትርጓሜ አንድ ወገን ተከራካሪ
ወጎን ተከራካሪ አሰሪ ሌላው ወገን
ተከራካሪ ደግሞ ሰራተኛ ሊሰኙ ይገባል ፡፡ ከአዋጁ አግባብ ቀጣሪው አሰሪ
ተቀጣሪው ደግሞ ሠራተኛ ሊባሉና ሁለቱም በድንጋጌው የተቀመጠውን
የትርጓሜ መስፈርት እንዲያሟሉ ያስፈልጋል ፡፡
እንደተመለከተው
አመልካች
አስተዳደር ሥራ የሚያካሄድ የመንግሥት መ / ቤት በመሆኔ ድርጅት
የሚችል አይደለም ፡፡ አመልካቹ አሰሪ ድርጅት ባለመሆነም
ተጠሪዋ በአዋጁ እሰሪ ከተባለ አካል ጋር የሥራ ውል ግንኙነት ያላት
ሠራተኛ ናት ልትባል የምትችል አይደለችም ፡፡ ይህ ደግሞ ሁለቱም
በእዋጁ የተቀመጠውን ትርጓሜ አስማሟላታቸውን የሚያመላክት ነው ፡፡
በእርግጥ ተጠሪ በመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ያልታቀፈች ሠራተኛ መሆንዋን በመግለጽ መከራከርዋን ተገንዝበናል ፡፡
ይህም አዋጁ ተፈፃሚ የማይሆነው ሰአዋጁ አንቀጽ 3 / 2 / ሠ / መሠረት
በልዩ ሕግ ለሚተዳደሩ የመንግሥት አስተዳደር ሠራተኞች እንጂ ለእኔ በልዩ አዋጁ ላልታቀፍኩት አይደለም በሚል ዓይነት መሟገቷን ያመላክታል ፡፡ ይሁን እንጂ ተጠሪ እንደምትከራከረው በመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር አዋጁ የታቀፈች አይደለችም ሊባል የሚችል አይነት ቢሆን እንኳ አለመታቀፉ ብቻውን እርሷን በአዋጅ ቁ . 42/85 መሠረት ሠራተኛ አመልካቹን ደግሞ ድርጅት ሊያሰኛቸው የሚችል አይደለምና ግንኙነታቸው በተጠቀሰው አዋጅ የሚሸፈን ነው የሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርሰን አይሆንም ፡፡ አመልካች ድርጅት ተጠሪ ደግሞ የድርጅት ሠራተኛ መሆናቸው በአልተረጋገጠበት ሁኔታ የአዋጅ ቁ . 42 / 85 ን ለክርክራቸው ተገቢነት ሊኖረው የሚችልበት ሕጋዊ አግባብ አይኖርም ፡፡ እንዲሁም ተጠሪ አለኝ የምትለውን የመብት ጥያቄ ለግንኙነታቸው ተፈፃሚ ሊሆን ከሚገባው ሕግ አኳያ አቃንታ ልታቀርብ ከሚገባት በቀር የአዋጅ ቁ . 42/85 ድንጋጌዎችን ለመብቷ መጠየቂያ ልታደርግ አትችልም ፡፡ በዚህ ምክንያት የሥር ፍ / ቤቶች የተቀጠሰውን አዋጅ ተመስርተው የሰጡትን ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ፍርድ ይህ ችሎት አልተቀበለውም ፡፡
ው ሣ ኔ
ወረዳ ፍ / ቤት የምዕራብ ወለጋ ከፍተኛ ፍ / ቤት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት እና በመ / ቁ . 0235 የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በአዋጅ ቁ .42 / 85 መሠረት አይተው የሰጡት ከፍ ሲል የተመለከተው ውሣኔ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 348 / 1 / መሠረት ተሽሯል ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?